5 months ago
" ኢትዮጵያ ትቅደም '’
መፈክር የፈጠሩት አቶ ከበደ አኒሳ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ታሪክ ፈር ቀዳጅ ከሆኑት መሐከል አንዱ ነበሩ። አቶ ከበደ አኒሳ ጎሮ ታህሳስ 19 ቀን 1924 በቀድሞው አጠራር ወለጋ ጠቅላይ ግዛት ነቀምት ከተማ ተወልደው እዚያው ነቀምት የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀዳማዊ ኃ/ ሥላሴ ትምህርት ቤት ካጠናቀቁ በኋላ በተከታታይ በአዲስ አበባ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል ።ወደ ውጭ በማቅናትም በቆጵሮስና እስራኤል ማህበራዊ ሳይንስ በአሜሪካን ማካለስተር ኮሌጅ ጋዜጠኝነት ተምረዋል።
#ከዚያም በተማሩት ሙያዎች በመምህርነት፣ በትምህርት ቤት ሥራ መሪነት፣በኢንስፔክተርነት ለአሥር ዓመታት ከዚያም በማስታወቂያ ሚኒስቴር፣ በአገር አስተዳደር ሚኒስቴር፣ ሕዝባዊ ኑሮ እድገትና ዘመቻ መምሪያ ለሃያ ሰባት ዓመታት በጠቅላላው ለ37 ዓመታት አገራቸውን አገልግለዋል።
#አቶ ከበደ አኒሳ በልዩ ልዩ ቦታዎች እየተዘዋወሩ የሠሩ ከመሆናቸው ጋር በጋዜጠኝነት ሙያቸው የታወቁ ነበሩ። በራሳቸው አንደበት ከተናገሩትና በጽሑፍም ካስቀመጡት ማስታወሻ በኢትዮጵያ ድምፅ ጋዜጣና የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅነት፣በአሜሪካን ድምፅ ሪፖርተርነት፣እንዲሁም ለኢትዮጵያን ሔራልድ የሠራሁበትን ጊዜ በጣም እኮራበታለሁ ብለዋል።
"በጋዜጠኝነቴ ዘመን የላቀ ደስታ የሰጠኝ ነገር ቢኖር ይላሉ አቶ ከበደ"የኢትዮጵያ ድምፅ ጋዜጣ ላይ መሪ መፈክር አድርጌ ያስቀመጥኩት "ኢትዮጵያ ትቅደም” የሚለው ቃል ነው። ይህንን የፃፍኩት ደርግ ከመፈጠሩ ዘጠኝ ዓመታት በፊት በ1957 ነው'’ በማለት ጽፈዋል። የሙያ አጋራቸው የሆኑትና ከ35 ዓመታት በላይ የቅርብ ወዳጃቸው የሆኑት አንጋፋው የሮይተርስ ጋዜጠኛ አቶ ፀጋዬ ታደሰ በሰጡት ምስክርነት " በወቅቱ ቀዳማዊ ኃ/ ሥላሴ ኢትዮጵያ ትቅደም ስትል ምን ማለትህ ነበር ብለው ጠይቀውት ነበር። እሱም"ኢትዮጵያን ስለምወድ፣ሕዝቡንም ስለማከብር ሃገሬ በሁሉ ነገር ቀድማ ማየት ስለምፈልግ ነው ብሎ መልሷል። የረዢም ጊዜ ጓደኛዬ ነበረ። ሲለየኝ በጣም አዝኛለሁ።" ብለዋል።
#እኚህ አንጋፋ ጋዜጠኛ ለብዙ ዓመታት በጋዜጠኝነት ሲያገለግሉ ብዙዎቻችን የሙያችን ተምሳሌትና ለኛም እንደ አባት የምናያቸው ድንቅ ጋዜጠኛ ነበሩ::አቶ ከበደ አኒሳ የዘጠኝ ልጆች አባት ሲሆኑ ስምንት የልጅ ልጆችን አይተዋል።
✍️Guenet Ayele Gruenberg
#ኢትዮጵያትቅደም
#enkssm #ethiopianhistoryandtourism

6 months ago
“ልዑል መኰንን"
#ethiopia | ሕይወቱ ከመርካቶ ጋር የተቆራኘው የልዑል መኰንን ኃይለ ሥላሴ ት/ቤት አገራቸውን በተለያያ መስክ ያገለገሉና በማገልገል ላይ የሚገኙ አያሌ ምሩቃንን አፍርቷል።
