3 hours ago
የህወሃት ሃይሎች ሽሬን ለቀው መውጣታቸው ተሰማ!
የህወሃት ሃይሎች ሽሬን ለቀው መውጣታቸውን በስልክ ያነጋገሯቸውን ነዋሪዎች ዋቢ አድርጎ አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል። ይሁንና ዜናው እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ መከላከያም ሆነ የትግራይ ሰላም ሃይል ወደ ከተማዋ ያልገቡ ሲሆን እየመጡ ነው የሚል ወሬ እንደሰሙና ዝርፊያ እንዳይፈጸም በመፍራት ሁሉም ሱቁንና ቤቱን ዘግቶ እየተጠባበቀ እነደሆነ ገልጸዋል።
📸 Archive
@YeneTube FikerAssefa

6 hours ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቢኔያቸውን እጩ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡
1. ተመስገን ጥሩነህ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3. አዲሱ አረጋ (ዶ/ር) - የግብርና ሚኒስትር
4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) - የገንዘብ ሚኒስትር
5. አቶ መሃመድ እድሪስ - የመከላከያ ሚኒስትር
6. ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) - የትምህርት ሚኒስትር
7. ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ - የፍትሕ ሚኒስትር
8. ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
10. ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) - የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
11. መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) - የጤና ሚኒስትር
12. አቶ አወሉ አብዲ- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ - የገቢዎች ሚኒስትር
14. አቶ በረከት ፍስሃጽዮን - የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
15. ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
16. ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ - የማዕድን ሚኒስትር
17. አቶ ሳዳት ነሻ - የሎጂስቲክስ ሚኒስትር
18. ወ/ሮ ሻዊት ሻንካ - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
19. አቶ ሙሳ አደም - የሰላም ሚኒስትር
20. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
21. መሃመድ አብዱራሃማን (ኢ/ር) - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
22. ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) - የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) - የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው በእጩነት ቀርበዋል፡፡

Sponsored by
Surafel
8 hours ago
«በደቡብ ጎንደር አምስት ሰዎች በፌዴራል ፖሊስ አባላት ተኩስ ቆሰሉ፤ የአንድ ታዳጊ ሕይወት አለፈ»
በደቡብ ጎንደር ዞን በእስቴ ወረዳ ጉቢቻ ቀበሌ የጉምሩክ ጥበቃ የሚያደርጉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በከፈቱት ተኩስ ንጹሃን ሰዎች መመታታቸው ተገለጸ።
የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ «ኮንትሮባንድ እቃ ይዛለች» ባሏት አንድ ባጃጅ ላይ በከፈቱት ተኩስ ጥቃቱ መከሰሱ ተገልጿል።
በተከፈተው ተኩስ ወደ ስፖርት በመሄድ ላይ የነበረ አንድ ታዳጊ ወጣት ሕይወቱ ሲያልፍ፣ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት በማድረስ ላይ የነበሩ የእድሜ ባለጸጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች በጽኑ ቆስለዋል።
ተጎጂዎቹ ምንም የማያውቁ ንጹሃን መሆናቸውንና በባጃጇ ተጭኖ የነበረውም እቃ ኮንትሮባንድ ሊባል የማይችል እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
@Yenetube Fikerassefa

18 hours ago
የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ
ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ መንግሥት አስጠነቀቀ
የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ አዲግራት ከተማን መቆጣጠሩን ሲነገር፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮንኗል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ እንደተናገሩት፣ የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ አሳስበዋል። ይህ መግለጫ የኤርትራ ጦር ሀገሪቱን በቀጥታ መውረሩን ያረጋገጠ ይፋዊ አቋም ነው።
ይህ ውጥረት የተፈጠረው ህወሓት ከሌሎች አማፂ ቡድኖች ጋር አብሮ አዲስ ጥቃት ከከፈተ በኋላ ነው። መንግሥት እንደሚለው፣ ኤርትራ እነዚህን አማፂያን ከጀርባ ስትደግፍ ቆይታ አሁን ደግሞ ጦሯን በቀጥታ በማስገባቷ ሁለቱ አገራት ወደ ቀጥተኛ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

20 hours ago
#update
በግጭቶች ባሉበት አካባቢ የሚከሰቱ ክንውኖችን ይፋ በማድረግ የሚታወቀው አክለድ የተባለው አለም አቀፍ ተቋም በዛሬው እለት ከዕዳጋ ሓሙስ ወደ አፅቢ በሚወስደው መንገድ ይጓዙ የነበሩ የኤርትራ ወታደሮች ዕዳጋ ዓርቢ በተባለ ቦታ ሲደርሱ የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የሚገልጸውን የዶይቸ ቨሌ ዘገባ አጠናክሮታል።
ይሁን እንጂ ተቋሙ መረጃውን ስላገኘበት መንገድ ያለው ነገር የለም።
@YeneTube FikerAssefa የኤርትራ ወታደሮች ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመባቸው ተባለ! -መረጃውን ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ ግን አልተቻለም በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከዕዳጋ ሓሙስ ወደ አፅቢ በሚወስደው መንገድ ይጓዙ የነበሩ የኤርትራ ወታደሮች ዕዳጋ ዓርቢ በተባለ ቦታ ሲደርሱ የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የትግራይ የሰላም ኃይል አንድ ወታደራዊ አዛዥ ገለጹ። የኤርትራ ወታደሮች በዛሬው ዕለት ከዛላምበሳ አቅጣጫ የዓዲ ግራት ከተማን…

