12 days ago
የትምህርት ሚኒስቴር ፈተና በማውጣት መምህራንን የሚያግዝ Application ወደ ሥራ አስገባ 🔥
ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የሥራ ጫና ለመቀነስ እና የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል “ኤጀንቲክ መምህር ረዳት” (Agentic AI Teacher Assistant) የተሰኘ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ አበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ስራ ላይ አውሏል።
ይህ ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ ያለኢንተርኔት የሚሰራ ሲሆን፣ በማዕከላዊ ሰርቨር ወይም በክላውድ ቴክኖሎጂ ላይ ሳይመሰረት በአካባቢያዊ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተጭኖ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።
በተጨማሪም መተግበሪያው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን መጽሐፍት በሙሉ ዳታሴት በመውሰድና በማስተካከል የተዘጋጀ ነው።
በመተግበሪያው ምን ምን ነገሮች ማከናወን ይቻላል ?
- የትምህርት እቅድ (Lesson Plan) ማዘጋጀት፣
- ደረጃቸውን የጠበቁ የፈተና ጥያቄዎችንና አሳይመንቶችን ማመንጨት፣
- የማስተማሪያ ስልቶችን በራሱ ማቀናጀት ይችላል።
በማንኛውም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላይ ተጭኖ የሚሰራ ቀላል ሞዴልበማንኛውም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላይ ተጭኖ የሚሰራ ነውም ተብሎለታል።
በኢንተርኔት ኔትወርክ በሌላቸው የገጠርና ራቅ ያሉ አካባቢዎች ያለምንም ወጪ እና መቆራረጥ በመስራትም በከተማና በገጠር ትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን ያጠባል ተብሎ ታምኖበታል።
በሙከራ ደረጃ የሚገኘው ይኸው መተግበሪያ ቀጣይ የማስፋፊያ ሥራዎቹ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በሚንቀሳቀሰው የኢትዮጵያ የትምህርት ለውጥ ኦፕሬሽን (ETOL) ፕሮጀክት ድጋፍ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል።
መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።
Seledadotio

5 months ago
🎓 የነፃነት ጮራ!
ለ60 ዓመታት ትውልድ የቀረፁት መምህር ጠምቀ...
#ethiopia | ከአክሱም ማይብራዚዬ ገዳም የቤተ ክህነት እውቀት እስከ ጎንደር ዘመናዊ ትምህርት... ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በ1957 ዓ.ም በቄራ እና ጎፋ አካባቢ "የነፃነት ጮራ ትምህርት ቤትን" የመሰረቱት ታላቁ አባት!
መምህር ጠምቀ፤ ትምህርት ቤታቸው በደርግ ዘመን ቢወረስም፤ ዓላማቸውን ግን ማንም አልወረሰባቸውም።
በፅናት እና በታማኝነት መምህርነትን እንደ ሥራ ሳይሆን እንደ ሕይወት ተልዕኮ በመቁጠር በርካታ ሀኪሞችን፣ ኢንጂነሮችን፣ ጋዜጠኞችን እና ተመራማሪዎችን አፍርተዋል።
ልዩ የክብር መርሐግብር!
እኚህን በሕይወት ያሉ ታላቅ ባለውለታ ለመዘከር እና ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለማክበር፤ በቀድሞ ተማሪዎቻቸው፣ ወዳጆቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ጥያቄ መሰረት ልዩ ዝግጅት ተሰናድቷል።
📅 ጥር 16 ቀን 2018 ዓ.ም
በዕለቱ ምን ይጠበቃል?
📘 የሕይወት ታሪካቸውን የሚዘክረው "የትምህርት ጮራ" የተሰኘ ባለ 80 ገጽ መጽሐፍ ይመረቃል።
🎙 ከትምህርት ባልደረቦቻቸው እና ከተማሪዎች ጋር የፓናል ውይይት ይደረጋል።
🎖 የትምህርት ቢሮ እና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ምስጋና ይቀርባል።
በሕይወት እያሉ ባለውለታዎቻችንን እናክብር!
