22 hours ago
ወንድሜ ሞተብኝ
የእናቴ ልጅ ገና በወጣትነቱ ሞተብኝ
ወንድሜ ብርሃንዬ ምንም ሳይሆን ማታ ላይ ፀሎት ወደሚያደርግበት ክፍል ለፀሎት ገብቶ በዛው ሞተብን 🥹💔
በልጅነቱ ከተወለደ ጀምሮ ለደብረሊባኖስ ገዳም ተሰቶ በዛው ተምሮ ተምሮ በዛው አድጎ በዛው ሞተብኝ
ያለፉት 9 ቀኖች ለቤተሰባችን በጣም ከባድ ሀዘን ነበር .. እንደአይን ብሌናችን የምንሳሳለት ወንድማችን , ለሰው እንኳን ወንድማችን ነው ብለን ለማውራት የምንፈራለት የምንሳሳለት ወንድማችን አጣነው....
የደብረሊባኖስ ገዳም እና የእኛ ቤተሰብ ታሪክ የሚጀምረው እንደዚህ ነው ... አያቴ እናቴን በወለደች በ 20 ቀኗ ባለቤቷ ድንገት ሲሞትባት እናቴ ሶስት ወር ሲሆናት ለአያቷ ሰታት እሷ በ 17 አመቷ ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም ሂዳ ምንና መንኩሳ ከ 60 አመት በላይ በቆብ ( በምንኩስና) ገዳሙን በፈታይነት እንዲሁም ሌሎች በገዳሙ ሴቶች ሊሰሩት የሚችሉትን እየሰራች እና ገዳሙን እያገለገለች ኑራ ነበር ... አባቴ ደሞ በደርግ ጊዜ በስራ ምክንያት የተለዩ ክፍለሀገራት ይሄድ ነበር እናቴንም ልጆቹንም ይዞ ነው ስሄድ እና እየሰራ ሲኖር የነበረው የኔ ታላላቆች የተለያየ ቦታ ነው የተወለዱት ይህ ወንድሜ በሰሜን ሸዋ ፍቼ ነው የተወለደው ከዛ በኃላ አባቴ ከልጆቹ አንድ ሰው ቤቤተክርስትያን እንዲያድግ ምኞቱ ስለነበረ ሁላችን ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም አያቴ ጋር እየሄድን እና እየተቀመጥን ፊደል ቆጥረናል እኔም በዜማ መምህር በነበሩት በየንታ መርአዊ ወንበር ስር ተቀምጬ እስከ መዝሙረ ዳዊት ድረስ በግዕዝ ተምሬጨርሼ ነው ከዛ ወደዘመናዊ ትምህርት የገባሁት ...ወንድሜ ብርሃኑ ግን ከ አራት አመቱ ጀምሮ በገዳም ሊማር እንድሄደ በዛው እየቀጠለ እየቀጠለ እድሜውን ሙሉ ተምሯል , ከዚህ በታች ያለውን ስርአተ ፍትሀቱ ላይ አባቶች ካነበቡለት ከመሰከሩለት ከህይወት ታሪኩ ላይ ነው የወሰድኩትኝ ...
እድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ወደዚህ ታላቁ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም መጥተው በመጀመሪያ ደረጃ የንባብ ትምህርታቸውን
ከመምህር አባ ኢያሱ አሰፋ ጉባኤ ቤት በመግባት በልዩ ኹኔታ መዝሙረ ዳዊቱን በቃል ጭምር አጠናቀው ተምረዋል፡፡
በመቀጠልም በዚሁ ገዳም ውስጥ ስመጥርና አንጋፋ ከኾኑት ከአለቃ መርዓዊ ሣህለ ሚካኤል ጉባኤ ቤት በመግባት ከውዳሴ ማርያም ዜማ ጀምረው ጾመ ድጓ እና ድጓ አጠናቀው
በሚገባ ተምረዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ከታላቁ ሊቅ የተክሌ አቋቋም መምህር ከኾኑት ከየኔታ በትረ ማርያም ገ/መድኅን የተክሌ አቋቋምን በመምህርነት ደረጃ በሚገባ አጠናቀው ተምረዋል፤ የቅኔ ሰዋስው ትምህርትንም ከመምህራን ቀጽለዋል፡፡
ክቡር አጋፋሪ ብርሃኑ እነዚህን ሁሉ ትምህርቶች ተምረው ለዚህ ሁሉ ሊቅነት ምሁርነትና ተጠያቂነት ያበቃቸው የእናታቸው የወይዘሮ ፍሬሕይወት ታፈሰ በጎ ምኞት ቅን አመለካከትና
የከፈሉት ታላቅ የእናት መሥዋዕትነት የአያታቸው የእማሆይ ብዙነሽ ታሃለው ጥብቅ ክትትል፣ ጥረትና ጸሎት ሲኾን ክቡር አጋፋሪ ብርሃኑ የዜማ ትምህርታቸውን ተምረው ገብተው
በልጅነት ጎናቸው አርፋለሁ ሲሉ አያታቸው እማሆይ ብዙነሽ የመጣኸው ለትምህርት እንጅ ለመኝታ መች መጣህ? እያሉ ከገድል ቤቱ በንባብ ከቅኔ ማሕሌቱ አገልግሎት እንዳይለዩ
አድርገው ተከታትለው ስላስተማሯቸው ነው፡፡
በዚህ መልኩ በመንፈሳዊ አገልግሎት በክርስትና ሕይወት አምረውና አሸብርቀው ከአደጉ በኋላ በተለያዩ የሥራ ቦታዎች ላይ ተመድበው አገልግለዋል፡፡
ከሁለት ሺሕ እስከ ሁለት ሺሕ ዐሥር ዓመተ ምሕረት በቅኔ ማሕሌቱ በኩል በአጋፋሪነት ማዕርግ ተመድበው የቦታውን ይትበሃል ከታላላቆች የቦታው ሊቃውንት ከአለቃ መርዓዊ
ሣህለ ሚካኤል እና ከየኔታ በትረ ማርያም ገ/መድኅን በማጥናት ብሎም በእጃቸው ጭምር በመጻፍ ለቦታው የይትበሃሉ ተጠያቂ የሥርዐተ ማሕሌቱ መሪ በመኾን
ሥርዐቱን በመጠበቅና በማስጠበቅ ከሊቃውንቱ ጋር በመከባበርና በመፈቃቀር ረጅሙን ዓመት በሚገባ
· አገልግለዋል፡፡
ክቡር አጋፋሪ ብርሃኑ ከዐሥር ዓመት የአጋፋሪነት ማዕርግ አገልግሎት በኋላ በሌሎች ልዩ ልዩ ሥራዎች ላይ እያገለገሉ በቅኔ ማሕሌቱ በኩልም የማሕሌቱ ኮከብ የሊቃውንቱ ጌጥ
የዝማሜው ውበት ነበሩ ከዚህ የተነሳ ሊቃውንቱም አጋፋሪ ይዝመመው አጋፋሪ ይወርበው፣አጋፋሪ ያንብበው ይሏቸዋል፣ እርሳቸውም ቢቃኙ፤ቢዘሙ፤ቢወርቡ ቢያነብቡ የማይሰለቹ
አንደበተ ርቱዕ አንደበተ ቀልጣፋ ድንቅ፣ ታላቅ፣ ሊቅና ምሁር ነበሩ፡፡
ከሁሉ የበለጠ ጸጋና ስጦታም አላቸው ለተራበ የሚያበሉ ለተጠማ የሚያጠጡ ለታረዘ የሚያለብሱ ካዘነው ጋር አዝነው የሚያረጋጉ ከተደሰተውም ጋር የሚደሰቱ ርኅሩኅ ታማኝ ሰው ወዳጅ ወንድም ነበሩ፡፡ " ....
ወንድሜ ገና ልጅ ነው እድሜው ከ 39 ወደአርባ እየሄደ ነበር ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ወቶ እዚህ አዲስ አበባ የተለያዩ አድባራት እንዲሁ በአሜሪካ ያሉ አድባራት ላይ እንዲያገለግል የተለያዩ እድሎች መተውለት ቢጠየቅም በተደጋጋሚ አልፈልግም ገዳሙን ትቼ አልወጣም በማለት ኑሯል እኛ ፕሮግራም እንኳን ኑሮን አዲስ አበባ ከመጣ አንድ ቀን ብቻ አድሮ ነው የሚሄደው ከገዳሙ መለየት በፍፁም አይፈልግም ነበር .. ወንድሜ በድንግልና የኖረ መናኝ ነበር በሚቀጥሉት አመታቶች ላይ መንኩሶ ዻዻስ የሚሆን እና እረጅም አመት ኑሮ እኛን እህት እና ወንድሞቹን ሁሉ ቀብራችንን አሳምሮ ከዛ በኃላ ይሞታል ብዬ የማስበው ወንድሜ ሰስቼው ለሰው የማላወራው ወንድሜ አንደተለመደው የቀን ውሎውን በሰላም ውሎ ሁሌ ከመተኛቱ በፊት እንደሚያደርገው ሊፀልይ ወደ ፀሎት ክፍሉ እንደገባ ሞተብኝ 💔 ሳላስታምመው ምንህን ነው ወንድሜ ሳልለው በቃ እንዲሁ ቀረብኝ 🥹💔
በጣም እረጅሙ ቆንጆው ባለግርማ ሞገሱ የእግዚአብሔር አገልጋይ የእግዚአብሔር ባሪያ .. ያ እኔ እንዲሆንልኝ እንዲሳካልኝ የሚፀልይልኝ ወንድሜን ጨክኜ ቀብርኩት

