ሊቨርፑል ከ ሪያል ማድሪድ
ማን ያሸንፋል? ~ ይገምቱ
* አርኖልድ እና አሎንሶ ወደ ቀድሞ ቤታቸው የሚመለሱበት ጨዋታ
#ethiopia | በሊቨርፑል መለያ 354 ጨዋታዎችን ያደረገው ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ወደ አደገበት ቤቱ ተመልሶ በተቃራኒ ይቆማል፡፡
በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው እንግሊዛዊው ተከላካይ በመርሲሳይዱ ክለብ ደማቅ አቀባበል የሚጠብቀውም ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል የወቅቱ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ በተጫዋችነት 6 ዓመታትን ያሳለፈበትን ሊቨርፑልን ይገጥማል፡፡ አንድ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ጨምሮ ብዙ ክብሮችን ከሊቨርፑል ጋር ያሳከው ስፔናዊ ዛሬ ምሽት የዓለማችን ሀያሉን ክለብ እየመራ በአንፊልድ ሊቨርፑልን ለማሸነፍ ይፋለማል፡፡
ሁለቱ የቀድሞው የሊቨርፑል ተጫዋቾች አሌክሳንደር አርኖልድ እና ዣቢ አሎንሶ ከሌሎች የቡድን አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በቅርቡ በመኪና አደጋ ህይወቱ ለለፈው ዲያጎ ዦታ መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ለተጫዋቹም ለክለቡም ያላቸውን ክብር አሳይተዋል፡፡
ሊቨርፑል ከ ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒዮን ሊግ 4ኛ ዙር ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በአንፊልድ የሚገናኙበት ጨዋታ ትልቅ ግምት አግኝቷል፡፡ በአውሮፓ መድረክ ለ13ኛ ጊዜ የሚገናኙ ሲሆን ከ2017 በኋላ ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ ነው ዛሬ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት፡፡
ከባለፉት 8 ጨዋታዎች በስድስቱ የተሸነፈው ሊቨርፑል ዛሬ ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ በሜዳው እና ደጋፊው ፊት ከማድሪድ ሌላ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡
በሊጉ አስደናቂ ጉዞ እያደረገ የሚገኘው ማድሪድ በቻምፒዮንስ ሊግም ሦስቱንም ጨዋታዎች አሸንፏል፡፡ በተለይ የኬይሊያን ምባፔ ድንቅ አቋም በቀላሉ ግብ ለሚቆጠርበት የሊቨርፑል ተከላካይ ሌላ ፈተና እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ፒኤስጂ ከባየር ሙኒክ ይገናኛሉ፡፡ ያደረጓቸውን ሁሉንም ጨዋታዎች በማሸነፍ ምድቡን በእኩል ዘጠኝ ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው እየመሩ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች በፓርክ ዴስ ፕሪንስ የሚገናኙበት ሌላኛው ተጠባቂ መርሀ ግብር ሆኗል፡፡
በሁሉም መድረኮች ያደረጋቸውን ሁሉንም ጨዋታዎች ያሸነፈው ባየር ሙኒክ ከባለፈው ዓመት የሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ በሚገናኝበት ጨዋታ ምን አልባትም የዓመቱ የመጀመርያው ትልቁን ፈተና ለመወጣት ይጫወታል፡፡
አርሰናል ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ወደ ቼክ ሪፐብሊክ አምርቶ ስላቪያ ፕራግን ይገጥማል፡፡ ሦስቱንም የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታች ያሸነፈው አርሰናል በመድረኩ አንድም ግብ ያልተቆጠረበት ሲሆን ተጋጣሚው ስላቪያ ፕራግ ደግሞ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም፡፡
ናፖሊም በተመሳሳይ ሰዓት ከአይንትራ ፍራንክፈርት ጨዋታውን የሚያደርግ ሲሆን ቶተንሀም ሆትስፐር ከ ኮፐንሀገን፣ ጁቬንቱስ ከ ስፖርቲንግ ሊዝበን፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሴንት ጊሎስ እና ቡዶ ጊልሜት ከሞናኮ ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ሌሎች ጨዋታች ናቸው፡፡
በአንተነህ ሲሳይ

9 months ago