7 months ago
በጋርዲዮላ ብዙ ጊዜ የተሸነፈው አርሰናል
#ethiopia | ስፔናዊው ታክቲሺያን ፔፕ ጋርዶዮላ በአሰልጣኝነት ዘመኑ ነገ 1000ኛ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡የቀድሞው የባርሴሎና ኮከብ አሰልጣኝ ሆኖ በመራቸው 999 ጨዋታዎች ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል፡፡
ፔፕ ባሳለጠነባቸው የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ታላላቅ ከሚባሉ ክለቦች ጋር ለበርካታ ጊዜ ተገናኝቷል፡፡የወቅቱ የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ በአሰልጣኝነት ዘመኑ እንደ አርሰናል ቀሎት ያሸነፈው ቡድን የለም፡፡ አሰልጣኙ ከአርሰናል በተገናኘባቸው 33 ጨዋታዎች 20ዎቹን አሸንፏል፡፡
ይሄም አርሰናል በፔፕ ጋርዲዮላ የአሰልጣኝነት ዘመን ብዙ ጊዜ የተሸነፈ የመጀመርያው ክለብ ሆኗል፡፡አሰልጣኙን ብዙ ጊዜ ያሸነፉት ክለቦች ክለብ ደግሞ ሌላኛው የሰሜን ለንደን ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐር እና ሊቨርፑል ናቸው፡፡
ቶተንሀም እና ሊቨርፑል ከፔፕ ጋርዲዮላ ስብስብ በተገናኙባቸው 24 ጨዋታዎች በ10ሩ አሸንፈዋል፡፡
ፔፕ ከሁለቱ ክለቦች በመቀጠል ዘጠኝ ጊዜ የተሸነፈው በማንችስተር ዩናይትድ ነው፡፡
በሌላ በኩል በፔፕ ጋርዲዮላ ስር በርካታ ግብ በማስቀፐጠር ቀዳሚው ተጫዋች የስምንት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ ሲሆን ኤርሊንግ ብሮውት ሃላንድ 2ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡
አርጀንቲናዊው ኮከብ በጋርዲዮላ አሰልጣኝነት ስር ሆኖ 211 ግቦችን ሲያስቆጥር ሃላንድ 142 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል፡፡
ፔፕ ካሰለጠናቸው ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ረጅም ጊዜውን ያሳለፈው አሁን ባለበት ማንችስተር ሲቲ ሲሆን በ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነገ ከሊቨርፑል 1000ኛ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡
#ebcdotsteram

በቻይና ሰውነት ላይ ታስሮ መብረር የሚያስችል መሣሪያ ይፋ ሆነ
#ethiopia | በቻይና በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ፣ የጄትሮብ ቡድን በመባል የሚታወቅ የተመራማሪዎች ቡድን በጀርባ ላይ የሚታዘል እንዲሁም በክንድ ላይ የሚጠለቁ ሞተሮች ያሉት መብረሪያ መሣሪያን ይፋ አድርጓል።
መሣሪያው በአምስት ሞተሮች የሚንቀሳቀስ ሲሆን አብራሪው አቅጣጫውን እና ከፍታውን በክንድ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጣጠር ያስችለዋል።
ሰዎች መሣሪያውን በመጠቀም አየር ላይ ሆነው አካባቢያቸውን እየተመለከቱ ከመሬት ከፍ ብለው መብረር ይችላሉ ተብሏል።
በቅርብ ጊዜ በተደረገ ሙከራ አንድ ሰው በመሣሪያው ታግዞ በሰዓት 100 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችል የሲጂቲኤን ዘገባ አመላክቷል።

8 months ago
“እንደ እኔ የተሰቃዩትን ከስቃያቸው መፈወስ ትልቅ ደስታ ይሰጠኛል”፦ በሐምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል ከታካሚነት እስከ አገልጋይነት የዘለቁት እናት
#ethiopia | በዶ/ር ካትሪን እና በዶ/ር ሬጂናልድ ሐምሊን ከተመሠረተ ከ65 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ሐምሊን የፊስቱላ ማዕከል ችግሩ ላጋጠማቸው በርካታ ሴቶች የሕክምና ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ተቋም ነው።
ማዕከሉ ከሚሰጠው የፊስቱላ ሕክምና አገልግሎት ባሻገር ታካሚዎቹን በተለያዩ ሙያዎች በማሰልጠን በዚያው በተቋሙ ውስጥ እንዲያገለግሉም ዕድል ይሰጣል።
በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ሐምሊን ፊስቱላ ማዕከል በጎ ፈቃደኛ እና ረዳት አገልጋይ የሆኑት ማሚቱ ጋሼ፤ በወሊድ ምክንያት ችግር ደርሶባቸው ነበር ከበርካታ ዓመታት በፊት ወደ ሆስፒታሉ የመጡት።
በሐምሊን የፊስቱላ ማዕከል ታክመው ከሕመማቸው ካገገሙ በኋላም በዚያው በማዕከሉ የሕክምና ስልጠና ወስደው በርካታ ሴቶችን እያገለገሉ የሚገኙ እናት ናቸው።
ዶ/ር ሬጂናልድ ቀዶ ሕክምና ሲሠሩ ከስር ስር እየተከተሉ ሥራቸውን እንዲመለከቱ በማድረግ እንዳስተማሯቸው ይገልጻሉ።
ዶ/ር ሬጂናልድን፣ አባዬ፤ ካትሪንን ደግሞ እማዬ እያሉ የሚጠሩት ማሚቱ ጋሼ፤ ሥራዬን በጣም ነው የምወደው፣ እንደ እኔ የተሰቃዩትን ከስቃያቸው መፈወስ ትልቅ ደስታ ይሰጠኛል ይላሉ።
ሕምተኞችን ማገልገል በእጅጉ እንደሚያስደስታቸው የሚገልጹት በጎ ፈቃደኛ አገልጋይዋ፤ የተማሩትን እና በልምድ ያገኙትን ዕውቀት ለሌሎች ከማጋራት ባሻገር ‘ሂሊንግ ላይቭስ’ የተሰኘ በእርሳቸው የሕይወት ተሞክሮ ላይ የተመሠረተ መጽሐፍ ስለመታተሙም ገልጸዋል።

Comments