ቋንጤ ለጀግናዋ ወርኮ እየወረደች ትገኛለች
#ethiopia | የአዝማች ይርጋ ገብሬ ድረታ በትውልድ አካባቢያቸው በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ቋንጤ የለቅሶ ስነ ስርዓት(ወርኮ)እየተካሄደ ይገኛል።
አዝማች ይርጋ ገብሬ ድረታ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ከእናታቸው ከእቴት ጫሙት ስፍር እና ከአባታቸው ከአዝማች ገብሬ ድረታ በአዲስ አበባ ተወለዱ።
በቄስ ትምህርት ቤት፣ ቀጥሎም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኮከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት በመግባት መደበኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
ሐረር መምህራን ማሠልጠኛ ተቋም በመግባት የመምህርነት ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዮኒቨርሲቲ በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
በመቀጠልም አሜሪካን ሀገር ከሚገኘው ዌስተርን ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን፣ እንዲሁም ከኔዘርላንድ ሀገር ዴልፍት ዮኒቨርሲቲ በማኔጅመንት ዲፕሎማ እና በልዩ ልዩ ሞያ ዘርፎች በርካታ ሰርተፍኬቶችን አግኝተዋል።
አዝማች ይርጋ ሀገርን ማገልገል በመምህርነት ሙያ ሲሆን በቀድሞው ሲዳሞ ክፍለሃገር፣ በኤርትራ እና በአሜሪካን ሀገር ቨርጅን አይላንድስም በአማርኛ መምህርነት ሠርተዋል።
በመምህራን ማሠልጠኛዎችም በአዲስ አበባ፣ በጅማ እና በሐረር ከመምህርነት አንሥቶ በምክትል ዳይሬክተርነት እና በተማሪዎች ዲንነት አገልግለዋል።
ከመምህርነት በተጨማሪ በትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ መምህራን የትምህርት ኤክስፐርት፣ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ዋና አስተባባሪ፣ የአጠቃላይ ሥርዓተ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ፣ የጎልማሶች ትምህርት የፕላን፣ የምርምር፣ የክትትል እና ግምገማ ዋና ኃላፊ፣ የፕላን ኤክስፐርት፣ እንዲሁም የጎልማሶች ትምህርት መምሪያ ኃላፊ እና እጅግ በጣም የተመሰገኑበት የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ ላእላይ አመራር በመሆን አገራቸውን አገልግለዋል።
ወቅቱም መኀይምነትን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት በ15 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተካሄደውን የመሠረተ ትምህርት ዘመቻን በመወጠን፣ ቅርጽ በማስያዝ እና በመምራት የጎልማሶች ትምህርት ስኬታማነትን በማረጋገጥ ባሳዩት እጅግ የላቀ አመራር ከፍተኛ እውቅና እና ሽልማቶችን አግኝተውበታል።
ከዚህም በተጨማሪ አዝማች ይርጋ በመሠረታዊ ትምህርት ዘመቻ ሂደት የጉራጌ ቋንቋ የፊደል ገበታ ቀረጻ ሥራን ከሠሩት ምሁራን አንዱ ሲሆኑ ይህም ሥራቸው የጉራጊኛ ቋንቋ መጽሐፍት ህትመት እንዲዳብር ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓዋል።
ከመንግሥት ኃላፊነቶች በተጨማሪ የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅትን ለ10 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት መርተዋል።
በጉራጌ ዞን ብቸኛ የነበረውን የእመድብር 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በዘመናዊ መልኩ እንዲደራጅ ማድረግን ጨምሮ በርካታ ትምህርት ቤቶችን በእንዲሰሩ አስተባረዋል፡፡