22 hours ago
የኤርትራ ወታደሮች ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ ተባለ!
-መረጃውን ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ ግን አልተቻለም
በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከዕዳጋ ሓሙስ ወደ አፅቢ በሚወስደው መንገድ ይጓዙ የነበሩ የኤርትራ ወታደሮች ዕዳጋ ዓርቢ በተባለ ቦታ ሲደርሱ የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የትግራይ የሰላም ኃይል አንድ ወታደራዊ አዛዥ ገለጹ። የኤርትራ ወታደሮች በዛሬው ዕለት ከዛላምበሳ አቅጣጫ የዓዲ ግራት ከተማን ጥሰው ዕዳጋ ሐሙስ ከተማ መግባታቸውን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የትግራይ የሰላም ኃይል አዛዥ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
በምዕራባዊ የትግራይ ክፍልም የኤርትራ ወታደሮች በሸራሮና ሽረ እንዳስላሰ ከተሞች መሐል በሚገኙ ዓዲ ነብሪ ኢድና ዛግር ወደ ተባሉ አካባቢዎች መግባታቸውንም ገልጸዋል።
አንድ የዓዲ ግራት ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው የኤርትራ ወታደዎች የዓዲግራት ከተማን ጥሰው በማለፍ ወደዕዳጋ ሓሙስ መግባታቸውን እንደተመለከቱ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ለማነጋገር ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ፣ ለመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይና ለኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር በእጅ ስልኮቻቸው ብንደውልም ስልክ ባለማንሳታቸው ሐሳባቸውን ማካተት አልቻልንም።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የገለጹት የትግራይ የሰላም አዛዥ እንደሚሉት ዕዳጋ ሓሙስ ከገቡት የኤርትራ ወታደሮች ወደ አፅቢ ወንበርታ አቅጣጫ በ2 የጭነት መኪኖች ተጭነው በሚጓዙበት ወቅት በድሮን ተመተዋል። ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን ተሰልፎ የሚዋጋው ታጣቂ ቡድን አመራር ተፈጽሟል ያሉትን የድሮን ጥቃት ዶይቼ ቬለ በገለልተኝነት አላረጋገጠም።
(DW)
@YeneTube FikerAssefa ሰበር ዜና! የኤርትራ ጦር አዲግራትን አልፎ ወደ መሃል ትግራይ እየተጓዘ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ! የኤርትራ ጦር ሠራዊት በትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የአዲግራት ከተማ መግባቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ወታደሮቹ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ የኤርትራ ወታደሮች “በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነው…

24 hours ago
በዉቅሮ ዙሪያ የከባድ መሣሪያ እየተሰማ ይገኛል!
በዉቅሮ ዙሪያ የከባድ መሣሪያ እየተሰማ እንደሚገኝ አንድ የከተማው ነዋሪ ለዶቸ ቬለ ተናገሩ። የትግራይ የሰላም ኃይል አባላት ዉቅሮ መድረሳቸውን የታጣቂ ቡድኑ አንድ አዛዥ እንደተናገሩ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቦ ነበር።
ይሁንና ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪ ግን ከትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ በ50 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው ዉቅሮ “በአሁኗ ሰዓት ከሁሉም ውጪ ናት” ሲሉ አስረድተዋል። እስከ ትላንት ማታ ድረስ በከተማው የትግራይ ኃይሎች አባላት እንደነበሩ የገለጹት የዉቅሮ ነዋሪ በአዲግራት እና ሐውዜን አቅጣጫዎች መውጣታቸውን ገልጸዋል።
ነዋሪው “ስለ ኤርትራ ጦር በዉቅሮ አካባቢ የታየ ክስተት የለም” ሲሉ ተናግረዋል።ዶቸ ቬለ በአካባቢው ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በገለልተኝነት ማረጋገጥ አልቻለም።
ከመቐለ ወደ አዲግራት የሚያልፉ መንገደኞች የመከላከያ ሠራዊት “እየመጣ ነው የሚል መረጃ” ለከተማው ነዋሪዎች በመናገራቸው “ሰዉ ራሱን እየጠበቀ” ይገኛል።
እሁድ እና ሰኞ በዉቅሮ “የተለያዩ [የዘረፋ]ሙከራዎች ስለነበሩ እሱን ለመከላከል በቡድን አካባቢውን እየጠበቀ” እንደሆነ አስረድተዋል። የከተማው ነዋሪዎች “ተባራሪ ጥይት እንዳይመጣ ተኩስ እንዳይከፈት ሥጋት” እንዳላቸው ከዉቅሮ በስልክ ያስረዱት እማኝ “እስካሁን ግን ከከባድ መሳሪያ ድምጽ ውጪ” የተሰማ አለመኖሩን ገልጸዋል።በከተማው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ባይቋረጡም ኤሌክትሪክ አለመኖሩን የዉቅሮው ነዋሪ ገልጸዋል።
Via DW