3 days ago
#moe
ትምህርት ሚኒስቴር በ2019 ዓ.ም በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች በዕጩ መምህርነት ለመሰልጠን ለሚወዳደሩ አመልካቾች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የትምህርት ቢሮዎች በቀን 19/01/2019 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ፤ የመቁረጫ ነጥቡ የክልሎችን ነባራዊ ሁኔታ እና የ2018 ዓ.ም የፈተና ውጤት ባገናዘበ መልኩ መወሰኑን ገልጿል።
ለዲፕሎማ (12+2) ፕሮግራም
● ለተፈጥሮ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 215 እና ከዚያ በላይ ፤ ለሴት ተማሪዎች 205 እና ከዚያ በላይ
● ለአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ እና ሴት ተማሪዎች 185 እና ከዚያ በላይ
● ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 185 እና ከዚያ በላይ
● በተፈጥሮ ወይም ማኅበራዊ ሳይንስ አካል ጉዳት ያለባቸው ወንድ እና ሴት ተማሪዎች 185 እና ከዚያ በላይ
● በማኅበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውራን ወንድ እና ሴት ተማሪዎች 150 እና ከዚያ በላይ
ለሰርተፊኬት (12+1) ፕሮግራም
● ለተፈጥሮ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 210 እና ከዚያ በላይ ፤ ሴት ተማሪዎች 195 እና ከዚያ በላይ
(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)
ይህ የመቁረጫ ነጥብ የሚያገለግለው ለ2019 ዓ.ም የዕጩ መምህራን ውድድር ብቻ መሆኑ ተገልጿል።
@tikvahuniversity

መምህራኖቿችሁን አመስግናችሁ ታውቃላችሁ ወይ?
#ethiopia | መስከረም 25 በዓለም አቀፍ ደረጃ "የመምህራን ቀን" ተብሎ ሲከበር፣ የትምህርት አባቶችንና እናቶችን ድካም፣ መስዋዕትነት እና የማይተካ ማህበራዊ ሚና ለማሰብና ለማስከበር ነው።
እ.ኤ.አ. በ1994 በዩኔስኮ ይፋ የተደረገው ይህ ታላቅ ዕለት፣ በየዓመቱ የመምህራንን ድምፅ ለማሰማትና ለትውልድ ግንባታ የሚያደርጉትን ያልተቋረጠ አስተዋጽዖ ለዓለም ለማስታወስ ያገለግላል።
መምህራን የማህበረሰብ መሰረትና የዕውቀት ብርሃን መሪዎች እንደመሆናቸው መጠን፣ አዲስ ትውልድን በስነ-ምግባር፣ በእውቀት እና በክህሎት ኮትኩቶ በማሳደግ ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።
በየትኛውም የሙያ መስክ የተሰማሩ ሀገር ተረካቢ ባለሙያዎች፣ከህክምና እስከ ኢንጂነሪንግ፣ ከአመራር እስከ ፈጠራ ባለቤቶች፣ሁሉም ያለፉበት የህይወት መንገድ የመምህር እጅና እይታ ያለበት በመሆኑ መምህር ማለት የነገዋን ዓለም ዛሬ በክፍል ውስጥ የሚቀርጽ ትልቅ ባለሙያ ነው።
ይሁን እንጂ ይህ ዓለም አቀፍ ቀን የምስጋናና የክብር መግለጫ ብቻ ሳይሆን የመምህራንን ነባራዊ ሁኔታና የሚጋፈጧቸውን ፈተናዎች በጥልቀት የምንፈትሽበትም አጋጣሚ ነው።
በአሁኑ ወቅት መምህራን ከስራቸው ክብደትና መስዋዕትነት ጋር ያልተመጣጠነ አነስተኛ ክፍያና የማህበራዊ ዋስትና እጥረት ይፈታተናቸዋል።
በተለይም በታዳጊ ሀገራት በቂ የመማሪያ ቁሳቁስና ምቹ የሥራ አካባቢ አለመኖር፣ እንዲሁም ከዘመናዊው የመረጃ ዘመን ጋር በፍጥነት ለመራመድ የሚያስችል ቀጣይነት ያለው ስልጠና እና የዲጂታል መሳሪያዎች እጥረት የሙያውን ጉዞ አዳጋች አድርጎታል።
ስለሆነም ቀኑን ማከበር በአንድ ቀን ስነ-ስርዓት ወይም መግለጫ ብቻ የሚገደብ ሳይሆን የመምህራንን ክብር በተግባር ለማደስ፣ የኑሮ ደረጃቸውን ለማሻሻል፣ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እና ቀጣዩ ትውልድ ወደ ሙያው በስፋት እንዲቀላቀል ማራኪ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያስችል ሁለንተናዊ ንቅናቄን ይጠይቃል።
መምህርነት ተራ የሥራ ዘርፍ ሳይሆን የህይወት ጥሪና ተልዕኮ በመሆኑ፣ መስከረም 25 የህይወታችንን መንገድ ላበሩልን፣ እውቀታቸውን ለለገሱልን ለነዚህ የብርሃን ባለቤቶች ሁላችንም ከልብ የምናመሰግንበትና ከጎናቸው የምንቆምበት ታሪካዊ ዕለት ነው።
መምህሮቿቹሁን ዛሬ አመስግኗቸው...
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

4 days ago
የትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።
የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በ2019 ዓ.ም በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች በዕጩ መምህርነት ለመሰልጠን ለሚወዳደሩ አመልካቾች መወዳደሪያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ ለሁሉም ክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች የትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ይፋዊ ደብዳቤ፤ የመቁረጫ ነጥቡ የተወሰነው የክልሎችን ነባራዊ ሁኔታ እና የ2018 ዓ.ም የፈተና ውጤት ባገናዘበ መልኩ መሆኑን ገልጿል።
በዚህም መሰረት በዲፕሎማ (12+2) እና በሰርተፊኬት (12+1) የሙያ ስልጠናዎች መግቢያ ነጥብ እንደሚከተለው ተወስኗል፦
ለዲፕሎማ (12+2) ፕሮግራም ፦
◦ ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 215 እና ከዚያ በላይ
◦ ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 205 እና ከዚያ በላይ
◦ ለአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ወንድና ሴት ተማሪዎች 185 እና ከዚያ በላይ
◦ ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 185 እና ከዚያ በላይ
◦ በተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ አካል ጉዳት ያለባቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 185 እና ከዚያ በላይ
◦ በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውራን ወንድና ሴት ተማሪዎች 150 እና ከዚያ በላይ
ለሰርተፊኬት (12+1) ፕሮግራም ፦
- ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 210 እና ከዚያ በላይ
- ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 195 እና ከዚያ በላይ
- ለአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች 180 እና ከዚያ በላይ
- ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ተፈታኞች 180 እና ከዚያ በላይ
በደብዳቤው ላይ እንደተመለከተው፣ ይህ የተወሰነው መቁረጫ ነጥብ የሚያገለግለው ለ2019 ዓ.ም (2018 ዓም የ 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ለወሰዱ) የዕጩ መምህራን ውድድር ብቻ ሲሆን፣ ሌሎች መስፈርቶች በዕጩ መምህራን ምልመላና መረጣ መመሪያ መሰረት ተግባራዊ እንደሚደረጉ ተጠቅሷል።
@tikvahethiopia

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደብዳቤውን ትክክለኝነት ከትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዳስ አበባ
መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም

Sponsored by
Surafel
9 days ago
#ጥቆማ
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በ2019 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስተር (Postgraduate Diploma in Alternative Teacher Education) በመደበኛ እና በእረፍት ቀናት ተማሪዎችን ተቀብሉ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
የስልጠና ዘርፎች፡-
Mathematics, Biology, Chemistry, Economics, English, Information Communication Technology, Physics, History and Geography.
መስፈርቶች፡-
● አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ ያላቸው፣
● በመምህርነት ለማገልገል ፍላጎት ያላቸው፣
● ከመንግሥት ተቋማት የተመረቁ አመልካቾች ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲ ስለመመረቃቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
● ከግል ተቋማት የተመረቁ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኛነት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
የማመልከቻ ጊዜ 👇
ከመስከረም 21-29/2019 ዓ.ም
የማመልከቻ አማራጮች 👇
በዩኒቨርሲቲው ዋናው ሬጅስትራር ቢሮ ቁ. 41 በአካል በመቅረብ ወይም ኦንላይን ለማመልከት የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረ-ገፅ (https://portal.hu.edu.et) አካውንት በመፍጠር አስፈላጊ መረጃዎችን መሙላት ይጠበቅባችኋል።
ለመደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች የመኝታ፣ ምግብ እና ጤና አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በመንግሥት የሚሸፈን ይሆናል። የእረፍት ቀናት አመልካቾች የትምህርት ወጪያቸውን ራሳቸው የሚሸፍኑ መሆኑ ተገልጿል።

11 days ago
የመንግሥት ትምህርት ቤቶች መምህራን የደረጃ ዕድገት ለማግኘት ከሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ውስጥ ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት 5ዐ በመቶ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ አለነት፡፡ - የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ መመሪያ
ትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ 1ኛ እስከ 2ኛ ደረጃ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ ተፈጻሚ የሚሆን "የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ 1148/2018" ይፋ አድርጓል።
መመሪያው በማስተማር ሥራቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ መምህራንን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በመመሪያው መሠረት የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የእድገት መሰላል በሰባት ደረጃዎች ማለትም፦
➻ ጀማሪ መምህር
➻ መለስተኛ መምህር
➻ መምህር
➻ ከፍተኛ መምህር
➻ ተባባሪ መሪ መምህር
➻ መሪ መምህር እና
➻ ከፍተኛ መሪ መምህር በሚሉ እርከኖች የተከፋፈሉ ናቸው።
በመመሪያው የተቀመጠው የቆይታ ጊዜም ከጀማሪ ወደ መለስተኛ መምህርነት ለመሸጋገር ሁለት ዓመት፣ በቀጣዮቹ ደረጃዎች ደግሞ በእያንዳንዱ እርከን የሦስት ዓመታት ቆይታ የሚጠይቅ ነው።
ይሁን እንጂ አንድ መምህር በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ በውድድር ሁለት ጊዜ እድገት ማግኘት ካልቻለ ለሦስተኛ ጊዜ የመወዳደር ዕድል እንደማይኖረው በመመሪያው ተደንግጓል።
መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል።
ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል።
በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል።
ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው።
አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስቀምጧል።
(መመሪያው ከላይ ተያይዟል፡፡)

