Logo
Getu Temesgen
በጋርዲዮላ ብዙ ጊዜ የተሸነፈው አርሰናል
#ethiopia | ስፔናዊው ታክቲሺያን ፔፕ ጋርዶዮላ በአሰልጣኝነት ዘመኑ ነገ 1000ኛ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡የቀድሞው የባርሴሎና ኮከብ አሰልጣኝ ሆኖ በመራቸው 999 ጨዋታዎች ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል፡፡

ፔፕ ባሳለጠነባቸው የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ታላላቅ ከሚባሉ ክለቦች ጋር ለበርካታ ጊዜ ተገናኝቷል፡፡የወቅቱ የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ በአሰልጣኝነት ዘመኑ እንደ አርሰናል ቀሎት ያሸነፈው ቡድን የለም፡፡ አሰልጣኙ ከአርሰናል በተገናኘባቸው 33 ጨዋታዎች 20ዎቹን አሸንፏል፡፡

ይሄም አርሰናል በፔፕ ጋርዲዮላ የአሰልጣኝነት ዘመን ብዙ ጊዜ የተሸነፈ የመጀመርያው ክለብ ሆኗል፡፡አሰልጣኙን ብዙ ጊዜ ያሸነፉት ክለቦች ክለብ ደግሞ ሌላኛው የሰሜን ለንደን ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐር እና ሊቨርፑል ናቸው፡፡

ቶተንሀም እና ሊቨርፑል ከፔፕ ጋርዲዮላ ስብስብ በተገናኙባቸው 24 ጨዋታዎች በ10ሩ አሸንፈዋል፡፡

ፔፕ ከሁለቱ ክለቦች በመቀጠል ዘጠኝ ጊዜ የተሸነፈው በማንችስተር ዩናይትድ ነው፡፡

በሌላ በኩል በፔፕ ጋርዲዮላ ስር በርካታ ግብ በማስቀፐጠር ቀዳሚው ተጫዋች የስምንት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ ሲሆን ኤርሊንግ ብሮውት ሃላንድ 2ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡

አርጀንቲናዊው ኮከብ በጋርዲዮላ አሰልጣኝነት ስር ሆኖ 211 ግቦችን ሲያስቆጥር ሃላንድ 142 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል፡፡

ፔፕ ካሰለጠናቸው ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ረጅም ጊዜውን ያሳለፈው አሁን ባለበት ማንችስተር ሲቲ ሲሆን በ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነገ ከሊቨርፑል 1000ኛ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡
#ebcdotsteram

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.