9 days ago
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዶ/ር በርናንድ እና ሲ/ር እማዋይሽ ጅምር ሆስፒታል ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውል ስምምነት አደረገ
#ethiopia | በጎንደር ከተማ የተጀመረው የዶክተር በርናንድ አንደርሰን እና የሲስተር እማዋይሽ ገሪማ መታሰቢያ ጅምር ሆስፒታል ለኢትዮጵያ ህዝብ የጤና አገልግሎትና የምርምር ማዕከል ሆኖ እንዲቀጥል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከኑዛዜ ወራሾች እና ተጠቃሚዎች ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነት በ2008 ዓ.ም ተጀምሮ የነበረውን ሀገራዊ አላማ ከውልና ማስረጃ እንዲሁም ከእንደራሴው አቶ ዳዊት ደርበው ጋር በመተባበር ዳር ለማድረስ ያስቻለ ምዕራፍ መሆኑ ነው።
በተደረገው ስምምነት መሠረት ሆስፒታሉ የማይሸጥ፣ የማይለወጥ፣ ቅርጽና ይዘቱ ሳይለወጥ እንዲሁም ስመ ንብረቱ ወደ ሌላ ሶስተኛ ወገን ሳይተላለፍ የለጋሾቹ የዘላለም መታሰቢያ ሆኖ እንዲኖር ዋስትና ይሰጣል።
የተከናወነው ስምምነት መሠረት ዩኒቨርሲቲው ህንጻውን አጠናቆ ለህዝብ የህክምና አገልግሎት፣ ለትምህርት እና ለምርምር ማዋል የሚችለውን ጠንካራ መሰረት የጣለ ሲሆን፣ በኑዛዜው የተገለጹት ተጠቃሚዎች መብቶችም ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ ተደርጓል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሥራት አፀደወይን ለጋሾቹ ለህዝብ ጥቅም የለገሱት ይህ በጎ አድራጎት ለወደፊቱ ትውልድ ትልቅ አርአያ የሚሆንና የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ እንዲሁም የህክምና ቱሪዝም የሚያሳድግ መሆኑን ገልጸዋል።
የወራሾችን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ ዳዊት ደርበው እንደገለጹት፣ በዕለቱ የተገኙበት ዋና ምክንያት በሲስተር ማዋይሽ ገሪማ ኑዛዜ መሠረት የተጀመረውን ሆስፒታል አጠናቀው ወደ ተግባር ለማዋል እንደሆነ አስረድተዋል።
እርሳቸውም በኑዛዜው እንደራሴ በመሆን የተሰጣቸውን ሙሉ ስልጣን በመጠቀም ሥራውን ለማስፈጸም እንደተገኙ ገልጸው፣ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሲስተር ማዋይሽ በህይወት በነበረችበት ጊዜ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር አድርጋው የነበረውን ውል እንደገና በማነቃቃት የጀመሩትን ሂደት ለማጠናቀቅ መሆኑን አብራርተዋል።
ስምምነቱ ከተጠናቀቀ በኋላም ተሳታፊዎች የዶክተር በርናንድ አንደርሰን እና የሲስተር እማዋይሽ ገሪማ መታሰቢያ ሙዚየምን እንዲሁም የሆስፒታሉን ጅምር ግንባታ በጋራ ጎብኝተዋል።
#gondaruniversity #drbernardandsisteremawesh #gondar #ethiopia #healthcare #medicalresearch #legacy #publichealth

2 months ago
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለዶክተር ሰለሞን አሊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፀደቀ
#ethiopia | የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማኔጅመንት ቦርድ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ለዶክተር ሰለሞን አሊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል።
ኮሌጁ የባለሙያውን ሰነዶችና የስራ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ ይህንን ከፍተኛ የትምህርት ማዕረግ አፅድቆላቸዋል።
ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ በህክምና ምርምርና በማይክሮባዮሎጂ ዘርፍ በስፋት የሚታወቁ አንጋፋ ስፔሻሊስት ናቸው።
የምርምር ስራዎቻቸውም በዋናነት በተላላፊ በሽታዎች፣ በፀረ ጀርም መድኃኒቶች መላመድ እንዲሁም አዲስና ዳግም በሚቀሰቀሱ የቫይረስ አይነቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው።
ፕሮፌሰሩ ባለፉት 20 ዓመታት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅና በጅማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በመምህርነት፣ በምርምርና በሕክምና አገልግሎት አገራቸውን በቅንነት ያገለገሉ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው ምሁር ናቸው።
በማስተማር ስራቸውም በርካታ የሕክምና፣ የጤና ሳይንስ፣ የማይክሮባዮሎጂና የክሊኒካል ሬዚደንት የቅድመና ድህረ ምረቃ ተማሪዎችን አፍርተዋል።
እስካሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው የምርምር መጽሔቶች ላይ 56 የምርምር ውጤቶችን ያሳተሙ ሲሆን ስድስት ታላላቅ ዓለም አቀፍ የትብብር የምርምር ፈንዶችንም ማሸነፍ ችለዋል።
በተጨማሪም ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ የሀገሪቱን የምርምርና የማይክሮባዮሎጂ አገልግሎት መሠረተ ልማት ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
በዚህም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የመጀመሪያውን የጤና ምርምር መጽሔት፣ ዘመናዊ የተላላፊ በሽታዎች የዘረመል ምርምር ላቦራቶሪ፣ ለቀጣይ ጥናቶች የሚሆኑ ናሙናዎችን ለረጅም ጊዜ ማቆያ ማዕከልና የማይክሮባዮሎጂ መረጃዎችን በዲጂታል መንገድ የማደራጃ ሥርዓት መስርተዋል።
ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ በጤናው ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ ሙያዊ አስተዋፅኦ በቅርቡ ከጤና ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ እውቅና ሽልማት መበርከቱ ይታወሳል።
The Managing Board of Saint Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC), at its regular meeting held today, June 16, 2026, approved the promotion of Dr. Solomon Ali to the rank of Full Professor.
After carefully reviewing her academic, clinical, research, and service achievements, the Board endorsed his promotion in recognition of his outstanding contributions to medical education, research, and institutional leadership
Professor Solomon Ali is a distinguished microbiologist and medical research specialist whose work focuses on infectious diseases, antimicrobial resistance, and emerging/reemerging viral pathogens.
He has served his country for over 20 years at St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) and Jimma University (JU), contributing extensively to academic, clinical, and research activities.
Professor Solomon has trained, mentored, and supervised undergraduate, Master’s, and PhD students, guiding numerous research theses. Throughout his academic and research career, he has published more than 56 articles in reputable international journals and has secured six major competitive international research grants. Prof. Solomon has also played a pivotal role in strengthening research and health service infrastructures.
He has established Millennium Journal of Health, the first scholarly journal in SPHMMC, Infectious Diseases Research and Molecular Laboratory (IDReaM Lab) with integrated bio-banking system, and digitalizing hospital microbiology service laboratory data management system through a DHIS2 based platform.
Recently, Prof. Solomon Ali received national recognition from the Federal Ministry of Health of Ethiopia as the recipient of the 2026 Award for outstanding professional contribution in the health sector.
#stpaulshospital #medicalresearch #microbiology #educationethiopia #healthethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ መልክ የተደራጀውን የአርማውር ሐንሰን የምርምር ማዕከል መረቁ
#ethiopia | ለበርካታ ዓመታት በአለርት የሕክምና ማዕከል ውስጥ በተወሰነ አቅም የምርምር ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየው የአርማውር ሐንሰን የምርምር ተቋም በመንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በአዲስ መልክ ሪፎርም ተደርጓል።
ይህ ተቋም በአዋጅ በድጋሚ እንዲደራጅ ከተደረገ በኋላ አስፈላጊው የግንባታ ሥራ ተጠናቆለትና ዘመናዊ ግብዓቶች ተሟልተውለት በዛሬው ዕለት በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
ተቋሙ ወደዚህ አዲስ ምዕራፍ የተሸጋገረው በሀገሪቱ የጤና ምርምር ዘርፍ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና የሳይንስ ምርምርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ታቅዶ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ዘመናዊ የምርምር ማዕከል በውስጡ 40 የሚደርሱ ላቦራቶሪዎችን የያዘ ሲሆን በተለይም የላቁ የጂኖሚክስ እና የባዮኢንፎርማቲክስ የምርምር ቦታዎችን በማካተቱ በዘርፉ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪም ማዕከሉ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራት፣ ደህንነትና ብቃት በተገቢው ሁኔታ የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ ማዕከልን በውስጡ አካቶ የያዘ በመሆኑ ለሀገር በቀል የመድኃኒት ኢንዱስትሪ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።
ይህ ግዙፍ የምርምር ተቋም መገንባቱ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ራሷን ችላ የሕዝቧን ደህንነት ለመጠበቅ ለምታደርገው ጥረት እንደ ትልቅ ስኬት የሚቆጠር ነው።
#ethiopia #ahri #medicalresearch #healthinnovation #abiyahmed #scienceandtechnology #genomics #bioinformatics #publichealth

Comments