የነፃነት ጮራ ፍሬዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
#netsanetchora #school #education #teachertemke #tribute #addisababa #kera #gofa #ethiopia #alumni #education #hero #teacher #netsanetchora #thankyouteacher

8 months ago
በልጆቻችን “ከሰኞ እስከሰኞ ትምህርት ቤት የመዋል ውሳኔ” ላይ የግሌ አስተያየት
(መላኩ ብርሃኑ)
#ethiopia | አንድ እንደዋዛ ሳናብላላው ያለፈ ፣ ቢያንስ በኔ እይታ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን የከተማው አስተዳደር ውሳኔ አለ፡፡ የ11ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትምህርት ሰዓት ጭማሪ ጉዳይ፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሰሞኑ “የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል” በሚል ምክንያት በከተማዋ የሚገኙ የግልና የመንግሥት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፤ ከሰኞ እስከ አርብ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት እንዲማሩ ፣ ጠዋት ደግሞ በአንድ ሰዓት ወደ ትምህትት ቤት እንዲገቡ ፣ በተጨማሪም በተመረጠ ትምህርት ቤት አንድ ላይ ቅዳሜና እሁድ እንዲማሩ የሚያስገድድ መመሪያ አውጥቷል፡፡
እርግጥ ነው...የ12ኛ መልቀቂያ ፈተና ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል ወደዩኒቨርሲቲ የሚያልፉት እጅግ አናሳ ቁጥር ያላቸው ብቻ መሆናቸው እንደወላጅ እኛን፣ እንደአስተዳዳሪ አካልም መንግስትን ማሳሰቡ ተገቢ ነው፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር እንደባለቤት በየዓመቱ የወደቁ ተማሪዎችን ቁጥር ለወላጅ ከማርዳት በተሻለ ለዚህ አሳሳቢ ችግር መፍትሄ ማፈላለግ ግዴታው ነበር፡፡በዚህ ዙሪያ ምን እየሰራ እንደሆነ እኔ አልሰማሁም፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ግን ከሰሞኑ ይህንን ‘የመውደቅ ምጣኔ’ 'በማለፍ ምጣኔ' ለመቀየር ብሎ ያወጣውን አስገዳጅ መመሪያ ሰምቻለሁ፡፡ በግሌ ይህ ውሳኔ የተጠና እና ሳይንሳዊ ነው ብዬ አላምንም፡፡
በራሴ ቤት ትዝብት ልጀምር፡፡ ናኒዬ ዘንድሮ 10ኛ ክፍል ናት፡፡ ትምህርት ከተጀመረ ቀን አንስቶ ከኛ ጋር ቁጭ ብላ ለማውራት ደቂቃ ጊዜ እንኳን የላትም፡፡ ከትምህርት ቤት መጣች ፣ ጥቂት እረፍት አድርጋ ሃይል ሰበሰበች …ከዚያ ክፍሏ ገብታ እስከእኩለ ሌሊት ከትምህርት ቤትና ከኦንላይን ምንጮች ጋር ትንቅንቅ ላይ ናት፡፡ ጥናትና የቤት ስራ ብቻ ሳይሆን ያልገቧትን ሃሳቦች ማብራሪያ ፍለጋ ኦንላይን ምንጮችን ስታስስ ታመሻለች፡፡ በቀን ያለማጋነን ከ13 ሰዓት በላይ ትምህርት ላይ ነው የምታሳልፈው፡፡