1 day ago
የ18 ቁጥር ማዞሪያ ቀለበት መንገድ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል ተባለ
በአዲስ አበባ ከመርካቶ በመሳለሚያ በኩል ወደ 18 ቁጥር ማዞሪያ የሚወስደውን የመንገድ ግንባታ ለማፋጠን የ18 ቁጥር ማዞሪያ ቀለበት መንገድ ከቅዳሜ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለጊዜው ለትራፊክ እንደሚዘጋ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አስታውቋል።የመንገዱ ፕሮጀክት በ18 ቁጥር ማዞሪያ አካባቢ የላይና የታች የትራፊክ ማሳለጫ ድልድዮችን የሚያካትት መሆኑ ተገልጿል።
በመሆኑም ከጦር ኃይሎች፣ ከ3 ቁጥር ማዞሪያና ከአየር ጤና ወደ ዊንጌት፣ ሸጎሌና አዲሱ ገበያ የሚጓዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች በኮካና ልደታ አደባባዮች፣ በአማኑኤልና አብነት በኩል ወይም በሆላንድ ኤምባሲ አካባቢ በሚገኙ አማራጭ መንገዶች እንዲጓዙ ተመላክቷል። ከአዲሱ ገበያና ከሸጎሌ ወደ 18 ቁጥር ማዞሪያ ወይም ጦር ኃይሎች የሚጓዙ ከባድ መኪኖች ደግሞ በዊንጌት አደባባይ በላይኛው መተላለፊያ ድልድይ እንዳይጠቀሙ ተገልጿል።
ቀላልና መካከለኛ ተሽከርካሪዎች ግን በተዘጋጁት የውስጥ ለውስጥ አማራጭ መንገዶች መጓዝ እንደሚችሉ የባለሥልጣኑ ምክትል ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በተጨማሪም ከአሸዋ ሜዳና ቡራዩ በ18 ቁጥር ማዞሪያ በኩል ወደ ዊንጌት የሚጓዙ ከባድ ተሽከርካሪዎችም ትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ በአንፎ አደባባይ፣ በዓለም ባንክ ወይም በቀራንዮ አደባባይ በኩል የጉዞ መስመራቸውን እንዲያስተካክሉ ተመክረዋል።
ባለሥልጣኑ በአማራጭ መንገዶች ላይ ትራፊክን የሚያውክ መኪና ማቆም በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ገልፆ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ምልክቶችንና የትራፊክ ፖሊሶችን መመሪያ እንዲከተሉ አሳስቧል።የመንገዱ መዘጋት ጊዜያዊ በመሆኑ በቀጣይ የሚሰጡ ተጨማሪ መመሪያዎችንና ማሻሻያዎችን የመንገድ ተጠቃሚዎች በትኩረት ሊከታተሉ ይገባል ሲሉ አቶ እያሱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ፌስታል ይዘው የተገኙ ተቋማት ከ480ሺህ ብር በላይ ተቀጡ በ30 ማዳበሪያ ከረጢት የተከማቸ ፌስታል መወረሱ ተገልጿል
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 መሰረት ያደረገ የፕላስቲክ ክልከላ፣ ቁጥጥርና የእርምት እርምጃ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልፆ በዚህም ከ480ሺህ በላይ የገንዘብ ቅጣትን ጨምሮ በርካታ የተከለከሉ ኩንታልና ማዳበሪያ ፌስታሎች መወረሳቸውን አስታውቋል።
በተደረገው የቁጥጥር ዘመቻ መሰረትም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኙ 38 ንግድ ተቋማት ማለትም ሱቆች፣ ዳቦ ቤቶች፣ ጫት ቤቶችና ስጋ ቤቶች ላይ በተደረገ ቁጥጥር አዋጁን ጥሰው የተገኙ 4 ተቋማት እያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር እንዲሁም 7 ተቋማት እያንዳንዳቸው 5ሺህ ብር በአጠቃላይ 235ሺህ ብር ቅጣት እንዲቀጡ ተደርጎ ፌስታሎች መወረሳቸው ታውቋል።

ሰበር ዜና!
የኤርትራ ጦር አዲግራትን አልፎ ወደ መሃል ትግራይ እየተጓዘ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ!
የኤርትራ ጦር ሠራዊት በትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የአዲግራት ከተማ መግባቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ወታደሮቹ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ የኤርትራ ወታደሮች “በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ደቡብ አቅጣጫ” እየተጓዙ መሆናቸውን በአዲግራት ከሚገኙ ነዋሪዎች መስማታቸውን ገልጸዋል።
የአዲግራት ከተማ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኗንም ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር በ40 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው አዲግራት የኤርትራ ወታደሮች እንደገቡ በተመሳሳይ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።ወታደሮቹ ከአዲግራት በደቡባዊ አቅጣጫ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ እንደሚገኙ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት የመረጃ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
(AFP/DW)

የትግራይ ሠራዊት አባላት ከዛሬ ጀምሮ በመቀሌ እንዲሰባሰቡ መንግስት ጥሪ አቀረበ
የብሔራዊ ተሃድሶ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው የትግራይ ሠራዊት አባላት ከዛሬ ጀምሮ በመቀሌ አካባቢ በተዘጋጀው የተሃድሶ ማዕከል እንዲሰባሰቡና ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ።
ምክትል ኮሚሽነሩ በቪዲዮ በተሰራጨው አጭር መልዕክታቸው፤ የመንግሥት ጥሪን በመጠበቅ ላይ የሚገኙ በርካታ ታጣቂዎች እንዳሉ ገልጸው፣ ከዛሬ ረቡዕ ጀምሮ ወደተዘጋጀው የዲሞቢላይዜሽን ማዕከል መግባት እንደሚቻል አስታውቀዋል።
ጄኔራሉ፤ ለመልሶ ማቋቋምና ተሃድሶ (ዲ.ዲ.አር) ፕሮግራም የተዘጋጁ በርካታ ወጣቶች መኖራቸውን ጠቁመው፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ሰላም ለመምጣት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው በርካታ ታጣቂዎች በየአካባቢው በሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒቶች እጅ እየገቡ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
ምክትል ኮሚሽነሩ መንግሥት ለብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስፈላጊውን በጀት መመደቡንና ኮሚሽኑም ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በተጨማሪም የትግራይ ወጣቶች ከጦርነት እሳት ወጥተው ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱና የልማት ኃይል እንዲሆኑ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኩል ከፍተኛ ድጋፍ መኖሩን አስረድተዋል።
በመሆኑም ታጣቂዎች በየአካባቢው ለሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒቶች በግለሰብም ሆነ በተደራጀ መንገድ ሪፖርት በማድረግ፣ የጦር መሣሪያና ወታደራዊ ቁሳቁሶቻቸውን በማስረከብ በመቀሌ አካባቢ ወደተዘጋጀው የዲሞቢላይዜሽን ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀርቧል።
ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ በመግለጫቸው “ወጣቱ ለተወሰኑ ጽንፈኞችና ግለሰቦች ዓላማ ተብሎ በጭፍን ማለቅ የለበትም፤ ሁሉም ጨለማ አይደለም፣ ብርሃን አለ” ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም መጀመሪያ ላይ በራሳቸው ፍላጎት የተቀላቀሉም ሆነ በኋላ ላይ ተገድደውና ታፍሰው የገቡ ወጣቶች አማራጭ እንዳለ አውቀው ወደ መንግሥት እንዲገቡ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ታጣቂዎቹ ወደ ተሃድሶ ማዕከላት በመግባት ተሃድሶ ከወሰዱ በኋላ፣ በመልሶ ማቋቋምና በመልሶ ማደራጀት ሥራ ውስጥ ተካተው የራሳቸውን፣ የቤተሰቦቻቸውን፣ የትግራይ ክልልን እንዲሁም የሀገርን አቅም መገንባት እንዲችሉ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀረበ ሲሆን፣ ከዛሬ ጀምሮ በመቀሌ በተዘጋጀው የተሃድሶ ማዕከል መግባት እንደሚቻል ተገልጻል።

