Logo
YenetaTube
ዘጠኝ ስደተኞች በጅቡቲ የባህርዳርቻ ሞቱ

በጁቡቲ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ከትናንት በስተያ የሰመጠች ጀልባ ውስጥ ከነበሩት ስደተኞች ዘጠኙ መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) አስታወቀ። ድርጅቱ እንዳለው ሌሎች 45 ስደተኞች ደግሞ ይኑሩ ይሙቱ አልታወቀም።

አደጋው የደረሰው ከትናንት በስተያ መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሊት ጅቡቲ ከምትገኘው ኦቦክ ከተባለችው ትንሽ ከተማ በስተሰሜን ባለ የባህር ዳርቻ መሆኑን IOM አስታውቋል። ጀልባዋ 320 ሰዎችን አሳፍራ ነበር ።

በፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ መሠረት የምሥራቅ መስመር በሚባለው በዚህ የፍልሰት መንገድ ከሚሰደዱት አብዛኛዎቹ ከኢትዮጵያ የሚመጡ ናቸው። በዚህ መስመር በጎርጎሮሳዊው 2024 ዓ.ም. የ922 ስደተኞች ሕይወት አልፏል። ይህም እስከዛሬ ከተመዘገበው ሞት ከፍተኛው ተብሏል።

DW Amharic

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.