Logo
FastMereja
ፕሮፌሰር ማርታ ኩዌ ኩምሳ
==================
ጋዜጠኛ፣ ፖለቲከኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ፕሮፈሰር ማርታ ኩዌ ኩምሳ ትባላለች። በ1946 ዓ.ም በደምቢዶሎ ከተማ ተወለደች። የፕርስባይቴሪያን ሚሲዮን ልጅ የሆነችው ማርታ፣ ስሟን ያገኘችው አንድ ማርታ ከሚትባልና ካዋለደቻት ነርስ ስም ነው። ኩዌ የሚለውን ስም ደግሞ ከአንድ የኦሮሞ ታሪክ ውስጥ የሚትታወቅ የጀግና ስም ነው የወሰደችው። ማርታ ኩዌ ኩምሳ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እንዳጠናቀቀች አዲስ አበባ ወደሚገኘው ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ አመራች።

ፍላጎቷም ኢንጂኔር መሆን ነበር። ነገር ግን በ1963 ዓ.ም ኩምሳ አዲስ አበባ እንደደረሰች አብዮቱ ፈነዳ። በዚም ኩምሳ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመሆን የአፄ ሀይለስላሴን ከስልጣን መውረድ ደግፋ አደባባይ ወጣች። ኩዌ ኩምሳ እንደጓደኞቿ ሁሉ አፄ ሀይለስላሴ ከስልጣን ከወረደ ምዕራባዊያን ከጫንካችን ላይ ይወርዳሉ፣ ሶሻሊዝም ከተተገበረ መሬት የደሃዎች ይሆናል ብላ ታስብ ነበር፤ ነገር ግን ደርግ ልክ ስልጣን እንደያዘ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተይዘው የነበሩትን ሀብትና መሬት ለግለሰቦች ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ በመንግስት ባለቤትነት እንዲተዳደሩ አደረገ። የኩዌ ኩምሳና ጓደኞቿ ተቃውሞም ቀጠለ።

በዚያን ጊዜም ኩዌ ኩምሳ የጋዜጠኝነት ሙያን አዲስ አበባ በሚገኘው በሉተራን ወርልድ ፌደሬሽን አማካኝነት ሰለጠነች። በመቀጠልም ኩዌ የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ ከሆነውና የትውልድ አገሯ ልጅ ጋር ትዳር መሰረተች። እሱም ሌንጮ ለታ ይባላል። በ1968 ዓ.ም የመጀመሪያ ልጃቸውን አገኙ። ስሙንም ሁሪያ አሉ። ሁሪያ ማለት በአረብኛ ነፃነት ማለት ነው።

ስቃዩ አልቆመም፣ መንግስቱ ቀይ ሽብርን አወጀ። በዚህን ጊዜ ሁለት ልጆችን ሁሪያና ሮበሌን ወልዳ ሶስተኛ ልጇን ለመውለድ ነፍሰጡር እያለች በዛኔ የኦነግ መሪ የነበረው ባሏን መጥተው ከቤት አፍኖ ወሰዱት። ሮበሌም የእናቱ እግር ላይ ተደፍተው ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ሌንጮ ለታን በስድስት ወር ውስጥ አራት ጊዜ በሌሊት ከቤታቸው ወስደው አሰሩት። ባሏ ሌንጮም እስር ቤት እያለ ሶስተኛ ልጃቸውን ጎሊን ወለደች። ጎሊ አንድ አመት ቢሞላውም ሌንጮ ግን ዬት እንደገባ ልታውቅ አልቻለችም ነበር። ይባስ ብሎም በ1973 ዓ.ም ኩዌ ኩምሳን አሰሯት እዚያም አመፁ ላይ ተሳትፈሻል በማለት ቶርቸር አደረጓት። ገና በ20ዎች እድሜ እያለች ከአስር ጊዜ በላይ ወደ ቶርቸር ክፍል እንደወሰዷት ትናገራለች።

ከዚያም በኋላ ለዘጠኝ አመታት እስርቤትን ቤቷ አድርጋ ነበር። የተማረችውን የጋዜጠኝነት ሙያ ተጠቅማ በ1970ዎቹ መጨረሻ በኢትዮጵያ የነበረውን አስከፊ ረሃብ ለአለም ዘግባለች። እስርቤት እያለችም እራሷን የፈረንሳይኛና ትግርኛ ቋንቋን አስተምራለች፤ እንዲሁም ባዮሎጂ ህሳብና ጂኦግራፊን ለእስረኞችና ለእስርቤቱ አስተዳዳሪዎች ልጆች ታስተምር ነበር። ኩዌ እንደምትለው ምርጥ ጭንቅላት ያለው እስርቤት ውስጥ ነው።

እስርቤት እያለችም በአመኒስቲ ኢንተርናሽናልና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግፊት ኩዌ ለህክምና ወደ ሆስፒታል እንድትሄድ ተፈቀደላት። ሆስፒታል እያለችም የናፈቋት ልጆቿን ለማግኘት ስለማይፈቀድ ለጠባቂዎቹ ጉቦ ተሰጠና ከልጆቿ ጋር ለ15 ደቂቃ ያክል አወራች።

በእስርቤት እያለች PEN የተባለው ድርጅት አንድ ፖስትካርድ ላከላት፣ የተፃፈበት መልዕክትም እንዲ ይላል፦ "We know about you. You are not alone.” ይህም ተስፋዋን አለመለመ። ኩዌ የካናዳ አባቴ ብላ የሚትጠራው የካናዳ ታዋቂ ፀሐፊ Timothy Findleyም እስርቤት እያለች ደጋግሞ “Hope against despair” የሚል መልዕክትን የያዘ ፖስታ ይልክላት ነበር። አንድ እሁድ ላይ ልጆቿ ሊጎበኛት ሲለሚመጡ ፀጉሯን እየታጠበች እያለች ስሟ በድምፀማጉዪያ ተጠራ። ጥሪው ለሞትም ሊሆን ይችላል ነገር ግን ነፃ እንደወጣች ተነገራት። ቀኑ እሁድ ጳጉሜ 5፣ 1981 ዓ.ም ነበር። ልጆቿንም አገኘች ባሏ ሌንጮ ግን የለም። ሶስቱንም ልጆቻቸውም ይዛ በ1983 ዓ.ም ወደ ካናዳ ሄደች። አንድ አመት እንደቆየችም ትምህርቷን ጀምራ በ1988 ዓ.ም ከዮርክ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪዋን በሶሻል ዎርክ ያዘች። በዚም አመት የህዩማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch) የሰብዓዊ መብት ሽልማት ተበረከተላት። ከአመት በኋላም በቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ድግሪዋን አጠናች ። በ1995 ዓ.ም በዊልፍርድ ላውረር ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ተቀጥራ እየሰራች በጎን ደግሞ የዶክተሬት ትምህርቷን በቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ አጠናች። አሁን ፕሮፌሰር ማርታ ኩዌ ኩምሳ በካናዳ አገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እያስተማረች ትገኛለች።

ምንጭ: Ancient history of Oromoo

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.