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያን ይፋ አደረገ።
የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ ተፈጻሚ የሚሆን "የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1148/2018" አውጥቷል።
ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ያዘጋጀው ይህ መመሪያ፣ በማስተማር ሥራቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ መምህራንን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በመመሪያው ድንጋጌ መሠረት የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የእድገት መሰላል በሰባት ደረጃዎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ እነሱም ፦
- ጀማሪ መምህር፣
- መለስተኛ መምህር፣
- መምህር፣
- ከፍተኛ መምህር፣
- ተባባሪ መሪ መምህር፣
- መሪ መምህር እና ከፍተኛ መሪ መምህር ናቸው።
በመመሪያው የተቀመጠው የቆይታ ጊዜም ከጀማሪ ወደ መለስተኛ መምህርነት ለመሸጋገር 2 ዓመት፣ በቀጣዮቹ ደረጃዎች ደግሞ በእያንዳንዱ እርከን የ3 ዓመታት ቆይታ የሚጠይቅ ነው።

በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል።
አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል።
በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል።
በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል።
የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል።
አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም

12 days ago
#ጥቆማ
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም በአማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም (Alternative Teachers' Training Program) ለዘጠኝ ወራት ሰልጥነውና ውል ፈርመው በተለያዩ ክልሎች በመምህርነት ለማገልገል የሚፈልጉ አመልካቾችን ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም #ወጪያቸውን_ሸፍኖ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
የስልጠና ዘርፎች
➻ Biology
➻ Chemistry
➻ Mathematics
➻ Physics
➻ History
➻ Geography
➻ Citizenship
➻ Economics
➻ Agriculture
➻ Performing & Visual Arts
➻ English Language
➻ Information Communication Technology
የማመልከቻ መስፈርቶች፦
● አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመርያ ዲግሪ ያላቸው እና የመውጫ ፈተና ያለፉ
● ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲ የኦፊሺያል ትራንሰከሪፕት ማስላክ የሚችሉ
● በመምህርነት ለማገልገል ፍላጎት ያላቸው
● ከግል ትምህርት ተቋማት የተመረቁ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኝነት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👇
መስከረም 25/2019 ዓ.ም
ያመልክቱ 👇
https://forms.gle/PhDzQiRb...
ከላይ በተገለፀው ሊንክ ላይ በመግባት አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላትና የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በማያያዝ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።
ለሴት አመልካቾች እንዲሁም የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት ለማይፈልጉ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

1 month ago
ተማሪዎችን ለሥራ ዓለም የሚያዘጋጀው "The Vocational Shift" መጽሐፍ ለንባብ በቃ!
#fastmereja :-በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ የሚታየውን የንድፈ-ሃሳብ (Theory) እና የተግባር ትምህርት ክፍተት በመቅረጽ፣ ተማሪዎችን ለሥራ እና ለሥራ ፈጠራ የሚያዘጋጅ አዲስ መጽሐፍ በዛሬዉ እለት ተመርቆ ለንባብ በቃ።
በዶ/ር ታደሰ መኮንን የተደረሰው "The Vocational Shift: A Practical Guide to Integrating TVET and CTE into General Education" የተሰኘዉ ይህ መጽሐፍ፣ የሙያ እና ቴክኒክ ትምህርትን (TVET) እንዲሁም የሙያ መመሪያ ትምህርትን (CTE) ከጠቅላላ የትምህርት ካሪኩለም ጋር በማቀናጀት ተማሪዎችን ከትምህርት ወደ ብቃት የሚያሸጋግር ተግባራዊ መመሪያ (Guidebook) እንደሆነ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ደራሲው ዶ/ር ታደሰ መኮንን እንደገለጹት፣ የመጽሐፉ መነሻ ምክንያት በትምህርት ዘርፍ ከመምህርነት እስከ ኮሌጅ አመራርነት በቆዩባቸው ረጅም የሥራ ዓመታት እና በዶክትሬት (PhD) ምርምራቸው ወቅት የታዘቧቸውን የትምህርት ክፍተቶች መሰረት በማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።
ዶ/ር ታደሰ አክለዉም መጽሐፉ በዋነኝነት የትምህርት ሥርዓቱ ተማሪዎችን ለፈተና ማለፍ ብቻ ሳይሆን፣ ለሕይወት እና ለሥራ ዓለም ማዘጋጀት እንዳለበት እንደሚያተኩርም ነዉ የተገለፀዉ።
በ4 ዋና ዋና ክፍሎች እና በ11 ምዕራፎች የተዋቀረው ይህ መጽሐፍ፣ የትምህርት አመራሮች፣ መምህራን፣ ተማሪዎችና ማህበረሰቡ ለሙያ ትምህርት ያላቸውን አመለካከት እንዲቀይሩ ለማስቻል ያለመ ስለመሆኑም ተመላክቷል።
መጽሐፉ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በዚህ ቋንቋ የመዘጋጀቱ ዋና ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ባለው የትምህርት ካሪኩለም የሚጠቀመውን የማስተማሪያ ቋንቋ መሰረት በማድረግ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፣ በቀጣይም መልእክቱ ሰፊው ማህበረሰብ ዘንድ እንዲደርስ በልዩ ልዩ የሀገሪቱ ቋንቋዎች ተተርጉሞ እንደሚዘጋጅ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም መጽሐፉ በመደርደሪያ ላይ የሚቀመጥ ሳይሆን በትምህርት ቤቶች ውስጥ ወርዶ በተግባር ላይ እንዲውል እና የሚመለከታቸው የፖሊሲ አውጪዎችና አመራሮች ለትግበራው በትብብር እንዲሰሩ አሳስበዋል።

2 months ago
በመምህርነት 9 አመት ሞላኝ!
በ17ሺ ብር ደሞዝ እንዴት ይኖራል።
በ23 አመቴ በ2009 በድግሪ በዩኒቨርሲቲ መምህርነት ከተቀጠርኩ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በዚህ ሞያ ውስጥ እያገለገልኩ እገኛለው። በኛ ግዜ በትምህርታቸው ከፍተኛ የተባለ ውጤት ያላቸው አብዛኞቹ ልጆች በዪኒቨርሲቲ መምህርነት ይቀጠሩ ነበር። ደሞዛችንም በ 9 አመት ውስጥ ከ 6700 አሁን 17ሺ ብር ደርሷል። ግን በዚህ ደሞዝ እንዴት ነው
* በልቶ ማደር የሚቻለው?
* ከቤተስብ፣ከጓደኛ ጋር መዝናናት የሚቻለው?
* ልጅ ማሳደግ፣ ትዳር መምራትም፣ መመስረትም የሚቻለው?
* ብንታመም መታከም የሚቻለው?
መምህራን የእድሜያቸውን ግማሽ ያህሉን አስተምረው እንኳን ለቤት ኪራይ እና ጫማ ለመቀየር ሲቸገሩ ማየት ያሳዝናል።
ሁሌም እንደምለው ትኩረት ይሰጠን!!
Note:- መምህርነት በጣም ደስ የሚል ሞያ ብቻ ሳይሆን የአካዳሚክ ህይወቱን ማስቀጠል ላይ መደራደር ለማይፈልግ ለእኔ አይነት ሰው እጅግ ተመራጭ ሞያ ነው። በገንዘብ ደረጃ ግን አሁን ለኔ ቲክቶክ ባይኖር ቤተሰቤም እኔም መበተናችን አይቀርም ነበር።
ሁሉም መምህራን ተገቢ ክብር እና ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል።
ብሩክ ጫላ (ብሩክ ኒውስ)

3 months ago
አቶ ደሳለኝ ጫኔ ከቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ
ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት ታዋቂው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ አቶ ደሳለኝ ጫኔ፣ የፓርላማ ቆይታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ከማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መውጣታቸውን በይፋ ገለጹ።
በትናንትናው ዕለት የምክር ቤቱ ዘመን ማክተሙን ተከትሎ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት አቶ ደሳለኝ፣ ለጊዜው በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ በአባልነትም ሆነ በደጋፊነት እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል።
ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲ መምህርነት እና በሲቪክ ማኅበራት መሪነት ያገለገሉት ምሁር ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በፖለቲካ አመራርነት እንዲሁም የባሕር ዳር ከተማ መራጮችን በመወከል በፓርላማ በንቁ ተቃዋሚነት አገልግለዋል።
በዚህ ጉዟቸው ወቅትም ለ45 ቀናት መታሰራቸውን ጠቅሰዋል።
ከ10 ዓመታት የፖለቲካ ድካም መልስ ወደ ግሉ ዘርፍ በመግባት በሙያቸው ሀገርን ለማገልገልና ለቤተሰባቸው ጊዜ ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
ከተቃውሞ ፖለቲካው ቢወጡም፣ በሀገራዊ የሰላም እና የብሔራዊ ውይይት ጉዳዮች ላይ በሙያቸው አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
Seledadotio

