2 days ago
በአሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የአማዞን ሶፍትዌር መሐንዲስ በሌክ ታሆ በውሃ አደጋ ሕይወቱ አለፈ
#ethiopia | በአሜሪካ የቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚሠራው የ32 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ የአማዞን (Amazon) ሶፍትዌር መሐንዲስ ያዴሳ እሚሩ አጋ (Yadessa Emiru Aga) በካሊፎርኒያና ኔቫዳ ድንበር በሚገኘው ታዋቂው ሌክ ታሆ (Lake Tahoe) በውሃ አደጋ ሕይወቱ ማለፉን የአሜሪካ የዜና አውታሮች ዘግበዋል።
በሪፖርቶቹ መሠረት፣ አደጋው እ.ኤ.አ. ጁላይ 27 ቀን 2026 በሌክ ታሆ ምስራቃዊ ዳርቻ በሚገኘው ሳንድ ሃርበር (Sand Harbor) ተከስቷል።
ያዴሳ ወደ ሀይቁ ውስጥ ከገባ በኋላ ድንገት ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቶ በውሃ ውስጥ ጠልቆ መታየቱ ተገልጿል።
በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በፍጥነት ወደ ዳርቻ ቢያወጡትም፣ የፖሊስና የሕክምና ቡድኖች ያደረጉት የሕይወት ማዳን ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
የዋሾ ካውንቲ ሸሪፍ መሥሪያ ቤት ክስተቱን እንደ "በአጋጣሚ የተከሰተ የመስጠም አደጋ" እየመረመረው ሲሆን፣ የሞት ትክክለኛ መንስኤ በሕክምና ምርመራ ውጤት እንደሚገለጽ ተነግሯል።
ከአደጋው በኋላ ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ የመጨረሻ ሰዓቶቹ ምን እንደነበሩ ለማወቅ ጥረት እያደረጉ ነው።
በተለይም በአደጋው ወቅት በሳንድ ሃርበር የነበሩ ሰዎች ያነሱትን ፎቶ፣ ቪዲዮ ወይም የዓይን እማኝነት መረጃ እንዲያጋሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በተመሳሳይ ወደ ኢትዮጵያ የአስከሬን መጓጓዣና የቀብር ወጪ ለመሸፈን የGoFundMe የድጋፍ ዘመቻ መጀመሩም ተዘግቧል።
የያዴሳ የLinkedIn መረጃ እንደሚያሳየው፣ ከ2022 ጀምሮ በአማዞን የሶፍትዌር ልማት መሐንዲስ (Software Development Engineer) በመሆን በአውስቲን፣ ቴክሳስ ይሠራ ነበር። ከዚያ በፊትም በአዲስ አበባ በሶፍትዌር ልማት ዘርፍ ሰርቶ እንደነበር ተገልጿል።
ባለሙያዎች ሌክ ታሆ በግልጽ ውሃና በውብ ተፈጥሮው ቢታወቅም፣ የውሃው ከፍተኛ ቀዝቃዛነት በድንገት የሰውነት ምላሽን በመቀየር ለመስጠም አደጋ እንደሚያጋልጥ ያስጠነቅቃሉ።
በዚህ ሀይቅ በየዓመቱ በአማካይ 6 እስከ 7 የመስጠም አደጋዎች እንደሚመዘገቡም ተጠቁሟል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

5 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ባለፈው ሳምንት በሌክ ታሆ ውስጥ ሰጥሞ ህይወቱ ያለፈው ኢትዮጵያዊው የአማዞን ሶፍትዌር መሃንዲስ ጓደኞች፣ በህይወቱ የመጨረሻ ደቂቃዎች ውስጥ በትክክል ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ የአይን እማኞች መረጃ በመስጠት እንዲተባበሯቸው ጥሪ አቀረቡ።
የ32 ዓመቱ የኦስቲን ቴክሳስ ነዋሪ የሆነው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ያደሳ እምሩ አጋ፣ ጁላይ 27 ቀን በኔቫዳ የባህር ዳርቻ በሚገኘው ሳንድ ሀርበር አቅራቢያ ውሃ ውስጥ እያለ ራሱን ስቶ ነበር። በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ወደ ዳርቻው ያወጡት ሲሆን፣ ፖሊሶች እና የህክምና ባለሙያዎች ህይወቱን ለመታደግ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
የዋሾ ካውንቲ ፖሊስ ሞቱን እንደ ድንገተኛ የውሃ ውስጥ የመስመጥ አደጋ እየመረመረው ይገኛል። ሆኖም የካውንቲው የህክምና መርማሪ የመጨረሻውን የሞት ምክንያት እስካሁን ይፋ ስላላደረገ፣ የያደሳ ጓደኞች እና ዘመዶች በውሃው ውስጥ በትክክል ምን እንደተፈጠረ ግልጽ የሆነ መረጃ ለማግኘት እየጣሩ ነው።
በሬዲት ላይ ራሱን የሟች የቅርብ ጓደኛ መሆኑን የገለጸ ግለሰብ፣ በዚያ ምሽት ሳንድ ሀርበር የነበረ ማንኛውም ሰው ፎቶግራፎችን፣ ቪዲዮዎችን ወይም በአካል የተመለከተውን መረጃ እንዲያካፍል ጠይቋል።
