18 days ago
ማንቸስተር ዩናይትድና ፉልሃም 1-1 ተለያዩ
#ethiopia | በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቸስተር ዩናይትድ ከፉልሃም ጋር 1-1 አቻ ተለያይቷል።
በክራቨን ኮቴጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ፣ ፉልሃም በ63ኛው ደቂቃ በማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በራሱ መረብ ላይ በተቆጠረች ግብ መሪነቱን ወስዷል።
ዩናይትድ ግን ጨዋታው ወደ መገባደጃው ሲደርስ በ89ኛው ደቂቃ ማቲያስ ኩኛ ባስቆጠራት ግብ ውጤቱን አመጣጥኗል።
ይህ ውጤት ማንቸስተር ዩናይትድ በአምስት የሊግ ጨዋታዎች ያስመዘገበው ሁለተኛው አቻ ውጤት ሲሆን፣ ቡድኑ በ5 ነጥቦች 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ፉልሃም በበኩሉ በውድድር ዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ አቻ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን፣ በ1 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
#epl #premierleague #manchesterunited #fulham #matchday #football #sports #ebc

5 months ago
ለዋንጫ የሚሆን በቂ ነዳጅ አለን፡- የቬንገርን ሪከርድ ለመስበር የሚጫወተው ሚኬል አርቴታ
********************
በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሊጉ መሪ አርሰናል በለንደን ደርቢ ዛሬ በሜዳው ከፉልሀም ይጫወታል፡፡ ከሁለት የሊጉ ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ባለፈው ሳምንት ኒውካስትልን በማሸነፍ ወደ ድል የተመለሰው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ወደ ዋንጫው ለመቅረብ በሚያደርገው ጨዋታ ከፉልሀም ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡
ጨዋታው ምሽት 1 ሰዓት ከ 30 ላይ በኤምሬትስ የሚደረግ ሲሆን አርሰናል በሜዳው ከፉልሀም ባደረጋቸው ያለፉት 32 ጨዋታዎች አልተሸነፈም፡፡ 25 ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ በሰባቱ አቻ ተለያይቷል፡፡ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከ20 ዓመት በኋላ ለፍጻሜ ለመድረስ ከአትሌቲኮ ማድሪድ አንድ የ90 ደቂቃ ፍልሚያ ብቻ የሚቀረው አርሰናል ዛሬ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ ካሸነፍ የማንችስተር ሲቲ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እንደተጠበቁ ሆነው የነጥብ ልዩነቱን ወደ ስድስት ከፍ የሚያደርግ ይሆናል።
ከወሳኙ ጨዋታ በፊት ሚኬልል አርቴታ በሰጠው ሃሳብ አርሰናል ለዋንጫ የሚያበቃው ነዳጅ (አቅም) አለው ብሏል፡፡ ስፔናዊው አሰልጣኝ “ሊጉ ሊጠናቀቅ አራት ጨዋታዎች ሲቀሩት መገኘት ያለብን ደረጃ ላይ ተገኝተናል ለሁሉም ፈተና ዝግጁ ነን በውድድር ዓመቱ ሁሉ ስናደርግ የነበረውን የማሸነፍ ፍላጎት ይዘን እስከ መጨረሻው እንጓዘለን” ብሏል፡፡ ደጋፊዎች በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ላይ ለተጫዋቾች የሚያሳዩት አዎንታዊ ድጋፍ ውጤቱን ይበልጥ የተሻለ እንደሚያደርገውም ገልጿል፡፡
በሌላ በኩል፣ ሚኬል አርቴታ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ በአንድ የውድድር ዓመት አርሰን ቬንገር ካስመዘገቡት የድል ብዛት በላይ በማሸነፍ በክለቡ አዲስ ታሪክ ይጽፋል። ፈረንሳዊው አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በ2001/02 የውድድር ዓመት በ60 ጨዋታዎች 39 ድሎችን ያስመዘገቡ ሲሆን፤ አርቴታ በበኩሉ በዘንድሮው የውድድር ዓመት እስካሁን ባደረጋቸው 57 ጨዋታዎች 39ኙን በማሸነፍ የአንጋፋውን ሰው ታሪክ ተጋርቷል። በመሆኑም ዛሬ ፉልሃምን ማሸነፍ የሚችል ከሆነ የቬንገርን የቆየ ክብረ ወሰን በማሻሻል በክለቡ ታሪክ በአንድ የውድድር ዓመት ብዙ ጨዋታዎችን ያሸነፈ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሆኖ ስሙን በደመቀ ሁኔታ ይጽፋል።
የፉልሀሙ አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ እንዲህ አይነት ጨዋታዎችን ማድረግ ያስደስተኛል በመሆኑም ለዋንጫ ከሚፋለመው አርሰናል የምንጫወተው ሦስት ነጥብ ለማግኝት ነው ብለዋል፡፡ በጨዋታው ካይ ሀቨርዝ እና ዩሪየን ቲምበር በጉዳት ከስብስቡ ወጭ ሲሆኑ ማርቲን ኦዴጋርድ ለጨዋታው እንደሚደርስ ሚኬል አርቴታ ተናግሯል፡፡
በሌላ ጨዋታ በሊጉ ለመቆየት እየታገለ የሚገኘው ዌስትሀም ዩናይትድ 11 ሰዓት ላይ ከሜዳው ወጭ ከብሬንትፎርድ ይጫወታል፡፡ በ36 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ዌስትሀም ከባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች የተሸነፈው በአንዱ ብቻ ሲሆን 18ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቶተንሀም እንዳይደርስበት የሚፋለም ይሆናል፡፡
ኒውካስትል ዩናይትድ ከብራይተን እና ከሊጉ መሰናበቱን ያረጋገጠመው ዎልቭስ ከሰንደርላንድ በተመሳሳይ 11 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
በአንተነህ ሲሳይ
#ethiopiabroadcastingcorporation #epl #arsenal #fulham

