3 months ago
u1240u120bu120d u1218u1295u1308u12f5 u12a0u12edu12f0u1208u121d ud83dudc49 https://youtu.be/HF5C_zxPE...
ቀላል መንገድ አይደለም 👉 https://youtu.be/HF5C_zxPE...
4 months ago
የተከለከለ ንጥረ መድሃኒት በመጠቀሟ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለአራት ወራት ከውድድር ታገደች
የአትሌቲክስ ስነ ምግባር ክፍል (AIU) ባለ ሁለት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮና እና የኦሎምፒክ ሜዳሊያ ባለቤቷ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ላይ የ4 ወራት እገዳ መጣሉን ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ አደረገ።
ይህ እገዳ እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
የእገዳው መንስኤ ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ከተወሰደባት የሽንት ናሙና ላይ ‘ሌትሮዞል’ የተባለ የተከለከለ ንጥረ ነገር በመገኘቱ ነው።
አትሌቷ ክሱ በደረሳት ማግስት ንጥረ ነገሩ ለታመመችው ህክምና በሀኪም የታዘዘላት መሆኑን የሚያሳይ ሙሉ የህክምና ሰነድ አቅርባለች።
የዓለም አትሌቲክስ የህክምና ኮሚቴ ጉዳፍ ህክምናው እንደሚያስፈልጋት ቢያረጋግጥም፣ ከዓለም ፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) አስቀድማ የህክምና ፈቃድ (TUE) ሳታስፈቅድ በመቅረቷ የላቀ ኃላፊነት ህግን ተላልፋለች ብሏል።
ይሁን እንጂ አትሌቷ ሆን ብላ ያደረገችው አለመሆኑ በመረጋገጡ እና ጥፋቱን በፍጥነት በመቀበሏ፣ ሊጣልባት ይችል የነበረው የሁለት ዓመት ቅጣት ወደ አራት ወራት ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
Seledadotio

አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ እና አትሌት ዘመናይ አያና የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት መፈፀማቸው በመረጋገጡ ቅጣት ተጣለባቸው።
አትሌት ጉዳፍ ፀጋየ እና አትሌት ዘመናይ አያና ቀደም ሲል በተደረጉ የአበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ምርመራዎች የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ በመጠቀም ተጠርጥረው ጉዳያቸው ሲጣራ ቆይቷል።
በዚህም መሰረት የአለም አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት(AIU) እ.ኤ.አ ዲሴምበር 05 ቀን 2025 ዓ.ም ከውድድር ጊዜ ውጭ ባካሄደው ምርመራ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ‘ሌትሮዞል’ (Letrozole) የተባለውንና በማንኛውም ጊዜ እንዳይሰድ የተከለከለውን መድኃኒት ተጠቅማ መገኘቷ ተረጋግጧል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ባለፉት ጊዜያት ጉዳዩ ሲታይ የቆየ ሲሆን የአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) እና የአለም አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) ከአትሌቷ ጋር በተፈጠረ የጋራ ስምምነት (Case Resolution Agreement) በአትሌቷ ላይ እ.ኤ.