የልጅ እናት
የግማሽ ማራቶን አሸነፈች
#ethiopia | በአስደናቂ ሁኔታ የተመለሰችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሀብታምነሽ ተስፋይ በ2025 የትሬንቶ ግማሽ ማራቶን The TRENTO HALF MARATHON በማሸነፍ አስደናቂ ብቃት አሳይታለች።
ድሏን የበለጠ የሚያስገርመው ደግሞ በቅርቡ እናት መሆኗ ነው።
የ31 አመቷ አትሌት ውድድሯን በ1 ሰአት ከ11 ደቂቃ እና 53 ሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቃለች ።
ሀብታምነሽ እኤአ በ2012 የአለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ ተወዳድራ ያከናወነች ሲሆን በሴቶች 3000 ሜትር ሩጫ አራተኛ ወጥታ ነበር።
አትሌቷ በ2013 የአፍሪካ ወጣቶች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በ9፡32.3 የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ነበረች።
በ2018 የአፍሪካ ጨዋታዎች በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር 6ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች ።
2018 በአፍሪካ ሻምፒዮናዎች በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ሰባተኛ ደረጃን ይዛ ፈፅማለች ።
አትሌት ሀብታምነሽ በ2018 የዱባይ ማራቶን የገባችበት 2:20:13 የግል ምርጥ ሰዓቷ ሲሆን የውድድሩ አራተኛው ፈጣን ሰዓት ነበር ።
የ31 አመቷ አትሌት በወሊድ ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከውድድር እርቃ መቆየቷ ይታወሳል።
ከወሊድ በኋላ በስፖርቱ መቆየት እንደሚቻል የሀብታምነሽ የዳግም ምልሰት ለሁሉም እህቶቻችን ጥሩ ምሳሌ ነው።#ወርቅነህ ጋሻሁን

10 months ago