2 days ago
በአድዋ ከተማ ሶሎዳ ሆቴል ላይ ከትናንት በስቲያ እኩለ ሌሊት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 5 ሰዎች መገደላቸውን ዋዜማ ሠምታለች። በድሮን ጥቃቱ፣ ከታጠቁ የጸጥታ ጥበቃ አባላት በተጨማሪ በሆቴሉ ሲስተናገዱ የነበሩ ሌሎች 3 ሰዎች አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሕክምና ተቋም መወሠዳቸውን ምንጮች ነግረውናል።
በሆቴሉ ውስጥ የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልና ሌሎች የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች እንደነበሩና በጥቃቱ የተገደሉት የአመራሮቹ የጥበቃ አባላት መሆናቸውን ዋዜማ መረጃ የደረሳት ቢሆንም፣ የቡድኑ አመራሮች በወቅቱ በሆቴሉ ውስጥ ስለመኖራቸው ወይም በጥቃቱ የተገደሉት በትክክል የአመራሮቹ የጥበቃ አባላት ስለመሆናቸው ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ዋዜማ ከገለልተኛ አካል ማረጋገጥ አልቻለችም።
@Yenetube Fikerassefa
በሆቴሉ ውስጥ የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልና ሌሎች የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች እንደነበሩና በጥቃቱ የተገደሉት የአመራሮቹ የጥበቃ አባላት መሆናቸውን ዋዜማ መረጃ የደረሳት ቢሆንም፣ የቡድኑ አመራሮች በወቅቱ በሆቴሉ ውስጥ ስለመኖራቸው ወይም በጥቃቱ የተገደሉት በትክክል የአመራሮቹ የጥበቃ አባላት ስለመሆናቸው ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ዋዜማ ከገለልተኛ አካል ማረጋገጥ አልቻለችም።
@Yenetube Fikerassefa
2 days ago
«የአማራ የሰላም ኃይል (APF) ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ተገለጸ»
የአማራ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ቀያቸው የተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎችን እና ፈቃደኛ ግለሰቦችን «የአማራ የሰላም ኃይል» በሚል ስያሜ አደራጅቶ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እያሰማራ ይገኛል።
አዲሱ አደረጃጀት አካባቢን መሠረት ባደረገ መልኩ የተዋቀረ ሲሆን፣ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጎን ለጎን በጥብቅ ክትትልና ዲሲፕሊን እንደሚንቀሳቀስ ተገልጿል።
የጎንደር አካባቢ የቀድሞ ታጣቂዎች ሥልጠና አጠናቅቀው ለግዳጅ የተሰማሩ ሲሆን፣ በወሎም ተመሳሳይ አደረጃጀቶች እየተፈጠሩ ይገኛሉ።
ከክልሉ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረሙት የቀድሞው የፋኖ ከፍተኛ አመራር ካፕቴን ማስረሻ ሠጤ አዲሱን አደረጃጀት በማዋቀር ሂደት ውስጥ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል።
አደረጃጀቱ አካባቢን የማረጋጋት እና ሌሎች ታጣቂዎችን ወደ ሰላም አማራጭ የመመለስ ዓላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

❗️የአማራ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እጅ የሠጡ የቀድሞ የፋኖ ታጣቂዎችን አደራጅቶ እያሠማራ መሆኑን ዋዜማ ከምንጮች ሠምታለች።
"የአማራ የሰላም ኃይል" በሚል ስያሜ በተደራጀው ኃይል ውስጥ በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ ያልነበሩ ፈቃደኛ ግለሰቦችም ተካተዋል። ታጣቂዎቹ ራሳቸው በመረጡትና አካባቢያቸውን መሠረት ባደረገ መልኩ እንደሚደራጁ የገለጡት ምንጮች፣ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጎን ለጎን በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ለመንቀሳቀስ መስማማታቸውን ምንጮች ተናግረዋል።
የጎንደር አካባቢ የቀድሞ የፋኖ ታጣቂዎች ሥልጠና አጠናቅቀው ለግዳጅ የተሠማሩ ሲኾን፤ በተመሳሳይ በወሎ የፋኖ አባል የነበሩ ግለሰቦች የሚመሯቸው አደረጃጀቶች እየተፈጠሩ መኾኑን ምንጮች ገልጸዋል።
ከክልሉ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈታረሙት የቀድሞው የፋኖ ከፍተኛ አመራር ማስረሻ ሠጤ፣ አዲሱን አደረጃጀት በመፍጠር ሂደት ውስጥ እንዳሉበት ተረድተናል።

