22 days ago
ሻምፒዮኑ አርሰናል ሲያሸንፍ፣ ዌስትሀም ወረደ ቶተንሀም ተረፈ
ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀው የመድፈኞቹ የዋንጫ ጥማት ዛሬ በደመቀ ሁኔታ ተቋጭቷል።
አርሰናል በ38ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታው ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን የክብር አክሊል ይረከባል።
በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ገብርኤል ጀሱስ ያስቆጠራት ግብ የድሉን መንገድ የጠረገች ሲሆን፤ ቡድኑ እስከ ጨዋታው ፍጻሜ ድረስ ብቃቱን በማስመስከር የለንደን ጎዳናዎችን በደስታ እና በእልልታ እንዲሞሉ አድርጓል።
በሌሎች የዛሬው የመጨረሻ ሳምንት መርሃ ግብሮች ማንቸስተር ሲቲ በአስቶን ቪላ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲሸነፍ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ብራይተንን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ረቷል።
ዌስትሃም ሊድስን በ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም ወደታችኛው ሊግ ወርዷል።
ቶተንሃም ኤቨርተንን 1 ለ 0 አሸንፎ በሊጉ መቆየት ችሏል።
በሌላ በኩል ሊቨርፑል ከብሬንትፎርድ ጋር 1 ለ 1፣ ፉልሃም ኒውካስትልን 2 ለ 0፣ ሰንደርላንድ ቼልሲን 2 ለ 1 በማሸነፍ ያልተጠበቀ ውጤት አስመዝግቧል።
በርንሌይ ከዎልቭስ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከቦርንማውዝ ጋር 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት የውድድር ዘመኑን አጠናቀዋል።
Seledadotio

1 month ago
ቶተንሀም ሆትስፐር ከሊድስ ዩናይትድ ጋር አቻ ተለያየ
***********
በ36ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቶተንሀም ሆትስፐር ከሊድስ ዩናይትድ አንድ አቻ ተለያይቷል።
ማቲያስ ቴል ለቶተንሀም ሆትስፐር፣ ዶሚኒክ ካልቨርት ሌዊን ደግሞ በፍጹም ቅጣት ምት ለሊድስ ዩናይትድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ቶተንሀም ሆትስፐር ከጨዋታው አንድ ነጥብ ማግኝቱን ተከትሎ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ከሚገኘው ዌስትሀም ዩናይትድ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ከፍ አድርጓል።
በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው ሊድስ ዩናይትድ ነጥቡን 44 በማድረስ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቶተንሀም ሆትስፐር ደግሞ በ38 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
#ebc #football #premierleague #englishpremierleague

ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል
************
በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ ዛሬ 11 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ትላንት በተደረገው ጨዋታ ብራይተን በኒውካስትል ዩናይትድ መሸነፉን ተከትሎ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ያረጋገጠው ማንችስተር ዩናይትድ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ለማረጋገጥ ከሚታገለው ሊቨርፑል ይጫወታል፡፡
ከዩናይትድ በሦስት ነጥብ ዝቅ ብሎ በ58 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የመርሲሳይዱ ክለብ፣ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን በይፋ የሚያረጋግጥ ይሆናል። ዩናይትድ ከሊቨርፑል ጋር በተገናኘባቸው ያለፉት 19 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ሦስቱን ብቻ ሲሆን፣ በኦልድ ትራፎርድ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎችም በሦስቱ ተሸንፏል፡፡
ማይክል ካሪክ ሩብን አሞሪምን ተክቶ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ከመጣ በኋላ፣ እንደ እሱ ብዙ ነጥብ የሰበሰበ አሰልጣኝ በሊጉ የለም። ለዛሬው ጨዋታ ማቲያስ ኩኛ ከጉዳቱ በማገገሙ ሊሰለፍ ይችላል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ሉክ ሾውም በተመሳሳይ ወደ ሜዳ ሊመለስ ይችላል። ሆኖም ማቲያስ ዴሊክት ልምምድ ቢጀምርም በዛሬው ስብስብ ውስጥ እንዳልተካተተ ማይክል ካሪክ አረጋግጠዋል።
በሊቨርፑል በኩል በርካታ የጉዳት ያሉ ሲሆን ግብ ጠባቂዎቹ አሊሰን ቤከር እና ጆርጂ ማማርዳሽቪል በጉዳት ከቡድኑ ውጭ በመሆናቸው፣ ሦስተኛው ግብ ጠባቂ ፍሬዲ ውድማን በቋሚነት የሚሰለፍ ይሆናል። በተጨማሪም ሞሃመድ ሳላህ፣ ሁጎ ኢኪቲኬ እና ኮኖር ብራድሊ በጉዳት ምክንያት ከዛሬው ስብስብ ውጭ ናቸው። ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ለ244ኛ ጊዜ ይገናኛሉ፡፡
በሊጉ ለመቆየት እየታገለ የሚገኘው ቶተንሀም ሆትስፐር ምሽት 3 ሰዓት ላይ ከሜዳው ውጭ ከአስቶን ቪላ ጋር ይጫወታል። በ34 ነጥብ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው የሰሜን ለንደኑ ክለብ፣ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት ከሚታገለው አስቶን ቪላ ሌላ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።
ዌስትሃም ትላንት በብሬንትፎርድ መሸነፉን ተከትሎ፣ ቶተንሃም ዛሬ ካሸነፈ ከወራጅ ቀጠናው የመውጣት ዕድል ይኖረዋል። ሆኖም ስፐርስ ዛሬም እንደ ሞሃመድ ኩዱስ፣ ቤን ዴቪስ፣ ቪካሪዮ እና ክርስቲያን ሮሜሮ ያሉ ወሳኝ ተጫዋቾችን በጉዳት ምክንያት የማይጠቀም ይሆናል። በተጨማሪም 10 ሰዓት ላይ ቦርንማውዝ ከክሪስታል ፓላስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በአንተነህ ሲሳይ
#ethiopiabroadcastingcorporation #epl #manchesterunited #liverpool

