Logo
FIDEL POST NEWS
ዕውቁ ኤርትራዊ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር አስምሮም ለገሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ፕሮፌሰር አስምሮም በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሞ የገዳ ስረዓት ላይ ባደረጉት ምርምር እና ለዓለም በማስተዋወቅ እንደሚታወቁ የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ፕሮፌሰሩ በተለይ በ1960ዎቹ አጋማሽ የዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ስረዓት የሆነውን የኦሮሞ የገዳ ስረዓት ፣ ታሪክ ባህል እና ወግ በማጥናት ቀጥለው ለመጡ ተመራማሪዎች በር መክፈታቸው ይነገርላቸዋል።

በምርምራቸውም በርካታ መጽሃፍት እና ጥናታዊ ዘገባዎችን ማቅረባቸው የሚነገርላቸውን ፕሮፌሰር አስምሮም ለገሰ በ2010 ዓ/ም ለረዥም ዓመታት ካገለገሉት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል።

ፕሮፌሰር አስምሮን ለገሰ ባለትዳር እና የሶስት ልጆች አባት ነበሩ ።

DW Amharic
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.