በአዲስ አበባ ጥሬ ወተት ላይ ለካንሰር አጋላጭ መርዛማ ንጥረ-ነገሮች መገኘታቸው ተገለጸ
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሁሉም 11 ክፍለ ከተሞች በተካሄደ የዳሰሳ ጥናት፣ ለሽያጭ በሚቀርብ ጥሬ ወተት ላይ ከውኃ እስከ ለካንሰር አጋላጭ የሆኑ መርዛማ ባዕድ ንጥረ-ነገሮች ተጨምረው መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ፀጋ ለማ እንደገለጹት፤ ጥናቱ ቁጥጥር ከሚያደርጉ ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት የተከናወነ ሲሆን፣ በየመንደሩ ለሽያጭ በሚቀርበው ወተት ላይ የሚጨመሩ ባዕድ ነገሮች መበራከታቸው ተረጋግጧል።
በወተቱ ላይ የሚጨመረው ውኃ አስፈላጊውን ንጥረ-ነገር የሚያሳጣ ሲሆን፤ ወተቱ ሳይበላሽ ከ4 እስከ 5 ቀናት እንዲቆይ ተብለው የሚጨመሩት ንጥረ-ነገሮች ደግሞ የኅብረተሰቡን ጤና ለከፍተኛ አደጋ እና እንደ ካንሰር ላሉ ከባድ በሽታዎች የሚያጋልጡ መርዛማ ነገሮች ናቸው።
ይህንን የጤና ስጋት ለመግታት እና የቁጥጥር ሥራውን ለማጠናከር ኮሚሽኑ አዲስ የሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ዶክተር ፀጋ አስታውቀዋል።

በእስር ላይ የሚገኙ የዋስትና ውሳኔ ይፈጸም ወይም ይግባኙ በአፋጣኝ ይታይ ሲል ኢሕአፓ ጠየቀ!
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢሕአፓ) በእስር ላይ ያሉ የፓርቲው አባላት በተመለከተ ቀደም ሲል የተሰጠው የዋስትና ውሳኔ እንዲፈጸም ወይም በውሳኔው ላይ የቀረበው ይግባኝ በአፋጣኝ ተመርምሮ ተገቢው የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሰጥ ጠየቀ።ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፤ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ይስሐቅ ወልዳይ፣ አባሉ አበበ ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተጠሪው ደረጄ ደለና እንዲሁም ጠበቃ አበራ ንጉስ አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጿል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከተደጋጋሚ የምርመራ ቀጠሮዎች በኋላ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. በ50 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰጥቶ እንደነበር አስታው፤ የፌዴራል ፖሊስ በዋስትና ውሳኔው ላይ ይግባኝ በማቅረቡ ጉዳዩ በይግባኝ ሂደት ላይ ይገኛል፤ በዚህም ተጠርጣሪዎቹ እስካሁን ከእስር እንዳልተለቀቁ አመልክቷል።
ኢሕአፓ የዋስትና ጉዳዩ በአፋጣኝ እንዲታይ፣ ቀደም ሲል የተሰጠው የዋስትና ውሳኔ እንዲፈጸም ወይም ይግባኙ በፍጥነት ተመርምሮ ተገቢው የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል።በተጨማሪም የተጠርጣሪዎቹ የግል ነፃነትና የፍትሕ መብት እንዲከበር፣ የፍርድ ሂደቱም በተደጋጋሚ ቀጠሮዎች እንዳይጓተት እና የፍርድ ቤቶች ነፃነትና ገለልተኛነት እንዲጠበቅ አሳስቧል።ፓርቲው የአባላቱ ጉዳይ በፍጥነት፣ በግልጽነትና በሕግ መሠረት እንዲታይ በመግለጫው አሳስቧል።
Via Addis Maleda

«ጌታቸው ረዳ ወደ መቐለ ተመለሱ‼️
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ መቐለ ከተማ ከህወሓት ታጣቂዎች ነፃ መውጣቷን ተከትሎ ወደ ከተማዋ መመለሳቸውን ሮይተርስ ዘገበ።
🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
ወደ መቐለ መመለስ፦ የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ወደ ክልሉ መዲና መቐለ መድረሳቸውን የአለም አቀፉ የዜና ተቋም ሮይተርስ አረጋግጧል።
አካባቢያዊ ሁኔታ፦ አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ ከተማዋ የተመለሱት መቐለ ከህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ነፃ መውጣቷን ተከትሎ መሆኑ ተመላክቷል።
ወቅታዊ ሁኔታ፦ የአካባቢውን ሰላምና ወታደራዊ ሁኔታ በተመለከተ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በትግራይ ክልል በሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) መጋዝን ላይ ከትላንት በስቲያ እሁድ ዘረፋ መፈጸሙን የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ ምክትል ቃል አቃባይ ገለጹ።
በክልሉ ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ የዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ድርጅቶች መጋዘኖች እና መገልገያዎች በተመሳሳይ መልኩ መዘረፋቸውንም ቃል አቃባዩ ተናግረዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ምክትል ቃል አቃባይ ፋራህን ሃቅ ይህንን የተናገሩት፤ ትላንት ሰኞ መስከረም 25፤ 2019 ምሽት በሰጡት ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
የእሁዱ ዘረፋ በትግራይ ክልል የትኛው አካባቢ እንደተፈጸመ እና በጋዜጣዊ መግለጫቸው ያልጠቀሱት ምክትል ቃል አቃባይ ፋራህን፤ ሆኖም በክስተቱ የሰብአዊ አቅርቦቶች መጥፋታቸውን አስረድተዋል።
በዘረፋው ከተሰረቁት ውስጥ ምግብ፣ ምርጥ ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያዎች እና የውሃ ፖምፖች እንደሚገኙበት የተመድ ዋና ጸሀፊ ምክትል ቃል አቃባይ ገልጸዋል።
የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች፣ ተቋማት እና ንብረቶች “በፍጹም የጥቃት ኢላማ ሊሆኑ አይገባም” ያሉት ፋራሃን፤ በሁሉም ጊዜያት “ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ” ጨምረው አሳስበዋል።
Via Ethiopia Insider