እንደ ጸሃፊው ገለጻ ያደሳ ጀምበር ልትጠልቅ ስትል ከሌሎች ጋር እየዋኘ እንደነበር እና ከዚያም ከውሃው ውስጥ የድረሱልኝ ጩኸት እንደተሰማ የአይን እማኞች ተናግረዋል። ሁለት ጓደኞቹ እሱን ለማዳን ሲሞክሩ እንደተቸገሩ እና በፓድል ቦርድ ላይ የነበሩ ሰዎች ሶስቱንም ዋናተኞች ወደ ዳርቻው ለማውጣት እንደረዱ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ደግሞ የያደሳ የሊንክድኢን ፕሮፋይል ፎቶግራፍ ታችኛው ግራ ጥግ ላይ በትንሽ ፊደላት "አዝናለሁ !!!!!" (I am Sorry !!!!!) የሚል ጽሑፍ መገኘቱ ብዙዎችን አነጋግሯል። ይህ ጽሑፍ የሚታየው ምስሉ ሲጎላ ብቻ መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ እንቆቅልሽ አድርጎታል።
ለሟች መታሰቢያ የተከፈተው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ገጽ (GoFundMe) እንዳስነበበው፣ ያደሳ ከቤተክርስቲያን ኮንፈረንስ እየተመለሰ በሌክ ታሆ ከጓደኞቹ ጋር ጊዜ እያሳለፈ በነበረበት ወቅት አደጋው ያጋጠመው እጅግ መንፈሳዊ ወጣት ነበር። በደግነቱ፣ በሞቅታው እና በለጋስነቱ የሚታወቅ መሆኑን የገለጸው ማሰባሰቢያው፣ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለቀብር ስነ-ስርዓት እና አስከሬኑን ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ ለመመለስ እንደሚውል አስታውቋል።

17 days ago
ለሰባት ጊዜ ቀዶ ጥገና የተደረገለት የሦስት አመት ህፃን ልጅ ጉዳይ ትኩረት ስቧል
#ethiopia | በእንግሊዝ በአንድ መካነ አራዊት ውስጥ በአዞ ጥቃት የደረሰበት የሦስት ዓመት ሕፃን ልጅ በሂወት መኖሩ አስገራሚ ሆኗል።
ለህፃኑ ህክምና እና ማገገሚያ እንዲረዳውም በስሙ በተከፈተ
ጎ ፈንድሚ እስካሁን ድረስ ከ100,000 ፓውንድ በላይ ገንዘብ ተሰብስቧል።
የሦስት ዓመቱ ሕፃን የአዞ ማቆያ ውስጥ ከገባ በኋላ በአዞ ጥቃት ደርሶበት ለከፍተኛ ህክምና ሆስፒታል ገብቶ ነበር።
የሕፃኑ ቤተሰቦች እንደገለጹት ልጃቸው እስከ አሁን ድረስ ለሰባት ጊዜ ያህል ቀዶ ጥገና የተደረገለት ሲሆን አሁን ግን ሁኔታው እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል።
ለቤተሰቡ ድጋፍ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ገጽ (GoFundMe) የተከፈተ ሲሆን እስካሁን ከ105,000 ፓውንድ በላይ ተሰብስቧል።
የተሰበሰበው ገንዘብ የሕፃኑን የረጅም ጊዜ ህክምና ማገገሚያ እና ቤተሰቡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከሥራቸው ርቀው ከልጃቸው ጋር በመቆየታቸው ያለባቸውን ወጪ ለመሸፈን ነው ተብሏል።
የህፃኑ ወላጆች ሕዝቡ ላሳያቸው ድጋፍና ርህራሄ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #englandboyinjuredcrocs #huntingdoncambridgeshire

26 days ago
Sponsored by
Surafel
2 months ago
"የሕክምና ልብሴ ልጄን ከስቃዩ አልሸፈነልኝም"
ውድ ኢትዮጵያውያን፣
#ethiopia | ዶ/ር የሮም ጌታቸው እባላለሁ። ከስድስት ዓመት በላይ በህክምና ሙያ ውስጥ ሕሙማንን በማከም፣ የተሰበሩ ቤተሰቦችን በማጽናናት እና ለብዙዎች ተስፋ በመሆን ኖሬያለሁ። በስራዬ ምክንያት ብዙ ወላጆች በልጆቻቸው አልጋ አጠገብ ሲያለቅሱ አይቻለሁ፣ ብዙ ሰዎች ሕይወትን ለማትረፍ ሲታገሉ ተመልክቻለሁ።
ዛሬ ግን ያ አባት እኔ ሆኛለሁ።
የ3 ዓመት ከ6 ወር ህፃን ልጄ በአጥንት ካንሰር ተጠቅቶ ከባድ የህክምና ፈተና ውስጥ ይገኛል። በየቀኑ ህመሙን ሲታገል ማየት፣ የልጄን ስቃይ እያየሁ ምንም ማድረግ አለመቻሌ ልቤን ይሰብረዋል።
እንደ ሀኪም የበሽታውን ስም አውቃለሁ። እንደ አባት ግን የልጄን ህመም እሸከማለሁ።
ልጄ ሕይወቱን ለማትረፍ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ ልዩ የአጥንት ቀዶ ጥገና እና ተከታታይ ህክምና ማድረግ ያስፈልገዋል። ለዚህም ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተጠይቆብናል።