ለዋንጫ የሚሆን በቂ ነዳጅ አለን፡- የቬንገርን ሪከርድ ለመስበር የሚጫወተው ሚኬል አርቴታ
********************
በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሊጉ መሪ አርሰናል በለንደን ደርቢ ዛሬ በሜዳው ከፉልሀም ይጫወታል፡፡ ከሁለት የሊጉ ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ባለፈው ሳምንት ኒውካስትልን በማሸነፍ ወደ ድል የተመለሰው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ወደ ዋንጫው ለመቅረብ በሚያደርገው ጨዋታ ከፉልሀም ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡
ጨዋታው ምሽት 1 ሰዓት ከ 30 ላይ በኤምሬትስ የሚደረግ ሲሆን አርሰናል በሜዳው ከፉልሀም ባደረጋቸው ያለፉት 32 ጨዋታዎች አልተሸነፈም፡፡ 25 ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ በሰባቱ አቻ ተለያይቷል፡፡ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከ20 ዓመት በኋላ ለፍጻሜ ለመድረስ ከአትሌቲኮ ማድሪድ አንድ የ90 ደቂቃ ፍልሚያ ብቻ የሚቀረው አርሰናል ዛሬ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ ካሸነፍ የማንችስተር ሲቲ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እንደተጠበቁ ሆነው የነጥብ ልዩነቱን ወደ ስድስት ከፍ የሚያደርግ ይሆናል።
ከወሳኙ ጨዋታ በፊት ሚኬልል አርቴታ በሰጠው ሃሳብ አርሰናል ለዋንጫ የሚያበቃው ነዳጅ (አቅም) አለው ብሏል፡፡ ስፔናዊው አሰልጣኝ “ሊጉ ሊጠናቀቅ አራት ጨዋታዎች ሲቀሩት መገኘት ያለብን ደረጃ ላይ ተገኝተናል ለሁሉም ፈተና ዝግጁ ነን በውድድር ዓመቱ ሁሉ ስናደርግ የነበረውን የማሸነፍ ፍላጎት ይዘን እስከ መጨረሻው እንጓዘለን” ብሏል፡፡ ደጋፊዎች በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ላይ ለተጫዋቾች የሚያሳዩት አዎንታዊ ድጋፍ ውጤቱን ይበልጥ የተሻለ እንደሚያደርገውም ገልጿል፡፡
በሌላ በኩል፣ ሚኬል አርቴታ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ በአንድ የውድድር ዓመት አርሰን ቬንገር ካስመዘገቡት የድል ብዛት በላይ በማሸነፍ በክለቡ አዲስ ታሪክ ይጽፋል። ፈረንሳዊው አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በ2001/02 የውድድር ዓመት በ60 ጨዋታዎች 39 ድሎችን ያስመዘገቡ ሲሆን፤ አርቴታ በበኩሉ በዘንድሮው የውድድር ዓመት እስካሁን ባደረጋቸው 57 ጨዋታዎች 39ኙን በማሸነፍ የአንጋፋውን ሰው ታሪክ ተጋርቷል። በመሆኑም ዛሬ ፉልሃምን ማሸነፍ የሚችል ከሆነ የቬንገርን የቆየ ክብረ ወሰን በማሻሻል በክለቡ ታሪክ በአንድ የውድድር ዓመት ብዙ ጨዋታዎችን ያሸነፈ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሆኖ ስሙን በደመቀ ሁኔታ ይጽፋል።
የፉልሀሙ አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ እንዲህ አይነት ጨዋታዎችን ማድረግ ያስደስተኛል በመሆኑም ለዋንጫ ከሚፋለመው አርሰናል የምንጫወተው ሦስት ነጥብ ለማግኝት ነው ብለዋል፡፡ በጨዋታው ካይ ሀቨርዝ እና ዩሪየን ቲምበር በጉዳት ከስብስቡ ወጭ ሲሆኑ ማርቲን ኦዴጋርድ ለጨዋታው እንደሚደርስ ሚኬል አርቴታ ተናግሯል፡፡
በሌላ ጨዋታ በሊጉ ለመቆየት እየታገለ የሚገኘው ዌስትሀም ዩናይትድ 11 ሰዓት ላይ ከሜዳው ወጭ ከብሬንትፎርድ ይጫወታል፡፡ በ36 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ዌስትሀም ከባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች የተሸነፈው በአንዱ ብቻ ሲሆን 18ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቶተንሀም እንዳይደርስበት የሚፋለም ይሆናል፡፡
ኒውካስትል ዩናይትድ ከብራይተን እና ከሊጉ መሰናበቱን ያረጋገጠመው ዎልቭስ ከሰንደርላንድ በተመሳሳይ 11 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
በአንተነህ ሲሳይ
#ethiopiabroadcastingcorporation #epl #arsenal #fulham

Sponsored by
Surafel
3 months ago
የዛሬው የደመቀ የእግር ኳስ ምሽት! ⚽️
#ethiopia | በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ መድረክ ተጠባቂ የሆኑ ታላላቅ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፍልሚያዎች ከሰዓት በጉጉት ሲጠበቁ፣ ምሽቱን ደግሞ የአውሮፓ ሀያላን ክለቦች እርስ በእርስ የሚፋለሙበት ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች ዝርዝር፦
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ
* 10:00 | አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ
* 10:00 | ሀዋሳ ከተማ ከ መቐለ 70 እንደርታ
በዓለም አቀፍ መድረክ
* 2:45 | ጋላታሳራይ ከ ሊቨርፑል
* 5:00 | አታላንታ ከ ባየር ሙኒክ
* 5:00 | አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ቶተንሀም
* 5:00 | ኒውካስል ዩናይትድ ከ ባርሴሎና
ለኳስ አፍቃሪያን ድንቅ ምሽት ይሁንላችሁ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopianpremierleague #football #matchday #liverpool #barcelona #bayernmunich #sportsnews #አዳማ #ሀዋሳ #የዛሬጨዋታዎች

4 months ago
🏆 የሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ዕጣ ዛሬ ይወጣል፦ የአውሮፓ ነገሥታት ይፋለማሉ! ⚽️🔥
#ethiopia | ዛሬ በስዊዘርላንድ ኒዮን የሚወጣው የሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ድልድል፣ ከወዲሁ የእግር ኳስ ዓለምን ትኩሳት ከፍ አድርጎታል። ስድስት ክለቦችን ይዞ የመጣው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበላይነቱን ሲይዝ፣ ላሊጋ በሦስት ክለቦች ይከተላል።
በጉጉት የሚጠበቁ ድልድሎች (Scenarios)፦
ዛሬ በሚወጣው ዕጣ የሚከተሉት ትልልቅ ክለቦች የመገናኘት ዕድላቸው ሰፊ ነው ተብሏል፦
ሪያል ማድሪድ 🆚 ማንችስተር ሲቲ ወይም ስፖርቲንግ ሊዝበን
ፒኤስጂ 🆚 ባርሴሎና ወይም ቼልሲ
አታላንታ 🆚 አርሰናል ወይም ባየር ሙኒክ
ኒውካስትል 🆚 ባርሴሎና ወይም ቼልሲ
ጋላታሳራይ 🆚 ሊቨርፑል ወይም ቶተንሀም
የአርሰናል እና የባየር ሙኒክ ልዩ ሁኔታ፦
በምድብ ጨዋታዎች ሁሉንም ያሸነፈው አርሰናል እና በደረጃ ሰንጠረዡ 2ኛ የነበረው ባየር ሙኒክ፣ እስከ ግማሽ ፍጻሜው ቢጓዙ እንኳ ሁሉንም የመጀመሪያ ጨዋታዎቻቸውን ከሜዳቸው ውጭ (Away) የሚያደርጉ ይሆናል።
📅 የጨዋታ ቀናት፦
የመጀመሪያ ጨዋታዎች፦ በሚያዚያ ወር መጀመሪያ።
የመልስ ጨዋታዎች፦ ከመጀመሪያው ጨዋታ ከስምንት ቀናት በኋላ።
#ucldraw #championsleague #realmadrid #mancity #arsenal #fcbarcelona #bayernmunich #footballethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

አርሰናል ቶተንሀምን 4 ለ 1
#ethiopia | 199ኛው የሰሜን ለንደን ደርቢ በአርሰናል ፍጹም የበላይነት ተጠናቋል። የሊጉ መሪ አርሰናል ከሜዳው ውጭ ባደረገው በዚህ ታላቅ ፍልሚያ፣ ተቀናቃኙን 4 ለ 1 በማሸነፍ ለ22 ዓመታት የናፈቀውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ለማንሳት አንድ ትልቅ እርምጃ ወደፊት ተራምዷል።
የጨዋታው ኮከቦች፦
ኤቤሬቺ ኤዜ፦ በክረምቱ ቶተንሀምን አልፈልግም ብሎ አርሰናልን የመረጠው ኤዜ፣ ዛሬም በሁለት ድንቅ ግቦች የቀድሞ ፈላጊዎቹን አስለቅሷል። ኤዜ በሁለት ጨዋታዎች ብቻ በቶተንሀም ላይ 5 ግቦችን በማስቆጠር "የደርቢው ንጉሥ" መሆኑን አረጋግጧል።
ቪክቶር ዮኬሬስ፦ የንጉሥ ቲየሪ ሄንሪን ቁጥር 14 መለያ የለበሰው ስዊዲናዊው አጥቂ፣ ቀሪዎቹን ሁለት ግቦች በማስቆጠር የሰሜን ለንደንን ድል አድምቋል።
የደረጃ ሰንጠረዡ ለውጥ፦
አርሰናል፦ በ61 ነጥብ መሪነቱን ሲያጠናክር፣ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 5 አስፍቷል።
ቶተንሀም፦ በሜዳው ካደረጋቸው 14 ጨዋታዎች 12ቱን ማሸነፍ ያልቻለው ቶተንሀም፣ በ29 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ የመውረድ ስጋት ውስጥ ይገኛል።
ትንታኔ፦
አርሰናል ካለፉት ሁለት ጨዋታዎች መደናቀፍ በኋላ በዚህ ደረጃ ተመልሶ መምጣቱ ለዋንጫው ያለውን ብቁነት ያሳየበት ነው። በተቃራኒው ቶተንሀም በሜዳው የሚያሳየው ደካማ አቋም እና በአርሰናል ፍጹም የበላይነት መወሰዱ በክለቡ ላይ ትልቅ ቀውስ መኖሩን ያሳያል።
የእርስዎ አስተያየት፦
"ሰሜን ለንደን ቀይ ናት!" ለማለት አሁን ትክክለኛው ጊዜ ነው? አርሰናል በዚህ ብቃቱ ዋንጫውን የሚያነሳ ይመስላችኋል? ቶተንሀምስ ከውርደት ይተርፋል?
#northlondonderby #arsenal #coyg #eze #gyokeres #premierleague #tottenham #footballanalysis #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

