5 months ago
🎓 የነፃነት ጮራ!
ለ60 ዓመታት ትውልድ የቀረፁት መምህር ጠምቀ...
#ethiopia | ከአክሱም ማይብራዚዬ ገዳም የቤተ ክህነት እውቀት እስከ ጎንደር ዘመናዊ ትምህርት... ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በ1957 ዓ.ም በቄራ እና ጎፋ አካባቢ "የነፃነት ጮራ ትምህርት ቤትን" የመሰረቱት ታላቁ አባት!
መምህር ጠምቀ፤ ትምህርት ቤታቸው በደርግ ዘመን ቢወረስም፤ ዓላማቸውን ግን ማንም አልወረሰባቸውም።
በፅናት እና በታማኝነት መምህርነትን እንደ ሥራ ሳይሆን እንደ ሕይወት ተልዕኮ በመቁጠር በርካታ ሀኪሞችን፣ ኢንጂነሮችን፣ ጋዜጠኞችን እና ተመራማሪዎችን አፍርተዋል።
ልዩ የክብር መርሐግብር!
እኚህን በሕይወት ያሉ ታላቅ ባለውለታ ለመዘከር እና ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለማክበር፤ በቀድሞ ተማሪዎቻቸው፣ ወዳጆቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ጥያቄ መሰረት ልዩ ዝግጅት ተሰናድቷል።
📅 ጥር 16 ቀን 2018 ዓ.ም
በዕለቱ ምን ይጠበቃል?
📘 የሕይወት ታሪካቸውን የሚዘክረው "የትምህርት ጮራ" የተሰኘ ባለ 80 ገጽ መጽሐፍ ይመረቃል።
🎙 ከትምህርት ባልደረቦቻቸው እና ከተማሪዎች ጋር የፓናል ውይይት ይደረጋል።
🎖 የትምህርት ቢሮ እና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ምስጋና ይቀርባል።
በሕይወት እያሉ ባለውለታዎቻችንን እናክብር!
የነፃነት ጮራ ፍሬዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
#netsanetchora #school #education #teachertemke #tribute #addisababa #kera #gofa #ethiopia #alumni #education #hero #teacher #netsanetchora #thankyouteacher

Comments