እኔ ሀኪም መሆኔ፣ ህዝቤን ለበርካታ አመታት በቅንነት ማገልገሌ ይህን ወጪ ለመሸፈን አላስቻለኝም።
በሀገራችን ያለው የጤና ስርዓት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈ ነው። የጤና ባለሙያዎች ሌት ተቀን የሕዝብ ሕይወትን ለማዳን ቢተጉም፣ የሚያገኙት ገቢ እና ድጋፍ ብዙ ጊዜ ከሚሸከሙት ኃላፊነት ጋር አይመጣጠንም። ሌሎችን የምናክም እጆቻችን፣ የራሳችንን ልጆች ለማዳን ሲያንሱ ማየት እጅግ ያማል።
የሕክምና ልብሴ ልጄን ከስቃዩ አልሸፈነልኝም። የዶክተርነት ማዕረጌም የልጄን ህመም አላስቆመውም። ዛሬ በፊታችሁ የቆምኩት እንደ ዶክተር ሳይሆን፣ ልጁን ለማጣት የሚፈራ አባት ሆኜ ነው።
ስለዚህ ውድ ወገኖቼ፣ ልጄ የመኖር እድል እንዲያገኝ፣ እና በድጋሚ ሳቁን እንድናይ በአቅማችሁ የምትችሉትን እርዳታ እንድታደርጉልኝ ከልብ እጠይቃለሁ።
ለእናንተ ትንሽ የሚመስለው አስተዋፅኦ ለልጄ ግን ሕይወት ሊሆን ይችላል።
"ሌሎችን ለማከም የቆምኩት እኔ፣ ዛሬ ግን የራሴን ልጅ ለማዳን የወገኖቼን እጅ እጠብቃለሁ።"
እግዚአብሔር የምታደርጉትን ቸርነት በብዙ ይክፈላችሁ።
ዶ/ር የሮም ጌታቸው
CBE - 1000149557982
Abay - 2091011011819814
Awash : 013201344371300
Tele birr: 0910119336
GoFundMe: https://www.gofundme.com/f...
[Share]

ለወንድማችን ፀጋዬ እንድረስለት
በቅርቡ የራሱንና የቤተሰቡን ሒወት ለመቀየር በትምህርት ምክንያት ወደ አሜሪካ የመጣዉ ወንድማችን ባልተጠበቀ ሁኔታ በice ኣካላት ተይዞ በሕግ ከለላ ዉስጥ ዉሏል። በዚህም ምክንያት እሱም ቤተሰቡም ከባድ የሆነ ጫና ዉስጥ ወድቀዋል።
ሆኖም የስቱደንት ቪዛውን ለማደስ እንቅስቃሴ ጀምሮ በነበረበት ጊዜ ስለሆነ ይህ ያጋጠመው ጠበቃ ቀጥሮ ጉዳዩን እስኪከታተል በነሱ ቁጥጥር ስር አውለውታል
። ነገር ግን ጠበቃ ቀጥሮ ለመከራከር የሚያስችል አቅም ስለሌለዉ ለእናንተ ደጋግ ኢትዮጵያዉን የእርዳታ እጃችሁን እንድትዘረጉለት በትህትና እንጠይቃለን
የgofundme link እና የወረቀት ማስረጃዎችን ከታች ኮሜንት ቦክስ ውስጥ አለ💚💚
ሼር በማድረግ ውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ጋር አድርሱልኝ Please

3 months ago
በአሰቃቂ አደጋ ለተቀጠፈው የናዖል ገመዳ ቤተሰቦች የገንዘብ ማሰባሰቢያ ጥሪ ቀረበ
#ethiopia | በአሜሪካ ካንሳስ ግዛት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ህይወቱ ለላለፈው ወጣት ናዖል ገመዳ የቀብር ስነ ስርዓት ማስፈጸሚያ እና ለተጎዱ ቤተሰቦቹ መደገፊያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ተጀምሯል።
ወጣት ናዖል ባለፈው አርብ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም (ሜይ 15 ማታ) ከስራ ወደ ቤቱ እየተመለሰ በነበረበት ወቅት በደረሰበት ከባድ የመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል።
ይህ የ31 ዓመት ወጣት ከባለቤቱ ሌንሳ አብዲሳ ጋር ከደንቢዶሎ ኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ አሜሪካ ካንሳስ ካቀና ገና አንድ ዓመት እንኳ ያልሞላው ሲሆን አዲስ ህይወት ለመመስረት እና ኑሮውን ለማስተካከል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ በነበረበት ወቅት ነው ይህ አሳዛኝ አደጋ የገጠመው።
ናዖል በትምህርቱም ሆነ በስራው ጠንካራ፣ ትልቅ ተስፋና ህልም የነበረው እንዲሁም የነርሲንግ ትምህርቱን ለመቀጠል እየተዘጋጀ የነበረ መልካም ወጣት እንደነበር የቅርብ ወዳጆቹ ይመሰክራሉ።
የቀብር ስነ ስርዓቱን ለማስፈጸም እና አስከሬኑን ወደ ሀገር ለመላክ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን የጎፈንድሚ (GoFundMe) የገንዘብ ማሰባሰቢያ ገጽ የተከፈተ ሲሆን ወዳጅ ዘመዶቹ እና የሟች ቤተሰቦች የተቻለዎትን ሁሉ በማድረግ ከጎናቸው እንዲቆሙ እና የበጎ አድራጎት ድጋፍ እንዲያደርጉ በፈጣሪ ስም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
https://gofund.me/21158cd8...
