Logo
Getu Temesgen
ማን ያሸንፋል?
ቶተንሀም ከ ማንችስተር ዩናይትድ
✍በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ
#ethiopia | የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚዎቹ ተጠባቂ ጨዋታ በ2025 የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ አንድ ለዜሮ በማሸነፍ የ17 አመት የዋንጫ ረሀባቸውን ያስታገሱት ስፐርሶች በመጨረሻዎቹ ሰባት የሊግ ጨዋታዎች የበላይነት የወሰዱባቸውን ቀያይ ሰይጣናቱን በሜዳቸው ያስተናግዳሉ።

ባለፈው የውድድር አመት ከ1959/60 የውድድር አመት በኃላ ለመጀመሪያ ግዜ በዩናይትድ ላይ የደርሶ መልስ ድል የተጎናፀፉት ስፐርሶች ዛሬም በሊጉ ለተከታታይ ሶስተኛ ድል ተዘጋጅተዋል። ቶማስ ፍራንክ የአቋም መዋዠቅ የሚያሳየውን ቡድናቸው ያለፉትን አራት ጨዋታዎች ሳይሸነፍ ከቀጠለው ዩናይትድ ከባድ ፈተና ይገጥመዋል

ጥቂት እውነታዎች

✅ቶተንሃም ሆትስፐርሶች ዩናይትድን በሊጉ ለተከታታይ ሶስት ግዜ ማሸነፍ የቻሉት በ1959/60 የውድድር ዘመን ነበር።

✅ቶተንሃም ሆትስፐርሶች በሁሉም ውድድሮች የመጨረሻዎቹን ሰባት ጨዋታዎች በማንችስተር ዩናይትድ አልተሸነፉም።

✅በ2025 በሊጉ በርካታ ጨዋታዎችን በሜዳው የተሸነፈው ቡድን ቶተንሃም ነው

✅ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለዩናይትድ መጫወቶ ከጀመረበት ገሰዜ አንስቶ በሊጉ 53 ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል ይህም ከዴብሩይን(58) እንዲሁም ሞ ሳላህ(64) በመቀጠል ሶስተኛ ሲያደርገው ባለፉት ሁለት የሜዳ ውጪ ጨዋታዎች ጎል አመቻችቶ ሲያቀብል ዛሬ ደግሞ አመቻችቶ ማቀበል ከቻለ ከህዳር 2020 በኃላ ለመጀመሪያ ግዜ ነው።

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.