Logo
YenetaTube
አሜሪካ ለመግባት 15 ሺሕ ዶላር፤-ኢትዮጵያም ተጨመረች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር አሜሪካ መግባት በሚፈልጉ የተለያዩ ሐገራት ዜጎች ላይ የጣለዉ የገንዘብ ማስያዢያ ከመጪዉ መጋቢት 24 ጀምሮ ተግባራዊ ሊሆን ነዉ።

የትራምፕ መስተዳድር ከዚሕ ቀደም ባወጣዉ ደንብ የ38 ሐገራት ዜጎች የአሜሪካ ቪዛ ለማግኘት ከሌሎች ነባር መመዘኛዎች በተጨማሪ 15ሺሕ ዶላር እንዲያስዙ ወስኗል።ትናንት ደግሞ የኢትዮጵያን ጨምሮ የሌሎች 12 ሐገራት ዜጎች ከዝርዝሩ ዉስጥ መካተታቸዉን የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።

አብዛኞቹ የአፍሪቃ ሐገራት ናቸዉ
ከመጋቢት 24 ጀምሮ ገቢር ይሆናል በተባለዉ ደንብ መሠረት የ50ዎቹ ሐገራት ዜጎች ለሥራና ሐገር ለመጎብኘት የሚያገለግለዉን B1 እና B2 የተባለዉን ቪዛ ለማግኘት 15 000 ዶላር ማስያዝ አለባቸዉ።ተጓዞቹ ወደየሐገራቸዉ ሲመለሱ ማስያዢያዉ ይመለሳል ተብሏል።

DW Amharic

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.