#kansas #gofundme #dembidolo #oromo #ethiopiancommunity #supportnaol #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ታምነች ፈይሳ እባላለሁ ዕድሜዬ 39 ዓመት ሲሆን ረጅም ታሪኬን በአጭር ጽሁፍ ለማቅረብ እሞክራለሁ።
በ21 ዓመቴ የኩላሊት ኢንፌክሽን በሽታ እንዳለብኝ የታወቀ ሲሆን በ23 ዓመቴ ትዳር ይዤ ህይወትን መኖር በጀመርኩበት ጊዜ በድንገት ሁለቱም ኩላሊቶቼ መስራት አቆሙ።
ላለፉት 15 ዓመታት የገንዘብ አቅም ኖሮኝ ሳይሆን በአንዳንድ ደጋግ ወገኖች ድጋፍ በኩላሊት እጥበት (በዲያሌሲስ) እስከ አሁን በህይወት አለሁ።
በእነዚህ ዓመታት በእጥበት ወቅት ለሞት የሚዳርጉ ሁኔታዎች ብዙ ጊዜ ያጋጠሙኝ የነበር ቢሆንም እግዚአብሔር ግን ደግፎኝ ዛሬ ደርሻለሁ።
በእነዚህ 15 አመታት፣ ለዳያሊስስ የሚያገለግለው ካቴተር ደም ስሩ ሲዘጋ እየተለወጠ መጀመሪያ ላይ አንገቴ ላይ ቀጥሎ ተራ በተራ ሁለት እጆቼ ላይ በመጨረሻ፣ እግሮቼ ላይ ተደርጎ ዲያሌሲሱ ሲሰራልኝ የቆየ ሲሆን ለረዥም ዓመታት ስለተሰራባቸው የደም ስሮቼ ተዘግተው ጥቅም ላይ መዋል ስላልቻሉ በአሁኑ ወቅት ሀኪሞቹ በጉበቴ ላይ ለማስቀመጥ የመጨረሻውን አማራጭ የሰጡኝ እና ይህም ለስድስት ወራት ብቻ ሊያገለግለኝ እንደሚችልና በህይወት ለመቆየት ያለኝ የመጨረሻ አማራጭ የንቅለ ተከላ ስራ ማሰራት እንደሆነ ገልጸውልኛል፡፡
በተጨማሪም ከዚሁ ጋር ተያይዞ የልብ ከባድ ህመምን ጨምሮ ሌሎች የጤና ችግሮች እያጋጠመኝ ይገኛል።
ወደ ውጭ አገር በመሄድ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ቀዶ ጥገና ሕክምና ለማድረግ የሚረዳ የቦርድ የምስክር ወረቀት እና አስፈላጊውን መረጃዎች ሰጥተውኛል፡፡ እንዲሁም ወንድሜ ኩላሊት ሊሰጠኝ ፈቃደኛ ነው፡፡
ነገር ግን ለህክምና እና ተያያዥ ወጪዎች የሚፈለገው ገንዘብ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ዶላር ስለሆነና አቅም ስለሌለኝ ይህንን GoFundMe በመክፈት እርዳታ ለመጠየቅ ተገድጃለሁ፡፡
ሁላችሁም አነሰ ሳትሉ የምትችሉትን እንድትደግፉኝና በህይወት እንድቆይ እንድትረዱኝ በፈጣሪ ስም እጠይቃለሁ፡፡ ለምታደርጉልኝ በጎነት አመሰግናለሁ፡፡
https://gofund.me/fde9f3f8...

የወጣቱን እስጢፋኖስ አምሃን ሕይወት እንታደግ
#ethiopia | የ17 ዓመቱ ወጣትና የ11ኛ ክፍል ተማሪው እስጢፋኖስ አምሃ፣ በደም ካንሰር (Leukemia) ህመም ምክንያት በከባድ ፈተና ውስጥ ይገኛል።
ለ6 ወራት በኬሞቴራፒ ታክሞ ወደ ጤናው ተመልሶ የነበረ ቢሆንም፣ በሽታው በድጋሜ በማገርሸቱ በአስቸኳይ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ መታከም እንዳለበት ሐኪሞች አዝዘዋል።
የህክምና ወጪ
ለህክምናው ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል። ይህ መጠን ለቤተሰቡ ከአቅም በላይ በመሆኑ የእናንተን የደጋግ ወገኖቹን እገዛ ይፈልጋል።
እናቱ ዝናሽ ተፈራ እንዲህ ይላሉ
"የልጄን ህይወት ለመታደግ የእናንተን እገዛ እፈልጋለሁ... በሃገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር የምትገኙ ደጋግ ወገኖቼ በቻላችሁት ሁሉ እንድታግዙኝ በፈጣሪ ስም እጠይቃችኋለሁ።"
ድጋፍ ለማድረግ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000760949918
GoFundMe: https://gofund.me/47505f93...