🏟️ የለንደን ደርቢ፡ እረፍት ላይ !
#ethiopia | በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሰሜን ለንደን ደርቢ የመጀመሪያ አጋማሽ ተጠናቆ፣ ሁለቱ ተቀናቃኞች 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።
ምንም እንኳን መድፈኞቹ በኳስ ቁጥጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ቢበልጡም፣ ስፐርሶች ባገኙት አጋጣሚ ግብ በማስቆጠር ጨዋታውን ሚዛናዊ ማድረግ ችለዋል።
⚽ የግብ አግቢዎች
* አርሰናል፡ ኢዜ (Eze) መሪ የሚያደርጋቸውን ግብ አስቆጥሯል።
* ቶተንሀም፡ ኮሎ ሙኣኒ (Kolo Muani) ለስፐርሶች የአቻነቷን ግብ መረብ ላይ አሳርፏል።
📊 የጨዋታው ቁጥራዊ መረጃዎች
የመጀመሪያው አጋማሽ የአርሰናል የፍፁም ብልጫ የታየበት ነበር፦
* የኳስ ቁጥጥር፡ አርሰናል 73% — 27% ቶተንሀም
ማስታወሻ፦ አርሰናል ኳሱን መቆጣጠር ቢችልም፣ ቶተንሀም በመልሶ ማጥቃት አደገኛ መሆኑን አሳይቷል።
🟨 የማስጠንቀቂያ ካርዶች
ጨዋታው እንደ ደርቢነቱ ግለት የታየበት ሲሆን፣ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ተጫዋቾች በቢጫ ካርድ ተቀጥተዋል፦
* ጁሪየን ቲምበር (አርሰናል)
* አርቺ ግሬይ (ቶተንሀም)
በሁለተኛው አጋማሽ የትኛው ቡድን የበላይነቱን ይወስድ ይሆን? አብረን የምናየው ይሆናል!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #premierleague #northlondonderby #arsenal #tottenham #epl #footballnews

ከሀገር ውስጥ እስከ አውሮፓ ያሉ ተጠባቂ ፍልሚያዎችን በዝርዝር አቀናጅተንላችኋል
#ethiopia | 🇪🇹 የሀገር ውስጥ ታላላቅ ፍልሚያዎች በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና በከፍተኛ ሊግ ደረጃ ዛሬ በጉጉት የሚጠበቁ ጨዋታዎች አሉ።
* 9:00 | አርባምንጭ ከተማ 🆚 ነገሌ አርሲ
* 9:00 | ሀዋሳ ከተማ 🆚 ድሬዳዋ ከተማ (የሁለቱ ከተማዎች ፉክክር!)
* 12:00 | ሲዳማ ቡና 🆚 ወልዋሎ አዲግራት ዩ.
* 12:00 | ሸገር ከተማ 🆚 ኢትዮ ኤሌክትሪክ
🏴 እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ
የሊጉ ፉክክር እያየለ ባለበት በዚህ ሰዓት፣ በተለይ የሰሜን ለንደኑ ደርቢ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።
* 11:00 | ኖቲንግሃም ፎረስት 🆚 ሊቨርፑል (ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ሶስት ነጥብ ያገኝ ይሆን?)
* 1:30 | ቶተንሀም 🆚 አርሰናል (የቀኑ ትልቁ ጨዋታ—ለንደን በማን ትቀላለች?)
🇮🇹 የጣሊያን ሴሪ አ
የታክቲክ ፍልሚያ የሚበዛባቸው የጣሊያን ጨዋታዎች ዛሬም ይቀጥላሉ።
* 11:00 | አታላንታ 🆚 ናፖሊ (ጥቃት ማጥቃት!)
* 2:00 | ኤሲ ሚላን 🆚 ፓርማ
* 4:45 | ሮማ 🆚 ክሪሞኔንስ
🇪🇸 የስፔን ላ ሊጋ
* 12:15 | ባርሴሎና 🆚 ሌቫንቴ (ባርሳ ውጤቱን ለማስጠበቅ ወደ ሜዳ ይገባል)
ማሳሰቢያ፦ ሰዓቶቹ በኢትዮጵያ አቆጣጠር መሆናቸውን ልብ ይበሉ። የዛሬው የለንደን ደርቢ (ቶተንሀም ከ አርሰናል) ውጤት ምን ሊሆን ይችላል ብለው ይገምታሉ?
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #የዛሬጨዋታ #የእግርኳስዜና #ethiopianpremierleague #premierleague #arsenal #tottenham #liverpool #barcelona #footballupdate

የሰሜን ለንደን ደርቢ
የሁለት ዓለም ሰዎች ፍልሚያ
ዛሬ ምሽት 1፡30 ላይ መላው ለንደን ብቻ ሳይሆን የእግር ኳስ ዓለም አይኑን ወደ ሰሜን ለንደን ያደርጋል። የማይታረቁት ጎረቤታሞች አርሰናል እና ቶተንሀም ሆትስፐር ለ199ኛ ጊዜ ፊት ለፊት ይገናኛሉ።
🏆 አርሰናል፦ ዋንጫ ወይንስ መደናቀፍ?
መድፈኞቹ ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለመሳም እጅግ ተቃርበዋል። ሆኖም ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ነጥብ መጣላቸው በአርቴታ ልጆች ላይ ጥያቄ አስነስቷል። ለዛሬው ጨዋታ ቁልፍ ተጫዋቾቻቸው ኦዴጋርድና ካይ ሃቨርዝ ከጉዳት መመለሳቸው ትልቅ እፎይታ ቢሆንም፣ የደርቢ ጨዋታ ስነ-ልቦናዊ ጫናው ሌላ ፈተና ነው።
📉 ቶተንሀም፦ የመትረፍ ተጋድሎ!
በታሪኩ አስከፊ የሚባል የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ቶተንሀም፣ ወራጅ ቀጠናው አፋፍ ላይ ይገኛል። አዲሱ አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር በሜዳቸው እጅግ ደካማ የሆነውን የክለቡን ታሪክ ቀይረው አርሰናልን በማደናቀፍ ለደጋፊዎቻቸው ደስታን ለመስጠት ይገባሉ።
📊 ቁልፍ እውነታዎች፦
የአርሰናል የበላይነት፦
መድፈኞቹ ካለፉት 7 የደርቢ ጨዋታዎች 6ቱን አሸንፈዋል።
የሜዳ መርገም፦
ቶተንሀም ዘንድሮ በሜዳው ካደረጋቸው 13 ጨዋታዎች ያሸነፈው 2ቱን ብቻ ነው።
የተጫዋቾች ዜና፦
ቶተንሀም ቁልፍ ተከላካዩን ክርስቲያን ሮሜሮን በቅጣት ያጣ ሲሆን፣ አርሰናል ግን ሙሉ ጥንካሬውን ይዞ ይቀርባል።
የአሰልጣኞች አስተያየት፦
ሚካኤል አርቴታ፦
"ትኩረታችን ደርቢው ላይ ነው፤ ገና ረጅም መንገድ ይቀረናል!"
ኢጎር ቱዶር፦
"ይህ ጨዋታ ምን ማለት እንደሆነ እረዳለሁ፤ ሁሉም እኛን እየጠበቀ ነው!"
የእርስዎ ግምት፦
የዛሬው ጨዋታ ለማን ይሳካል? አርሰናል የዋንጫ ግስጋሴውን ይቀጥላል ወይንስ ቶተንሀም በደርቢው ድል ከውርጅ ስጋት ይላቀቃል? ግምታችሁን በኮሜንት አጋሩን። 👇
#northlondonderby #arsenal #tottenham #epl #footballnews #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