የቀድሞው የፓርላማ አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ራሳቸውን ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ማግለላቸውን ይፋ አደረጉ
#fastmereja I ባለፉት 5 ዓመታት (ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት ታዋቂው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፣ የፓርላማ ቆይታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ከማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን በይፋ አስታውቀዋል። በትናንትናው ዕለት በተጠናቀቀው የምክር ቤት ዘመን ማግስት ውሳኔያቸውን ያሳወቁት ዶ/ር ደሳለኝ፣ ለጊዜው በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ በአባልነትም ሆነ በደጋፊነት እንደማይሳተፉ ገልጸዋል።
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ወደ ፖለቲካው ዓለም ከመግባታቸው በፊት በዩኒቨርሲቲ መምህርነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በጣና ሐይቅ የእንቦጭ አረም መከላከል ንቅናቄ ላይ በአክቲቪዝም እና በሲቪክ ማኅበራት መሪነት በግንባር ቀደምትነት ሰርተዋል። ባለፉት 8 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከፓርቲ ምስረታ እስከ ከፍተኛ አመራርነት የተጓዙት ዶ/ር ደሳለኝ፣ ባለፉት 5 ዓመታት ደግሞ የባሕር ዳር ከተማ መራጮችን በመወከል በፓርላማ የነቁ ተቃዋሚ ሆነው አገልግለዋል። በዚህ የፖለቲካ ጉዟቸው ወቅትም ለ45 ቀናት መታሰራቸውን አስታውሰዋል።
በትናንትናው የምክር ቤት ጉባዔ ማጠቃለያ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ «አብረን እንስራ» በማለት ለተቃዋሚዎች ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። ከጉባዔው በኋላ በተደረገ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዶ/ር ደሳለኝ በሰጡት አስተያየት፣ በ7ኛው ዙር ምርጫ በባሕር ዳር ከተማ ለመወዳደር ቢመዘገቡ ኖሮ ብልጽግና ፓርቲ እጩ ላለማቅረብ ወስኖ እንደነበርና በምክር ቤቱ ቢቀጥሉ ፍላጎታቸው እንደነበር ገልጸውላቸዋል።
ይሁን እንጂ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የቀረበላቸውን የፖለቲካ ፍላጎት በበጎ ካዩት በኋላ፣ ከ10 ዓመታት ተከታታይ የፖለቲካ ድካም በኋላ አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ግሉ ዘርፍ (Startups) በመግባት በሙያቸው ሀገርን ለማገልገልና ለቤተሰባቸው ጊዜ ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል። ቀጥተኛ የፖለቲካ ተሳትፏቸው ቢያበቃም፣ የአማራን ሕዝብ አንድነትና ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር ያለውን አብሮነት በሚያጠናክሩ እንዲሁም በሀገራዊ የሰላም እና የብሔራዊ ውይይት ጉዳዮች ላይ በሙያቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
#ፖለቲካ

''የውቦች ንግስት''
በምህረት
#Ethiopia | ምህረት ደግፍ ትውልድና እድገቷ አዲስ አበባ ፤ በልዩ ስሙ ኮልፌ 18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሐምሌ 19 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሁለተኛ ደረጃን በየካቲት 23 ት/ቤት ፣ የመሰናዶ ትምህርቷን ደግሞ በአዲስ ከተማ መሰናዶ ተከታትላ ጨርሳለች።
ቀጥሎም በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት በመመረቅ ትምህርቷን ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በአሁኑ ወቅትም በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ሥነ-ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ ናት።
የጋዜጠኝነት ሞያን ከከፍታ የትምህርት ሥልጠና እና የማማከር ተቋም ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በፋክት ቼኪንግ እና ሌሎችም ተያያዥ ሥልጠናዎችን ከሌሎች የሃገር ውስጥ እና የውጪ ተቋማት በሰርተፊኬት ማግኘት ችላለች።
ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር ሙሉ የልጅነት ሕይወቷ ያለፈው በደብረ ገሊላ አማኑኤል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው። አሁን ላለችበትም መሰረት የጣለችው ሰንበት ትምህርት ቤት በነበረችበት ወቅት ነው። በተለይም በሥነ-ጽሑፍ ረገድ ዝንባሌ ሊኖራት የቻለው ከልጅነት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤት እና በመደበኛ ት/ቤት በነበራት ተሳትፎ ነው። እንደ ግጥም ፣ መነባንብ ፣ ድራማ እና ሌሎችም ላይ የበዛ ተሳትፎ ታደርግ ነበር። ይህ ተሳትፎ አሁንም ድረስ ተከትሏት በመምጣት ለፍሬ እንደደረሰ ታምናለች።
በት/ቤት ፣ በወረዳ እና በክፍለ ከተማ ብሎም በከተማ አቀፍ በነበሩ የሥነ-ጸሑፍ ውድድሮች ፣ መድረኮች እና መሰል ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ የተለያዩ ሽልማቶችን እና የምስጋና ወረቀቶችን ማግኘት ችላለች። በመንፈሳዊም በኩል በተመሳሳይ ሁኔታ በነበሯት ተሳትፎዎች በርካታ ሽልማቶችን አግኝታለች። እስከዛሬ ድረስም በተለያዩ የሥነ-ጸሑፍ መድረኮች ሥራዎቿን እያቀረበች ትገኛለች።
ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንደተመረቀች በአጼ ፋሲል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለሁለት ዓመት ያህል በመምህርነት አገልግላለች። በሞያው በቆየችባቸው ጥቂት ዓመታት የተለያዩ የምስጋና እና የደረጃ ሽልማቶችን ማግኘት ችላለች።
ከዚያ በመቀጠል በተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ለአንድ ዓመት ያህል በፕሮግራም አዘጋጅነት የሠራች ሲሆን ፤ የራሷን መንፈሳዊ ፕሮግራሞች እና ሥራዎች በመሥራት ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት በሐገሬ ቴሌቪዥን በከፍተኛ ሪፖርተርነት መደብ እየሠራች የምትገኝ ሲሆን ፤ ላለፈው አንድ ዓመት ያህል በዚሁ ጣቢያ የዜና ክፍል ባልደረባ በመሆን ቆይታለች።
ከልጅነት ጀምሮ የተከተላት የሥነ-ጽሑፍ ፍቅር አሁንም ድረስ ተከትሏት የመጣ ሲሆን ፤ የመጀመሪያ የሆነውንና ” የውቦች ንግሥት” ስትል የሰየመችውን መጽሐፏን ለአንባቢያን ለማድረስ ዝግጅቷን አጠናቃለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ለበርካታ ትውልዶች በሚቺጋኑ ካላማዙ ኮሌጅ ከኢኮኖሚክስ መምህርነትም የዘለለ አሻራ ያሳረፉት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ አህመድ ሁሴን የህይወት ጉዟቸውን የሚያወሳ አዲስ መጽሐፍ አሳትመዋል። ፕሮፌሰሩ በኮሌጁ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ፣ የአካባቢ ጥበቃ ትምህርት መስራች፣ እንዲሁም የኮሌጁ ከፍተኛ የማስተማር ክብር የሆነው የፍሎረንስ ጄ. ሉካሴ ሽልማት ተሸላሚ በመሆን ትልቅ ታሪክ ሰርተዋል። ሆኖም ከተማሪዎቻቸው አዕምሮ የማይጠፋው ማዕረጋቸው ሳይሆን፣ ለተማሪዎቻቸው ስኬት የነበራቸው ልባዊ ፍላጎት፣ ያበረከቱት የላቀ የምክር አገልግሎት እና ደግነታቸው ነው።
አሁን ደግሞ "ዘ ዴሴ ኪድ" (The Dessie Kid) በተሰኘው አዲሱ ማስታወሻቸው፣ ከኢትዮጵያ ደሴ ከተማ የልጅነት ጊዜያቸው አንስቶ አህጉራትን እስካቋረጠው የአካዳሚክ የህይወት ጉዟቸው ድረስ ያለውን ታሪክ ወደኋላ መለስ ብለው ዳስሰውታል። መጽሐፉ ፕሮፌሰሩ በጃፓን ዋሴዳ ዩኒቨርሲቲ፣ በዚምባብዌ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም በቦትስዋና ዩኒቨርሲቲ ያሳለፉትን ጊዜያት ጨምሮ፣ ስለ ጽናት፣ ምስጋና፣ ቤተሰብ እና ህይወታቸውን ስለቀረጹ ሰዎች ጥልቅ የሆነ ግላዊ ምልከታን የያዘ ነው።
ፕሮፌሰሩ ይህንን ማስታወሻ ለመጻፍ ስላነሳሳቸው ምክንያት ሲገልጹ፣ ዓለማዊ ትምህርት ገና ባልተስፋፋበት ወቅት፣ መደበኛ ትምህርት ከሌላቸው ቤተሰቦች የተገኘ አንድ ልጅ እንዴት በአሜሪካ የአካዳሚክ ዓለም ውስጥ ስኬታማ ሊሆን እንደቻለ ለመረዳት መሆኑን ይናገራሉ። በተለይም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የክርስትና ትምህርት ተጽዕኖ አለባቸው ተብሎ በሚታሰብበት ማህበረሰብ ውስጥ አድገው ይህንን ደረጃ ላይ መድረሳቸው ታሪካቸውን ልዩ ያደርገዋል።
ጸሃፊው አክለውም ታሪካቸው የተለመደውን የስደተኞች ህይወት የሚያስተጋባ ቢሆንም፣ መጽሐፉን የጻፉት የግል ስኬታቸውን ለማክበር አለመሆኑን ያብራራሉ። ይልቁንም፣ ማንም ሰው ብቻውን ስኬት ላይ እንደማይደርስ በማመን፣ ህይወታቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች፣ እንዲሁም በትክክለኛው ጊዜ በደረሱላቸው ሰዎች እና ተቋማት ደግነት የተቀረጸ መሆኑን ለማሳየት ነው። መጽሐፉ በዋናነት የተጻፈው ቤተሰቦቻቸው ታሪካቸውን እንዲያውቁ፣ እንዲሁም በጉዟቸው ላይ ለረዷቸው መምህራን፣ ጓደኞች እና ተማሪዎች ምስጋና ለማቅረብ ነው።
በካላማዙ ኮሌጅ ያሳለፉት 34 ዓመታት በሙያ ህይወታቸው ውስጥ ትልቅ ስፍራ እንዳለው የሚያወሱት ፕሮፌሰሩ፣ ኮሌጁ ሙያዊ ክህሎታቸውን ከማሳደግ ባሻገር ማንነታቸውን ሙሉ በሙሉ የተቀበለ እና ያከበረ የመጀመሪያው ተቋም እንደነበር ይመሰክራሉ። ኮሌጁ ከነጭ-ተኮር ተቋምነት ወደ አካታች እና ብዝሃነት ወዳለው ማህበረሰብ ሲቀየር በዓይናቸው ማየታቸውም በህይወታቸው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጡት ክስተቶች አንዱ ነው።
ጡረታ ከወጡ በኋላ ጊዜያቸውን ከልጅ ልጆቻቸው ጋር በማሳለፍ በማንበብ እና ከህይወት አጋራቸው ጋር በመጓዝ ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር አህመድ፣ ይህን መጽሐፍ ለማጠናቀቅ ወደ ስድስት ዓመታት ገደማ እንደፈጀባቸው ገልጸዋል። የህትመት እና የስርጭት ሂደቱንም የጥራት ደረጃውን ለመጠበቅ ሲሉ ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ወጪ እንዳከናወኑት ጠቁመው፣ አንባቢያን መጽሐፉን ለዚሁ ዓላማ ከተዘጋጀው ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

