በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ለ3 ቀናት የሚቆይ ክልላዊ የሐዘን ቀን መታወጁን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ገለጹ ፡፡
የአገልግሎቱ ሃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በአደጋው ህይታቸውን ያጡ ወገኖችን ለማሰብ ክልሉ ከመጋቢት 05/2018 ቀን ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሀዘን ቀን እንዲሆን መወሰኑን አስታውቀዋል ፡፡
በናዳ ተቀብረው ከሚገኙት መካከል 4 ተጨማሪ አስክሬን መገኘቱንና የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ እስከአሁን 74 አስከሬን ለማግኘት መቻሉን ነው የአገልግሎቱ ሃላፊ በመግለጫቸው የጠቀሱት ፡፡
በአደጋው የ125 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የጠቀሱት የአገልግሎቱ ኃላፊ “ ቀሪ አስክሬኖችን የማፈላለጉ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል “ ብለዋል ፡፡ አደጋው በደረሰበት አካባቢ የሚገኘው የመንገድ መሠረተ ልማት ምቹ አለመሆን ለተጎጂዎች ሰብዓዊና ቁሳዊ ድጋፍ የማድረስ ሂደቱን ፈታኝ ቢያደርገውም የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝም አቶ ኃይለማሪያ አብራርተዋል ፡፡
በአደጋው ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁት የአገልግሎቱ ኃላፊ በዘላቂነት የሟቋቋሙ ሥራ ጎን ለጎን እንደሚሰራም ተናግረዋል። በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ፣ ካምባ ዙሪያ ፣ ቦንኬ እና አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳዎች ባለፈው ማክሰኞ በተከሰተው የመሬት ናዳ እና የጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪ 3 ሺህ 480 የቤተሰብ አባላት ያሏቸው 575 አባወራና እማወራዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።
DW Amharic

3 months ago