የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን የኢራን ታማኝ ወዳጅ ሆነው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ። ፑቲን ይህን ያስታወቁት ዛሬ የሚከበረውን የኢራን የአዲስ አመት መለወጫ (ኑሩዝ) አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
የሩስያ ፕረዚደንት ፅሕፈት ቤት እንዳለው ፑቲን የመልካም ምኞት መግለጫቸውን ያስተላለፉት ለኢራኑ ከፍተኛ መሪ አያቶላሕ ሙጂታባ ካመኒና ለኢራኑ ፕረዚደንት መሱድ ፔዢሽኪያን ነው።
ፕረዚደንት ፑቲን ለኢራን ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት ደግሞ «ይህን አስቸጋሪ ሁኔታ በፅናት ታልፉታላችሁ ብዬ አምናለሁ፤ ሩስያ የኢራን ታማኝ ወዳጅ ሆና እንደምትቀጥልም እገልጻለሁ» ማለታቸውን የዘገበው ሮይተርስ የዜና ወኪል ነው።
DW Amharic

3 months ago