አ ከሰኔ 01/2026 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2026 ዓ.ም የአራት (4) ወር እገዳ (Period of Ineligibility) ቅጣት ተጥሏል፡፡ በተጨማሪም አትሌቷ እ.ኤ.አ ከዲሴምበር 5/2025 ዓ.ም ጀምሮ ያስመዘገበቻቸው የውድድር ውጤቶች በሙሉ እንዲሰረዙ፣ ሜዳሊያዎች እና የገንዘብና ሌሎችም ሽልማቶች እንዲመለሱ ተወስኗል። የህግ ጥሰቱ የተፈፀመው ከአትሌቷ ጤንነት ጋር በተያያዘ በተሰጠ የህክምና ፈቃድ አገልግሎት (Therapeutic Use Exemption) እንደሆነ የተመላከተ ሲሆን የተሰጠው ውሳኔም ይግባኝ የማይቀርብበትና የመጨረሻ ውሳኔ መሆኑ ታውቋል።
በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-ADA) በአትሌት ዘመናይ አያና ላይ እ.ኤ.አ
ግንቦት 4/2025 ዓ.ም ከውድድር ጊዜ ውጪ ባካሄደው የአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራ አትሌቷ 'የአናቦሊክ አንድሮጄኒክ ስቴሮይድ’ (Testosterone) ንጥረ ነገር ተጠቅማ መገኘቷ ታውቋል፡፡ ይህንንም መነሻ በማድረግ ባለፉት ጊዜያት በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ምርመራ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን አትሌቷ ጥፋተኛ መሆኗ በመረጋገጡ ጊዜያዊ እገዳ ከተጣለበት እ.ኤ.አ ከጥር 21/2026 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 22/2030 ዓ.ም ድረስ ለአራት (4) ዓመታት በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ እንዳትሳተፍ እገዳ (Period of Ineligibility) ተጥሎባታል፡፡ በተጨማሪም አትሌት ዘመናይ ምርመራ ከተደረገበት እ.ኤ.አ ከግንቦት 4/2025 ዓ.ም ጀምሮ ያስመዘገበቻቸው ማንኛውም የውድድር ውጤቶች፣ ሜዳሊያዎች እና የገንዘብ ሽልማቶች በሙሉ እንዲሰረዙና ተመላሽ እንዲሆኑ ተወስኗል።
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-ADA) አትሌቶችም ይሁን ሌላ ማንኛውም አካል የስፖርቱን ደህንነትና የአገርን ገጽታ ከሚያበላሹ መሰል የአበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ወንጀሎች እንዲታቀቡና የግል ኃላፊነት (Strict Liability) መርህን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ በድጋሚ ያሳስባል። በየደረጃው የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥርም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን !!!

አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በዶፒንግ ምርመራ የአራት ወር እገዳ ተጣለባት
#fastmereja | የዓለም 5,000 እና 10,000 ሜትር የቀድሞ ሻምፒዮን አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣ በዶፒንግ ምርመራ ወቅት በሰውነቷ ውስጥ "ሌትሮዞል" የተባለ ንጥረ ነገር በመገኘቱ የአራት ወር እገዳ ተላልፎባታል።
እንደ አትሌቲክስ ዊክሊ ዘገባ በአትሌቷ የተገኘው ንጥረ ነገር የታዘዘላትን የህክምና ችግር ለመቆጣጠር ትጠቀምበት የነበረ መሆኑን በማስረጃ ማቅረቧን ተከትሎ፣ የዓለም አትሌቲክስ ጥብቅና ክፍል (AIU) ከረዥም ጊዜ ቅጣት ይልቅ የአራት ወር እገዳን እንዲወስን ስምምነት ላይ ተደርሷል።
የ29 ዓመቷ አትሌት ጉዳፍ፣ ይህን ተከትሎ የ2026 የውድድር ዓመትን የትራክ ውድድሮች በሙሉ እንደማትሳተፍ ተገልጿል።