የሰሜን ለንደን ደርቢን ትኩሳት የሚያቀጣጥል አስተያየት ከአዲሱ የቶተንሀም አለቃ!
#ethiopia | የቶተንሀም ሆትስፐሩ አዲሱ አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር፣ በጉጉት ለሚጠበቀው የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ ቡድናቸው ያለውን ዝግጁነት እና የሚከተለውን የጨዋታ እቅድ በልበ ሙሉነት ይፋ አድርገዋል።
"አርሰናልን ለመግጠም በድፍረት እንገባለን!"
ቱዶር ይህ ጨዋታ ለክለቡ እና ለደጋፊው ያለውን ትልቅ ዋጋ በመገንዘብ፣ "በጣም አስፈላጊ እና ለመጫወት የሚያስደስት ጨዋታ ነው" ሲሉ ገልጸውታል። አሰልጣኙ አክለውም ቡድናቸው ወደ ሜዳ ሲገባ ተሽቆጥቁጦ ሳይሆን፣ ደጋፊው በሚወደውና በሚኮራበት መንገድ እንደሚሆን ቃል ገብተዋል።
የአሰልጣኙ የጨዋታ ፍልስፍና ምን ይመስላል?
* ማጥቃት፣ ማጥቃት፣ ማጥቃት!
ቱዶር የእግር ኳስ ፍልስፍናቸውን ሲያስረዱ፣ "የመጀመሪያው አላማዬ በማጥቃት ላይ የተመሰረተ እግር ኳስ መጫወት ነው፤ ይህም እኔን ያስደስተኛል" በማለት በደርቢው ላይም ይህንኑ አጥቂ አጨዋወት እንደሚተገብሩ ጠቁመዋል።
* ድፍረት ከብልሃት ጋር
ጨዋታውን ለማሸነፍ ባዶ "ድፍረት" ብቻ በቂ እንዳልሆነ ያመላከቱት አሰልጣኙ፣ "ወደ ሜዳ የምንገባው በድፍረት ነው፤ ነገር ግን ይህ ድፍረት ከብልሃት እና ከክህሎት ጋር የተዋሃደ መሆን አለበት" በማለት ታክቲካዊ ዝግጁነታቸውን አሳይተዋል።
በመጨረሻም ኢጎር ቱዶር የጨዋታውን ግብ ሲያጠቃልሉ፣ "ወደ ሜዳ የምንገባው የምንፈልገውን ለማሳካት ነው፤ የምንፈልገው ደግሞ ግልጽ ነው - ማሸነፍ!" ሲሉ ለመድፈኞቹ የማስጠንቀቂያ ደወል አሰምተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nld #northlondonderby #tottenham #arsenal #igortudor #premierleague #coys #spurs #ethiopiasports

🔴 ኦልድ ትራፎርድ በድል ደምቋል!
ማይክል ካሪክ የዩናይትድን ትንሳኤ እያበሰረ ነው! 🏟️⚽️
ማንችስተር ዩናይትድ 2 - 0 ቶተንሀም ሆትስፐር
#ethiopia | በ25ኛ ሳምንት የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድ ትራፎርድ ቶተንሀምን አስተናግዶ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በመርታት የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ተስፋውን አጠናክሯል።
የጨዋታው ወሳኝ ኩነቶች:
⚽️ ጎሎች: የዩናይትድን የድል ጎሎች ብሪያን ምቤሞ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ አስቆጥረዋል።
🟥 ቀይ ካርድ: የቶተንሀሙ ክርስቲያን ሮሜሮ በ29ኛው ደቂቃ ካስሜሮ ላይ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ይህም ለስፐርሶች የዓመቱ 10ኛ ሽንፈት ምክንያት ሆኗል።
የማይክል ካሪክ ተፅእኖ:
ሩብን አሞሪምን ተክቶ የመጣው ማይክል ካሪክ፤ ቡድኑን እየመራ በኦልድ ትራፎርድ 4ኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።
የካሴሚሮ ሚልስቶን:
በዓመቱ መጨረሻ ክለቡን እንደሚለቅ ያሳወቀው ብራዚላዊው አማካይ ካስሜሮ፤ በፕሪሚየር ሊጉ 100ኛ ጨዋታውን በዚህ ድል አጅቦ አድርጓል።
የካሪክን አሰልጣኝነት እንዴት አያችሁት? ዩናይትድ ወደ ቀድሞ ክብሩ እየተመለሰ ነው?
ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡ! 👇
#manutd #ggmu #pl #michaelcarrick #brunofernandes #mbeumo #oldtrafford #football #win #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

የዛሬ ጨዋታዎች
🇪🇹 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የጥሎ ማለፍ ፍልሚያዎች
የአገር ውስጥ እግር ኳስ ዛሬ በታላላቅ ክለቦች ግጥሚያ ይሞቃል። በተለይ በ "አፄዎቹ" እና በ "ፈረሰኞቹ" መካከል የሚደረገው ጨዋታ የሁሉንም ትኩረት ስቧል።
* 07:00 | ወልዋሎ አዲግራት ዩ. ከ አርባምንጭ ከተማ
* 09:00 | መቐለ 70 እንደርታ ከ ኢትዮጵያ ቡና
* 10:00 | ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ተጠባቂው የሳምንቱ ጨዋታ)
* 12:00 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ነጌሌ አርሲ
🏴 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ
በእንግሊዝ ሊግ ዛሬ የምሽቱ ማሳረጊያ የሚሆነው በቶተንሀም እና በማንችስተር ሲቲ መካከል የሚደረገው ፍልሚያ ነው። ፔፕ ጋርዲዮላ ወደ ሰሜን ለንደን የሚያቀኑት ወሳኝ ነጥብ ፍለጋ ነው።
* 11:00 | አስቶን ቪላ ከ ብሬንትፎርድ
* 11:00 | ማንችስተር ዪናይትድ ከ ፉልሀም
* 01:30 | ቶተንሀም ከ ማንችስተር ሲቲ
🇪🇸 ላ ሊጋ እና 🇮🇹 ሴሪ አ
በስፔን ሪያል ማድሪድ የደረጃ ሰንጠረዡን ለመምራት ራዮን ያስተናግዳል፤ በጣሊያን ደግሞ ጁቬንቱስ እና ኢንተር ሚላን የድል ጉዟቸውን ለመቀጠል ወደ ሜዳ ይገባሉ።
* 10:00 | ሪያል ማድሪድ ከ ራዮ ቫይካኖ
* 11:00 | ኮሞ ከ አታላንታ
* 02:00 | ክሪሞኔንሴ ከ ኢንተር ሚላን
* 04:45 | ፓርማ ከ ጁቬንቱስ
መልካም የኳስ ምሽት ይሁንላችሁ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopianpremierleague #premierleague #laliga #seriea #matchday #footballethiopia #realmadrid #mancity #saintgeorgesa

5 months ago
የአርሰናል አስደናቂ የጥሎ ማለፍ ትኬት
ውጤት፡ አርሰናል 3 - 1 ኢንተር ሚላን (በሚላን ሜዳ)
#ethiopia | ጋብርኤል ጄሱስ (2 ግቦች) እና ተቀይሮ የገባው ቪክቶር ዮኬሬስ (1 ግብ) ለአርሰናል አስቆጥረዋል፡፡ የኢንተርን ብቸኛ ግብ ያገባው ፔትራ ሱቺች ነው፡፡
አርሰናል ያደረጋቸውን 7ቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ በ21 ነጥብ ምድቡን እየመራ ወደ ጥሎ ማለፉ ማለፉን አረጋግጧል፡፡
ጠንካራ መከላከል፡ በሰባት ጨዋታዎች የተቆጠረባቸው 2 ግቦች ብቻ ናቸው፡፡
የሪያል ማድሪድ የጎል ዝናብ
ውጤት፡ ሪያል ማድሪድ 6 - 1 ሞናኮ
ኮከብ ተጫዋች፡ ኪሊያን ምባፔ በልጅነት ክለቡ ላይ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡ ቪኒሺየስ ጁኒየር፣ ጁድ ቢሊንግሀም እና ማስታንቱኖ ተጨማሪ ግቦችን ሲያስቆጥሩ አንድ ግብ በሞናኮ ተጫዋች (Own Goal) ተቆጥሯል፡፡
የሌሎች ጨዋታዎች ውጤቶች
ቶተንሀም 2 - 0 ቦርሲያ ዶርትሙንድ
ስፖርቲንግ ሊዝበን 2 - 1 ፒኤስጂ
አያክስ 2 - 1 ቪያሪያል
ኦሎምፒያኮስ 2 - 0 ባየር ሊቨርኩሰን
ናፖሊ 1 - 1 ኮፐንሀገን
አርሰናል እያሳየ ባለው ወቅታዊ እና የማይሸነፍ ብቃት የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን የማንሳት እድሉ ምን ያህል ነው ብለው ይገምታሉ?

