የሰሜን ለንደን ደርቢን ትኩሳት የሚያቀጣጥል አስተያየት ከአዲሱ የቶተንሀም አለቃ!
#ethiopia | የቶተንሀም ሆትስፐሩ አዲሱ አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር፣ በጉጉት ለሚጠበቀው የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ ቡድናቸው ያለውን ዝግጁነት እና የሚከተለውን የጨዋታ እቅድ በልበ ሙሉነት ይፋ አድርገዋል።
"አርሰናልን ለመግጠም በድፍረት እንገባለን!"
ቱዶር ይህ ጨዋታ ለክለቡ እና ለደጋፊው ያለውን ትልቅ ዋጋ በመገንዘብ፣ "በጣም አስፈላጊ እና ለመጫወት የሚያስደስት ጨዋታ ነው" ሲሉ ገልጸውታል። አሰልጣኙ አክለውም ቡድናቸው ወደ ሜዳ ሲገባ ተሽቆጥቁጦ ሳይሆን፣ ደጋፊው በሚወደውና በሚኮራበት መንገድ እንደሚሆን ቃል ገብተዋል።
የአሰልጣኙ የጨዋታ ፍልስፍና ምን ይመስላል?
* ማጥቃት፣ ማጥቃት፣ ማጥቃት!
ቱዶር የእግር ኳስ ፍልስፍናቸውን ሲያስረዱ፣ "የመጀመሪያው አላማዬ በማጥቃት ላይ የተመሰረተ እግር ኳስ መጫወት ነው፤ ይህም እኔን ያስደስተኛል" በማለት በደርቢው ላይም ይህንኑ አጥቂ አጨዋወት እንደሚተገብሩ ጠቁመዋል።
* ድፍረት ከብልሃት ጋር
ጨዋታውን ለማሸነፍ ባዶ "ድፍረት" ብቻ በቂ እንዳልሆነ ያመላከቱት አሰልጣኙ፣ "ወደ ሜዳ የምንገባው በድፍረት ነው፤ ነገር ግን ይህ ድፍረት ከብልሃት እና ከክህሎት ጋር የተዋሃደ መሆን አለበት" በማለት ታክቲካዊ ዝግጁነታቸውን አሳይተዋል።
በመጨረሻም ኢጎር ቱዶር የጨዋታውን ግብ ሲያጠቃልሉ፣ "ወደ ሜዳ የምንገባው የምንፈልገውን ለማሳካት ነው፤ የምንፈልገው ደግሞ ግልጽ ነው - ማሸነፍ!" ሲሉ ለመድፈኞቹ የማስጠንቀቂያ ደወል አሰምተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nld #northlondonderby #tottenham #arsenal #igortudor #premierleague #coys #spurs #ethiopiasports

6 months ago