"ልጅ የአባቱን ይወርሳል"
#ethiopia | ዛሬ እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ14ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን እጩ መምህራን አስመርቋል።
ካስመረቃቸው 818 ተማራዎች መካከልም አንድ ባለ ብሩህ አእምሮ ወንድ እጩ መምህር እጅግ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የዋንጫና የሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።
እጩ መምህር አማኑኤል በረከት ይባላል።አማኑኤል በሂሳብ ትምህርት ክፍል 3.99 በማምጣት ነው ተሸላሚ የሆነው።
ጊዜውን በአግባቡ መጠቀሙ ፣የመምህራንና የቤተሰቦቹ እገዛ ውጤታማ እንዲሆን አስችሎታል።
"ያለ መምህር የተኛውም ሙያ ሊኖር አይችልም" የሚለው አማኑኤል መምህርነት የሙያዎች ሁሉ እናት እንደሆነ ይገልፃል።
"ልጅ ያባቱን ይወርሳል " ነውና ብሂሉ እኔም ልክ እንደአባቴ ትውልድን ከእኔ በተሻለ ለመቅረፅ ተዘጋጅቻለሁ ብሏል።
የአማኑኤል አባት መምህር በረከት ታፈረ በዳንግላ ወረዳ ጫራ ት/ቤት መምህር ናቸው።ትውልድ ቀረፃ ሙያ ከጀመሩም 18 አመትት አስቆጥረዋል።
አማኑኤልንም ባላስተምረውም የ8 ክፍል ፈተናን የማስፈተን እድል አጋጥሞኛል ይላል።
አማኑኤል ከታች ጀምሮ የደረጃ ተማሪ እንደነበር የሚያስታውሰን መምህሩ መምህር የመሆን ፍፋላጎትና ራዕይ እንደነበረውም መምህር በረከት ተናግረዋል።
መምህር የሙያዎች ሁሉ እናት!!

እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ14ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 818 እጩ መምህራንን አስመረቀ።
#ethiopia | በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአዊ ብሄ/አስ ዋና አሥተዳዳሪ እና የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ ቴዎድሮስ እንዳለው ፥ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ የገጠመውን ስብራት ለመጠገን ከተመራቂዎች ብዙ ይጠበቃል ብለዋል።
ቃልኪዳናችሁ እውን እንዲሆን እስከአሁን ያገኛችሁትን እውቀት ትውልዱ ላይ ብርሃን እንዲያበራ ከራሳችሁ ጋር የተስማማችሁ ሁኑ ሲሉም አሳስበዋል ።
ተመራቂ እጩ መምህራን ልጆች የሚፈልጉትን እውቀት ለማስጨበጥ የተዘጋጃችሁ ብቁ ትውልዶች ናችሁ ነው ያሉት።
ትውልዱ ላይ በተሰጣችሁ አደራና በገባችሁት ቃል ኪዳን ላይ አተኩራችሁ ስሩ ብለዋል።
"ሀገር ካለች ሁሉም አለ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በምክንያት የምታምኑ እና ከሁሉም ከግለሰባዊ ጉዳይ ሀገራችሁን አስቀድሙ "ነው ያሉት።
ወደ ፊት ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን በዕውቀታቸው እንዲያገለግሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲን ጌታቸው አድማስ፥ተመራቂዎች ከብዙ አመታት ትጋትና ጥረት በኋላ ለምረቃት በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከተመሠረተ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በዲፕሎማ መርሐ ግብር ከ30ሺህ በላይ ምሩቃንን ለሀገር አበርክቷል።
በ2018ዓ.ም በተለያዩ የትምህርት መስኮች ለ14 ዙር በመደበኛው፣በኤክስቴንሽንና በክረምት መርሃ ግብር በዲግሪና በዲፕሎማ ያሠለጠናቸውን 818 እጩ መምህራንን ነው ያስመረቀው።
ከነዚህም ውስጥ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የሰለጠኑ ለመጀመሪያ ጊዜ 322 መምህራንን በዲግሪ በማስመረቅ አዲስ የስኬት ምዕራፍ ላይ መድረሱን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።
ኮሌጁ ከመማር ማስተማር ፣ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ጎን ለግን ራሱን ለማስተዳደር በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ልማቶች ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።
ተመራቂዎች የእናንተ አስተምህሮ የነገዋን ኢትዮጲያ የሚቀርፅ ነው ብለዋል። ስለሆነም በመምህርነት ሙያችሁ የትውልድንና የሀገርን አደራ እንድትወጡ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
መምህር ማለት ህዝብን የመገንባት ተልዕኮ ነው ያሉት ዲኑ የዛሬ የዲግሪና የዲፕሎማ ሰርትፍኬት የጉዞ መጨረሻ ሳይሆን የአዲስ ሀላፊነት መጀመሪያ ነው ብለዋል።
ወላጆች የኢኮኖሚ ችግር ተቋቁማችሁ ለልጆቻችሁ ትምህርት ቅድሚያ ሰጣችሁ አስተምራችኋልና ክብር ይገባችኋል ።
በትምህርት የመገንባት ሂደት ላይ የተሳተፉትን መምህራን ፣የኮሌጁ አመራሮች እና ሰራተኞች ዲኑ አመስግነዋል።
ተመራቂ ተማሪዎች ከኮሌጁ ባገኙት ዕውቀት እና ክህሎት ለአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተግበራ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ እጩ መምህራን የዋንጫና የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

4 months ago
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ከሊበርቲ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ተቀበሉ
#ethiopia | የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በአሜሪካ ከሚገኘው ሊበርቲ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት አመራር (Educational Leadership) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቀቁ።
ብፁዕነታቸው ይህንን የትምህርት ማዕረግ በስኬት በማግኘታቸው በበላይ ሊቀ ጳጳስነት የሚመሩት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ለፕሬዝዳንቱ የተሰማውን ጥልቅ ደስታ በይፋ ገልጿል።
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ በስፋት የሚታወቁ ሲሆን ከዚህ ቀደም በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማዘጋጀትና በማሳተም እንዲሁም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በመምህርነትና በአስተዳደር ኃላፊነት የላቀ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩና አሁንም በማገልገል ላይ የሚገኙ ምሁር አባት ናቸው።
ከዚህም ባለፈ ባከናወኗቸው ሰፊ አካዳሚያዊ ተግባራትና ተከታታይ አገልግሎቶች ምክንያት ላለፉት ዓመታት የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማግኘታቸው ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያስታውሳል።

አባትና ልጅ ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አገኙ 🔥
•ፕሮፌሰር ባዬ ይማም (አባት) እና ፕሮፌሰር ቃለአብ ባዬ ይማም (ልጅ)
ሁለቱም የከፍተኛ ትምህርት ህይወታቸውን በአንጋፋው አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ጀምረው በሞያቸው እያገለገሉና ተተኪ ምሁራንን እያፈሩ የሚገኙ ፕሮፌሰሮች ናቸው።
ፕሮፌሰር ባዬ ይማም 44 ዓመታትን እንዲሁም ፕሮፌሰር ቃለዓብ ባዬ 15 ዓመታትን በመምህርነት፣ በተመራማሪነት፣ እንዲሁም በተለያዩ የስራ ሀላፊነቶች ያገለገሉ እና እያገለገሉ የሚገኙ ምሁራን ናቸው።
ሁለቱም የፒኤችዲ ዲግሪያቸውን በሰሩ ልክ በ10ኛው አመት የሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ናቸው።
ዘገባው የዶች ኤችዲ ነው