የዛሬው የእግር ኳስ ድግስ፦ የደርቢዎች እና የሀያላን ፍልሚያ
#ethiopia | ዛሬ ቅዳሜ የእግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቁት ልዩ ቀን ነው። በሀገር ውስጥ ሊግ እና በአውሮፓ ታላላቅ መድረኮች የሚደረጉትን ጨዋታዎች በሰዓት ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ቀርበዋል፦
🇪🇹 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የአፍሪካ ፍልሚያ
በሀገር ውስጥ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች ሲደረጉ፣ በብሔራዊ ቡድን ደረጃም የግብፅ እና ናይጄሪያ ጨዋታ ትኩረት ይስባል።
* 7:00 | አርባ ምንጭ ከተማ 🆚 መቻል
* 9:00 | ኢትዮጵያ ቡና 🆚 ሀዋሳ ከተማ
* 10:00 | ቅዱስ ጊዮርጊስ 🆚 ድሬዳዋ ከተማ
* 12:00 | አዳማ ከተማ 🆚 ሲዳማ ቡና
* 1:00 | ግብፅ 🆚 ናይጄሪያ (የአፍሪካ ሀያላን ፍልሚያ)
🏴 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ (የማንችስተር ደርቢ!)
የዛሬው ቀዳሚ ትኩረት በታላቁ የማንችስተር ደርቢ ላይ ያርፋል
* 9:30 | ማንችስተር ዩናይትድ 🆚 ማንችስተር ሲቲ (ተጠባቂው ደርቢ)
* 12:00 | ቼልሲ 🆚 ብሬንትፎርድ
* 12:00 | ሊቨርፑል 🆚 በርንሌይ
* 12:00 | ቶተንሀም 🆚 ዌስትሀም ዩናይትድ
* 2:30 | ኖቲንግሃም ፎሬስት 🆚 አርሰናል
🇪uropean Giants (ሌሎች የአውሮፓ ሊጎች)
በስፔን፣ ጣሊያን እና ጀርመን ታላላቅ ክለቦች ወደ ሜዳ ይገባሉ።
* 10:00 | ሪያል ማድሪድ 🆚 ሌቫንቴ
* 11:00 | ዩዴኒዜ 🆚 ኢንተር ሚላን
* 2:00 | ናፖሊ 🆚 ሳሱሎ
* 2:30 | ሌፕዚግ 🆚 ባየር ሙኒክ (የጀርመን ሀያላን)
* 4:45 | ካግሊያሪ 🆚 ጁቬንቱስ
ለመሆኑ የእርስዎ ክለብ ዛሬ ይሸነፍ ይሆን ወይስ ያሸንፍ? ግምታዊ ውጤትዎን በልቦናዎ ይያዙ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#እግርኳስ #የዛሬጨዋታዎች #ማንችስተርደርቢ #ኢትዮጵያፕሪሚየርሊግ #አርሰናል #ሪያልማድሪድ #ሊቨርፑል #footballday #derbyd

⚽ ከሀገር ቤት እስከ አውሮፓ ሜዳዎች
#ethiopia | ዛሬ ቅዳሜ የእግር ኳስ አፍቃሪው አይኑን ከስክሪን ላይ የማይነቅልበት ልዩ ዕለት ነው። በሜዳችንም ሆነ በባህር ማዶ የሚደረጉ ጨዋታዎች ትልቅ ግምት ተሰጥቷቸዋል።
🇪🇹 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
የሀገር ውስጥ ሊጉ በደማቅ ፍልሚያዎች ተሞልቷል። በተለይ በ9:00 እና በ10:00 የሚደረጉት ጨዋታዎች የሊጉን መሪነትና ደረጃ ለመቀየር ትልቅ ሚና አላቸው።
* 7:00 | መቻል 🆚 ባሕርዳር ከተማ
* 9:00 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 🆚 ሀድያ ሆሳዕና
* 10:00 | ፋሲል ከነማ 🆚 ኢትዮጵያ ቡና (ተጠባቂ)
* 12:00 | ወላይታ ድቻ 🆚 ኢትዮጵያ መድን
🏴 በእንግሊዝ ሜዳዎች (ኤፍ ኤ ካፕ/ሊግ)
በእንግሊዝ ታላላቆቹ ክለቦች ማንችስተር ሲቲ፣ ቶተንሀም እና ቼልሲ ወደ ሜዳ የሚገቡበት ምሽት ነው።
* 9:15 | ኤቨርተን 🆚 ሰንደርላንድ
* 12:00 | ማንችስተር ሲቲ 🆚 ኤክስተር
* 12:00 | ኒውካስል 🆚 በርንማውዝ
* 2:45 | ቶተንሀም 🆚 አስቶን ቪላ (የምሽቱ ታላቅ ጨዋታ)
* 5:00 | ቻርልተን 🆚 ቼልሲ
🌍 የአፍሪካ ኃያላን እና ጣሊያን
በአፍሪካ ምድር የሚደረጉት የሀገራት ፍጥጫዎች በጉጉት ይጠበቃሉ።
* 1:00 | አልጄሪያ 🆚 ናይጄሪያ
* 2:00 | ሮማ 🆚 ሳሱሎ (ሴሪአ)
* 4:00 | ግብፅ 🆚 ኮትዲቯር (የአፍሪካ ደርቢ)
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#እግርኳስ #የዛሬጨዋታዎች
#ኢትዮጵያፕሪሚየርሊግ #ማንችስተርሲቲ #ቼልሲ #ቶተንሀም #ኢትዮጵያቡና #ፋሲልከነማ #footballdaily #matchday #ethiopianpremierleague

☕ ''የአርሰናል አርማ ባለበት መጠጫ መጠጣቴን አላስተዋልኩም ነበር"- ቶማስ ፍራንክ
#ethiopia | የቶተንሀም ሆትስፐሩ አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ቡድናቸው በበርንማውዝ ከመሸነፉ በፊት የያዙት መጠጫ (Coffee Cup) በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።
🔍 ክስተቱ ምን ነበር?
ቶተንሀም ከበርንማውዝ ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ የከተማ ተቀናቃኛቸው የአርሰናል አርማ በግልጽ የሚታይበት መጠጫ ይዘው ታይተዋል። ይህ አጋጣሚ በተለይ የሰሜን ለንደን ደርቢ ተቀናቃኝ በሆኑት ሁለቱ ክለቦች ደጋፊዎች ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶችን ሲያስተናግድ ቆይቷል።
🗣️ የአሰልጣኙ ምላሽ
ከጨዋታው በኋላ ስለጉዳዩ የተጠየቁት አሰልጣኙ፣ ድርጊቱ ሆን ተብሎ የተደረገ አለመሆኑን በመግለጽ ምላሽ ሰጥተዋል፦
> "በመጠጫው ላይ የአርሰናል አርማ መኖሩን በፍጹም አላስተዋልኩም ነበር፤ ባውቅ ኖሮ አልይዘውም ነበር። እንደዚህ አይነት ተራ ነገር አስቤበት ላደርግ አልችልም፤ እንዲህ ያለ ጥያቄ መጠየቁም ራሱ አሳዛኝ ነው"
💡 ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል?
እንደ መረጃዎች ከሆነ፣ አሰልጣኙ የያዙት መጠጫ ባለፈው ሳምንት አርሰናል በተመሳሳይ ስታዲየም (በርንማውዝ) ከነበረው ጨዋታ ተዘጋጅቶ የተረፈ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።
የቶተንሀም ደጋፊዎች በአሰልጣኙ ድርጊት ግራ ቢጋቡም፣ ቶማስ ፍራንክ ግን ክስተቱ አጋጣሚ እንጂ ምንም አይነት ስውር መልዕክት እንደሌለው በቁጭት ገልጸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ቶተንሀም #አርሰናል #ቶማስፍራንክ #ፕሪሚየርሊግ #እግርኳስ #የለንደንደርቢ #tottenham #arsenal #thomasfrank #epl

