Logo
Getu Temesgen
በተለያዩ የጎዳና ውድድሮች በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

በዛሬው ዕለት በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊነትን ጨምሮ የመድረክ ላይ ውጤቶችን አስመዝግበዋል።

በኖርዌይ በተካሄደው የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር አቡዱሰላም ወርቁ 3ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ፣ በተመሳሳይ ሀገር በተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር ቢኒያም መላክ 27:29 በሆነ ሰዓት በመግባት የውድድሩን ድል አስመዝግቧል።

በሮማኒያ በተካሄደው የብራዞቭ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ካህሪ ቤጂጋ አሸናፊ ሲሆን፣ ንብረት ክንዴ 2ኛ እና ዘነበ አየለ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።

በሴቶች ውድድር ደግሞ አሰፉ አብርሃ 1ኛ ስትወጣ፣ አይናዲስ መብራቱ 2ኛ እና የኔነሽ ሽመክት 3ኛ ደረጃን አግኝተዋል።

በስፔን አልባሴቴ ግማሽ ማራቶን ከይሩ ከድር የወንዶችን ውድድር አሸንፏል። በሴቶች ደግሞ ሲሳይ እሸቱ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

በእንግሊዝ የካርዲፍ ግማሽ ማራቶን የባለፈው ዓመት አሸናፊ የነበረው ይስማው ድሉ በዚህ ዓመት 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በሴቶች ውድድር ደግሞ ውዴ ከፋለ 2ኛ፣ ትግስት ከተማ 3ኛ ደረጃን አግኝተዋል።

በፖላንድ የፓዝናን ማራቶን ባሬቻ ቶሎሳ አሸናፊ ሆኗል። በሴቶች ውድድር ብርቱካን አበራ 2ኛ እና ትግስት ቢቂላ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።

በስሎቫኪያ ኮዜክ ማራቶን አበራሽ ፈይሳ የሴቶችን ውድድር አሸንፋለች።

በጀርመን ኮሎኝ ማራቶን በወንዶች ሀብታሙ ብርሌው 2ኛ ደረጃን ሲይዝ፣ በሴቶች ፋንቱ ሹጌ 2ኛ እና አያንቱ ኩሜላ 3ኛ ደረጃን አግኝተዋል።

በተለያዩ ሀገራት በአንድ ዕለት የተመዘገቡት እነዚህ ውጤቶች፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በጎዳና ላይ ውድድሮች ያላቸውን ተወዳዳሪነት እንደገና ያሳዩበት ነው።
#ethiopia #ethiopianathletics #running #marathon #getutemesgen

1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.