ረዳት ፕሮፌሰር እና ሠዓሊ ልዑል ሣኅለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ውስጥ ለረጅም ዘመናት በሥነጥበብ መምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ታዋቂው ሰዓሊና ረዳት ፕሮፌሰር ልዑል ሣኅለማርያም ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል።
ረዳት ፕሮፌሰር ልዑል ሣኅለማርያም በሀገራችን ዘመናዊ የሥነጥበብ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ካሳረፉ ታዋቂ ሰዓልያን መካከል አንዱ ሲሆኑ የፖይንት ግሩፕ የሥነጥበብ ስብስብ መሥራችና አባልም ነበሩ።
ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በትምህርት ቤቱ ውስጥ በረዳት ፕሮፌሰርነትና በትምህርት ክፍል ኃላፊነት በመሥራት በርካታ ተተኪ የጥበብ ባለሙያዎችን ያፈሩ ተወዳጅ መምህር ነበሩ።
በተጨማሪም በትምህርት ቤቱ አስተዳደራዊና አካዳሚያዊ ሥራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ጠንካራ ሙያተኛ እንደነበሩ ይነገራል።
ታዋቂው የጥበብ ሰው ልዑል ሣኅለማርያም በሙያዊ ብቃታቸው ብቻ ሳይሆን በማኅበራዊ ሕይወት ተሳትፏቸው፣ በደግነታቸውና በሰው ወዳድነታቸው በብዙዎች ዘንድ የተመሰገኑ ነበሩ።
የሥነጥበብ ሥራዎቻቸውንም በሀገር ውስጥና በተለያዩ የውጭ ሀገራት በግልና በቡድን ለዕይታ በማቅረብ ትልቅ ስም ያተረፉ ባለሙያ ናቸው።
የደራሽ የጥበብ ሰው የቀብር ሥነሥርዓት ረቡዕ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት እንደሚፈጸም ታውቋል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የጥበብ ማኅበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን።
ነፍስ ይማር።
#aleschooloffineartsanddesign #addisababauniversity #ethiopianart #leulsahlemaryam #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለዶክተር ሰለሞን አሊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፀደቀ
#ethiopia | የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማኔጅመንት ቦርድ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ለዶክተር ሰለሞን አሊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል።
ኮሌጁ የባለሙያውን ሰነዶችና የስራ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ ይህንን ከፍተኛ የትምህርት ማዕረግ አፅድቆላቸዋል።
ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ በህክምና ምርምርና በማይክሮባዮሎጂ ዘርፍ በስፋት የሚታወቁ አንጋፋ ስፔሻሊስት ናቸው።
የምርምር ስራዎቻቸውም በዋናነት በተላላፊ በሽታዎች፣ በፀረ ጀርም መድኃኒቶች መላመድ እንዲሁም አዲስና ዳግም በሚቀሰቀሱ የቫይረስ አይነቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው።
ፕሮፌሰሩ ባለፉት 20 ዓመታት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅና በጅማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በመምህርነት፣ በምርምርና በሕክምና አገልግሎት አገራቸውን በቅንነት ያገለገሉ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው ምሁር ናቸው።
በማስተማር ስራቸውም በርካታ የሕክምና፣ የጤና ሳይንስ፣ የማይክሮባዮሎጂና የክሊኒካል ሬዚደንት የቅድመና ድህረ ምረቃ ተማሪዎችን አፍርተዋል።
እስካሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው የምርምር መጽሔቶች ላይ 56 የምርምር ውጤቶችን ያሳተሙ ሲሆን ስድስት ታላላቅ ዓለም አቀፍ የትብብር የምርምር ፈንዶችንም ማሸነፍ ችለዋል።
በተጨማሪም ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ የሀገሪቱን የምርምርና የማይክሮባዮሎጂ አገልግሎት መሠረተ ልማት ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
በዚህም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የመጀመሪያውን የጤና ምርምር መጽሔት፣ ዘመናዊ የተላላፊ በሽታዎች የዘረመል ምርምር ላቦራቶሪ፣ ለቀጣይ ጥናቶች የሚሆኑ ናሙናዎችን ለረጅም ጊዜ ማቆያ ማዕከልና የማይክሮባዮሎጂ መረጃዎችን በዲጂታል መንገድ የማደራጃ ሥርዓት መስርተዋል።
ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ በጤናው ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ ሙያዊ አስተዋፅኦ በቅርቡ ከጤና ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ እውቅና ሽልማት መበርከቱ ይታወሳል።
The Managing Board of Saint Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC), at its regular meeting held today, June 16, 2026, approved the promotion of Dr. Solomon Ali to the rank of Full Professor.
After carefully reviewing her academic, clinical, research, and service achievements, the Board endorsed his promotion in recognition of his outstanding contributions to medical education, research, and institutional leadership
Professor Solomon Ali is a distinguished microbiologist and medical research specialist whose work focuses on infectious diseases, antimicrobial resistance, and emerging/reemerging viral pathogens.
He has served his country for over 20 years at St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) and Jimma University (JU), contributing extensively to academic, clinical, and research activities.
Professor Solomon has trained, mentored, and supervised undergraduate, Master’s, and PhD students, guiding numerous research theses. Throughout his academic and research career, he has published more than 56 articles in reputable international journals and has secured six major competitive international research grants. Prof. Solomon has also played a pivotal role in strengthening research and health service infrastructures.
He has established Millennium Journal of Health, the first scholarly journal in SPHMMC, Infectious Diseases Research and Molecular Laboratory (IDReaM Lab) with integrated bio-banking system, and digitalizing hospital microbiology service laboratory data management system through a DHIS2 based platform.
Recently, Prof. Solomon Ali received national recognition from the Federal Ministry of Health of Ethiopia as the recipient of the 2026 Award for outstanding professional contribution in the health sector.
#stpaulshospital #medicalresearch #microbiology #educationethiopia #healthethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ምሕረት ደግፍ ትውልድና እድገቷ አዲስ አበባ ፤ በልዩ ስሙ ኮልፌ 18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሐምሌ 19 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሁለተኛ ደረጃን በየካቲት 23 ት/ቤት ፣ የመሰናዶ ትምህርቷን ደግሞ በአዲስ ከተማ መሰናዶ ተከታትላ ጨርሳለች። ቀጥሎም በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት በመመረቅ ትምህርቷን ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በአሁኑ ወቅትም በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ሥነ-ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ ናት።
የጋዜጠኝነት ሞያን ከከፍታ የትምህርት ሥልጠና እና የማማከር ተቋም ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በፋክት ቼኪንግ እና ሌሎችም ተያያዥ ሥልጠናዎችን ከሌሎች የሃገር ውስጥ እና የውጪ ተቋማት በሰርተፊኬት ማግኘት ችላለች።
ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር ሙሉ የልጅነት ሕይወቷ ያለፈው በደብረ ገሊላ አማኑኤል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው። አሁን ላለችበትም መሰረት የጣለችው ሰንበት ትምህርት ቤት በነበረችበት ወቅት ነው። በተለይም በሥነ-ጽሑፍ ረገድ ዝንባሌ ሊኖራት የቻለው ከልጅነት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤት እና በመደበኛ ት/ቤት በነበራት ተሳትፎ ነው። እንደ ግጥም ፣ መነባንብ ፣ ድራማ እና ሌሎችም ላይ የበዛ ተሳትፎ ታደርግ ነበር። ይህ ተሳትፎ አሁንም ድረስ ተከትሏት በመምጣት ለፍሬ እንደደረሰ ታምናለች።
በት/ቤት ፣ በወረዳ እና በክፍለ ከተማ ብሎም በከተማ አቀፍ በነበሩ የሥነ-ጸሑፍ ውድድሮች ፣ መድረኮች እና መሰል ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ የተለያዩ ሽልማቶችን እና የምስጋና ወረቀቶችን ማግኘት ችላለች። በመንፈሳዊም በኩል በተመሳሳይ ሁኔታ በነበሯት ተሳትፎዎች በርካታ ሽልማቶችን አግኝታለች። እስከዛሬ ድረስም በተለያዩ የሥነ-ጸሑፍ መድረኮች ሥራዎቿን እያቀረበች ትገኛለች።
ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንደተመረቀች በአጼ ፋሲል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለሁለት ዓመት ያህል በመምህርነት አገልግላለች። በሞያው በቆየችባቸው ጥቂት ዓመታት የተለያዩ የምስጋና እና የደረጃ ሽልማቶችን ማግኘት ችላለች።
ከዚያ በመቀጠል በተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ለአንድ ዓመት ያህል በፕሮግራም አዘጋጅነት የሠራች ሲሆን ፤ የራሷን መንፈሳዊ ፕሮግራሞች እና ሥራዎች በመሥራት ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት በሃገሬ ቴሌቪዥን በከፍተኛ ሪፖርተርነት መደብ እየሠራች የምትገኝ ሲሆን ፤ ላለፈው አንድ ዓመት ያህል በዚሁ ጣቢያ የዜና ክፍል ባልደረባ በመሆን ቆይታለች።
ከልጅነት ጀምሮ የተከተላት የሥነ-ጽሑፍ ፍቅር አሁንም ድረስ ተከትሏት የመጣ ሲሆን ፤ የመጀመሪያ የሆነውንና ” የውቦች ንግሥት” ስትል የሰየመችውን መጽሐፏን ለአንባቢያን ለማድረስ ዝግጅቷን አጠናቃለች።
Via: Addis Books

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሀገራችን ትምህርት ቤቶች ውስጥ መምህራን በከፍተኛ የስራ ጫና በተጨናነቁ የመማሪያ ክፍሎች እና ጊዜን በሚሻሙ አስተዳደራዊ ተግባራት ሲፈተኑ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው። በተለይም አስተማማኝ የኢንተርኔት አገልግሎት እና የዘመናዊ ዲጂታል ቁሳቁሶች እጥረት፣ መምህራን ራሳቸውን እንዳያሳድጉ እና የመማር ማስተማሩን ሂደት በሚፈለገው ልክ እንዳያራምዱት ትልቅ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።
ይህንን አሳሳቢ የትምህርት ጥራት ማነቆ ለመፍታት የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ "ሰው ሰራሽ አስተውሎት" (AI) ቴክኖሎጂን በረዳት መምህርነት በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሊያሰማራ መሆኑን አስታውቋል።
የዚህ አዲስ ቴክኖሎጂ ትልቁ ማራኪ እና ተስፋ ሰጪ ጎን፣ ሙሉ በሙሉ ያለ ኢንተርኔት ግንኙነት መሥራት መቻሉ ነው። ከአዲሱ ሀገራዊ ሥርዓተ ትምህርት ጋር የተጣጣሙ የ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት አስቀድመው የተጫኑበት ይህ ሥርዓት ከፍተኛ አቅም ያላቸውን ዘመናዊ ኮምፒውተሮች አይጠይቅም፤ በማንኛውም ተራ ኮምፒውተር ላይ መሥራት መቻሉ የኔትወርክ እና የመሠረተ ልማት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ጭምር በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን ያደርገዋል። ቴክኖሎጂው የዕለታዊ ትምህርት እቅድ በማውጣት፣ የፈተና ጥያቄዎችን እና የቤት ሥራዎችን በማዘጋጀት እንዲሁም የተሻሉ የማስተማሪያ ዘዴዎችን በመጠቆም የመምህራንን የዕለት ተዕለት ድካም ያቀላል። ሚኒስቴሩ በግልጽ እንዳስቀመጠው፣ የዚህ ቴክኖሎጂ ዋነኛ ዓላማ የመምህራንን ጫና በማቃለል የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ መደገፍ እንጂ ፈጽሞ መምህራንን መተካት አይደለም።
ይህ ብሩህ ተስፋን የሰነቀው አሰራር ተግባራዊ የሚሆነው፣ በየካቲት 2025 የዓለም ባንክ ከ226 ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት በፈቀደለት የትምህርት ትራንስፎርሜሽን እና የኦንላይን ትምህርት ፕሮጀክት ድጋፍ ነው። የሁዋዌይ ኩባንያ ቴክኒካዊ ድጋፍ ያደረገበት ይህ ረዳት መምህር፣ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሙከራ ጊዜውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ተከትሎ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ወደ ስራ ሊገባ ነው። መምህራንም ቴክኖሎጂውን በብቃት እንዲጠቀሙበት ተገቢው ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን፣ ይህ አዲስ ርምጃ ትምህርት ቤቶች ለኢንተርኔት እና ለክላውድ አገልግሎቶች የሚያወጡትን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት ሚዛናዊ፣ ፍትሃዊ እና ዘመናዊ የትምህርት ሥርዓትን ለመገንባት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ተብሎ ይታመናል።