አርሰናል በርንማውዝን አሸንፈ
በሊጉ አናት ላይ ያለውን ልዩነት ወደ 7 ነጥብ አሳደገ
#ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ መርሐግብር የሊጉ መሪ አርሰናል ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን አስደሳች ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የአሸናፊነት ጉዞውን ቀጥሏል።
የጨዋታው ድምቀቶች
መድፈኞቹ ድሉን እንዲያሳኩ ያስቻሏቸውን ግቦች፦
* ዴክላን ራይስ (2 ግቦች) እና
* ጋብሬል ማግሀሌስ (1 ግብ) አስቆጥረዋል።
በበርንማውዝ በኩል ኢቫኒልሰን እና ክሩፒ ግቦችን ቢያስቆጥሩም ቡድናቸውን ከሽንፈት ሊታደጉት አልቻሉም።
ቁልፍ ስታቲስቲክስ🔎
* የአርሰናል የበላይነት፦ መድፈኞቹ በፕሪሚየር ሊጉ አምስተኛ ተከታታይ ድላቸውን አስመዝግበዋል።
* የበርንማውዝ መንሸራተት፦ በርንማውዝ ካለፉት 11 የሊግ ጨዋታዎች ውስጥ አንዱንም ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።
የሊግ ደረጃ 🎲
ይህንን ውጤት ተከትሎ አርሰናል ተከታዮቹን በሰባት (7) ነጥቦች ልዩነት መምራት ጀምሯል፡
* አርሰናል፦ 48 ነጥብ (1ኛ ደረጃ)
* በርንማውዝ፦ 23 ነጥብ (15ኛ ደረጃ)
ቀጣይ ተጠባቂ ጨዋታዎች
ሁለቱም ክለቦች በሳምንቱ አጋማሽ ከባድ ፈተና ይጠብቃቸዋል፦
* ረቡዕ፦ በርንማውዝ ከ ቶተንሀም
* ሐሙስ፦ አርሰናል ከ ሊቨርፑል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#አርሰናል #በርንማውዝ #ፕሪሚየርሊግ #ዴክላንራይስ #እግርኳስ #arsenal #coyg #premierleague #declanrice #footballnews

6 months ago
"እንዳረሳችሁኝ ተስፋ አደርጋለው" ሶን ሁንግ ሚን
#ethiopia | ደቡብ ኮሪያዊ የቀድሞ የቶተንሀም ተጫዋች ሶን ሁንግ ሚን አስር አመታትን ወደ ቆየበት ክለቡ ሲመለስ የክለቡ ደጋፊዎችን እንዳረሳችሁኝ ተስፋ አደርጋለው በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል ።
ሰን አስር አመታትን የቆየበት ክለቡን ባለፈው የክረምት የዝውውር መስኮት በመልቀቅ በአሜሪካው ሜጀር ሊግ ሶከር ወደ ሚጫወተው ሎሳንጀለስ እግርኳስ ክለብ መዘዋወሩ የሚታወስ ነው ።
ትላንት ምሽት ቶተንሀም በቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ስላቭያፕራግን ካሸነፈበት ጨዋታ በፊት ንግግር ያደረገው ሶን ሁንግ ሚን ቶተንሀም ምንጊዜም ቤቴ ነው ሲል ገልጿል ።
ሶን እ.ኤ.አ በ2015 ከባየርሊቨርኩሰን ቶተንሀምን የተቀላቀለ ሲሆን በ454 ጨዋታዎች 173 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን በክለቡ የመጨረሻ አመት ቆይታውም የዩሮ ሊግ የዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል። #hageriesport

ሲቲ ወሳኝ ድል ሲያሳካ ቼልሲ ነጥብ ጥሏል !
#ethiopia | ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር ያደረገውን የፕርሚየር ሊግ መርሐግብር 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ሩበን ዲያስ ፣ ግቫርዲዮል እና ፊል ፎደን አስቆጥረዋል።
ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት አጥብቧል።
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በበኩሉ ከበርንማውዝ ያደረገውን መርሐግብር 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።
በሌሎች ጨዋታዎች
- ኤቨርተን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2ለ0
- ኒውካስል ዩናይትድ በርንሌይን 2ለ1
- ቶተንሀም ብሬንትፎርድ 2ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
2️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 31 ነጥብ
4️⃣ ቼልሲ :- 25 ነጥብ
5️⃣ ኤቨርተን :- 24 ነጥብ
7️⃣ ሰንደርላንድ :- 23 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ማክሰኞ - አታላንታ ከ ቼልሲ ( ሻምፒየንስ ሊግ )
እሮብ - ሪያል ማድሪድ ከ ማንችስተር ሲቲ ( ሻምፒየንስ ሊግ )
#ts #sport #gtmc

ማንችስተር ሲቲ ፉልሀምን 5 ለ 4 አሸነፈ
#ethiopia | በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በክራቨን ኮቴጅ በተደረገው ጨዋታ ፊል ፎደን የሲቲን ሁለት ግበች ሲያስቆጥር፣ ሃላንድ፣ ቲጃን ሬይንደረስ እና በርግ በራሱ መረብ ላይ ቀሪዎቹን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
ሃላንድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 100ኛ ግቡን ነው ማስቆጠር የቻለው፡፡ ኖርጂያኑ አጥቂ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ በጥቂት ጨዋታዎች እዚህ ቁጥር ላይ ፈጥኖ የደረሰ የመጀመርያው ተጫዋችም ሆኗል፡፡
ሳሙኤል ቼኩዌዚ የፉልሀምን ሁለት ግቦች ከመረብ ሲያሳርፍ፣ ኢሚል ስሚዝ ሮው እና አሌክስ ኢዌቢ ቀሪዎቹን ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
እጅግ አዝናኝ በነበረው እና በርካታ ግቦች በተቆጠሩበት ጨዋታ ፉልሀም አሳዝኝ ተሸናፊ ሆኗል፡፡
ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት አጥብቧል፡፡
በሌላ ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ ከቶተንሀም ሆትስፐር የተገናኙበት ጨዋታ ሁለት አቻ ተጠናቋል፡፡
ቡሩኖ ጉማሬሽ እና አንቶኒ ጎርደን የኒውካስትልን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡ ከቅጣት የተመለሰው ክርስቲያን ሮሜሮ ሁለቱንም የቶተንሀም ግቦች ከመረብ አሳርፏል፡፡
ኤቨርተንም ቦርንማውዝን በጃክ ግሪሊሸ አንድ ግብ አሸንፎ ወጥቷል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ
#ebc #epl #city #fulham

