Logo
YenetaTube
በደሴ ከተማ የቆሻሻ ማከማቻ ስፍራ ላይ በተከሰተ የመደርመስ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ፤ ሁለት ሰዎች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የደሴ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ፅዳትና ዉበት ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀዉ ትናንት እኩለ ቀን ላይ የደረሰዉ የቆሻሻ ክምር መደርመስ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
ከ20አመት በላይ በደሴ ከተማ ለሚወገድ ቆሻሻ የማቃጠያ ስፍራ ሆኖ የሚያገለግለዉ ደምበልቄ በዚህ መልኩ የመደርመስ አደጋ ሲያጋጥመዉ የመጀመሪያ ባይሆንም የሰዉ ህይወት ግን ከዚህ ቀደም እንዳልጠፋበት የገለፁት የአካባቢዉ ኖሪ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ትናንት እኩለ ቀን ላይ የቆሻሻ ናዳዉ የተጫናቸዉን ሰዎች አስከሬን ለማዉጣት እስከ ዛሬ ድረስ ጥረት ብናደርግም አስከሬኑን ማዉጣት አልቻልንም ይላሉ።
የደሴ ከተማ አካባባ ጥበቃ ፅዳትና ዉበት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ሰይድ በበኩላቸዉ አስከሬን የመፈለግ ስራዉ ከአካባቢዉ መንግስት አቅም በላይ ሆኖል ማለታቸውን የደሴው ወኪላችን ኢሳያስ ገላው ዘግቧል።

DW Amharic

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.