Logo
Getu Temesgen
🎓 የነፃነት ጮራ!
ለ60 ዓመታት ትውልድ የቀረፁት መምህር ጠምቀ...
#ethiopia | ​ከአክሱም ማይብራዚዬ ገዳም የቤተ ክህነት እውቀት እስከ ጎንደር ዘመናዊ ትምህርት... ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በ1957 ዓ.ም በቄራ እና ጎፋ አካባቢ "የነፃነት ጮራ ትምህርት ቤትን" የመሰረቱት ታላቁ አባት!

​መምህር ጠምቀ፤ ትምህርት ቤታቸው በደርግ ዘመን ቢወረስም፤ ዓላማቸውን ግን ማንም አልወረሰባቸውም።

በፅናት እና በታማኝነት መምህርነትን እንደ ሥራ ሳይሆን እንደ ሕይወት ተልዕኮ በመቁጠር በርካታ ሀኪሞችን፣ ኢንጂነሮችን፣ ጋዜጠኞችን እና ተመራማሪዎችን አፍርተዋል።

​ልዩ የክብር መርሐግብር!
እኚህን በሕይወት ያሉ ታላቅ ባለውለታ ለመዘከር እና ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለማክበር፤ በቀድሞ ተማሪዎቻቸው፣ ወዳጆቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ጥያቄ መሰረት ልዩ ዝግጅት ተሰናድቷል።

​📅 ጥር 16 ቀን 2018 ዓ.ም

​በዕለቱ ምን ይጠበቃል?
📘 የሕይወት ታሪካቸውን የሚዘክረው "የትምህርት ጮራ" የተሰኘ ባለ 80 ገጽ መጽሐፍ ይመረቃል።

🎙 ከትምህርት ባልደረቦቻቸው እና ከተማሪዎች ጋር የፓናል ውይይት ይደረጋል።

🎖 የትምህርት ቢሮ እና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ምስጋና ይቀርባል።

​በሕይወት እያሉ ባለውለታዎቻችንን እናክብር!
የነፃነት ጮራ ፍሬዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

​#netsanetchora #school #education #teachertemke #tribute #addisababa #kera #gofa #ethiopia​ #alumni​ #education #hero #teacher #netsanetchora #thankyouteacher

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.