አዲሱ ጎበና የሲድኒ ማራቶን አዲስ የቦታው ክብረወሰን በማስመዝገብ አሸነፈ
#ethiopia | በዓለም አትሌቲክስ የሜጀር ማራቶን ደረጃ በተሰጠው የሲድኒ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት አዲሱ ጎበና የበላይነቱን በመቀዳጀት አሸናፊ ሆኗል።
ለ24ኛ ጊዜ በተካሄደው በዚህ ታላቅ ውድድር አዲሱ ጎበና ርቀቱን በ2 ሰዓት 04 ደቂቃ ከ42 ሴኮንድ በሆነ ፈጣን ጊዜ በመጨረስ የቀደመውን የስፍራውን ታሪክ በማሻሻል አዲስ ክብረወሰን አስመዝግቧል።
አትሌቱ በባለፈው ዓመት የሲድኒ ማራቶን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን፣ ዘንድሮ ግን ሰዓቱን ከአንድ ደቂቃ በላይ በማሻሻል አሸንፏል።
በሌላ በኩል አትሌት ጭምዴሳ ደበሌ በ2 ሰዓት 04 ደቂቃ ከ46 ሴኮንድ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ፣ አትሌት ጀማል መኮንን ደግሞ አምስተኛ ወጥቷል።
የባለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊና የቦታው ክብረወሰን ባለቤት የነበረው አትሌት ኃይለማሪያም ኪሮስ ስድስተኛ፣ አትሌት ዳዊት ወልዴ ደግሞ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በሴቶች መካከል በተደረገው ፉክክር ኬንያዊቷ አትሌት ፔሬስ ጄፕቺርቺር በ2 ሰዓት 18 ደቂቃ ከ31 ሴኮንድ በመግባት የመጀመሪያዋ ሆናለች።
ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ሹሬ ደምሴ፣ ሄቨን ኃይሉ እና መሰረት አበባየሁ ከሶስተኛ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቅቀዋል።
#ethiopia #athlete #athletics #marathon #marathonmajors #sydneymarathon #sports #ebc #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago