Logo
EBC
19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
*************

638 አትሌቶች የተሳተፉበት 19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

መነሻ እና መድረውሻን መስቀል አደባባይ ባደረገው ውድድሩ 455 ወንዶች እና 183 ሴቶች በድምሩ 638 ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብስራት ለጥይበሉ የውድድሩ ዓላማ በዴንማርክ ኮፐንሀገን ለሚካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ለመምረጥ እና ተተኪዎች ለማፍራት ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የፌዴሬሽኑ ውድድር እና ተሳትፎ ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ጊዜ አድነው በበኩላቸው የውድድር ኮርስ ካርታ ላይ ያበራሩ ሲሆን ከ1-6 ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች የገንዘብ፣ ሜዳልያ እና የዋንጫ ሽልማት እንደሚበረከተላቸው በማንሣት ውድድሩ ከአምናው 434 አትሌቶች ቁጥር ጭማሬ ማሳየቱን መናገራቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#ethiopia #ebc #athletics #marathon #halfmarathon

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.