አውሮፕላን አብራሪዎች (የሴት አብራሪ ሳትቀር)፣ አርኪቴክቶች፣ ምክትል ሚኒስትሮች፣ የመምሪያ ኃላፊዎች፣ ፕሮፌሰሮች፣ ወዘተ ...።
በግሌ በአካዳሚው ዓለም ስኬታማ እየሆንኩ ስሄድ ብዙ ጊዜ ሰዎች ይጠይቁኝ የነበረው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን የት እንዳጠናቀቅኩ ነበር።
አጠያየቃቸው ዊንጌት ወይ ተፈሪ መኰንን ወይ ኮተቤ ብዬ እንድመልስላቸው እንደ ሆነ ይገባኛል። እኔም “ልዑል መኰንን" ብዬ ስመልስላቸው በመገረም መርካቶ?! ብለው መልሰው ይጠይቁኛል።
እኔም ደረቴን ነፍቼ “ አዎ! መርካቶ!" እላቸዋለሁ። አዎ! መርካቶ የሸቀጥ መቸርቸሪያ ብቻ ሳትሆን የዕውቀት አምባም ነበረች፤ ነችም።
ኅብር ሕይወቴ
በባህሩ ዘውዴ
ገጽ 53
#ethiopianhistoryandtourism #enkssm

7 months ago
#የአንጋፋው ድምፃዊ በረከት መንግስተዓብ ስርዓተ ቀብር ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በተገኙበት በአስመራ አርበኞች መቃብር ተፈፀመ።
📸Eritrean Media Network
#ethiopianhisoryandtourism #ethiopianhistoryandtourism #enkssm
📸Eritrean Media Network
#ethiopianhisoryandtourism #ethiopianhistoryandtourism #enkssm
7 months ago
ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም.
የግርማዊ ቀዳማዊ የዘውድ በዓል ሲዘከር።
"በክብር የነገሡት፤ በግርማ የታጀቡት"
► #በአበው ሥርዓት በግርማ ነግሠዋል፤ በአበው ሕግ ተገዝተዋል፤ ሀገራቸውን ያገለግሉ ዘንድ በሕያው አምላክ ፊት ቃል ኪዳን ገብተዋል፤ ቃል ኪዳናቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ታትረዋል።
#ከአበው የተቀበሏት፤ በዓምላክ ፈቃድ ዙፋን ተቀምጠው የሚመሯት፤ በበትረ መንግሥታቸው መንገዷን የሚጠርጉላት ሀገራቸው ከፍ ከፍ ትል ዘንድ ሠርተዋል።
#ተናግረው ይሰማሉ፤ መክረው ይመልሳሉ፤ ገስጸው ያስተካክላሉ፤ ዘምተው ያሸንፋሉ፤ አስበው ያደርጋሉ፤ ጀምረው አምላካቸውን ይዘው ይፈጽማሉ።
#አበው ስለ ጠበቋት ሀገራቸው በጽናት ቆመዋል፤ ከአበው ስለተቀበሏት የከበረችው ሠንደቅ ዓላማቸው በጀግንነት ተፋልመዋል፤ ነጻነቷን እንዳታጣ ከጠላቶቿ ጋር ተጋጥመዋል፤ ዓለም ሁሉ ፊቱን ባዞረባቸው ጊዜ እውነትን፣ ቃል ኪዳንን እና ተስፋን ይዘው ብቻቸውን ቆመዋል።
#ሃሰተኞች በሚፈርዱበት፣ ሀሰተኞች በሚመሰክሩበት፣ ሀሰተኞች የፍርዱን ውሳኔ በሚያጸኑበት፣ የፍርድ ሚዛን ሁሉ ወደ ቅኝ ገዢዎች በምታዘነብልበት በዚያ ጊዜ በተስፋ ቆመዋል፤ ከእውነት ጋር ቆመው የእውነት፣ በእውነት፣ ስለ እውነት ለሀገራቸው ነጻነት ታግለዋል።