የአትሌቲክስ ጥብቅና ክፍሉ ባወጣው መግለጫ፣ ጉዳፍ ምርመራው መገኘቱን አምና Case Resolution Agreement እንደፈረመች አስታውቋል።

7 months ago
አትሌቷ እገዳ ተጣለባት
ኬንያዊቷ ናንሲ ጄላጋት ሜቶ የተከለከለ አቅምን የሚያጎለብት ንጥረ ነገር ተጠቅማ በመገኘቷ ለሁለት ዓመታት ታገደች።
ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ናንሲ ጄላጋት ሜቶ በኬንያ ውስጥ ከውድድር ውጭ በተደረገላት የልምምድ ወቅት ምርመራ 'ፉሮሴማይድ' የተባለ የተከለከለ አቅምን የሚያጎለብት ንጥረ ነገር ተገኝቶባታል።
በወቅቱ ዕድሜዋ 38 ዓመት የነበረ ሲሆን፤ እንደ ሌሎች ኤሊት አትሌቶች ሁሉ እሷም በአለም አቀፍ የክትትል ዝርዝር ውስጥ ትገኝ ነበር።
ከሦስት ዓመታት ገደማ በኋላ የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) ትናንት በሰጠው መግለጫ የምርመራ ዝርዝር ሂደትን ካብራራ በኋላ ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ የሁለት ዓመት የዕገዳ ቅጣት ሊጥልባት ችሏል።
ምርመራው ከተደረገ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ጁን 22 የኬንያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ የአትሌቷ ናሙና ተልኮበት ከነበረው በሉዛን ከሚገኘው የዓለም የፀረ-አበረታች ቅመሞች ላቦራቶሪ ውጤቱን ካገኘ በኋላ፤ አትሌቷ የተከለከለ ንጥረ ነገር እንደተገኘባት አሳወቃት።
በመቀጠልም ኃላፊነቱ ወደ አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) የተዛወረ ሲሆን፤ ተቋሙም ኦገስት 21 የተገኘውን የላቦራቶሪ ውጤት ለሜቶ አሳወቃት። እሷም ውጤቱን ያስተባበለች ሲሆን፤ በደል እንደተፈጸመባትም ተከራክራለች።
በሴፕቴምበር ወር መጨረሻ ላይ ሜቶ "የመጀመሪያው ማሳወቂያ አልደረሰኝም በማለቷ (ምንም እንኳን ማሳወቂያው የተላከው እሷ ራሷ መልዕክት እየላከችበት ባለው የኢሜይል አድራሻ ቢሆንም)፤ AIU ጉዳዩን መልሶ ለኬንያው ADAK መርቶታል። የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በጉዳዩ ውስጥ ጣልቃ በመግባቱ ይፋዊ መግለጫው እንዲዘገይ አድርጓል።
እንደ ጋዜጣዊ መግለጫው ከሆነ AIU ለአትሌቷ የቢ (B) ናሙና ምርመራ እንዲደረግላት የመጠየቅና የተገኘውን የላቦራቶሪ ውጤት የሚያረጋግጡ የሰነድ ጥቅሎችን የማግኘት ተጨማሪ ዕድል ሰጥቷታል።
በተጨማሪም አትሌቷ በጉዳዩ ላይ እንዴት መቀጠል እንደምትፈልግ እንድታረጋግጥ፤ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ደንብ ጥሰቱንና የቀረበባትን ቅጣት እንድትቀበል፤ ወይም በስፖርት የግልግል ዳኝነት ችሎት ፊት ቀርባ እንድትከራከር ዕድል ተሰጥቷት ነበር።
ማርች 13 ቀን 2026 AIU በአትሌቷ የተፈረመ የደንብ ጥሰቱን አምኖ የመቀበልና ቅጣቱን የመቀበያ ቅጽ ደርሶታል። በዚህም መሰረት የእርሷ እገዳ ከጁላይ 11 ቀን 2024 ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ይሆናል።
አሁን ዕድሜዋ 40 ዓመት የደረሰው ይህች አትሌት በመጪው ክረምት ወደ ውድድር ልትመለስ ትችላለች።
ናንሲ ጄላጋት ሜቶ የ2021 የቫሌንሲያ ማራቶን አሸናፊ እንደነበረች የሚታወስ ነው። በወቅቱ የገባችበት 2:19.31 በርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቷ ሆኖ ተመዝግቦላታል።
ምስጋናው ታደሰ

የቫሌንሲያ ማራቶን አሸናፊዋ ናንሲ ጄላጋት ሜቶ በዶፒንግ ታገደች