እኔ በበኩሌ ራስን እረፍት በመንሳት የማጥናትና መማር ሂደትን ብዙም ባልደግፍም ከምትማራቸው ትምህርቶች ብዛት፣ በላይ በላይ ከሚሰጡ አሳይመንቶችና ከሚላኩት ፓወርፖይንቶች ብዛት፣ በአንድ ሳብጀክት ብቻ በየቀኑ ከሚሸፍኑት ፖርሽን ብዛት፣ ጠለቅ ብላ ለመረዳት ከምታስሳቸው ኦንላይን ምንጮች ብዛት ወዘተ አንጻር ሳየው “እንዲህም ሆና ቀኑ በበቃትና ጫናውን ተቋቁማ ከዘለቀች ጥሩ ነው” ብዬ ማለፍ ግድ ሆኖብኛል፡፡ የናኒ ጥቂት እረፍት ቅዳሜና እሁድ ከሰዓት ሰንበት ትምህርት ቤት ለመሄድ ከደብተሯ የምትለያይበት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ዓላማዋ ሩቅ ስለሆነ ዛሬ በልጅ ጉልበቷ አቅሙን ከሰጣት ‘ እንግዲህ ትቻለው’ ብዬ ትቻታለሁ፡፡
ናኒ እንደምትነግረኝ ከሆነ አሁን አሁን በትምህርት ቤት መምህራን ከሚሰጣቸው ትምህርት በላይ ከመጽሃፍትና ኦንላይን በሚገኙ አጋዠ ግብዓቶች በንባብ የሚገኘው ዕውቀት ጥልቅ እና የበለጠ ደጋፊ ነው፡፡ “መምህራኖቻችን መሰረታዊውን ጉዳይ ብቻ ያስጨብጡናል፣ እኛ ደግሞ ከዚህም ከዚያም ፈላልገን በርዕሰጉዳዩ ላይ አንብበንና ሰርተን እውቀታችንን እናሰፋለን’ ነው ያለችኝ፡፡ ከ2 ዓመት በኋላ ለሚጠብቃት ፈተና ራሷን እያዘጋጀችበት ያለችበት መንገድም ይኼው ነው፡፡ አዲሱ ውሳኔ ግን ገና ከአሁኑ ውጤታማነቷ ላይ ተጽዕኖ እንዳያሳድር በጣም አስግቷታል፡፡
አስተዳደሩ ተማሪዎች ከሚማሩበት ጊዜ ይልቅ የሚያርፉበት ጊዜ የበለጠ መስሎት በተገበረው አዲስ መመሪያ መሰረት ግን ናኒ ከሚቀጥለው አመት በኋላ ከሰኞ እስከሰኞ ከአዳር በመለስ ውሎዋ ሁሉ ትምህርት ቤት ሊሆን ነው፡፡
በነበረው አሰራርና መምህራንና ተማሪዎች በተስማሙበት አካሄድ የክፍል ትምህርት አማራጭ ምንጮች ተጨምረውበት ካልተነበበ በመምህራን ገለጻ ብቻ የማይገፋ ነው፡፡ አሁን ግን ተመልሶ ወደክፍል ጥገኝነትና ሁሉንም ነገር በመምህራን ትከሻ ላይ ወደመጣል ሊሸጋገር ነው፡፡ ያ ደግሞ በአንጻራዊነት ሲታይ ተማሪዎች ከአንድ ከተቀነበበ ከባቢ ወጥተው ጥቂት እያረፉም ብዙ እየሰሩም የሚያካሂዱትን የቤት ውስጥና የላይብረሪ ጥናት ጊዜያቸውን ሙሉ በሙሉ ይበላባቸዋል፡፡
ትምህርት በተፈጥሮው የተጠና የእረፍት ጊዜ ከሌለው በጣም አሰልቺ ሂደት ነው፡፡ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ከክፍል ትምህርት ባለፈ extracurricular activities የሚደረጉት ይህንን መሰልቸት ለማስቀረትም ጭምር ነው፡፡ የሰው ልጅ አንድን ነገር ምን ቢወደው በተመሳሳይ ሁኔታ ሲያገኘው ይሰለቸዋል፣ ይጠላዋል፡፡ ይህ ተፈጥሮ ነው፡፡
ተማሪዎች በቀን የተወሰነ ሰዓት፣ በሳምንትም እንዲሁ ተሰልቶ ሰፋ ላለ ሰዓታት እረፍት ቢያደርጉ ይመከራል፡፡ ለግል ንጽህና መጠበቂያ ፣ ለሃይማኖታዊ ስርዓት መከታተያ፣ ከቤተሰብ ጋር ጊዜ ለመውሰጃ እና ለመወያያ የሚሆን ጊዜ በጣም ያስፈልጋቸዋል፡፡ School- Life Balance መተግበር ካልቻሉ Burnout ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ እንኳን የታቀደውን ውጤት ሊያመጣ ጭራሽ ብዙ ተማሪዎችን ከመስመር ሊያስወጣና ወዳልተፈለገ ጭንቀት፣ መንሸራተት እና ማፈግፈግ ሊመራ ይችላል የሚል ስጋት አለኝ፡፡ ብዙ የትምህርት ባለሙያዎችም እየተናገሩ ያሉት ይህንን ነው፡፡
ለመሆኑ ይህ ውሳኔ ምን አይነት ጥናት ተደርጎበትና በምን መልክ አዋጪ ይሆናል ተብሎ ነው ተግባራዊ እንዲደረግ የታዘዘው? ምን ያህልስ ሳይንሳዊ ነው?