#እውነትን ይዘው ሀሰተኞችን በፍርድ ዓደባባይ አሸንፈዋል፤ ቅኝ ገዢዎችም በጦር ሜዳ ድል መትተዋል፤ በድል አድራጊነትም በግርማ እና በከፍታ በዓደባባይ ታይተዋል፤ በዙፋን ላይ እንደ ጫካ አንበሳ በአስፈሪ ክብር ተቀምጠዋል ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ።
#በቅኝ ገዢዎች የተበተኑትን ሰብስበዋል፤ መለያየትን አውግዘው አንድነትን አምጥተዋል፤ የአንድነቱን መሠረት አጥብቀዋል፤ የተረሱትን አስታውሰዋል፤ አንገታቸውን የደፉትን ቀና እንዲሉ አድርገዋል፤ የተገፉትን ደግፈዋል፤ ስለ ራሳቸው በራሳቸው የማይመክሩትን ስለ ራሳቸው እንዲመክሩ፣ መፍትሔም እንዲያበጁ አድርገዋል።
#በቅኝ ገዢዎች የተበተኑትን በአንድነት ሰብስበው አቅማቸውን አደርጅተዋል፤ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲናገሩ መንገዱን አሳይተዋል፤ ስለ እነርሱ ከእነርሱ በላይ እንደሌለ አሳይተዋቸዋል፤ በቅኝ ገዢዎች ምክንያት የጨለመችባቸውን የነጻነት ጀንበር እንዲመለከቱ አድርገዋል፤ በነጻነት ጀንበር በብርሃን ይመላለሱ ዘንድ አድርገዋል ጃንሆይ።
#እኒህ አያሌ ታሪክ የሚነገርላቸው፤ አፍሪካውያን የአንድነታችን አባት የሚሏቸው ንጉሠ ነገሥት ዘውድ የጫኑት፣ በከበረው ዙፋን ላይ የተቀመጡት፣ በትረ መንግሥቱን የጨበጡት፤ ቅብዓ መንግሥቱን የተቀቡት፤ የአበውን አደራ ይሸከሙ ዘንድ እጃቸውን ከፍ አድርገው ቃል ኪዳን የገቡት በዛሬዋ ቀን ነበር፤ ጥቅምት 23/1923 ዓ.ም።
#የነገሡበት ቀን በሃያ ሦስት፣ የነገሡበት ዓመተ ምኅረት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሦስት፣ የነገሡበት ደብርም ክብረ በዓሉ የሚከበረው በሃያ ሦስት ነው። ሃያ ሦስት የተገጣጠመላቸው ባለ ግርማው ንጉሥ።
#ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሕይዎቴ እና የኢትዮጵያ እርምጃ በተሰኘው መጽሐፋቸው ስለ ንግሥናቸው ሲጽፉ መስከረም 17/1909 ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ ሲነግሡ እኔም ለአልጋ ወራሽነቱ እና ለእንደራሴነቱ ስለተመረጥሁ በባለ ሙሉ ሥልጣን እንደራሴነቴ የመንግሥቱን ሥራ እየሠራሁ 14 ዓመታት ቆየሁ።
#ንግሥት ዘውዲቱ መጋቢት 24/1922 ዓ.ም ስላረፉ በማግሥቱ የንጉሠ ነገሥቱ ዐዋጅ ተነግሮ በዙፋኑ ተቀመጥሁ።
#ወደ ፊት ያለው ወራቱ ክረምት ስለነበረ የዘውድ በዓላችን ሰባት ወራት እንዲቆይ አደረግን። በኢትዮጵያ ያሉ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ፣ ባላባቶችም ሁሉ፣ በየገዳማቱ ያሉ አባቶች፣ የየአድባራቱ አለቆች፣ መጥተው የደስታችን ተካፋዮች እንዲኾኑ የጥሪ ደብዳቤ ተላከላቸው። ለዘውድ በዓሉም ዝግጅት ተደረገ ብለዋል።
