ኢራን በዛሬው ዕለት በኬዌትና በባህሬን የሀይል መሰረተ ልማቶች ላይ ብርቱ ጥቃት መፈጸሟን የየሐገራቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
ኢራን በኩዌት ላይ በፈጸመችው ጥቃት በአንድ የነዳጅ ማጣያ መሰረተ ልማት ላይ ብርቱ ጉዳት ማድረሷን የኩዌት የፔትሮልየም ኮርፖሬሽን ገልጿል።
መንግስታዊው የነዳጅ ኮርፖሬሽን እንዳለው «ኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በኩዌት የሃይል መሰረተ ልማት ላይ አሰቃቂ ጥቃት ፈጽማለች።» ኮርፖሬሽኑ አክሎም «ጥቃቱ በእነዚህ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ቃጠሎ አድርሷል፤ ከፍተኛ ቁሳዊ ጉዳትም አድርሷል።» ነው ያለው።
በተመሳሳይ ዜና ኢራን በባሕሬይን 2 የሃይል መሰረተ ልማቶች ላይም ጥቃት ሰንዝራለች።
በጥቃቱ በሁለቱም የነዳጅ ማጣሪያ መሰረተ ልማቶች ከፍተኛ ቃጠሎ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን በእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ለማወቅ ተችሏል። በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ግን ባሕሬን አስታውቃለች። የዜናዎቹ ምንጭ አዣንስ ፍራንስ ፕረስና የጀርመን ዜና አገልግሎት ናቸው።
DW Amharic

2 months ago