Logo
YenetaTube
ትራምፕ በፍኖተ ሆርሙዝ የመርከቦች ጉዞን ከኢራን ጋር መቆጣጠር ይሻሉ

ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የፍኖተ ሆርሙዝ ለመርከቦች ክፍት መሆን የተኩስ አቁሙ ስምምነት ቁልፍ ቅድመ ሁኔታ እንደነበር ገለጠች ።

እንደ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጻ፦ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ደሕንነት በማስጠበቅ አብረው ሊሠሩ ይችላሉ ። ይህን በተመለከተም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሲናገሩ፦ በባሕረ ሆርሙዝ የሚያልፉ መርከቦች ደሕንነት በኢራን እና በአሜሪካ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል ።

ፕሬዚደንቱ ለኤቢሲ ኒውስ እንደተናገሩት ከሆነ፦ የመርከቦች ደሕንነትን ለማስጠበቅ በዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን መካከል የጋራ ፕሮጄክትን ለመተግበር እያሰቡበት መሆኑንም ገልጠዋል ።

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ኢራን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የነዳጅ እና የጋዝ ንግድ ወሳኝ መተላለፊያ የሆነውን ፍኖተ ሆርሙዝ ከከፈተች ለሁለት ሳምንታት የቦምብ ድብደባ እና ጥቃት ከመሰንዘር እንደሚቆጠቡ ገልጠው ነበር ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን፦ ኢራን አሁንም በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ የመርከብ ጭነቶችን መቆጣጠርዋን እንደቀጠለች መሆኑ ተዘግቧል ። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በሰጡት መግለጫ መሠረት፣ የመርከቦች ትራፊክ ፍሰት እንደቀድሞው ሁሉ «በኢራን የጦር ኃይሎች ፈቃድ» ተገዢ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል ።

እንደ የባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ገለጻ ደግሞ፦ በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ የሚተላለፉ መርከቦች የትራፊክ ፍሰት ዳግም እየጨመረ ነው ።

DW Amharic

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.