#ልብሠ መንግሥቱ፣ ዘውዱ እና ሉሉ፣ በትረ መንግሥቱ እና ሰይፉ፣ ቀለበቱ ይህንም የመሰለው ሁሉ በተለየ በወርቅ እና በአልማዝ እየኾነ ተሠራ። ለመሳፍንቱ፣ ለመኳንንቱ፣ ለጦር አበጋዞች ሁሉ እንደየ ክብራቸው የክብር ልብስ ተዘጋጀላቸው።
#በዘውድ በዓሉ ዋዜማ በጅሮንዱ የንጉሠ ነገሥቱን ልብሰ መንግሥት እና ዘውዱን፣ ሉሉን፣ በትረ መንግሥቱን፣ ሰይፉን፣ የአልማዝ ቀለበቱን፣ የእቴጌይቱንም ልበሰ መንግሥት እና ዘውድ፣ የአልማዝ ቀለበት በሠረገላ አስገብቶ በታላቅ ሰልፍ ወስዶ በመናገሻው በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ለሊቀ ጳጳሳቱ አስረክቦ ሌሊቱን ሙሉ ሲጸለይበት አደረ ይላሉ።
#ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱ በሌሊት ወደ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አቀኑ። ጸሎቱም ማካሄዱን ቀጠለ።
#ጃንሆይ ሲጽፉ ሥርዓተ ንግሡ ከመጀመሩ አስቀድሞ ሊቀ ጳጳሳቱ አቡ ቄርሎስ ገበታው የወርቅ የኾነ ወንጌል ይዘው ቀርበው የመሐላ ቃል እንድንፈጽም አደረጉ ብለዋል።
#ብላቴ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተሰኘው መጽሐፋቸው ሲጽፉ የዘውዱ ዋና በዓል ጥቅምት 23/1923 ዓ.ም እሑድ ነበር። ቅዳሜ ማታ የመናገሻ ጊዮርጊስ ካህናት እና ከየአድባራቱ ተመርጠው የመጡ መዘምራን ከማታው ጀምረው ማኅሌት ቆመው አደሩ።
#እኩሌቶቹ መወድስ ሲቆሙ እኩሌቶቹ ክስተት አርያም ያደርሱ ነበር እና ማኅሌቱ ደምቆ አደረ።
#ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱም በሌሊት በመሳፍንቱ እና በመኳንንቱ ታጅበው ወደ ቤተክርስቲያን መጥተው ለዚህ ማዕረግ ላበቃቸው ከዚህ ዕለት ላደረሳቸው አምላክ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ ወደ ማረፊያ ድንኳን ሄደው ጸሎተ ሕሊና ሲያደርሱ አደሩ።
#ጠዋት ሲነጋ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ ሙሉ የማዕረግ ልብሳቸውን ከኒሻን ጋር ለብሰው የራስ ሉል እና የራስ ወርቅ ደፍተው በአዳራሹ ውስጥ በተሰናዳላቸው ስፍራ በየማዕረጋቸው ተቀመጡ። ጳጳሳት እና መምህራን ለሥርዓቱ ተዘጋጁ።
#ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓተ ንግሥ ወደሚፈጸምበት ገቡ። በመንበሩ አጠገብ ተሳልመው ጸሎት አደረሱ። ጸሎታቸው እንደጨረሱ በተሰናዳው ዙፋን ላይ ተቀመጡ።
#በዚህም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ አቡነ ቄርሎስ ፊታቸውን ወደ መሳፍንቱ እና ወደ መኳንንቱ አዙረው እንዲህ አሉ።
"እናንት የኢትዮጵያ መሳፍንት እና መኳንንት፣ የጦር አለቆች ወታደሮች እና ሠራዊቶች፣ በቤተ ክህነትም ያላችሁ ሊቃውንት እና አለቆች መምህራን እና ቀሳውስት ሁሉ ንጉሠ ነገሥታችን ግርማዊ ኃይለ ሥላሴ ከሰሎሞን እና ከንግሥተ ሳባ ከተወለደው ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ ሳይቋረጥ ከመጣው መኾኑን ታውቃላችሁ።
#አሁን በእግዚአብሔር ፈቃድ እና ቸርነት ዘውድ ጭኖ እንዲነግሥ ልቀባው ነው እና በሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሥራው ሁሉ ሀገርም በማሠልጠን ሃይማኖትም በማጽናት በዘመኑም ኢትዮጵያ በዕውቀት እና በትምህርት በጥበብም ከፍ ከፍ እንድትል በመትጋት ከወሰን እስከ ወንሰን የኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲዘረጋ በማድረግ ይህንንም በመሰለው በመልካም ሥራው ሁሉ እንድትገዙለት እና እንድትረዱት አደራ እላችኋለሁ" አሉ።
#ሕዝቡም በዕልልታ አጀባቸው።
#ከዚያም ልብሰ መንግሥቱን አለበሷቸው፤ ቤተ መንግሥቱን አስጨበጧቸው፤ ሉሉንም ሰጧቸው፤ የአልማዙን ቀለበቱንም አጠለቁላቸው፤ የንግሥና ወግ እና ማዕረግ የኾነው ሰይፉን እና ጦሩንም ሰጧቸው፤ ቅብዓ መንግሥቱንም ቀቧቸው፤ ዘውዱንም ባርከው ደፉላቸው፤ በዚህም ጊዜ እልልታው አስተገባ፤ ታላቅ ደስታም ኾነ።
#ንጉሡም በግርማ ኾነው ከዙፋናቸው ላይ ተቀመጡ። የእተጌዋም በሥርዓቱ መሠረት ተፈጸመ። የአልጋ ወራሹም ከዙፋኑ ግርጌ ኾነው ቃል ኪዳን አሠሩ። እልልታውና ጭብጨው ከዳር እስከ ዳር አስተጋባ። ንጉሡና እና ንግሥቷ ከፍ ባለ ሥፍራ ኾነው በታዩ ጊዜ እልልታው ቀለጠ።
#በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የተፈጸመው ሥርዓት በተጠናቀቀ ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱና እቴጌይቱ በስድስት ፈረሶች በሚሳብ በወርቅ ሠረገላ ተቀምጠው፣ ከፊትም ከኋላም በመሳፍንት እና በመኳንንት ታጅበው፣ በሠራዊት ሰልፍ መካከል አልፈው ወደ ቤተ መንግሥታቸው ተመለሱ።
#መሳፍንት እና መኳንንት የመንግሥታት መልእክተኞችም በየማዕረጋቸው በሠረገላ እና በአውቶሞቢል ኾነው አጀቡ። እምቢልታውና መለከቱ ሲንካለል፣ ነጋሪቱ እየተጎሰመ ገብር ገብር ሲል እጅግ ደስ ያሰኝ ነበር።
#በመንገድ ዳር ኾኖ ለማየት የተሰበሰበውም ሕዝብ ሰላምታ እየሰጠና እጅ እየነሳ ሺህ ዓመት ያንግሥዎ እያለ አጨበጨበ። ከቤተ መንግሥት በደረሱ ጊዜም ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱ ለመሰናበቻ በተሰናዳው ሥፍራ ቆመው ሲያዩት ሕዝቡ ሁሉ እንደገና እያጨበጨበ ሺህ ዓመት ያንግሥዎ እያለ እየመረቀ ተሰናበተ። የዘውዱ በዓል ግብርም ተገባ ተብሎ ተመዝግቧል።
#አምባሳደር ዘወዴ ረታ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት በተሰኘው መጽሐፋቸው ንጉሠ ነገሥቱ እና ንግሥቲቱ በወርቅ ሰረገላ ኾነው ወደ ቤተ መንግሥታቸው ሲያመሩ ከሕዝቡ የጎረፈላቸው የደስታ መግለጫ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ነው እየተባለ ይነገራል ብለው ጽፈዋል።
#ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እስከ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ድረስ በተደረገው የአንድ ሰዓት የእርጋታ ጉዞ ላይ እምቢልታው እና መለከቱ ሲነፋ፣ ነጋሪቱ ሲጎሸም፣ ካህናቱ ሲዘምሩ፣ ወታደሩ ሲሸልል፣ ከዚህ ሁሉ ጋር የሴቶች እልዕልታ እና የወንዱ ጭብጨባ ሲያስተጋባ፣ የአዲስ አበባን የጥቅምት ፀሐይ እጅግ ያጋላው ይመስል ነበር።
#በዋዜማው ቅዳሜ ከማታው በአራት ሰዓት የተጀመረው ጸሎተ ቅዳሴ እና የንግሥ በዓል ሥርዓት የተፈጸመው በማግሥቱ እሑድ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሲኾን ነው።
#ለአሥራ አራት ሰዓታት ያለማቋረጥ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ንጉሠ ነገሥቱ እና ንግሥቲቱ ያሳዩትን ጥንካሬ እና የመንፈስ ጽናት ያላደነቀ አልነበረም።
#በተለይም በበዓሉ ተካፋይ ለመኾን ከአውሮፓ፣ ከእስያ እና ከአሜሪካ የመጡት የአሥራ አንድ ሀገራት እንደራሴዎች ከዚህ ቀደም በየትኛውም ዓለም ያላዩትን ይህን እጅግ ረጅም እና ከፍተኛ የኾነ ሥነ ሥርዓት ሲመለከቱ ኢትዮጵያ ያላት ጥንታዊ ባሕል ምን ያህል የሚደንቅ እና የሚከበር መኾኑን መገንዘብ የሚያስችላቸው ነው ብለው ጽፈዋል።
#ዘውድ በጫኑበት ዕለት በእርስዎ መሪነት ኢትዮጵያ ዘመናችን ያፈለቀውን ሥልጣኔ አግኝታ በዓለም ላይ የክብር ቦታ እንድትይዝ የሚያደርጉት ጥረት የተባረከ ይኹን ተብለው እንደተመረቁ ሁሉ ንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለ ሥላሴ በነጻነት የተቀበሏት ሀገራቸውን ታላቅ እና ገናና ትኾን ዘንድ አቅማቸው የፈቀደውን ሳይሰስቱ ሰጥተዋል።
#የኢትዮጵያን ክብር እና ጥቅም አስከብረዋል፤ ገናናቷን በአፍሪካ እና በቀረው ዓለም ደጋግመው አስመስክረዋል። የአፍሪካውያንን የአንድነት መሠረት ጥለው አልፈዋል።
#ኢትዮጵያን ስላገለገሉ እናመሰግንዎታለን፤ ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት፣ ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና ክብር ስለታተሩ እናከብረዋታል።
✍️በታርቆ ክንዴ(አሚኮ)

ሰንጋተራ – ጉራጌ ሰፈር
#ethiopia | ከታች ፎቶው የተያያዘው የመላኩ ተገኝ (ዶክተር) ግለ ታሪክ፣ የዚያ ትውልድ የወቅቱ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ትዝታንና ትውስታን መሰረት ተደርጎ የተጻፈ ባለ 300 ገጽ መጽሐፍ ነው።
በዚህ መጽሐፍ ላይ በ1940ዎቹ በአዲስ አበባ በተለይም ሰንጋ ተራ የሚኖሩ ጉራጌዎች ባህሪይ፣ ጠባይ እና የወቅቱ የአኗኗር ዘይቤ በጥቂቱ እንዲህ ሰፍሯል።
................