#ethiopia | የቀድሞዋ የቫሌንሲያ ማራቶን አሸናፊ ኬንያዊቷ ናንሲ ጄላጋት ሜቶ፣ የተከለከለ አበረታች ንጥረ ነገር (Doping) ተጠቅማ በመገኘቷ የሁለት ዓመት የእገዳ ቅጣት ተጣለባት።
የቅጣቱ ዝርዝር ሁኔታ፦
* የተገኘው ንጥረ ነገር፦ ‘ፉሮሴማይድ’ (Furosemide) የተባለ የአቅም ማጎልበቻ።
* ምርመራው የተደረገበት ወቅት፦ ሰኔ 2016 ዓ.ም. በኬንያ በነበረ የልምምድ ወቅት።
* የእገዳው ጊዜ፦ ከጁላይ 11 ቀን 2024 ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ይሆናል።
ከውጤቱ በስተጀርባ፦
አትሌቷ መጀመሪያ ላይ ጥፋተኛ አይደለሁም ብላ ብትከራከርም፣ የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) ባቀረበው ዝርዝር ማስረጃና የላቦራቶሪ ውጤት መሠረት፣ በመጨረሻም ማርች 13 ቀን 2026 ጥፋቷን አምና የቅጣት ቅጹን ፈርማለች።
የ40 ዓመቷ አትሌት ናንሲ ጄላጋት፣ በ2021 የቫሌንሲያ ማራቶንን በ2:19.31 በሆነ የግል ምርጥ ሰዓቷ አሸንፋ እንደነበር ይታወሳል። አትሌቷ ቅጣቷን ጨርሳ በመጪው ክረምት ወደ ውድድር እንደምትመለስ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nancyjelagat #athleticsnews #dopingban #kenyaathletics #aiu #breakingnews #sportsupdate #marathon #valenciamarathon

10 months ago
ለመመዝገብ ፍላጎት ላላችሁ‼️
በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተመርቃችሁ ለመምህርነት ሙያ ማመልከት ለምትፈልጉ
ቀደም ሲል በወጣው መመልመያ መስፈርት መሰረት ለመመዝገብ የምትፈልጉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶችና ተዛማጅ የትምህርት መስኮችን በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት ላይ በዚህ ሊንክ https://shorturl.at/ORED9 በመግባት “የትምህርት ዓይነትና ተዛማች የትምህርት መስኮች” የሚለውን download በማድረግ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ገልጸን፤ የ5 ዩኒቨርስቲዎችን የመመዝገቢያ ሊንኮች ማሳወቃችን ይታወሳል፤
ከተገለጹት 5 ዩኒቨርስቲዎች በተጨማሪ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ መመዝገብ የሚቻል ሲሆን ለመመዝገብ የምትፈልጉ አመልካቾች በዚህ ሊንክ https://docs.google.com/fo... በመግባት መመዝገብ ትችላላችሁ።
seledadotio

12 months ago
የአትሌቷ ቅጣትና የሪከርዱ ጉዳይ እንዴት ይሆናል?
(ምስጋናው ታደሰ)
#ethiopia | Hydrochlorothiazide (ሀይድሮክሎራይዝድ) HCTZ የተባለ የተከለከለ አበረታች ንጥረ ነገር መጠቀሟ የተረጋገጠባት ኬንያዊቷ የሴቶች ማራቶን የዓለም ሪከርድ ባለቤት ሩት ቼፕንጌቲች የሶስት ዓመታት እገዳ እንደተጣለባት The Athletics Integrity Unit (AIU) ዛሬ (ሐሙስ) ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ገልጬ ፅፌያለሁ።
ይህንን ተከትሎም የሪከርዱ ጉዳይ እንዴት ይሆናል? ለቀድሞዋ የሪከርዱ ባለቤት ትዕግስት አሰፋ ይመለሳል ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱ ይገኛሉ።
እናስ?
እናማ ሪከርዱ ወደ ትዕግስት አይመለስም፤ ከሩት ቼፕንጌቲች ጋር ይቆያል።
እንዴት ይህ ሊሆን ቻለ?