5 months ago
በሕዝብ ልብና አእምሮ ውስጥ የኖሩት ሊቅ፡- ዶ/ር ዘኪ አብዱራህማን!
በጎንደር ሕዝብና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ልብ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ያኖሩ፤ እርሳቸውም ጎንደርን በልባቸው ያተሙ፤ ታዋቂውና ተወዳጁ የጉበት፣ የቆሽትና የሀሞት ቀዶ ሕክምና ሰብ-ስፔሻሊስት ናቸው ዶክተር ዘኪ አብዱራህማን። አገራቸውንና ወገናቸውን ከልብ የሚያፈቅሩ፥ በትምህርታቸው የተመሰከረላቸው እና በተማሪዎቻቸው በእጅጉ የሚወደዱ ምሁር ናቸው። የሀገር ሀብት!
ከተማሪነት እስከ መምህርነትና ስመ-ጥር ሐኪምነት ወደቀሰሙበትና በቅንነት ወዳገለገሉበት ቀደመ ቤታቸው እንኳን በደህና መጡ። መምጣትዎ ለዩኒቨርሲቲያችን ማኅበረሰብ ታላቅ ደስታና ኩራት ነው። በጎንደር ሕዝብ እቅፍ ሆነው የወጣትነት ጊዜያቸውን ያሳለፉ ሁሉ ሁልጊዜም ከጎንደር አይለዩም!
እንደ ዶ/ር ዘኪ ዓይነት ለአገርና ለወገን የሚተርፉ እና ለተተኪ ትውልድ አርአያ የሚሆኑ ሊቃውንትን ማፍራት በመቻሉ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ኩራትና ክብር ይሰማዋል!!!
የጎንደር ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አፀደ ወይን

ታዋቂው የቀዶ ጥገና ሐኪም ተሸለሙ
የኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርና ታዋቂ የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር ስዩም ካሣ መርኔ (ተባባሪ ኘሮፌሰር) የኢትዮጵያ ቀዶ ጥገና ማህበር / Surgical Society of Ethiopia/ የ2026 የህይወት ዘመን ስኬት ተሸላሚ ኾኑ።
ዶ/ር ስዩም በኩባ የሕክምና ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ እኤአ ከ1992 ጀምሮ ላለፉት 33 ዓመታት በዋንኛነት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ዲፓርትመንት በመምህርነት፣ በቀዶ ጥገና ሐኪምነት፣ በዲንነት በተጨማሪም በዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል፣ በጳውሎስ ሆስፒታሎች በደረትና አካባቢው ቀዶ ጥገና ሐኪምነት ማገልገላቸው ታውቋል። በተጨማሪም በተለያዩ የግል ሆስፒታሎች የደረትና አካባቢው ቀዶ ጥገና ሕክምና በማስጀመር ጭምር አገልግለዋል።
ዶ/ር ስዩም ከ30 በላይ ከሙያው ጋር በቀጥታ የተገናኙ ጥናታዊ ጹሑፎችን በሀገር ውስና በውጭ ሀገር ታዋቂ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል።
ዶ/ር ስዩም የማኀበሩ 30ኛው ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል።
"ሽልማቱ ምን ስሜት እንደፈጠረባቸው ዶ/ር ስዩም ተጠይቀው የዓመታት ልፋትና ጥረታቸው ዕውቅና ያገኘበት በመኾኑ መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ዶ/ር ስዩም ሥራ ሲጀምሩ የደረትና አካባቢው ቀዶ ጥገና ሐኪሞች ቁጥር እሳቸውን ጨምሮ 3 ብቻ እንደነበሩ አስታውሰው በአሁን ሰዓት ግን ተተኪ ወጣቶችን በማስተማር የሐኪሞችን ቁጥርና ሕክምናውንም ለማዘመን በተደረገው ጥረት በአቅማቸው ባደረጉት አስተዋፅኦ ደስተኛ መኾናቸውን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ቀዶ ጥገና ማህበር / Surgical Society of Ethiopia / ከተቋቋመ 31 ኛ ዓመት ያስቆጠረ ሲኾን በየዓመቱ ኮንፈረንስ በማካኼድ፤ ከኮንፈረንሱ ጎን ለጎን በሙያው ውስጥ ላቅ ያለ አበርክቶ ላላቸው ባለሙያዎች የዕውቅና ሽልማት ይሰጣል።

ዶ/ር ስዩም በኩባ የሕክምና ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ እኤአ ከ1992 ጀምሮ ላለፉት 33 ዓመታት በዋንኛነት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ዲፓርትመንት በመምህርነት፣ በቀዶ ጥገና ሐኪምነት፣ በዲንነት በተጨማሪም በዳግማዊ ሚኒልክ ፣ በጳውሎስ ሆስፒታሎች በደረትና አካባቢው ቀዶ ጥገና ሐኪምነት ማገልገላቸው ታውቋል። በተጨማሪም በተለያዩ የግል ሆስፒታሎች የደረትና አካባቢው ቀዶ ጥገና ሕክምና በማስጀመር ጭምር አገልግለዋል።
ዶ/ር ስዩም ከ30 በላይ ከሙያው ጋር በቀጥታ የተገናኙ ጥናታዊ ጹሑፎችን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ታዋቂ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል።

ስለኢትዮጵያ ቀዶ ጥገና ማህበር

#ethiopia | የኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርና ታዋቂ የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር ስዩም ካሣ መርኔ (ተባባሪ ኘሮፌሰር) የኢትዮጵያ ቀዶ ጥገና ማህበር / Surgical Society of Ethiopia/ የ2026 የህይወት ዘመን ስኬት ተሸላሚ ኾኑ።
ዶ/ር ስዩም በኩባ የሕክምና ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ እኤአ ከ1992 ጀምሮ ላለፉት 33 ዓመታት በዋንኛነት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ዲፓርትመንት በመምህርነት፣ በቀዶ ጥገና ሐኪምነት፣ በዲንነት በተጨማሪም በዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል፣ በጳውሎስ ሆስፒታሎች በደረትና አካባቢው ቀዶ ጥገና ሐኪምነት ማገልገላቸው ታውቋል።
በተጨማሪም በተለያዩ የግል ሆስፒታሎች የደረትና አካባቢው ቀዶ ጥገና ሕክምና በማስጀመር ጭምር አገልግለዋል።

