ታዋቂው የቀዶ ጥገና ሐኪም ተሸለሙ
#ethiopia | የኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርና ታዋቂ የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር ስዩም ካሣ መርኔ (ተባባሪ ኘሮፌሰር) የኢትዮጵያ ቀዶ ጥገና ማህበር / Surgical Society of Ethiopia/ የ2026 የህይወት ዘመን ስኬት ተሸላሚ ኾኑ።
ዶ/ር ስዩም በኩባ የሕክምና ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ እኤአ ከ1992 ጀምሮ ላለፉት 33 ዓመታት በዋንኛነት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ዲፓርትመንት በመምህርነት፣ በቀዶ ጥገና ሐኪምነት፣ በዲንነት በተጨማሪም በዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል፣ በጳውሎስ ሆስፒታሎች በደረትና አካባቢው ቀዶ ጥገና ሐኪምነት ማገልገላቸው ታውቋል።
በተጨማሪም በተለያዩ የግል ሆስፒታሎች የደረትና አካባቢው ቀዶ ጥገና ሕክምና በማስጀመር ጭምር አገልግለዋል።
ዶ/ር ስዩም ከ30 በላይ ከሙያው ጋር በቀጥታ የተገናኙ ጥናታዊ ጹሑፎችን በሀገር ውስና በውጭ ሀገር ታዋቂ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል።
ዶ/ር ስዩም የማኀበሩ 30ኛው ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል።
"ሽልማቱ ምን ስሜት እንደፈጠረባቸው ዶ/ር ስዩም ተጠይቀው የዓመታት ልፋትና ጥረታቸው ዕውቅና ያገኘበት በመኾኑ መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ዶ/ር ስዩም ሥራ ሲጀምሩ የደረትና አካባቢው ቀዶ ጥገና ሐኪሞች ቁጥር እሳቸውን ጨምሮ 3 ብቻ እንደነበሩ አስታውሰው በአሁን ሰዓት ግን ተተኪ ወጣቶችን በማስተማር የሐኪሞችን ቁጥርና ሕክምናውንም ለማዘመን በተደረገው ጥረት በአቅማቸው ባደረጉት አስተዋፅኦ ደስተኛ መኾናቸውን ጠቅሰዋል።
ስለኢትዮጵያ ቀዶ ጥገና ማህበር
የኢትዮጵያ ቀዶ ጥገና ማህበር / Surgical Society of Ethiopia / ከተቋቋመ 31 ኛ ዓመት ያስቆጠረ ሲኾን በየዓመቱ ኮንፈረንስ በማካኼድ፤ ከኮንፈረንሱ ጎን ለጎን በሙያው ውስጥ ላቅ ያለ አበርክቶ ላላቸው ባለሙያዎች የዕውቅና ሽልማት ይሰጣል።

1 month ago