Logo
YenetaTube
ቅዱስ ኤፍሬም ለእመቤታችን ካለው ልዩ ፍቅር የተነሳ ... 🙏

አንዳንድ ምንጮች ከቅድስና ሕይወቱ በመነሳት ወላጆቹ ክርስቲያኖች እንደነበሩ ቢናገሩም በ306 ዓ.ም ገደማ በጥንቷ “ሜሶፖታሚያ” በአሁኑ ደቡባዊ ቱርክና ምዕራባዊ ሶርያ መካከል በምትገኝ “ንጽቢን” በምትባል ቦታ ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች እንደተወለደ ይታመናል ቅዱስ ኤፍሬም፡፡ ከወላጆቹ ጋር እስከ 10 ዓመቱ ብቻ የኖረ ሲሆን የእግዚአብሔር መንፈስ አመላክቶት የአካባቢ ተወላጅና ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ ከሆነው ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን ትምህርተ ክርስትናን ተምሮ ተጠመቀ፡፡ በኋላም በቅዱስ ያዕቆብ ዘንድ በብሕትውና ተወስኖ በመማርና በማስተማር በንጽቢን ለሚገኘው መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ኃላፊ እስክመሆን ደርሷል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ከመምህሩ ጋር አርዮስን ለማውገዝ በ325 ዓ.ም በተካሄደው የኒቅያው ጉባኤ ላይ ተገኝቷል፡፡ ከጉባኤው መልስ መንፈሰ እግዚአብሔር በራዕይ በገለፀለት መሠረት ቅዱስ ኤፍሬም ቁጥሩ ከሦስት መቶ አስራ ስምንቱ ሊቃውንት የሆነው ቅዱስ ባስልዮስን ለመገናኘት ወደ ቂሣርያ ሄዷል፡፡

ቅዱስ ባስልዮስም ዲቁና ሰጥቶ ከሀገረ ስብከቱ ከፍሎ እንዲያስተምር ወስኖ በእርሱ ዘንድ አኑሮታል፤ በዚያም ቦታ ብዙ ተአምራትን አድርጓል፣ መጻሕፍትም ጽፏል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በትውፊት እንደሚታወቀው ምንኩስናን በገቢር ገለጣት እንጂ ሥርዓተ ምንኩስናን መፈጸሙን በግልጽ የሚመለክት ማስረጃ አልተገኘም፡፡ እንዲያውም በሶርያውያን ክርስቲያኖች የሚዘወተረውን ራስን በአንድ ስፍራ ወስኖ በብሕትውናና በመምህርነት ቤተክርስቲያንን የማገልገል ሕይወት ይኖር እንደነበር ይታመናል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ለእመቤታችን ካለው ልዩ ፍቅር የተነሳ ምጽዋት እንኳ በእርሷ ስም ብቻ ይመጸውት ነበር፡፡ ይህን ፍቅሩን አይታም መጥታ አመስግነኝ ስትለው የሰባቱን ቀን ውዳሴያት መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት በፊቷ እየተናገረ አመስግኗታል፡፡

ከዚያም በኋላ አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ እስከሚል ድረስ እንደሌሎቹ የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አበው ሁሉ አስራ አራት ሺህ ድርሳናትንና ተግሳጻትን ደርሷል፡፡ ከደረሳቸው መጻሕፍት በተለየ ሁኔታ በየዕለቱ የሚጸለየውን ውዳሴ ማርያምን ጨምሮ ብዙዎቹ ወደ ግእዝ ተመልሰዋል፡፡ መጽሐፈ አክሱም እንደሚለው እርሱና ቅዳሴ ማርያምን የደረሰው አባ ሕርያቆስ በአክሱም ማይ ኪራህ በሚባል ስፍራ ከቅዱስ ያሬድ ጋር ተገናኝተው ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን ነግረውት ዜማ ሰርቶለታል፡፡ በእመቤታችን እናትነት ፈጽመው የታመኑ ገዳማውያንም እንደእርሱ ሁሉ በውዳሴ ማርያም “ሰዓሊ ለነ ቅድስት” ይሏታል፤ እርሷም በበረከት ትጎበኛቸዋለች፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የዚህ በረከታቸው ተካፋይ እንሆናለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.