ለተጨማሪ መረጃ፦
0968 881906
0930 288790
0923 669504
0911 158119
ወገኖቼ፣
ዛሬ የቡና ደጋፊዎች ደም በመለገስና ዮሚፍ ለንደን ላይ ታሪክ በመስራት ያስደሰቱን ቀን ነው። ይህንን ደስታችንን ሙሉ የምናደርገው ደግሞ እንደ እስጢፋኖስ ያሉ ተስፋ ያላቸው ወጣቶችን ከሞት አፋፍ ስንታደግ ነው።
7 ሚሊዮን ብር ለቤተሰቡ ትልቅ ቢሆንም፣ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ግን ተባብረን የማናሸንፈው ቁጥር አይደለም።
እባካችሁ በጸሎትም በገንዘብም ከጎኑ እንቁም!"
አንድ ሰው ለብዙዎች፣ ብዙዎች ለአንድ ሰው!
#getu #saveestifanos #helpestifanos #leukemiaawareness #ethiopianhumanity #emergencyappeal #healthcareethiopia #ድረሱልን #እስጢፋኖስአምሃ #ሰብአዊነት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago
የእርዳታ ተማጽኖ
#ethiopia | ለወጣቷ ሰብለ አሰፋ የህይወት አድን ጥሪ
ከካንሰር ጋር የምታደርገውን ትግል እንድታሸንፍ እንርዳት
#ethiopia | የደቡብ ጎንደር የወረታ ከተማ ተወላጅ የሆነችው የ21 ዓመቷ ወጣት ሰብለ አሰፋ፣ የትዳር ህይወቷን በደስታ ጀምራ ነበር።
ነገር ግን ይህ የደስታ ጊዜዋ ብዙም ሳይቆይ በአስደንጋጭ የጤና እክል ተተካ። መጀመሪያ ላይ የእርግዝና ምልክት መስሏት የነበረው ድካምና የትንፋሽ መቆራረጥ፣ ምርመራ ሲደረግላት ግን "አኪውት ማይሎብላስቲክ ሌውኬሚያ" (Acute Myeloblastic Leukemia) የተሰኘ ፈጣንና አስከፊ የደም ካንሰር መሆኑ ታወቀ።
ሰብለ ካንሰሩ ሲታወቅባት የ24 ሳምንት ነፍሰ ጡር ነበረች።
ዶክተሮች ካንሰሩን እያከሙ ፅንሱን ለማዳን ጥረት ቢያደርጉም፣ በህመሙ መፅናት ምክንያት ልጇ በማህፀን ውስጥ ሊሞት ችሏል።
በጥቂት ወራት ውስጥ የትዳር ደስታዋን፣ ልጇን እና ጤናዋን ያጣችው ሰብለ፣ አሁን ከሞት ጋር ብርቱ ትግል እያደረገች ትገኛለች።
በደጋፊዎች እርዳታ ወደ ህንድ ሀገር ለህክምና ያመራችው ሰብለ፣ ባለፉት ሦስት ወራት ሁለት ዙር የኬሞቴራፒ ህክምና ብታደርግም ካንሰሩ ሊጠፋላት አልቻለም።
አሁን ዶክተሮች ብቸኛው የህይወት ማዳኛ አማራጭ "የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ" (Bone Marrow Transplant) መሆኑን ገልጸዋል።
ይህንን የህይወት አድን ህክምና ለማድረግ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎችን ለመሸፈን 20,000 የአሜሪካ ዶላር በአስቸኳይ ያስፈልጋታል።
ሰብለ ገና 21 ዓመቷ ነው፤ መኖር ትፈልጋለች። ይህንን የገንዘብ አቅም ብቻዋን መቋቋም ስለማትችል ሁላችንም ከጎኗ እንቁም።
(የጎፈንድሚ (GoFundMe) ሊንክ : https://gofund.me/905858c8...
CBE: 1000220940121
Abay Bank: 2081011096364019
Telebirr: 0918094300
Tewodros Wondimu
ሰብለና ቤተሰቦቿ ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ እንዲያልፉ በጸሎታችሁ አስቧቸው።
ለሰብለ የምናደርገው እያንዳንዷ በጎነት ለህይወቷ ትልቅ ተስፋ ናት። ዛሬ ለወገን ደራሽ እንሁን።
#ሰብለአሰፋ #ለወገንደራሽ #ኢትዮጵያ #የደምካንሰር #እርዳታ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የ78 ዓመቱ አዛውንት የዕድል በር በድንገት ተከፈተላቸው፤ ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ እርዳታ ተሰበሰበ
በአሜሪካ ቴነሲ ግዛት ውስጥ የሚኖሩት የ78 ዓመቱ ሪቻርድ ፑሊ፣ በዕድሜያቸው መግፋት ምክንያት ሊያርፉ በሚገባበት ወቅት ለኑሮ ሲሉ በምግብ አቅርቦት (ዴሊቨሪ) ሥራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል።
ባለቤታቸው ሥራ በማጣቷ ምክንያት ጥንዶቹ የዕለት ጉርሳቸውን ለመሸፈን በከፍተኛ ድካም ሲሰሩ ነበር።
ታሪካቸው የተቀየረው ብሪታኒ ስሚዝ የተባለች ነርስ ቤት ቡና ለማድረስ በሄዱበት ወቅት ነው። አዛውንቱ በድካም ደረጃ ሲወጡ የተመለከተችው ስሚዝ፣ በደህንነት ካሜራ የቀረጸችውን ምስል በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራት የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከፈተች።
በአጭር ጊዜ ውስጥ ከለጋሾች የተሰበሰበው ገንዘብ 850,000 ዶላር (ከ134 ሚልየን ብር በላይ) ደርሷል።
ይህ ያልተጠበቀ ስጦታ ሪቻርድ እና ባለቤታቸው ብሬንዳ ከእንግዲህ በድካም ሳይሆን በደስታና በሰላም የጡረታ ዘመናቸውን እንዲያሳልፉ ዕድል ፈጥሮላቸዋል።
ምንጭ፦ GoFundMe

ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር በዛሬው ዕለት!