"እኔና ወንድሜ የተወለድነው ሰንጋተራ ከ'ደሬ ውኃ ስንቁ'' ሰፈርና ጉራጌ ሰፈር” መሀል ባለው በ'ብላታ በቀለ ግቢ ውስጥ ነው። እኔ ትዝ የሚለኝ ግን ጉራጌ ሰፈር ስንኖር ነው። ደሬ ጉራጌ ሰፈር ተብሎ የሚጠራው ዛሬ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ካለበት በስተጀርባ የነበረው ሰፈር ነው። ወይን ("ንብ ባንክ እና ዙርያ ገባው" አካባቢ)
የኛ ቤት በጉራጌ ሰፈር ዋናው መንገድ ላይ ሲሆን በጣም ብዙ ሰው የሚመላለስበት ነበር። ግመሎችን የሚነዱና ሸቀጥ በአህያ የጫኑ ነጋዴዎች ወደ መርካቶ ሲሄዱ፣ የኦርማ–ጋራዥ ሠራተኞችና ተማሪዎች በበራችን ሲያልፉ ትዝ ይለኛል።
ደጃፍ እናቴ የምትሠራውን እየሠራች ቁጭ ብዬ ወጪ ወራጁን እመለከት ነበር። ለዓይን ያዝ ሲያደርግ የጎረቤታችን የወንድሙ አባት ክራራቸውን ሲጫወቱ የሚያመሹት ነገር ዛሬም ድረስ አልተረሳኝም።
ጠዋት ጠዋት እማማ ትክከሏ #“በላለዴ ምጣ" ሳይሉ አያልፉም ነበር።
ከበስተኋላችን ከሚኖሩት ጎረቤቶች ደግሞ ጠዋት ጠዋት ላም ስትታለብ፣ ቡና ሲወቀጥ፣ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ሲዘገጃጁ ይሰማል፤ በሰንጋ ተራ።
አብዛኛው ነዋሪ ትሑትና ሰው አክባሪ ነበር።
በሳምንቱ በተወሰኑ ምሽቶች መንደርተኛው ሁሉ አቶ ባለሜና እማማ ትክከሏ ቤት ይሰባሰባል። ቡና በትልቅ ጀበና ይፈላል፤ የበቆሎ ቆሎ ቁርስ ይቆላል።
ትላልቁ ሰው ቡና ሲጠጣ እኛ ኩታሮቹ ቆሏችንን እንበላና ከበሮ ይመጣል። ከዚያ በኋላ በጉራጊኛ ዘፈንና ጭፈራ ቤቱ ይደምቃል። እኔም ወንድ ልጅ መጨፈር ያለበትን የጉራጊኛ ጭፈራ ስልት ተማርኩ።
ያኔ የነበሩ ጓደኞቼ አይረሱኝም። ፍቅሬ፣ ጉልላት፣ ፍቃዱ፣ እነ ገረመው ዘርጋው፣ ፍቃዱ ወልዴ፣ ግርማ ጣሴና አስራት ጣሴ ታላላቆቻችን ነበሩ። እናቴ ከጉራጌ ሰፈር ሴቶች ጋር ጥብቅ ወዳጅነት ስለነበራት ጉራጊኛ ልቅም አድርጋ ትናገር ነበር።"

Sponsored by
Surafel
10 months ago
ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ ሕንጻ
#ethiopia | የጎንደር ዩንቨርሲቲ ሴኔት ሐምሌ 24 ቀን 2017ዓ.ም ባካሄደው ጉባዔ ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ ላበረከተው ፈርጀ ብዙና ፈር ቀዳጅ የሙያ አስተዋጽዖ የሙዚቃ ትምህርት ቤቱን ሕንጻ "ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ ሕንጻ" ብሎ ሰይሞታል።
◾️ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ
#በሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ካሳረፉ ባለውለታዎች መካከል ኢትዮጵያዊው ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። በ1936 ዓ.ም በጅማ ከተማ የተወለደው አንጋፋው አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከጃዝ እና ላቲን ሙዚቃ ጋር በማስተጋበር ልዩ የሆነ የሙዚቃ ቀለም በመፍጠር የኢትዮጵያ ሙዚቃን ከፍ ያለ እውቅና እንዲያገኝ እና ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ያስተዋወቀ የአገር ባለውለታ ነው። በዚህም ምክንያት "የኢትዮ-ጃዝ አባት" ተብሎ ይጠራል።