3 days ago
በስህተት ወደ ባንክ አካውንቷ የገባውን 158ሺ ብር የፖሊስ አባሏ ለባለቤቱ መመለሳን የአዲስ በባ ፖሊስ ዋና መመሪያ አስታወቀ፡፡
ዋና ሳጅን ደገፈች ደሳለኝ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የቄራ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ስትሆን መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ወደ ስራዋ እያመራች አንድ የስልክ ጥሪ ይደርሰታል። ደዋዩ ሚኪያስ አንዳርጌ የተበለ ግለሰብ ሲሆን በስህተት 158ሺህ ብር ወደ እሷ አካውንት ገንዘብ ማስተላለፉን ይነግራታል።
በጋምቤላ ክልል እንደሚኖርና ወደ አዲስ አበባ መምጣት እንደማይችል፣ ገንዘቡን ያስተለለፈው ጋምቤላ ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲማ ቅርንጫፍ መሆኑንም ያስረዳታል።
የባንኩ ዲማ ቅርንጫፍ ከዋና ሳጅን ደገፈች ደሳለኝ ጋር በስልክ ከተነጋገረ በኋላም አዲስ አበባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ቅርንጫፍ በመሄድ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ ለባለቤቱ መልሳለች።
ፖሊስ የቆመለትን የህዝብ አገልጋይነትና ታማኝነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ያለችው ዋና ሳጅን ደገፈች ገንዘቡን መመለሴ እንደ ትልቅ ጀብድ መታየት የሌለበትና ኃላፊነቴን የተወጣሁበት አግባብ ነውም ብላለች፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ለዋና ሳጅን ደገፈች ደሳለኝ ባሳየችው ታማኝነትና የግለሰቡን ገንዘብ ያለ ምንም ጉድለት በመመለሷ የምስጋና የዕውቅና ሰርተፍኬት አበርክቶላታል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልእክት፦
ወንድሜን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ።
ዛሬ የመደመር መንግሥት ምሥረታን ስናከብር ላስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ለአህጉሩ አንድነት፣ ሰላም፣ ልማት እና ብሩህ ተስፋ ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ እና ታሪካዊ ግንኙነት አላቸው። አጋርነታችንን ይበልጥ ለማሳደግ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር እንደምናጠናክር ተስፋ አለኝ።

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ ተሰየሙ!
የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው የ7ኛው የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመንግሥት መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ የሰየመ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በይፋ ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዚህ የመንግሥት መመሥረታ ጉባኤ ላይ፣ የሁለቱ የምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ ተሰይመዋል።
በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ ቀደም ሲል የገንዘብ ሚኒስትር የነበሩትን አቶ አሕመድ ሽዴን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ፣ ወ/ሮ አየለች እሸቴን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ መርጧል።
በተጨማሪም የሥራና ከህሎት ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ፣ አቶ ደስታ ሌዳሞ ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰይመዋል።

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ እና በቀይ ባሕር ዙሪያ ያላትን መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በማንኛውም ኃይል ሊቀየሩ አይችሉም - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝ መነሻ ስትሆን፣ ከሞላ ጎደል አብዛኛው የዓባይ ውሃ የሚመነጨው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ነው፡፡ወንዙ ለናይል ወንዝ አጠቃላይ የውኃ መጠን 85 በመቶውን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም እና አስተዳደር ዙሪያ የሚደረጉ ማናቸውም ውይይቶች እነዚህን መሠረታዊ እውነታዎች ያገናዘቡ መሆን አለባቸው ብሏል፡፡
በተመሳሳይ ቀይ ባሕር ኢትዮጵያ መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ ትስስር ያላት የውኃ አካል መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፤ በጊዜ ሂደት የፖለቲካ ድንበሮች ቢቀያየሩም ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ጋር ያላት የጠበቀ ቁርኝት ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡የኢትዮጵያ ቅርብ የተባለው ድንበር ከባሕር ዳርቻው 48 ኪ.ሜ ብቻ ርቀት ላይ እንደሚገኝም አብራርቷል፡፡
በመሆኑም በቀጣናዊ የባሕር ላይ ጉዳዮች እና የደኅንነት መዋቅር ላይ የሚደረግ ማንኛውም ውይይት የኢትዮጵያን ሕጋዊ ጥቅሞች እና ከቀይ ባሕር ጋር ያላትን ዘላቂ ትስስር ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት ሲል አሳስቧል፡፡እነዚህ መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በፖለቲካዊ ዲስኩር፣ በማስገደድ እርምጃዎች ወይም ሀገርን በማተራመስ ድርጊቶች ሊቀየሩ እንደማይችሉ የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ በተላላኪዎች አማካይነት የሚወሰዱ እርምጃዎች ወይም የጥቃት ድርጊቶች መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንደማይቀይሩት ሁሉ፣ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሕጋዊ ጥቅም፣ ሚና እና ኃላፊነት ሊያሳንሱት አይችሉም ሲል አስምሮበታል፡፡
ኢትዮጵያ ሰላማዊ ግንኙነትን፣ የጋራ መከባበርን እና ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር እንደምትቀጥል ያረጋገጠው ሚኒስቴሩ፤ ሉዓላዊነቷን፣ የግዛት አንድነቷን እና ዋነኛ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለመጠበቅ ምንጊዜም ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም የቀጣናው ተዋናዮች የጋራ ፈተናዎችን ከግጭት እና አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ተጎጂ ከሚሆንበት (ዜሮ-ድምር) አካሄድ ይልቅ፣ ገንቢ በሆነ ውይይት፣ በአጋርነት እና በመልካም ጉርብትና መርሆች ላይ ተመሥርተው እንዲፈቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል፡፡
@YeneTube FikerAssefa Photo