በመቄዶንያ ለሚረዱ ወገኖቻችን የሚሆን ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ተጀምሯል። ሁላችንም በጋራ በመሆን አቅማችን የፈቀደውን እናድርግ።
• መቼ፡ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ
• የት፡ በመቄዶንያ እና በሌሎችም የዩቲዩብ (YouTube) ቻናሎች
እንዴት መርዳት ይቻላል?
• Zelle/CashApp: 240-938-2992
• GoFundMe: Mekedonia
• ባንክ አካውንት (ኢትዮጵያ): 7979 (ለሁሉም ባንኮች)
• ለበለጠ መረጃ: 8131 ወይም 0949494949
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ! 🇪🇹❤️

🙏 ለዳግማዊ ቁልቢ ገብርኤል እንቅልፍ የለንም!
በአዲስ አበባ ኮተቤ አካባቢ የሚገኘው ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል እያከበረ ይገኛል።
ይሁን እንጂ ታሪካዊው ቤተክርስቲያን ካለው ዕድሜና ከ82,000 ካሬ ሜትር በላይ ሰፊ ቦታ አንጻር፣ የሚከተሉት መሠረታዊ ችግሮች በምእመናኑ ዘንድ ትልቅ ኅዘን ፈጥረዋል፦
የቤተክርስቲያኑ ጣራ ማፍሰስ
የአብነት ትምህርት ቤት አለመኖር
ምንም ዓይነት የልማት ሥራዎች አለመከናወን
እነዚህን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትና የቤተክርስቲያኑን ክብር ለመመለስ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ተዘጋጅቷል።
📅 የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር
ቀን፦ የካቲት 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ (ለሁለት ተከታታይ ሌሊቶች)
ተሳታፊዎች፦
መምህራን፣ ዘማርያን፣ ቲክታከሮችና ዩቱበሮች ያለ እንቅልፍ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ምእመናን መርሃ-ግብሩን በቀጥታ ያስተላልፋሉ።
የእርዳታ ማድረጊያ መንገዶች
የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች ሁሉ አቅማችሁ በፈቀደው መጠን እጃችሁን እንድትዘረጉ ጥሪ ቀርቧል፦
የባንክ አካውንቶች፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000750349227
ሕብረት ባንክ፦ 190821
አሐዱ ባንክ፦ 00895583117001
🌐 የጎፈንድሚ (GoFundMe) ሊንክ፦
https://gofund.me/e7915c6c...
📞 ለመረጃና ለቃል ኪዳን ስልክ ቁጥሮች፦
0913105153
0912863999
0911233619
የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ረድኤትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።
#ዳግማዊቁልቢ #ቅዱስገብርኤል #ኮተቤ #ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ
የእህታችንን የሎዛ በዛብህን ሕይወት እንታደግ!
#ethiopia | በላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል በከፍተኛ የጉበት ህመም (Liver Cirrhosis) ምክንያት በህክምና ላይ የምትገኘው የ40 ዓመቷ ሎዛ በዛብህ፣ ሕይወቷን ለማዳን አፋጣኝ የጉበት ንቅለ ተከላ (Liver Transplant) ህክምና ያስፈልጋታል።
ሎዛ አገር ውስጥ ሊሰጥ የማይችል ከፍተኛ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋት ሲሆን፣ ዶክተሮች በሰጡት ምክር መሠረት በአፋጣኝ ወደ ውጭ አገር ሄዳ መታከም ይኖርባታል።
ጉበት የሚለግሳት ታናሽ ወንድሟ አስፈላጊውን ምርመራ ሁሉ አጠናቆ ዝግጁ ቢሆንም፣ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ብቻ ጉዞውና ህክምናው ተጓትቷል።
ለህክምና፣ ለጉዞ እና ለተያያዥ ወጪዎች በጠቅላላው 37,000 (ሠላሳ ሰባት ሺህ) ዶላር ተጠይቋል። ይህ መጠን ከቤተሰቧ አቅም በላይ በመሆኑና እስካሁንም ለነበረው የህክምና ቆይታ ከፍተኛ ወጪ ስለወጣ፣ ቤተሰቧ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የርዳታ እጃችሁን ዘርጉልን ሲሉ ተማጽነዋል።
🙏
"የወገን ደራሽ ወገን ነው"ና እህታችን ወደ ቀድሞ ጤናዋ ተመልሳ ለቤተሰቧ እንድትበቃ በአቅማችን ያለውን ድጋፍ እናድርግላት።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000492987755
ስም፦ ፀሐይ በዛብህ (Tsehay Bezabeh)
ጎፈንድሚ (GoFundMe)፦ https://gofund.me/3e76bea4...
ስልክ ቁጥሮች፦
0939 66 53 59 (ሎዛ በዛብህ)
0911 21 61 23 (ፀሐይ በዛብህ)
ዛሬ የምናደርገው ጥቂት እርዳታ የአንድን እናትና እህት ሕይወት ይታደጋል!