ፕሮፌሰር ማርታ ኩዌ ኩምሳ
==================
ጋዜጠኛ፣ ፖለቲከኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ፕሮፈሰር ማርታ ኩዌ ኩምሳ ትባላለች። በ1946 ዓ.ም በደምቢዶሎ ከተማ ተወለደች። የፕርስባይቴሪያን ሚሲዮን ልጅ የሆነችው ማርታ፣ ስሟን ያገኘችው አንድ ማርታ ከሚትባልና ካዋለደቻት ነርስ ስም ነው። ኩዌ የሚለውን ስም ደግሞ ከአንድ የኦሮሞ ታሪክ ውስጥ የሚትታወቅ የጀግና ስም ነው የወሰደችው። ማርታ ኩዌ ኩምሳ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እንዳጠናቀቀች አዲስ አበባ ወደሚገኘው ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ አመራች።
ፍላጎቷም ኢንጂኔር መሆን ነበር። ነገር ግን በ1963 ዓ.ም ኩምሳ አዲስ አበባ እንደደረሰች አብዮቱ ፈነዳ። በዚም ኩምሳ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመሆን የአፄ ሀይለስላሴን ከስልጣን መውረድ ደግፋ አደባባይ ወጣች። ኩዌ ኩምሳ እንደጓደኞቿ ሁሉ አፄ ሀይለስላሴ ከስልጣን ከወረደ ምዕራባዊያን ከጫንካችን ላይ ይወርዳሉ፣ ሶሻሊዝም ከተተገበረ መሬት የደሃዎች ይሆናል ብላ ታስብ ነበር፤ ነገር ግን ደርግ ልክ ስልጣን እንደያዘ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተይዘው የነበሩትን ሀብትና መሬት ለግለሰቦች ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ በመንግስት ባለቤትነት እንዲተዳደሩ አደረገ። የኩዌ ኩምሳና ጓደኞቿ ተቃውሞም ቀጠለ።
በዚያን ጊዜም ኩዌ ኩምሳ የጋዜጠኝነት ሙያን አዲስ አበባ በሚገኘው በሉተራን ወርልድ ፌደሬሽን አማካኝነት ሰለጠነች። በመቀጠልም ኩዌ የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ ከሆነውና የትውልድ አገሯ ልጅ ጋር ትዳር መሰረተች። እሱም ሌንጮ ለታ ይባላል። በ1968 ዓ.ም የመጀመሪያ ልጃቸውን አገኙ። ስሙንም ሁሪያ አሉ። ሁሪያ ማለት በአረብኛ ነፃነት ማለት ነው።
ስቃዩ አልቆመም፣ መንግስቱ ቀይ ሽብርን አወጀ። በዚህን ጊዜ ሁለት ልጆችን ሁሪያና ሮበሌን ወልዳ ሶስተኛ ልጇን ለመውለድ ነፍሰጡር እያለች በዛኔ የኦነግ መሪ የነበረው ባሏን መጥተው ከቤት አፍኖ ወሰዱት። ሮበሌም የእናቱ እግር ላይ ተደፍተው ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ሌንጮ ለታን በስድስት ወር ውስጥ አራት ጊዜ በሌሊት ከቤታቸው ወስደው አሰሩት። ባሏ ሌንጮም እስር ቤት እያለ ሶስተኛ ልጃቸውን ጎሊን ወለደች። ጎሊ አንድ አመት ቢሞላውም ሌንጮ ግን ዬት እንደገባ ልታውቅ አልቻለችም ነበር። ይባስ ብሎም በ1973 ዓ.ም ኩዌ ኩምሳን አሰሯት እዚያም አመፁ ላይ ተሳትፈሻል በማለት ቶርቸር አደረጓት። ገና በ20ዎች እድሜ እያለች ከአስር ጊዜ በላይ ወደ ቶርቸር ክፍል እንደወሰዷት ትናገራለች።
ከዚያም በኋላ ለዘጠኝ አመታት እስርቤትን ቤቷ አድርጋ ነበር። የተማረችውን የጋዜጠኝነት ሙያ ተጠቅማ በ1970ዎቹ መጨረሻ በኢትዮጵያ የነበረውን አስከፊ ረሃብ ለአለም ዘግባለች። እስርቤት እያለችም እራሷን የፈረንሳይኛና ትግርኛ ቋንቋን አስተምራለች፤ እንዲሁም ባዮሎጂ ህሳብና ጂኦግራፊን ለእስረኞችና ለእስርቤቱ አስተዳዳሪዎች ልጆች ታስተምር ነበር። ኩዌ እንደምትለው ምርጥ ጭንቅላት ያለው እስርቤት ውስጥ ነው።
እስርቤት እያለችም በአመኒስቲ ኢንተርናሽናልና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግፊት ኩዌ ለህክምና ወደ ሆስፒታል እንድትሄድ ተፈቀደላት። ሆስፒታል እያለችም የናፈቋት ልጆቿን ለማግኘት ስለማይፈቀድ ለጠባቂዎቹ ጉቦ ተሰጠና ከልጆቿ ጋር ለ15 ደቂቃ ያክል አወራች።
በእስርቤት እያለች PEN የተባለው ድርጅት አንድ ፖስትካርድ ላከላት፣ የተፃፈበት መልዕክትም እንዲ ይላል፦ "We know about you. You are not alone.” ይህም ተስፋዋን አለመለመ። ኩዌ የካናዳ አባቴ ብላ የሚትጠራው የካናዳ ታዋቂ ፀሐፊ Timothy Findleyም እስርቤት እያለች ደጋግሞ “Hope against despair” የሚል መልዕክትን የያዘ ፖስታ ይልክላት ነበር። አንድ እሁድ ላይ ልጆቿ ሊጎበኛት ሲለሚመጡ ፀጉሯን እየታጠበች እያለች ስሟ በድምፀማጉዪያ ተጠራ። ጥሪው ለሞትም ሊሆን ይችላል ነገር ግን ነፃ እንደወጣች ተነገራት። ቀኑ እሁድ ጳጉሜ 5፣ 1981 ዓ.ም ነበር። ልጆቿንም አገኘች ባሏ ሌንጮ ግን የለም። ሶስቱንም ልጆቻቸውም ይዛ በ1983 ዓ.ም ወደ ካናዳ ሄደች። አንድ አመት እንደቆየችም ትምህርቷን ጀምራ በ1988 ዓ.ም ከዮርክ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪዋን በሶሻል ዎርክ ያዘች። በዚም አመት የህዩማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch) የሰብዓዊ መብት ሽልማት ተበረከተላት። ከአመት በኋላም በቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ድግሪዋን አጠናች ። በ1995 ዓ.ም በዊልፍርድ ላውረር ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ተቀጥራ እየሰራች በጎን ደግሞ የዶክተሬት ትምህርቷን በቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ አጠናች። አሁን ፕሮፌሰር ማርታ ኩዌ ኩምሳ በካናዳ አገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እያስተማረች ትገኛለች።
ምንጭ: Ancient history of Oromoo

ታዋቂው መምህር፣ ደራሲና የሥነ ጽሑፍ ባለሙያ
የአቶ ወርቁ አበራ የ፵ ቀን መታሰቢያ መርሃ ግብር በመቄዶንያ
#ethiopia | ታዋቂው መምህር፣ ደራሲና የሥነ ጽሑፍ ባለሙያ የነበሩት የአቶ ወርቁ አበራ የ፵ ቀን መታሰቢያ መርሃ ግብር ዛሬ፣ ዓርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እየተከናወነ ነው።
ይህ የመታሰቢያ ፕሮግራም በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማኅበር ግቢ ውስጥ ከቀኑ 6:00 ሰዓት የጀመረ ሲሆን፣ በዕለቱም ለታሰበው ዝግጅት የተሰናዳው ፀበል ጻድቅ ይቀርባል።
አቶ ወርቁ አበራ በ1951 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተወልደው በባዮሎጂ የትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።
በደዶላ፣ በከበደ ሚካኤል እና በኢምፔሪያል አካዳሚ በትምህርት አመራርና በመምህርነት ሙያ ሀገራቸውን በታማኝነት አገልግለዋል።
ከሙያቸው ባሻገር ከ15 በላይ መጻሕፍትን በማርትዕና ክፉ ቀን ያልፋል ፅኑ ሰዎች ግን ያልፉታል እንዲሁም ፍርሃትህን አትፍራ የተሰኙ ተነባቢ መጻሕፍትን ወደ አማርኛ በመተርጎም በሥነ ጽሑፉ ዘርፍ ደማቅ አሻራ አሳርፈዋል።
ባለ ትዳርና የሦስት ልጆች አባት የነበሩት አቶ ወርቁ፣ በ67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።
ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በመቄዶንያ በሚገኘው አድራሻ በመታሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።
#workuabera #macedonia #literature #education #inmemoriam #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

7 months ago
ቅዱስ ኤፍሬም ለእመቤታችን ካለው ልዩ ፍቅር የተነሳ ... 🙏
አንዳንድ ምንጮች ከቅድስና ሕይወቱ በመነሳት ወላጆቹ ክርስቲያኖች እንደነበሩ ቢናገሩም በ306 ዓ.ም ገደማ በጥንቷ “ሜሶፖታሚያ” በአሁኑ ደቡባዊ ቱርክና ምዕራባዊ ሶርያ መካከል በምትገኝ “ንጽቢን” በምትባል ቦታ ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች እንደተወለደ ይታመናል ቅዱስ ኤፍሬም፡፡ ከወላጆቹ ጋር እስከ 10 ዓመቱ ብቻ የኖረ ሲሆን የእግዚአብሔር መንፈስ አመላክቶት የአካባቢ ተወላጅና ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ ከሆነው ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን ትምህርተ ክርስትናን ተምሮ ተጠመቀ፡፡ በኋላም በቅዱስ ያዕቆብ ዘንድ በብሕትውና ተወስኖ በመማርና በማስተማር በንጽቢን ለሚገኘው መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ኃላፊ እስክመሆን ደርሷል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ከመምህሩ ጋር አርዮስን ለማውገዝ በ325 ዓ.ም በተካሄደው የኒቅያው ጉባኤ ላይ ተገኝቷል፡፡ ከጉባኤው መልስ መንፈሰ እግዚአብሔር በራዕይ በገለፀለት መሠረት ቅዱስ ኤፍሬም ቁጥሩ ከሦስት መቶ አስራ ስምንቱ ሊቃውንት የሆነው ቅዱስ ባስልዮስን ለመገናኘት ወደ ቂሣርያ ሄዷል፡፡
ቅዱስ ባስልዮስም ዲቁና ሰጥቶ ከሀገረ ስብከቱ ከፍሎ እንዲያስተምር ወስኖ በእርሱ ዘንድ አኑሮታል፤ በዚያም ቦታ ብዙ ተአምራትን አድርጓል፣ መጻሕፍትም ጽፏል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በትውፊት እንደሚታወቀው ምንኩስናን በገቢር ገለጣት እንጂ ሥርዓተ ምንኩስናን መፈጸሙን በግልጽ የሚመለክት ማስረጃ አልተገኘም፡፡ እንዲያውም በሶርያውያን ክርስቲያኖች የሚዘወተረውን ራስን በአንድ ስፍራ ወስኖ በብሕትውናና በመምህርነት ቤተክርስቲያንን የማገልገል ሕይወት ይኖር እንደነበር ይታመናል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ለእመቤታችን ካለው ልዩ ፍቅር የተነሳ ምጽዋት እንኳ በእርሷ ስም ብቻ ይመጸውት ነበር፡፡ ይህን ፍቅሩን አይታም መጥታ አመስግነኝ ስትለው የሰባቱን ቀን ውዳሴያት መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት በፊቷ እየተናገረ አመስግኗታል፡፡
ከዚያም በኋላ አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ እስከሚል ድረስ እንደሌሎቹ የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አበው ሁሉ አስራ አራት ሺህ ድርሳናትንና ተግሳጻትን ደርሷል፡፡ ከደረሳቸው መጻሕፍት በተለየ ሁኔታ በየዕለቱ የሚጸለየውን ውዳሴ ማርያምን ጨምሮ ብዙዎቹ ወደ ግእዝ ተመልሰዋል፡፡ መጽሐፈ አክሱም እንደሚለው እርሱና ቅዳሴ ማርያምን የደረሰው አባ ሕርያቆስ በአክሱም ማይ ኪራህ በሚባል ስፍራ ከቅዱስ ያሬድ ጋር ተገናኝተው ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን ነግረውት ዜማ ሰርቶለታል፡፡ በእመቤታችን እናትነት ፈጽመው የታመኑ ገዳማውያንም እንደእርሱ ሁሉ በውዳሴ ማርያም “ሰዓሊ ለነ ቅድስት” ይሏታል፤ እርሷም በበረከት ትጎበኛቸዋለች፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የዚህ በረከታቸው ተካፋይ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Comments