የአራቱ ሀገራት መሪዎች በቀይ ባህር ጉዳይ ከቀጣናው ሀገራት ውጭ ማንም አይመለከታቸውም አሉ፤ በዓባይ ወንዝ ላይ ደግሞ የግብፅን አቋም አንፀባረቁ!
ግብፅ፣ ኤርትራ እና ሱዳን በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ጦርነት እጃቸው አለበት በሚል ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ሱዳንን ጨምረው ባካሄዱት ስብሰባ፤ የቀይ ባህር ጉዳይ የሚመለከተው ተዋሳኝ ሀገራትን እንጂ ሌሎችን አይደለም ሲሉ አቋም ያዙ፡፡ በስም አይጥቅሱ እንጂ ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄን ከ2015 ዓ.ም ክረምት አንስቶ እያንጸባረቀች መሆኑ ይታወቃል፡፡
በግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል-ሲሲ አስተናጋጅነት፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሃሙድ እና የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃን የተሳተፉበት አራትዮሽ የምክክር ጉባኤ ትናንትና መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም በግብጿ አዲስ ከተማ ኤል አላሜይን ከተማ ተካሂዶ የጋራ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል።
መሪዎቹ በጋራ ያወጡት መግለጫ፤ የኤል-አላሜይን ስምምነት በቀጣናዊና ወቅታዊ ጉዳዮች፣ በፖለቲካዊ፣ በንግድ እና በኢኮኖሚ ትብብር እንዲሁም በአካባቢያዊ መረጋጋት ዙሪያ ላይ ያተኮረ መሆኑን ያመላክታል።
መሪዎቹ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በምታነሳው የቀይ ባህር ጉዳይ ላይ ሰፊ ወይይት አድርገዋል።
በቀይ ባህር ላይ የካርጎና መርከቦች የነፃ ዝውውር መብት መከበር እንዳለበት መሪዎቹ ያረጋገጡ ሲሆን፣ የቀይ ባህር አስተዳደር እና ቁጥጥር ብቸኛ ኃላፊነትና መብት ቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ያሉ ሀገራት ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
የዓባይ ወንዝን ጨምሮ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን የሚገዙ ዓለም አቀፍ ህጎች መከበር እንዳለባቸው የጠቀሰው የመሪዎቹ መግለጫ፣ ጉዳት የሚመጣ መሆን እንደለሌበት ጠቅሰው በቅድሚያ ማስታወ፣ በምክክርና በስምምነት መስራት አስፈላጊ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
አክለውም፤ የታችኛውን የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት የውሃ ጥቅም የሚጎዱ ማንኛቸውንም በአንድ ወገን ብቻ የሚወሰዱ እርምጃዎች በጽኑ እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል። ግብፅ፤ ኢትዮጵያን የተናጠል እርምጃ እየወሰደች መሆኗን ስትገልጽ መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን ይህ የጋራ መግለጫቸውም የተለመደውን የግብፅን አቋም ያንፀባረቀ ነው።
በሌላ በኩል ደግም የሶማሊያ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ የገለፁት መሪዎቹ፣ የሶማሊያን ግዛታዊ አንድነት የሚሸረሽሩ ማንኛቸውንም ጣልቃ ገብነቶች፣ በተለይም ለሶማሊላንድ የሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና የመስጠት ጥረቶችን ውድቅ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪም ሶማሊያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት በመደገፍ ለአፍሪካ ህብረት የማረጋጋት ተልእኮ (አውሶም) ዘላቂ በጀት እንዲመደብ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም ለሱዳን ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና ህጋዊ ብሔራዊ ተቋማት አለን ያሉትን ድጋፍ እናረጋግጣለን ያሉ ሲሆን ከህጋዊ ተቋማት ውጪ ትይዩ አካላትን ማቋቋምም ሆነ የውጭ ቅጥረኛ ተዋጊዎችን ማሳተፍ ተቀባይነት እንደሌለው አሳስበዋል።አራቱ ሀገራት የጉባኤውን ውሳኔዎችና ስምምነቶች አፈጻጸም የሚከታተል እና በየጊዜው እየተሰበሰበ ቅንጅታቸውን የሚያጠናክር በጋራ የሚከታተል ቡድን ለማቋቋም ተስማምተዋል።
[Addis Maleda]

4 days ago
የኮቴ ክፍያ‼️
በተለያዩ አካባቢዎች የሚጠየቀው የአሽከርካሪዎች የኮቴ ክፍያ በ70% መቀነሱ ተገለጸ‼️
👉በ2019 የኮቴ ክፍያን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ይሰራል ተብሏል
በትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እና በፌደሬሽኑ ቅንጅታዊ አሰራር በተከናወነ ሥራ አሽከርካሪዎች የሚጠየቁት አግባብነት የሌለው የኮቴ ክፍያ በ70% መቀነሱን የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን አስታውቋል።
የፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ለአሐዱ ሬድዮ እንደተናገሩት፤ ክፍያው በሀገሪቱ ሕግ የማይፈቀድ በመሆኑ ከክልሎች ጋር በተደረገ ውይይት እንዲቀንስ ተደርጓል።
በአማራ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በጂቡቲ ኮሪደር የሚጠየቀው ክፍያ መቀነሱን ተናግረዋል።
የኮቴ ክፍያ አሁንም ባልቀረባቸው አካባቢዎች በ2019 የበጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት መንግሥት እና ፌደሬሽኑ በትኩረት እንደሚሠሩ አቶ ብርሃኔ ዘሩ ገልጸዋል።