7 months ago
“ ሀትሪክ እንድሰራ ጸሎት አድርጌ ነበር “ ኢዜ
#ethiopia | የመድፈኞቹን ሶስት ግቦች ያስቆጠረው ኤቤሪች ኢዜ
“ ቡድኑን በመርዳቴ እና በድሉ ተደስቻለሁ “ ሲል ከጨዋታው በኋላ ተናግሯል።
“ ሀትሪክ ለመስራት ፀሎት አድርጌ ነበር የገባሁት “ ያለው ኢዜ ፀሎቴ ፍሬ አፍርቷል ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ ሲል ገልጿል።
ባለፈው ክረምት ቶተንሀምን ለመቀላቀል ተቃርቦ ስለመሆኑ የተጠየቀው ኢዜ “ ስለእሱ ባናወራ “ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
ኢዜ ማነው?!
🥶 Thomas Frank on Friday: “WHO IS EZE?”.
Today, Eze scored an HAT-TRICK. 🫢
ከጨዋታው አንድ ቀን በፊት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ኤዜ ማነው በማለት ሊቀልዱ የሞከሩት የቶተንሀሙ አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ እንግሊዛዊው ተጫዋች ሀትሪክ በመስራት በሚገባ መልስ ሰጥቷቸዋል፡፡
Eberechi Eze: “A special night. I prayed for a hat-trick today… and God answered. Grateful for the moment, ready for the next challenge.”
🚨🚨
212ኛውን የሰሜን ለንደን ደርቢ በድል ያጠናቀቁት መድፈኞቹ ከተከታያቸው ቼልሲ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት በማስፋት ሊጉን በ29 ነጥብ እየመሩ ይገኛሉ፡፡

ቤንያሚን ሼስኮ ለ1 ወር ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል
#ethiopia | ይህ ማለት በዚህ ወር ማንቸስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን ፣ ዌስትሀም እና በርንማውዝ ጋር በሚያደርጉት መርሀ-ግብር ላይ ለክለቡ ተሰልፎ ግልጋሎት መስጠት የማይችል ይሆናል።
የ22 አመቱ ቁመተ መለሎ አጭቂ ቤንያሚን ሼስኮ ባሳለፍነው ቅዳሜ በፕሪሚየር ሊጉ መክፈቻ በነበረው በሰሜን ለንደን ከቶተንሀም ጋር 2 አቻ በሆነ ውጤት ዩናይትድ ጨዋታውን ባጠቀቀበት መርሀ-ግብር ላይ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ሼስኮ ቡድኑን ከአንድም ሁለቴ ዩናይትድን መሪ ማድረግ የሚችልባቸውን አጋጣሚዎች ሳይጠቀምበት መቅረቱ አይዘነጋም።
በተለይ በሁለተኛው አጋጣሚ ከግብ ጠባቂው ቪካሪዮ ጋር አንድ ለአንድ ቢገናኝም የሊጉ ፈጣን ተከላካይ ሚኪ ቫን ዲቨን እንዳስጣለው ይታወቃል። ሻስኮ ግን እድሉን በፍጥነት መጠቀም ሚችልበት እድል ነበረው በዛ ሂደት ሼስኮ ጉዳት እንዳጋጠመው እና ጨዋታውን መቀጠል ባለመቻሉ እንዲሁም ዩናይትድ ቅያሪ መጨረሳቸውን ተከትሎ 12 ደቂቃ በጎዶሎ ተጫዋች ለመጫወት መገዳዳቸው የሚታወስ ነው።
የቡድኑ የህክምና አባላት አሁንም ተጨማሪ ምርመራ ሲያደርጉ ቆይተዋል ፤ ጉዳቱ ግን የጉልበት ጉዳት መሆኑን ማረጋገጫ መስጠታቸው አይዘነጋም ፤ ታዲያ አሁን ተጫዋቹ ለአንድ ወር ያህል ከሜዳ እንደሚርቅ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
ይህም በፕሪሚየር ሊጉ ዩናይትድ ከኤቨርተን ፣ ዌስትሀም እና በርንማውዝ ጋር በሚያደርጓቸው መርሀ-ግብሮች ላይ መሰለፍ እንዳይችል ያደርጉታል።
በዝውውር መስኮቱ የአጥቂ መስመራቸውን እንዲመራ ታስቦ 66.4 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ የተደረገበት ቤንያሚን ሼስኮ የተጠበቀበትን ያህል እየተንቀሳቀሰ አይገኝም ፤ በሁሉም ጨዋታዎች 12 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተ ቢሆንም 2 ጎሎችን ብቻ ነው በስሙ ማስመዝገብ የቻለው።
ቀያዮቹ ሰይጣናት በሊጉ 7ኛ ደረጃ ላይ የቸቀመጡ ሲሆን በመጪው ጥር የዝውውር መስኮት ላይ አደመስ የፊት መስመር ተጫዋች ለማስፈረም ወደ ገበያው ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። #ts #sport #gtmc

ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሀም ሆትስፐር አቻ ተለያዩ
#ethiopia | በ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳው ውጭ ከቶተንሀም ሆትስፐር የተጫወተው ማንችስተር ዩናይትድ 2 አቻ ተለያይቷል፡፡
9 ሰዓት ከ 30 ላይ በተጀመረው ጨዋታ ብሪያን ምቤሞ እና ማቲያስ ዴሊት የዩናትድን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
ማቲስ ቴል እና ሪቻርልሰን ደግሞ የቶተንሀም ሆትስፐርን ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ማን ያሸንፋል?
ቶተንሀም ከ ማንችስተር ዩናይትድ
✍በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ
#ethiopia | የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚዎቹ ተጠባቂ ጨዋታ በ2025 የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ አንድ ለዜሮ በማሸነፍ የ17 አመት የዋንጫ ረሀባቸውን ያስታገሱት ስፐርሶች በመጨረሻዎቹ ሰባት የሊግ ጨዋታዎች የበላይነት የወሰዱባቸውን ቀያይ ሰይጣናቱን በሜዳቸው ያስተናግዳሉ።
ባለፈው የውድድር አመት ከ1959/60 የውድድር አመት በኃላ ለመጀመሪያ ግዜ በዩናይትድ ላይ የደርሶ መልስ ድል የተጎናፀፉት ስፐርሶች ዛሬም በሊጉ ለተከታታይ ሶስተኛ ድል ተዘጋጅተዋል። ቶማስ ፍራንክ የአቋም መዋዠቅ የሚያሳየውን ቡድናቸው ያለፉትን አራት ጨዋታዎች ሳይሸነፍ ከቀጠለው ዩናይትድ ከባድ ፈተና ይገጥመዋል
ጥቂት እውነታዎች
✅ቶተንሃም ሆትስፐርሶች ዩናይትድን በሊጉ ለተከታታይ ሶስት ግዜ ማሸነፍ የቻሉት በ1959/60 የውድድር ዘመን ነበር።
✅ቶተንሃም ሆትስፐርሶች በሁሉም ውድድሮች የመጨረሻዎቹን ሰባት ጨዋታዎች በማንችስተር ዩናይትድ አልተሸነፉም።
✅በ2025 በሊጉ በርካታ ጨዋታዎችን በሜዳው የተሸነፈው ቡድን ቶተንሃም ነው
✅ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለዩናይትድ መጫወቶ ከጀመረበት ገሰዜ አንስቶ በሊጉ 53 ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል ይህም ከዴብሩይን(58) እንዲሁም ሞ ሳላህ(64) በመቀጠል ሶስተኛ ሲያደርገው ባለፉት ሁለት የሜዳ ውጪ ጨዋታዎች ጎል አመቻችቶ ሲያቀብል ዛሬ ደግሞ አመቻችቶ ማቀበል ከቻለ ከህዳር 2020 በኃላ ለመጀመሪያ ግዜ ነው።

ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች !
7:00 ባህርዳር ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
9:00 ምድረ ገነት ሽረ ከ ሲዳማ ቡና
9:30 ቶተንሀም ከ ማንችስተር ዩናይትድ
10:00 ኢትዮጵያ መድን ከ አርባ ምንጭ ከተማ
11:00 ኮሞ ከ ካግሊያሪ
11:30 ዩኒየን በርሊን ከ ባየር ሙኒክ
11:30 ሀምቡርግ ከ ዶርትመንድ
12:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ወልዋሎ አ/ዩ
1:00 ማርሴይ ከ ብረስት
2:00 ጁቬንቱስ ከ ቶሪኖ
2:30 ሰንደርላንድ ከ አርሰናል
4:45 ፓርማ ከ ኤሲ ሚላን
5:00 ቼልሲ ከ ዎልቭስ
#ts #sport #gtmc
7:00 ባህርዳር ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
9:00 ምድረ ገነት ሽረ ከ ሲዳማ ቡና
9:30 ቶተንሀም ከ ማንችስተር ዩናይትድ
10:00 ኢትዮጵያ መድን ከ አርባ ምንጭ ከተማ
11:00 ኮሞ ከ ካግሊያሪ
11:30 ዩኒየን በርሊን ከ ባየር ሙኒክ
11:30 ሀምቡርግ ከ ዶርትመንድ
12:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ወልዋሎ አ/ዩ
1:00 ማርሴይ ከ ብረስት
2:00 ጁቬንቱስ ከ ቶሪኖ
2:30 ሰንደርላንድ ከ አርሰናል
4:45 ፓርማ ከ ኤሲ ሚላን
5:00 ቼልሲ ከ ዎልቭስ
#ts #sport #gtmc
7 months ago
በጋርዲዮላ ብዙ ጊዜ የተሸነፈው አርሰናል
#ethiopia | ስፔናዊው ታክቲሺያን ፔፕ ጋርዶዮላ በአሰልጣኝነት ዘመኑ ነገ 1000ኛ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡የቀድሞው የባርሴሎና ኮከብ አሰልጣኝ ሆኖ በመራቸው 999 ጨዋታዎች ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል፡፡
ፔፕ ባሳለጠነባቸው የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ታላላቅ ከሚባሉ ክለቦች ጋር ለበርካታ ጊዜ ተገናኝቷል፡፡የወቅቱ የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ በአሰልጣኝነት ዘመኑ እንደ አርሰናል ቀሎት ያሸነፈው ቡድን የለም፡፡ አሰልጣኙ ከአርሰናል በተገናኘባቸው 33 ጨዋታዎች 20ዎቹን አሸንፏል፡፡
ይሄም አርሰናል በፔፕ ጋርዲዮላ የአሰልጣኝነት ዘመን ብዙ ጊዜ የተሸነፈ የመጀመርያው ክለብ ሆኗል፡፡አሰልጣኙን ብዙ ጊዜ ያሸነፉት ክለቦች ክለብ ደግሞ ሌላኛው የሰሜን ለንደን ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐር እና ሊቨርፑል ናቸው፡፡
ቶተንሀም እና ሊቨርፑል ከፔፕ ጋርዲዮላ ስብስብ በተገናኙባቸው 24 ጨዋታዎች በ10ሩ አሸንፈዋል፡፡
ፔፕ ከሁለቱ ክለቦች በመቀጠል ዘጠኝ ጊዜ የተሸነፈው በማንችስተር ዩናይትድ ነው፡፡
በሌላ በኩል በፔፕ ጋርዲዮላ ስር በርካታ ግብ በማስቀፐጠር ቀዳሚው ተጫዋች የስምንት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ ሲሆን ኤርሊንግ ብሮውት ሃላንድ 2ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡
አርጀንቲናዊው ኮከብ በጋርዲዮላ አሰልጣኝነት ስር ሆኖ 211 ግቦችን ሲያስቆጥር ሃላንድ 142 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል፡፡
ፔፕ ካሰለጠናቸው ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ረጅም ጊዜውን ያሳለፈው አሁን ባለበት ማንችስተር ሲቲ ሲሆን በ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነገ ከሊቨርፑል 1000ኛ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡
#ebcdotsteram

ሊቨርፑል ከ ሪያል ማድሪድ
ማን ያሸንፋል? ~ ይገምቱ
* አርኖልድ እና አሎንሶ ወደ ቀድሞ ቤታቸው የሚመለሱበት ጨዋታ
#ethiopia | በሊቨርፑል መለያ 354 ጨዋታዎችን ያደረገው ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ወደ አደገበት ቤቱ ተመልሶ በተቃራኒ ይቆማል፡፡
በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው እንግሊዛዊው ተከላካይ በመርሲሳይዱ ክለብ ደማቅ አቀባበል የሚጠብቀውም ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል የወቅቱ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ በተጫዋችነት 6 ዓመታትን ያሳለፈበትን ሊቨርፑልን ይገጥማል፡፡ አንድ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ጨምሮ ብዙ ክብሮችን ከሊቨርፑል ጋር ያሳከው ስፔናዊ ዛሬ ምሽት የዓለማችን ሀያሉን ክለብ እየመራ በአንፊልድ ሊቨርፑልን ለማሸነፍ ይፋለማል፡፡
ሁለቱ የቀድሞው የሊቨርፑል ተጫዋቾች አሌክሳንደር አርኖልድ እና ዣቢ አሎንሶ ከሌሎች የቡድን አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በቅርቡ በመኪና አደጋ ህይወቱ ለለፈው ዲያጎ ዦታ መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ለተጫዋቹም ለክለቡም ያላቸውን ክብር አሳይተዋል፡፡
ሊቨርፑል ከ ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒዮን ሊግ 4ኛ ዙር ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በአንፊልድ የሚገናኙበት ጨዋታ ትልቅ ግምት አግኝቷል፡፡ በአውሮፓ መድረክ ለ13ኛ ጊዜ የሚገናኙ ሲሆን ከ2017 በኋላ ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ ነው ዛሬ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት፡፡
ከባለፉት 8 ጨዋታዎች በስድስቱ የተሸነፈው ሊቨርፑል ዛሬ ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ በሜዳው እና ደጋፊው ፊት ከማድሪድ ሌላ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡
በሊጉ አስደናቂ ጉዞ እያደረገ የሚገኘው ማድሪድ በቻምፒዮንስ ሊግም ሦስቱንም ጨዋታዎች አሸንፏል፡፡ በተለይ የኬይሊያን ምባፔ ድንቅ አቋም በቀላሉ ግብ ለሚቆጠርበት የሊቨርፑል ተከላካይ ሌላ ፈተና እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ፒኤስጂ ከባየር ሙኒክ ይገናኛሉ፡፡ ያደረጓቸውን ሁሉንም ጨዋታዎች በማሸነፍ ምድቡን በእኩል ዘጠኝ ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው እየመሩ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች በፓርክ ዴስ ፕሪንስ የሚገናኙበት ሌላኛው ተጠባቂ መርሀ ግብር ሆኗል፡፡
በሁሉም መድረኮች ያደረጋቸውን ሁሉንም ጨዋታዎች ያሸነፈው ባየር ሙኒክ ከባለፈው ዓመት የሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ በሚገናኝበት ጨዋታ ምን አልባትም የዓመቱ የመጀመርያው ትልቁን ፈተና ለመወጣት ይጫወታል፡፡
አርሰናል ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ወደ ቼክ ሪፐብሊክ አምርቶ ስላቪያ ፕራግን ይገጥማል፡፡ ሦስቱንም የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታች ያሸነፈው አርሰናል በመድረኩ አንድም ግብ ያልተቆጠረበት ሲሆን ተጋጣሚው ስላቪያ ፕራግ ደግሞ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም፡፡
ናፖሊም በተመሳሳይ ሰዓት ከአይንትራ ፍራንክፈርት ጨዋታውን የሚያደርግ ሲሆን ቶተንሀም ሆትስፐር ከ ኮፐንሀገን፣ ጁቬንቱስ ከ ስፖርቲንግ ሊዝበን፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሴንት ጊሎስ እና ቡዶ ጊልሜት ከሞናኮ ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ሌሎች ጨዋታች ናቸው፡፡

8 months ago
“ለቆመ ኳስ ምስጋና ይግባውና አርሰናል ዋንጫ ሊበላ በመንገድ ላይ ነው “ ቶማስ ፍራንክ
#ethiopia ||የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ዋና አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ከጨዋታው በኋላ ስለ ቆመ ኳስ አስፈላጊነት አንስተው ተናግረዋል።
ቶተንሀም ዛሬ ኤቨርተንን 3ለ0 ሲያሸንፍ ሁለቱን ግቦች ያስቆጠረው በቆመ ኳስ ነበር።
ስለ ሁነቱ የተጠየቁት አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ “ የቆመ ኳስ በጣም ወሳኝ ነገር ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም “ ለቆመ ኳስ ምስጋና ይግባውና አርሰናል አሁን የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ ሊያነሳ በመንገድ ላይ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

Comments