በፍሎሪዳ ወደሚገኘው የትራምፕ መኖሪያ ቤት መሳሪያ ይዞ የገባ ግለሰብ መገደሉን የደህንነት መሥሪያ ቤቱ አስታወቀ
የአሜሪካ የደህንነት አገልግሎት ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ቤት «ሊገባ ሞክሯል» ያለውን አንድ መሣሪያ የታጠቀ ግለሰብ ተኩሶ መግደሉን አስታወቀ። ሟች በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኝ ነው ተብሏል።
ግለሰቡ ወደ ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት በሕገ ወጥ መንገድ ለመግባት በሞከረበት በዛሬው ዕለት ትራምፕና ባለቤታቸው በዋሽንግተን ዲሲ እንደነበሩ የደህንነት መሥሪያ ቤቱ አክሏል። የግለሰቡ ማንነትም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ይፋ አለመደረጉን የዘገበው አሶሽየትድ ፕረስ ነው። ይሁንና የሟች ቤተሰቦች ልጃቸው ከ2 ቀናት በፊት መሰወሩን ሪፖርት አድርገው እንደነበረ ዜናው አክሏል።
ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በሐምሌ13 ቀን 2024 በምረጡኝ ዘመቻ ላይ እያሉ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ነበረ። በዚያው ዓመት በመስከረም 15 ደግሞ በዌስትፓልም የባሕር ዳርቻ የጎልፍ ስፖርት በሚጫወቱበት ጊዜ ተመሳሳይ ሙከራ እንደተካሄደባቸውም ይታወቃል። የግድያ ሙከራ አድራጊው በዚህ ወር መጀመሪያ የዕድሜ ይፍታህ እስር ተፈርዶበታል።
DW Amharic

3 months ago