15 hours ago
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለመቄዶንያ ከ4.6 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አበረከተ
#ethiopia | አዲስ አበባ | ኢትዮጵያ – የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የመስሪያ ቤቱን ማኔጅመንት፣ ሰራተኞች እና ታራሚዎች በማስተባበር ለመቄዶንያ አረጋውያንና ህጻናት መረዳጃ ማህበር ከ4.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አበርክቷል።
ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በገባው ቃል መሰረት በየዓመቱ ሐምሌ 28 መቄዶንያን የመጎብኘት ልማዱን በመቀጠል፣ በዚህ ዓመትም 547 ሺህ 65 ብር ጥሬ ገንዘብ እና ከ4.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለማህበሩ አስረክቧል።
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ዋና ኮሚሽነር የኑስ ሙሉ፣ መቄዶንያ ለሚያከናውነው ሰብዓዊ አገልግሎት በኮሚሽኑ ስም ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና ገልጸዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የኮሚሽኑ የህክምና ልዑካን ቡድን ከ770 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶችን በማበርከት ብቻ ሳይሆን፣ ለማህበሩ ተገልጋዮች የህክምና አገልግሎትም ሰጥቷል።
በተጨማሪም በኮሚሽኑ ስር የሚገኙ ታራሚዎች በእጃቸው ያመረቷቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶች በስጦታ በማበርከት ከመልካም ምኞት መልዕክታቸው ጋር ለማህበሩ አስረክበዋል።
የመቄዶንያ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር ዶ/ር ቢንያም በለጠ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ የማህበሩ ተገልጋይ አረጋውያንም በተደረገላቸው ጉብኝትና ድጋፍ ያላቸውን ደስታ ገልጸዋል።
ጌጡ ተመስገን
#ethiopia #federalprisoncommission #macedonia #charitysupport #givingback #humanitarianassociation #getutemesgen #ጌጡተመስገን

3 months ago
ታዋቂው መምህር፣ ደራሲና የሥነ ጽሑፍ ባለሙያ
የአቶ ወርቁ አበራ የ፵ ቀን መታሰቢያ መርሃ ግብር በመቄዶንያ
#ethiopia | ታዋቂው መምህር፣ ደራሲና የሥነ ጽሑፍ ባለሙያ የነበሩት የአቶ ወርቁ አበራ የ፵ ቀን መታሰቢያ መርሃ ግብር ዛሬ፣ ዓርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እየተከናወነ ነው።
ይህ የመታሰቢያ ፕሮግራም በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማኅበር ግቢ ውስጥ ከቀኑ 6:00 ሰዓት የጀመረ ሲሆን፣ በዕለቱም ለታሰበው ዝግጅት የተሰናዳው ፀበል ጻድቅ ይቀርባል።
አቶ ወርቁ አበራ በ1951 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተወልደው በባዮሎጂ የትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።
በደዶላ፣ በከበደ ሚካኤል እና በኢምፔሪያል አካዳሚ በትምህርት አመራርና በመምህርነት ሙያ ሀገራቸውን በታማኝነት አገልግለዋል።
ከሙያቸው ባሻገር ከ15 በላይ መጻሕፍትን በማርትዕና ክፉ ቀን ያልፋል ፅኑ ሰዎች ግን ያልፉታል እንዲሁም ፍርሃትህን አትፍራ የተሰኙ ተነባቢ መጻሕፍትን ወደ አማርኛ በመተርጎም በሥነ ጽሑፉ ዘርፍ ደማቅ አሻራ አሳርፈዋል።
ባለ ትዳርና የሦስት ልጆች አባት የነበሩት አቶ ወርቁ፣ በ67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።
ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በመቄዶንያ በሚገኘው አድራሻ በመታሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።
#workuabera #macedonia #literature #education #inmemoriam #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
የጡት ካንሰር ምርመራ ውጤት የሕይወት ማብቂያ ሳይሆን የትግልና የተስፋ መጀመሪያ ነው!
የጡት ካንሰር መኖሩ ሲረጋገጥ የሚፈጠር ድንጋጤና ፍርሃት ተፈጥሯዊ ቢሆንም፣ በዘመናዊ ሕክምና የታገዘ የቅድመ መከላከልና የሕክምና እርምጃዎች ውጤታማ እየሆኑ መጥተዋል።
እውቀት ኃይል ነው፦ የምርመራ ውጤቱን በዝርዝር ከሐኪምዎ ጋር ይወያዩ። የካንሰሩ ዓይነትና ደረጃ ላይ ግልጽ መረጃ መያዝ ለቀጣይ ሕክምና ዝግጁ ያደርጋል።
የቡድን ድጋፍ፦ ሕክምናው በባለሙያዎች (የቀዶ ጥገና ሐኪሞች፣ የአእምሮ ሐኪሞችና የአመጋገብ ባለሙያዎች) የታገዘ በመሆኑ ብቻዎን እንዳልሆኑ ይገንዘቡ።
የእናትነት ተስፋ፦ የጡት ካንሰር መገኘት የእናትነት ህልምን አያበቃም። ከሕክምና በፊት በዘመናዊ የሕክምና ዘዴዎች ፅንስን የመቀጠል ዕድል አለ።
የአእምሮ ጥንካሬ፦ ከባለሙያዎችና ተመሳሳይ ተሞክሮ ካላቸው ሴቶች ጋር መወያየት ለውስጥ ሰላምና ለፈውስ ትልቅ ሚና አለው።
💡 መልዕክት፦ "ጡት ካንሰር ይታከማል፤ በቂ መረጃና ትክክለኛ የሕክምና ክትትል ካለ ሕይወት ካለፈው በበለጠ በብርታትና በተስፋ ይቀጥላል!"
🔗 ምንጭ፦ eMacedonia

Comments