ከኛ በእጅጉ የራቀው የሰለጠነው አለም ውጤት ለማምጣት የትምህርትና ጥናት ጊዜን ማርዘም ሳይሆን አጭር ግን ደግሞ በጣም ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀምን ይመክራል፣ የትምህርት አመራሩም በዚሁ መንገድ የተቃኘ ነው፡፡
ቻይና እኮ ከዘንድሮ ጀምሮ በወሰደችው እርምጃ እስከ12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በግዴታ ክፍል ውስጥ የተወሰነ ጊዜ እንቅልፍ እንዲተኙ አዝዛለች፡፡ ሲታጠፍ ወንበር፣ ሲዘረጋ አልጋ የሚሆን አዲስ ሞዴል የተማሪዎች ወንበር በሁሉም ግዛቶች ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ አንዲሆን አድርጋለች፡፡ ጥቂት ‘ናፕ’ ማድረግ ዐዕምሮን ያድሳል፣ ውጤታማ ያደርጋል ብላለች፡፡ ዝም ብላ አይደለም፣ ሰፊ ጥናት ተደርጎ የተደረሰበት መደምደሚያ ነው፡፡
እኛ ሃገር ምን አዲስ ነገር ተዘጋጀ? ምንም፡፡ ሰዓትና ቀን ግን ተጨመረ፡፡ በዚያ ጀርባና መቀመጫ በሚቆረቁር ዴስክ ላይ ለሰዓታት ተቀምጦ መዋል የሚፈጥረው የራሱ የጤና ችግር እንዳለ ሆኖ መምህራንስ በሳምንት ከ40 ሰዓት በላይ በማስተማር አይደክሙም ወይ? ተማረዎችስ ቢሆኑ ምን ትምህርት ቢወዱ በሂደቱ መሰልቸት ውስጥ አይገቡም ወይ? ክፍል ውስጥ ታፍኖ እያንቀላፉና እያዛጉ መማር ምን ረብ ሊያስገኝ ነው? አስተዳደሩስ ቢሆን ለምን የዚህን አዲስ ውሳኔ Rationale በይፋ አይነግረንም? ትምህርት በግድ ስለተቀጠቀጠ ውጤት ይመጣል ብሎ ማሰብ መነሻው ምን ይሆን?
በእውነት ለመናገር ይህ ጉዳይ እንደወላጅ እጅግ በጣም አሳስቦኛል፡፡ ብዙ ወላጆች ተቃውመውታል የተባለውን ይህንን አካሄድ 'ኦልሬዲ የተወሰነ ነገር ነው፣ ለናንተ ለማሳወቅ እንጂ የሚቀየር ነገር የለም' ብሎ ወደትግበራ መግባት የጤና ነው? ለመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ግን ይህንን ያውቃል? ይደግፋል? እናንተስ ልክ ነው ትላላችሁ? መገናኛ ብዙሃንስ ምነው ዝም አላችሁ? ምንም አልገባችሁም ማለት ነው?
እንደወላጅም፣ እንደባለሙያም በጉዳዩ ላይ ሃሳብ እንለዋዋጥ እስኪ፡፡
Education should not become a burden for children at all !! Pressure from teachers and the sheer volume of homework, including holiday classes and assignments, can detract from learning and lead to stress and burnout, making education feel like a chore instead of a privilege.

10 months ago
ለልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የመምህራን ቅጥር ምዝገባ!
ትምህርት ሚኒስቴር ባስገነባቸው ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2018 የትምህርት ዘመን ሥራ ለማስጀመር መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
በመሆኑም ከላይ የተገለፁ መስፈርቶችን የምታሟሉ መምህራን ከዛሬ ነሐሴ 07/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በ https://sbs.moe.gov.et/pro... ላይ በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
➫ ተፈላጊ መምህራን ብዛት፦ 42
➫ ቅጥር፦ በቋሚነት
➫ የጽሁፍ እና የቃል ፈተና ይሰጣል
ለመመዝገብ 👇
https://sbs.moe.gov.et/pro...
(የተቋሙ ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል።)
Via:tikvah

11 months ago
Parents, are you searching for the right school for your child?
Choose the School of Global Citizens where curiosity, creativity, and cultural values come together in a nurturing environment for children from KG to Grade 4.
With certified teachers and international experience, we provide the quality education your child deserves.
You won’t regret it—and this year, upon a request by several parents, enjoy a substantial tuition discount!
Enroll today.
Adress:- At 24 in front of Kokeb Building

Sponsored by
Surafel
12 months ago
ለዩኒቨርሲቲ መምህሩ አስናቀ ብርሃኑ እንድረስለት
Lets support Our Teacher
Yilkal Andualem is organizing this fundraiser.