#ለንደን፣ ኒውዮርክ እና ቦስተን በሚገኙ ስመጥር የሙዚቃ ትምህርት ቤቶች ተምሯል። በሙያው ብቁ በሆኑ ባለሙያዎች ሰልጥኗል። ጥበብና ክህሎቱን በትምህርት ካዳበረ በኃላ “Broken Flowers“ ለተሰኘው የእንግሊዝኛ ፊልም ማጀቢያ ሙዚቃ መሥራት ጨምሮ ታላላቅ አገራዊና ዓለም ዓቀፋዊ መድረኮች ላይ ሥራውን አቅርቧል።
#በዘመን ተሻጋሪ የጥበብ ሥራዎቹ የሀገራችንን ውብ የብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃ መሳሪያዎችና ውዝዋዜዎች የዓለም ትኩረት እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈ በታዋቂ አርቲስቶች ሥራዎች ላይ ጭምር እንዲካተቱ ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደር ችሏል። በዓለም ላይ ያሉ ብዙ የጥበብ ሰዎች እርሱ መድረክ ሥራ ላይ ይዟቸው ከቀረቡ የብሔረሰቦቻችን ሙዚቃ፣ ሙዚቃ መሳሪያ እና ውዝዋዜ አያሌ ትምህርቶችን እንደቀሰሙ ይነገራል።
#ይህ ጉምቱ የጥበብ ሰው የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ዜማ እና መሳሪያዎችን ለትውልድ ለማስተማርና ለማሳደግ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዜማ መሣሪያዎች ታሪካዊ ሚና እና በሀገሪቱ የሙዚቃ ቅርስ ላይ ያላቸውን ተፅእኖ የሚዳስስ መጽሐፍም አዘጋጅቷል።
#ሎሬት ሙላቱ ለዓለም ሙዚቃ ላበረከተው ታላቅ አስተዋጽኦ በኢትዮጵያ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ሽልማቶች ተበርክቶለታል። ከጅማ ዩንቨርስቲ የክብር ዶክትሬት እንዲሁም የህይወት ዘመን የክብር ሽልማት ተሸላሚ፤ ከበርክሌይ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ያገኙ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ፤ በጀርመን አገር በስሙ መንገድ የተሰየመለት፤ በፈረንሳይ መንግሥት የአገሪቱ ከፍተኛ የክብር ኒሻን "Ordre des Arts et des Lettres" ተሸላሚ፤ እንዲሁም ከኢጣልያ መንግሥትም 'Ordine della Stella d’Italia' ኒሻን ከተበረከቱለት እውቅናዎችና ሽልማቶች ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ።
#በጎንደር ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ ጊዚያት በተጋባዥነት እየተገኘ የሙዚቃ ትምህርት ክፍሉ እንዲጠናከር ልምድና እውቀቱን ለመምህራንና ተማሪዎች አካፍሏል።
#ስለሆነም የጎንደር ዩንቨርሲቲ ሴኔት ሐምሌ 24 ቀን 2017ዓ.ም ባካሄደው ጉባዔ ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ ላበረከተው ፈርጀ ብዙና ፈር ቀዳጅ የሙያ አስተዋጽዖ እውቅና ለመስጠትና ትውልዱ እንዲማሩበት በማሰብ የሙዚቃ ትምህርት ቤቱን ሕንጻ "ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ ሕንጻ" ብሎ ሰይሞታል።
©AsratAtsedeweyn

Comments