8 months ago
⚽️ የሊቨርፑል የባከነ ሰዓት ድል
አሌክሲስ ማክ አሊስተር አዳኝ ሆኗል
#ethiopia | በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ-ግብር ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ኖቲንግሀም ፎረስትን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል።
የጨዋታው ታሪክ፦
የአሸናፊነቷ ግብ፦ ጨዋታው በአቻ ውጤት ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰከንዶች ሲቀሩት፣ አሌክሲስ ማክ አሊስተር ድንቅ ግብ በማስቆጠር የመርሲሳይዱን ክለብ ለድል አብቅቷል።
የሊቨርፑል ግስጋሴ፦ ይህ ድል ሊቨርፑል በውድድር ዓመቱ ያስመዘገበው 13ኛ ድሉ ሲሆን፣ የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት አግዟል።
ደረጃ፦ ሊቨርፑል ነጥቡን ወደ 45 በማሳደግ በደረጃ ሰንጠረዡ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የሌሎች ጨዋታዎች ውጤት፦
ሰንደርላንድ 1-3 ፉልሀም፦ ፉልሀም ከሜዳው ውጪ ሰንደርላንድን በመርታት ጠቃሚ ሦስት ነጥብ አግኝቷል።
ክሪስታል ፓላስ 1-0 ዎልቭስ፦ ፓላስ በሜዳው ድል ቀንቶታል።
ሊቨርፑል ካጋጠሙት በርካታ የጉዳት ዜናዎች አገግሞ ወጥቶ ተከታታይ ድሎችን ማስመዝገቡ፣ አሰልጣኙ ለቡድኑ የሰጠው የተከላካይና የአጥቂ ጥምረት ውጤት እያመጣ መሆኑን ያሳያል። ቀሪዎቹ 11 ጨዋታዎች ለሊቨርፑል የአውሮፓ ተሳትፎ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ ይሆናሉ።
የእርስዎ ግምት፦
ሊቨርፑል የውድድር ዓመቱን በምርጥ አራት (Top 4) ውስጥ ተጠናቆ ለቻምፒዮንስ ሊግ ያልፋል ብለው ያስባሉ? ወይንስ የፉልሀም እና የሌሎች ክለቦች ግስጋሴ ስጋት ይሆንበታል?
#liverpool #lfc #alexismacallister #premierleague #footballnews #crystalpalace #fulham #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

10 months ago
ማንችስተር ሲቲ ፉልሀምን 5 ለ 4 አሸነፈ
#ethiopia | በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በክራቨን ኮቴጅ በተደረገው ጨዋታ ፊል ፎደን የሲቲን ሁለት ግበች ሲያስቆጥር፣ ሃላንድ፣ ቲጃን ሬይንደረስ እና በርግ በራሱ መረብ ላይ ቀሪዎቹን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
ሃላንድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 100ኛ ግቡን ነው ማስቆጠር የቻለው፡፡ ኖርጂያኑ አጥቂ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ በጥቂት ጨዋታዎች እዚህ ቁጥር ላይ ፈጥኖ የደረሰ የመጀመርያው ተጫዋችም ሆኗል፡፡
ሳሙኤል ቼኩዌዚ የፉልሀምን ሁለት ግቦች ከመረብ ሲያሳርፍ፣ ኢሚል ስሚዝ ሮው እና አሌክስ ኢዌቢ ቀሪዎቹን ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
እጅግ አዝናኝ በነበረው እና በርካታ ግቦች በተቆጠሩበት ጨዋታ ፉልሀም አሳዝኝ ተሸናፊ ሆኗል፡፡
ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት አጥብቧል፡፡
በሌላ ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ ከቶተንሀም ሆትስፐር የተገናኙበት ጨዋታ ሁለት አቻ ተጠናቋል፡፡
ቡሩኖ ጉማሬሽ እና አንቶኒ ጎርደን የኒውካስትልን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡ ከቅጣት የተመለሰው ክርስቲያን ሮሜሮ ሁለቱንም የቶተንሀም ግቦች ከመረብ አሳርፏል፡፡
ኤቨርተንም ቦርንማውዝን በጃክ ግሪሊሸ አንድ ግብ አሸንፎ ወጥቷል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ
#ebc #epl #city #fulham

12 months ago
አርሰናል ፉልሀምን 1 ለ 0 አሸነፈ
#ethiopia | በ8ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በለንደን ደርቢ ከሜዳው ውጭ ከፉልሀም የተጫወተው አርሰናል ወሳኝ ሦስት ነጥብ አግኝቷል፡፡
በክራቨን ኮቴጅ በተደረገው ጨዋታ ሌአንድሮ ትሮሳርድ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡
6ኛ ድላቸውን ያስመዘገቡት መድፈኞቹ ሊጉን በ19 ነጥብ እየመሩም ይገኛሉ፡፡
ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ በሊጉ ለ5ኛ ጊዜ ግብ ሳይቆጠርበት የወጣ ሲሆን ተከላካዩ ጋብርኤል ማጋሌሽ በአርሰናል መለያ 20 ግቦች ላይ ተሳትፎ አድርጓል። #fulham #arsenal

1 year ago
80" Fulham 1-1 Man-U
Bruno Fernandes misses a penalty against Fulham! 😮 #manchesterunited #fulham #premierleague

Sponsored by
Surafel
Comments