Logo
Getu Temesgen
የቫሌንሲያ ማራቶን አሸናፊዋ ናንሲ ጄላጋት ሜቶ በዶፒንግ ታገደች
#ethiopia | የቀድሞዋ የቫሌንሲያ ማራቶን አሸናፊ ኬንያዊቷ ናንሲ ጄላጋት ሜቶ፣ የተከለከለ አበረታች ንጥረ ነገር (Doping) ተጠቅማ በመገኘቷ የሁለት ዓመት የእገዳ ቅጣት ተጣለባት።

የቅጣቱ ዝርዝር ሁኔታ፦

* የተገኘው ንጥረ ነገር፦ ‘ፉሮሴማይድ’ (Furosemide) የተባለ የአቅም ማጎልበቻ።

* ምርመራው የተደረገበት ወቅት፦ ሰኔ 2016 ዓ.ም. በኬንያ በነበረ የልምምድ ወቅት።

* የእገዳው ጊዜ፦ ከጁላይ 11 ቀን 2024 ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ይሆናል።
ከውጤቱ በስተጀርባ፦

አትሌቷ መጀመሪያ ላይ ጥፋተኛ አይደለሁም ብላ ብትከራከርም፣ የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) ባቀረበው ዝርዝር ማስረጃና የላቦራቶሪ ውጤት መሠረት፣ በመጨረሻም ማርች 13 ቀን 2026 ጥፋቷን አምና የቅጣት ቅጹን ፈርማለች።

የ40 ዓመቷ አትሌት ናንሲ ጄላጋት፣ በ2021 የቫሌንሲያ ማራቶንን በ2:19.31 በሆነ የግል ምርጥ ሰዓቷ አሸንፋ እንደነበር ይታወሳል። አትሌቷ ቅጣቷን ጨርሳ በመጪው ክረምት ወደ ውድድር እንደምትመለስ ይጠበቃል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nancyjelagat #athleticsnews #dopingban #kenyaathletics #aiu #breakingnews #sportsupdate #marathon #valenciamarathon

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.