የጉራጌ ባህላዊ ህግ (የጆካ ቂጫ) የሽማግሌዎች ግብረሃይል በማቋቋም ወደ ሰነድነት እንዲቀየር እና እንዲሰራጭ ማብቃታቸው ዋነኛው ሰው ነበሩ።
አዝማች በብዙ ዘርፎች መስክ ስኬታማ የነበሩ ሰው በመሆናቸው እንደ ምሁር የሰላ አዕምሮ የነበራቸው አሰላሳይ፣ እንደ ሐገር ሽማግሌ ታሪክና ጨዋታ አዋቂ፣ እንደ ነጋዴም ኢንቬስተር የነበሩ ስኬታማ ሰው ነበሩ።
በተለይም ኢትዮጵያ የመሰረተ ትምህርት በማደራጀት ስኬታማ ስራ ሰርተዋል፡፡
በዚህም አልፋ የትምህርት እና ስልጠና አክሲዮን ማኅበር፣ ኮከብ የቴክኖሎጂ እና ንግድ ድርጅት፣ አልፋ አታሚዎች፣ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ፣ ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ ፣ ደቡብ ግሎባል ባንክ፣ ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ፣ አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ዳኪ የመጠጥ ውሃ ኩባንያ ሲመሰረቱ በመሥራችነት፣ በቦርድ አባልነት፣ በቦርድ ሊቀመንበርነት፣ እንዲሁም በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል፡፡
አዝማች ይርጋ ገብሬ ንቁ የፓለቲካ ተሳትፎ የሚያደርጉ ዜጋም የነበሩ ሲሆን በኢህአፓ፣ በኢሠፓ፣ በጉሕዴግ፣ በቅንጅት እና በኢዜማ የፓለቲካ ድርጅቶች በመደበኛ አባልነት እና አመራርነት ተሳትፈዋል።
አዝማች ይርጋ የመልካም ስነምግባር አምባሳደር፣ የጉራጌ አባት፣ ነገር አዋቂ፣ አንደበተ ርእቱ፣ የአገር ሽማግሌ በተለያዩ ተቋማት አንቱታን ያተረፉ ባለሞያ፣ ህግ አዋቂ በተለያዩ የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እና መሪ እንዲሁም የሚደነቅ የፓለቲካ አቋም እና የድፍረት ባለቤት እና ተንቀሳቃሽ ላይብረሪ ተብለው ይታወቁ ነበር።
አዝማች ይርጋ ገብሬ ድረታ ለዘመናት በጽናት ሀገራቸውን ያገለገሉ፣ የማኅበረሰብ መሪ እና አስታራቂ፣ በዘመዶቻቸው እና በቤተሰቦቻቸው ዘንድ ተወዳጅ አባት እና ባል ነበሩ።
አዝማች ይርጋ ከባለቤታቸው እቴት ዓለምነሽ ኃይለማርያም ጋር ከአራት ዐሥርት ዓመታት በላይ በትዳር የኖሩ ሲሆን የሁለት ሴት እና የሁለት ወንድ ልጆች አባት እና የአራት የልጅ ልጆች አያት ናቸው።
አዝማች ይርጋ ገብሬ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ታኅሣሥ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በ89 አመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ስርአተ ቀብራቸውም ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓም መላ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ፣ ጎረቤት ጓደኞቻቸው፣ ከፍተኛ የመንግስትና የግል ዘርፍ መሪዎች፣ እንዲሁም የሐይማኖት መሪዎች በተገኙበት በሳሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
ኧትምርት ሰማ አቆሚ ቤማ
እንም ኢትዮጵያ ይሰራንኸማ
ኧልማት ሳማ አቆሚ ቤማ
እንም ኢትዮጵያ ይሰራንኸማ።ኧብርጫሟኸ
አዝማች በትፈጠረ ንብረት ተጟከረ።ኧብርጫሟኸ
ሌሎችም ወርኮ እየተካሄደላቸው ይገኛል።
በዛሬው እለትም በተወለዱበት በጌታ ወረዳ ቋንጤ የለቅሶ ስነ ስርዓት(ወርኮ)እየተካሄደ ይገኛል።
በለቅሶ ስነ ስርአቱም ከፌደራል፣ከዞን፣ ከወረዳ የተወጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የወረዳው ማህበረሰብና መላው ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

6 months ago