የኢራን ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዤሺኪያን የትራንፕን ''እጅ ስጡ '' ውድቅ አደረጉ
የኢራን ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዤሺኪያን ሀገራቸው “ያለ አንዳች ቅድመ-ሁኔታ እጅ እንድትሰጥ” የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሰጡትን ማሳሰቢያ ውድቅ አደረጉ። ፔዢሽኪያን የዶናልድ ትራምፕን ማሳሰቢያ “ሕልም” ብለውታል።
በቪዲዮ ተቀርጾ በተላለፈ ንግግራቸው “ወደ መቃብራቸው ሊወስዱት ይገባል” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን “ያለ አንዳች ቅድመ-ሁኔታ እጅ እንድትሰጥ” ያሳሰቡት ትናንት አርብ ነበር።
ለዓለም አቀፍ ሕግ፣ የሰብአዊነት ማዕቀፍ እና ለመርሆዎቻቸው ኢራን ቁርጠኛ እንደሆነች የገለጹት ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዤሺኪያን “ለነዚያ መርሆዎች ቁርጠኛ መሆን አለባቸው። የኢራንን ጨምሮ የማንኛውንም ሀገር መብቶች ችላ ማለት አይችሉም” ሲሉ ተናግረዋል።
እስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን የገጠሙት ጦርነት ስምንተኛ ቀኑን ሲያስቆጥር ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዤሺኪያን ሀገራቸው በአጎራባች ሃገራት ላይ ለተፈጸሙ የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃቶች በራሳቸው ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።
የኢራን ወታደራዊ አዛዦች እና የሀገሪቱ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ፕሬዝዳንቱ “አረመኔያዊ” ባሉት ጥቃት በመገደላቸው የሀገሪቱ ጦር “አዛዦቻቸው ባለመኖራቸው ምክንያት በፍላጎታቸው ተኮሱ፤ አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ አደረጉ” ሲሉ ተናግረዋል። “በክብር እና በኃይል” ሀገራቸውን እንደተከላከሉም አሞግሰዋል።
ካሁን በኋላ ጎረቤት ሀገራት ጥቃት ካልፈጸሙ በስተቀር የኢራን ጦር ጥቃት እንዳይፈጽም ወይም ሚሳይል እንዳይተኩስ ጊዜያዊ የመሪዎች ምክር ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል። “ይህንን በዲፕሎማሲ መፍታት አለብን ብዬ አስባለሁ” ብለዋል። ፕሬዝዳንት ፔዜክሽያን በጥቃቶቹ ሳቢያ እየጨመረ የመጣውን የባሕረ ሰላጤው አረብ ሃገራት ቁጣ ለማርገብ ቢሞክሩም፣ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ግን የሚሳኤልና የድሮን ጥቃቶች በዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መፈጸማቸውን ተከትሎ በረራዎችን አስተጓጉለዋል።
የኤሜሬትስ አየር መንገድም በረራ መጀመሩን ከገለጸ ከአንድ ቀን በኋላ በድጋሚ በረራዉ መቋረጡን አስታውቋል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተባለ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ በኩል በጻፉት መልክዕት ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዤሺኪያን ይቅርታ የጠየቁት በኢራን ላይ “ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በፈጸሙት የማያቋርጥ ጥቃት” ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።
DW Amharic

3 months ago