የ31 ዓመቷ ኬንያዊት "ሀይድሮክሎራይዝድ" የተባለውን የተከለከለ ንጥረ ነገር መውሰዷ የተረጋገጠባት ማርች 14/2025 በተደረገላት የደምና የሽንት ምርመራ ነው። በመሆኑም ከዛን ጊዜ አንስቶ ጊዜያዊ እገዳ ተጥሎባት የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የሶስት ዓመት እገዳ ተጥሎባታል።
የAIU ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ብሬት ክሎዚዬ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት እገዳው የሚፀናባት ምርመራው ከተደረገላት ከማርች 2025 ወዲህ መሆኑንና ከዛ በፊት የነበሩት ውጤቶቿ የዓለም ሪከርድን ጨምሮ በእጇ እንደሚቆዩ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ስለዚህ ሪከርዱ ወደ ትዕግስት አሰፋ አይመለስም።
ይሁንና ይሄ እስከ መጨረሻው የሚፀና ውሳኔ ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም ይሄኛው ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ AIU ወደኋላ ተመልሶ በአትሌቷ ላይ ተጨማሪ ምርመራዎችን ጀምሯል።
ለምሳሌ በምርመራው ወቅት ቃለ-ምልልስ ሲደረግላት "ባመመኝ ሰዓት ይሄንን ሀይድሮክሎራይዝድ ጨምሮ ሌሎችንም የባህል መድሃኒቶችን የምትሰጠኝ የቤት ሰራተኛዬ ናት" የሚል ቃል ሰጥታለች። በዚህም ሰራተኛዋም ምርመራ እየተደረገባት ነው።
ቼፕንጌቲች "Rosa Associati" በተባለው የአትሌቲክስ ማኔጅመንት ስር ነው የምትወዳደረው። የዚህ ኩባንያ ባለቤት ጣልያናዊው ፌዴሪኮ ሮሳ (በ2ኛው ፎቶ የሚታየው) ነው።
ይህ ሰው ከ30 በላይ ስመጥር ኬንያውያን አትሌቶችን በስሩ የሚያስተዳድር ሲሆን ከዶፒንግ ጋር በተያያዘ ለቅጣት ከሚዳረጉት በርካታ የሀገሪቱ አትሌቶች መካከልም አብዛኛዎቹ በእሱ ስር የሚወዳደሩ ናቸው። የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከኦገስት 2025 አንስቶ እገዳ ጥሎበታል። ይህንን ተከትሎም እሱም በAIU ምርመራ እየተደረገበት ነው።
ይህም ብቻ ሳይሆን የቼፕንጌቲች የሞባይል ስልክ ላይም ምርመራ እየተደረገ ነው። አትሌቷ መጀመሪያ ላይ ሞባይሏን ላለማስፈተሽ አንገራግራ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ግን ተስማምታለች። ከፌዴሪኮ ሮሳ ጋር የተፃፃፈቻቸው መልዕክቶች እና የመድሃኒት ፎቶዎች እየተመረመሩ ነው።
የእነዚህ ምርመራ ገና በሂደት ላይ ነው። ወደ ኋላ ተሂዶ እየተደረገ ባለው ምርመራና የመጨረሻ ውጤት ከዚህ በፊትም ዶፒንግ ትወስድ እንደነበር ከተረጋገጠባት ሪከርዱን ልትነጠቅና ለትዕግስት አሰፋ ሊመለስላት ይችላል።

Sponsored by
Surafel
1 year ago
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በድርቤ ወልተጂ ዙሪያ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በህግ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት በስፖርት ውድድር ወቅትና ከውድድር ጊዜ ውጭ የአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራ የሚያካሂድ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት የምርመራ እቅድ(TDP) በማዘጋጀት እ.ኤ.አ የካቲት 25/2025 ለአትሌት ድርቤ ወልተጅ ከውድድር ጊዜ ውጭ ምርመራ (Out of Competition Test) ለማካሄድ ሙከራ ያደረገ ሲሆን ሳይሳካ ቀርቷል።