እባክዎን ይህንን መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን።
#የእርዳታጥሪ #ሎዛበዛብህ #የጉበትንቅለተከላ #ኢትዮጵያ #livertransplant #medicalhelp #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

📢 ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ!
ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ሕመምተኞች መርጃ ማዕከል የሚውል ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። ሁላችሁም ተሳታፊ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።
• ቀን፡ መጋቢት 6
• ሰዓት፡ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ
• ቦታ፡ በመቄዶንያ እና በሌሎች የዩቲዩብ ቻናሎች የቀጥታ ስርጭት (Live)
💰 ድጋፍ ለማድረግ፦
በጎነት ለራስ ነው! በሚከተሉት መንገዶች አሻራዎን ያሳርፉ፡
• በኢትዮጵያ ላሉ፡ በሁሉም ባንኮች የሂሳብ ቁጥር 7979
• በውጭ ሀገር ለሚገኙ፡ * Zelle/CashApp: 240-938-2992
• GoFundMe: Makedonia
• ለበለጠ መረጃ፡ 📞 8131 / 0949494949 / 0989898989
የቀረው 18 ቀን ብቻ ነው! ዛሬውኑ ይርዱ!

6 months ago
የመቅዶንያ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር
ቀን፦ መጋቢት 6 ቀን።
ሰዓት፦ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ።
የት፦ በመቅዶንያ እና በሌሎችም የዩቲዩብ (YouTube) ቻናሎች ቀጥታ ስርጭት (Live)።
ለመደገፍ የሚረዱ አማራጮች፦
የአገር ውስጥ ባንኮች፦ በሁሉም ባንኮች የሂሳብ ቁጥር 7979 በመጠቀም መርዳት ይቻላል።
Zelle/CashApp፦ 240-938-2992
GoFundMe፦ "Mekedonia" በሚል ስም የተከፈተ
ለበለጠ መረጃ፦ በነጻ መስመር 8131 ወይም በስልክ ቁጥሮች 0949494949 / 0989898989 መደወል ይቻላል።

ለነፃነት ወርቅነህ (ነፂ) ቤተሰቦች የድጋፍ ጥሪ!
#ethiopia | ሁሌም በሳቁ ለሚያሳቀን፣ በስራዎቹ ለሚያዝናናን ነፂ... ዛሬ ለቤተሰቦቹ አለን እንበላቸው!
በኢቢኤስ (EBS) በተላለፈ ልዩ ፕሮግራም ላይ የአርቲስቱ የቅርብ ጓደኛ የሆነው አርቲስት አስኔ፤ የነፂን ባለቤት እና ሦስት ልጆች ለመደገፍ የታቀዱ ወሳኝ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።
ይፋዊ የጎፈንድሚ (GoFundMe) ድጋፍ:
ለቤተሰቡ ቋሚ ድጋፍ ለማድረግ የተከፈተውን ይፋዊ ሊንክ በመጠቀም አቅምዎ የፈቀደውን ይለግሱ፡
👉 https://gofund.me/c3a0a4d7...
የዩቲዩብ ገቢ ለቤተሰቡ:
ነፂ ህይወቱ ካለፈበት ጊዜ ጀምሮ በEBS የሚተላለፉ እሱ ያለበት ፕሮግራሞች የዩቲዩብ ገቢ በሙሉ ለቤተሰቡ እንዲሰጥ ተወስኗል። (ቪዲዮዎቹን ማየት እና ማጋራትም ድጋፍ ነው)
3️⃣ የልደት ቀን ልዩ ዝግጅት:
በፊታችን የካቲት ወር በሚከበረው የነፂ የልደት ቀን፤ እሱን የሚዘክር እና ለቤተሰቦቹ ገቢ ማሰባሰቢያ የሚሆን ታላቅ መርሃ-ግብር ይካሄዳል።
ነፂ በስራዎቹ ሁሌም በልባችን ይኖራል፤
አሁን ደግሞ ከቤተሰቦቹ ጎን በመቆም ፍቅራችንን በተግባር እናሳይ!
#netsanetworkneh #netsi #support #gofundme #ebs #ethiopianartist #familysupport #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

8 months ago
የአቲካን ህይወት ለመታደግ የእናንተን ድጋፍ እንሻለን!**ለተከበራችሁ ወገኖቻችን እና በጎ አድራጊዎች በሙሉ፤
ዛሬ የምንጽፍላችሁ በጣም አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ላይ ስለምትገኘው የአንድ አመት ከ አራት ወር ህጻን ልጅ አቲካ ፉአድ ቢላል አህመድ ነው። አቲካ ገና በለጋ እድሜዋ ከፍተኛ የሆነ የልብ ህመም ተገኝቶባት በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ትገኛለች።
ይህቺን ትንሽ ጨቅላ ወደ ቀድሞ ጤንነቷ ለመመለስ እና ህይወቷን ለመታደግ በህንድ ሀገር በሚገኘው ማክስ (Max Healthcare) ሆስፒታል አስቸኳይ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና እንድታገኝ በሀኪሞች ታዟል። ሆኖም ለህክምናው የሚያስፈልገው 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) የአሜሪካ ዶላር ከእኛ አቅም በላይ ሆኖብናል።
የእያንዳንዳችሁ ትንሽ ድጋፍ ለአቲካ ትልቅ ተስፋ ነው። ይህንን የህክምና ወጪ አሟልተን ልጃችንን ለፈውስ እንድናበቃት እንድትረዱን በፈጣሪ ስም እንጠይቃችኋለን።
ለመርዳት፦
* በ GoFundMe በኩል፦ [https://gofund.me/cb166f5f...