ከመቀሌ ዛሬ የመጣ ፎቶ፡ የኢትዮጵያ ፌደራል እና አጋር ኃይሎች የትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና የሆነችውን መቀሌን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ፤ ከመንግስት ጎን የተሰለፉ የትግራይ የሰላም ኃይል (TPF) አባላት በመቀሌ ጎዳናዎች ላይ በፒክአፕ መኪና ጥበቃ እያደረጉ በምስሉ ላይ ይታያሉ።
የሰብዓዊ መብት ድርጅት ምንጮች ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደገለጹት፤ የህወሓት ኃይሎች ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የፌደራል ሰራዊት አባላት በመቀሌ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ቁጥጥር እያደረጉ ይታያሉ።
(ፎቶ፦ AFP)
@Yenetube Fikerassefa
የሰብዓዊ መብት ድርጅት ምንጮች ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደገለጹት፤ የህወሓት ኃይሎች ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የፌደራል ሰራዊት አባላት በመቀሌ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ቁጥጥር እያደረጉ ይታያሉ።
(ፎቶ፦ AFP)
@Yenetube Fikerassefa
Sponsored by
Surafel
4 days ago
ላለፉት 10 ቀናት በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ መጀመሩን የከተማይቱ አራት ነዋሪዎች ተናገሩ።
አገልግሎቱ ወደ ነበረበት የተመለሰው ዛሬ እሁድ መስከረም 24፤ 2019 ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ተኩል ገደማ እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።በአብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢዎች መንግስታዊው ኢትዮ ቴሌኮም ይሰጣቸው የነበሩት የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶች የተቋረጡት ሐሙስ መስከረም 14 ምሽት ላይ ነበር። ሌላኛው የቴሌኮም አገልግሎቶች ሰጪ ድርጅት የሆነው የሳፋሪኮም ኔትወርክ ግን እስከ አርብ እኩለ ቀን ድረስ ሲሰራ ቆይቶ ተቋርጧል።
የኢትዮ ቴሌኮም እና የሳፋሪኮም የኢንተርኔት እና የስልክ “ኔትወርኮቻቸውን እንዲያቋርጡ ትዕዛዝ” የሰጠው፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጭን ጨምሮ ስለጉዳዩ የሚያውቁ አራት ግለሰቦች እንደነገሩት “ሮይተርስ” በወቅቱ ዘግቦ ነበር። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዛሬ እሁድ ያነጋገረቻቸው የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች፤ በቀጥታ ስልክ መደወል እንደቻሉ የኢንተርኔት አገልግሎትም እየተጠቀሙ መሆኑን ተናግረዋል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

በኢትዮጵያ የኤርትራን መንግስት ወክለው ሲሰሩ የነበሩ ሁሉም ዲፕሎማቶች ሀገሪቱን ለቀው አስመራ ገቡ
በኢትዮጵያ የኤርትራ ኢምባሲ ጉዳይ አስፈፃሚ የነበሩትን አቶ ቢኒያም በርሄን ጨምሮ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች፣ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት (AU) እና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የኤርትራ ተወካዮች ሙሉ በሙሉ አዲስ አበባን ለቀው ወጥተዋል።
ዲፕሎማቶቹ አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት እና በአምባሳደር እስጢፋኖስ ደማቅ አቀባበል እንደተደረፈላቸው ተገልጿል።
ኢትዮጵያ የኤርትራ ዲፕሎማቶች
በ48 ሰዓታት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ቀነ ገደብ ማስቀመጧ የሚታወስ ነው።

5 days ago
“ሕወሓት በሀገር ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽሟል”
የትግራይ የሰላም ተልዕኮ አስተባባሪ ሌተናንት ኮሎኔል ገብረዋሕድ ኃይሉ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን ከውጭ ኃይሎችና ከሀገር ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመተባበር በሀገር እና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽሟል። የቡድኑ የ30 ዓመታት የፖለቲካ ውድቀት ትግራይን የጦርነት አውድማ በማድረግ ሕዝቡን በማያባራ የኢኮኖሚ ውድቀት፣ የሥነ ልቦና ስቃይ እና ማኅበራዊ ውጥንቅጥ ውስጥ እንደከተተው ተመላክቷል።
በትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ምስቅልቅል የቡድኑን የባንዳነት እና የፖለቲካ ከንቱነት የሚያሳይ መሆኑን ያስታወቁት ሌተናንት ኮሎኔሉ፣ ሕዝቡ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ የከፈለው መስዋዕትነት ወደ ባርነት መቀየሩን ገልጸዋል። ይህንን የቁልቁለት ጉዞ ለመቀልበስ ከዜሮ በመነሳት የፖለቲካ ምኅዳሩን፣ የሲቪል ማኅበራትን እና የሥነ ልቦና ግንባታን እንደ አዲስ መጀመር የግድ እንደሚል አጽንኦት ተሰጥቷል።
በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የትግራይ ለውጥ ኃይልና የፌደራል መንግሥት የየበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው ተጠቁሟል። የትግራይ ሕዝብ የሚመጥነውን መሪ በዲሞክራሲያዊ መንገድ መምረጥ እንዲችል ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች እና ወጣቶች መለያየትን በመተው የጋራ መድረክ እንዲፈጥሩ ጥሪ ቀርቧል።

Comments