ምርመራውም የተደናቀፈው አትሌቷ ፍቃደኛ ሳትሆን በመቅረቷና በምርመራ ባለሞያዎች (Sample Collection Personnel) ላይ ጫና በመደረጉ ምክንያት እንደሆነ መገንዘብ ተችሏል።
ይህንንም መሰረት በማድረግ ጉዳዩን በጥልቀት በማጣራት ነፃና ገለልተኛ በሆነ የዳኝነት አካል (Hearing Panel) እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ባለስልጣን መ/ቤቱ ያለውን መረጃና ማስረጃ በማቅረብ በአትሌቷ ላይ አግባብነት ያለው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተከራክሯል፡፡
ይሁን እንጅ የዳኝነት አካሉ ግራ ቀኙን ማለትም አትሌቷንና የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣንን በማከራከር በህግ አግባብ ትክክል ነው ብሎ ያመነበትን ውሳኔ ወስኗል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱም እንደ ከሳሽ አካል በውሳኔው ደስተኛ ባይሆንም በአለም አቀፉ ህግ መሰረት ውሳኔውን በመቀበል ለአትሌቷ እንዲሁም ለአለም አቀፍ ተቋማት አሳውቋል፡፡
ከዚህም በመነሳት የአለም አትሌቲክስ የኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) ጉዳዩን በተለይም የቀረቡትን ሰነዶችና ሌሎችንም መረጃዎች በመመርመር ለአለም አቀፉ የስፖርት ግልግል ፍ/ቤት (CAS) ይግባኝ አቅርቧል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በማንኛውም ደረጃ በሚፈፀሙ የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ ለማስቻል በትኩረት የሚሰራ መሆኑን እየገለፅን በአትሌት ድርቤ ወልተጅ ጉዳይ ላይም አግባብነት ያለው ፍትኃዊ ውሳኔ እንዲወሰን አስፈላጊውን ድጋፍና ያላሳለሰ ጥረት ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን ያረጋግጣል ያለው ኤ ኤም ኤን ነው፡፡

አትሌት ድርቤ ወልተጂ ከውድድሩ ውጪ ሆነች
ኢትዮጵያን በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በ 1500ሜ ለመወከል ተመርጣ የነበረችው አትሌት ድርቤ ወልተጂ ከውድድሩ ውጪ መሆኗ ተገልጿል።
አትትሌቷ ከውድድሩ ውጪ የሆነችው ሊደረግላት የነበረውን የአበረታች ንጥረነገር ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኗ መሆኑ ተነግሯል።
አትሌቶች አበረታች ዕፅ መጠቀም አለመጠቀማቸውን የሚቆጣጠረው "The Athletics Integrity Unit (AIU)" የዶፒንግ ምርመራ እንድትሰጥ ቢጠይቃትም ፈቃደኛ አለመሆኗ ተገልጿል።
ይህንንም ተከትሎ " AIU " አትሌቷ ከቶኪዮው የዓለም ሻምፒዮና ውጪ እንድትሆን ለዓለም አቀፉ የስፖርት ጉዳዮች ግልግል ችሎት (Court of Arbitration for Sport (CAS) ክስ አቅርቧል።
የክሱ ውሳኔው በዓለም አቀፉ የስፖርት ጉዳዮች ግልግል ችሎት የታወቀ ሲሆን አትሌት ድርቤ ወልተጂ ከውድድሩ ውጪ መሆኗ ታውቋል።
በርቀቱ ሁለተኛ ምርጥ ሰዓት ባለቤት የሆነችው አትሌቷ ለኢትዮጵያ ሜዳልያ ያስገኛሉ ተብለው ከሚጠበቁ አትሌቶች አንዷ ነበረች።
ምንጭ :- ጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ

Comments