Logo
Getu Temesgen
ማንችስተር ሲቲ ፉልሀምን 5 ለ 4 አሸነፈ
#ethiopia | በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በክራቨን ኮቴጅ በተደረገው ጨዋታ ፊል ፎደን የሲቲን ሁለት ግበች ሲያስቆጥር፣ ሃላንድ፣ ቲጃን ሬይንደረስ እና በርግ በራሱ መረብ ላይ ቀሪዎቹን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

ሃላንድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 100ኛ ግቡን ነው ማስቆጠር የቻለው፡፡ ኖርጂያኑ አጥቂ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ በጥቂት ጨዋታዎች እዚህ ቁጥር ላይ ፈጥኖ የደረሰ የመጀመርያው ተጫዋችም ሆኗል፡፡

ሳሙኤል ቼኩዌዚ የፉልሀምን ሁለት ግቦች ከመረብ ሲያሳርፍ፣ ኢሚል ስሚዝ ሮው እና አሌክስ ኢዌቢ ቀሪዎቹን ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

እጅግ አዝናኝ በነበረው እና በርካታ ግቦች በተቆጠሩበት ጨዋታ ፉልሀም አሳዝኝ ተሸናፊ ሆኗል፡፡

ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት አጥብቧል፡፡

በሌላ ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ ከቶተንሀም ሆትስፐር የተገናኙበት ጨዋታ ሁለት አቻ ተጠናቋል፡፡

ቡሩኖ ጉማሬሽ እና አንቶኒ ጎርደን የኒውካስትልን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡ ከቅጣት የተመለሰው ክርስቲያን ሮሜሮ ሁለቱንም የቶተንሀም ግቦች ከመረብ አሳርፏል፡፡

ኤቨርተንም ቦርንማውዝን በጃክ ግሪሊሸ አንድ ግብ አሸንፎ ወጥቷል፡፡

በአንተነህ ሲሳይ
#ebc #epl #city #fulham

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.