Donation protected
መምህራችን_ታሞብናል
ወደ ካንሰር ሊቀየር ይችላል....ሀኪሞች
ወጣት መ/ር አስናቀ ብርሃኑ አላምነህ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቅንነትና በታማኝነት እያገለገለ ያለ በሙያውም አንቱታን ያተረፈ በሥነ ምግባሩ ምስጉን ሰው አክባሪ፣ ለተቸገሩ ፈጥኖ ደራሽ ወንድማችን ነው::
በሒሳብ ትምህርት ክፍል የኑሜሪካል አናላይሲስ መምህር ሲሆን በዩኒቨርሲቲ ቆይታውም ከማስተማር ስራው ጎን ለጎን በጥናትና ምርምር ዘርፍ በሙያው አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው 6 (ስድስት) ጥናትና ምርምሮችን በማሳተም ለአንባቢያን አድርሷል::
ወንድማችን መ/ር አስናቀ ድንገት በገጠመው የጤና እክል በህይወት እና በሞት መካከል ሆኖ የድረሱልኝ ተማፅኖውን እያሰማ ይገኛል:: በገጠመው የጤና ዕክል በተለያዩ ስድስት (6) ሆስፒታሎች ህክምና ሲያደርግ ቆይቷል::
ከነዚህም ውስጥ በአንዱ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ሰርጀሪ ተሰርቶ ሊሻለው ባለመቻሉ ወደ አዲስ አበባ አለርት ኮምፕርሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎለት ክትትል እያደረገ ይገኛል::
በመሆኑም የአለርት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ቦርድ 30% አጠቃላይ ቋሚ የአካል ጉዳተኛ እንደሆነና የሚከተሉትን ውሳኔዎችን ወስኗል::
1ኛ. በግራ እግሩ ላይ ስድስት (6) ዓመት የቆየ ከባድ ቁስለት ወደ ካንሰር የመቀየር እድሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑን፣
2ኛ. ሁለቱም እግሮቹ ነርቫቸው የተጎዳና ስሜት አልባ መሆናቸውን፣
3ኛ. የግራ እግሩ ሙሉ አጥንቶቹ የተጎዱና ይዘታቸውን የቀየሩ መሆናቸውን
4ኛ. ቁሞ ማስተማርም ሆነ በእግሩ መንቀሳቀስ እንደማይችል የአለርት ሆስፒታል ሜዲካል ቦርዱ አረጋግጧል
መምህር አስናቀ ባለብዙ ተስፋና ብዙ ህልም የነበረዉ ሩጦ ያልጠገበ ወንድማችን እግሮቹ ደክመው እቤት እንዲውል ተገዷል::
የህመሙ ሁኔታ አሳሳቢ እና ለህይወቱም አስጊ ደረጃ ላይ በመድረሱ ወደ ህንድ አገር ሂዶ ህክምና እንዲያደርግ ሪፈር ተፅፎለታል:: የህክምና ወጭውም ከሁለት ሚሊየን (2,000,000) ብር በላይ እንደሚያስፈልገው ተነግሮታል::
ወንድማችንን ለማገዝ አነሰ በዛ ሳንል በአገር ውስጥና በውጭ ያላችሁ ትዉልደ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የእርዳታ እጃችሁን ትዘርጉ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን::
Asinake Birihanu Alamneh
ስልክ_ቁጥር 09 23 53 45 01
Lecturer Asnake Berhanu, who has been serving Hawassa University with integrity and honesty, is a respected, respectful, and helpful person who has earned a reputation in his profession.
He is a Numerical Analysis Lecturer in the Department of Mathematics.
During his time at the university, he has published 6 (six) internationally recognized studies and research papers in his field, and has reached readers.
Our brother,Teacher Asnake is suddenly in the middle of life and death due to a health problem he encountered.
He has been receiving treatment in six (6) different hospitals for his health problem. In one of them, he underwent surgery at Hawassa University Referral Hospital and was referred to Addis Ababa Alert Compressive Specialized Hospital for follow-up.
Therefore, the Alert Specialized Hospital Medical Board has determined that he is 30% permanently disabled and has made the following decisions:
1st. The six (6) year old severe ulcer on his left leg has a very high chance of turning into cancer,
2nd. Both his legs are nerve damaged and numb,
3rd. The entire bones of his left leg are damaged and their contents have changed,
4th. The Alert Hospital Medical Board has confirmed that he cannot stand or walk.
Our brother, Teacher Asnake, who had many hopes and dreams, has been forced to stay home due to tired legs. His condition is serious and life-threatening, so he has been referred to India for treatment. He has been told that the medical expenses will cost more than $15000 .
Please help support this visionary teacher as they navigate through an incredibly difficult time. The funds raised will go towards the cost of surgical treatment , and to help to cover the loss of income while taking some much needed time to recover.
Thank you for your generosity.
I am grateful for your help and wishes.
Thank you
"Let's save the life of the visionary teacher with sincere hearts and united hands!
Show your support for this GoFundMe

Comments