* **በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (1000657672215) ፉአድ ቢላል አህመድ
* **በስልክ ቁጥር፦097 363 9160 ቴሌ ብር ፉአድ ቢላል አህመድ
እባካችሁ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ይህንን መልዕክት ለሌሎች በማጋራት (Share በማድረግ) ድምጽ ሁኑን። አቲካን ፈጣሪ ይማራት፣ እናንተንም በጎ ስራችሁን ይክፈላችሁ።

በሲድኒ የሽብር ጥቃት ወቅት ታጣቂውን ትጥቅ ያስፈታው "የቦንዲው ጀግና" አህመድ አል አህመድ የዓለምን ትኩረት ስቧል
#ethiopia | በሲድኒ ቦንዲ ቢች በተካሄደ የሃኑካህ በዓል አከባበር ላይ በታጠቁ ግለሰቦች የተሰነዘረውን አሰቃቂ የሽብር ጥቃት፣ በጀግንነት ተጋፍጦ የብዙዎችን ህይወት የታደገው አህመድ አል አህመድ በመላው ዓለም አድናቆትን እያገኘ ይገኛል። አህመድ በወቅቱ ታጣቂውን በባዶ እጁ በመታገል ትጥቅ ያስፈታ ሲሆን፣ በዚህ ሂደት ላይም በደረሰበት ጥይት ቆስሎ በአሁኑ ወቅት በህክምና ላይ ይገኛል።
የ43 ዓመቱ አህመድ አል አህመድ፣ በሙያው የፍራፍሬ መሸጫ ሱቅ ባለቤት ሲሆን፣ ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በአካባቢው ቡና እየጠጣ ነበር። ታጣቂዎቹ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ በከፈቱበት ቅፅበት፣ አህመድ ከጥይቱ ከመሸሽ ይልቅ ወደ አደጋው በመሮጥ አንዱን ታጣቂ ከጀርባው አቅፎ በመያዝ እና ትጥቁን በመንጠቅ ጥቃቱ እንዳይባባስ አድርጓል።
በዚህ እጅግ አስገራሚ የጀግንነት ተግባር ወቅት አህመድ በትከሻው እና በእጁ ላይ ከ4 እስከ 5 የሚደርሱ የጥይት ቁስሎች ደርሰውበታል። የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎለት አሁን ላይ ነቅቶ በማገገም ላይ የሚገኘው አህመድ፣ ይህንን ያደረገው "ሰዎች ሲሞቱ ማየት ስላልቻለ" እና "ህሊናው ስላላስቻለው" መሆኑን ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ እና የኒው ሳውዝ ዌልስ ፕሪሚየር ክሪስ ሚንስ አህመድን በሆስፒታል ጎብኝተውታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አህመድ "የአውስትራሊያውያን የጀግንነት ተምሳሌት" መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም "በጣም ደፋርና የብዙዎችን ህይወት የታደገ ሰው" ሲሉ አወድሰውታል። ለአህመድ የህክምና እና የቤተሰብ ድጋፍ እንዲሆን የታቀደው የገቢ ማሰባሰቢያ (GoFundMe) በአንድ ቀን ውስጥ ከ1.3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማሰባሰብ ችሏል ያለው መናኸሪያ ኤፍ ኤም ነው።

በአውስትራሊያ የ43 አመቱ ሙስሊም ከጥቃት ፈፃሚው ጠመንጃ ነጥቆ የብዙ ሰው ህይወት በማትረፉ ከፍተኛ አድናቆት ተቸረው
ለዚህ ተግባሩ አንድ ባለሀብት ከፍተኛ ብር እሸልመዋለው ብለዋል።
እሁድ ምሽት አህመድ ኤል አህመድ በቦንዲ ባህር ዳርቻ በደረሰው አስከፊ የጅምላ ተኩስ ወቅት ከተኳሾች አንዱን ተጋፍጦ ጠመንጃውን ትጥቅ በማስፈታቱ ጀግና ተብሏል።
ይህ የሁለት ልጆች አባትየፍራፍሬ ነጋዴ የሆነው ።
አህመድ የ50 ዓመቱን ሽብር ፈጻሚ ተጋፍጦ በቀኝ እጁ ገዳዩን ትከሻ ላይ አድርጎ በሌላኛው እጁ ጥይት የሚተኩሰውን መሳሪያ ከእጁ ሊነጥቅ ችሏል።
አህመድ ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሁለት ጊዜ በጥይት ተመቶ በሴንት ጆርጅ ሆስፒታል ቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል። ደህና እንደሆነም ተነግሯል።
“ትልቅ ጀግንነት” ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአህመድን ጀግንነት አድነቀዋል።
ትራምፕ “አንድ እጅግ በጣም ጀግና የሆነ ሰው በእርግጥም ሄዶ ከተኳሾቹ አንዱን ፊት ለፊት በማጥቃት ብዙ ሕይወትን አድኗል። አሁን ሆስፒታል ውስጥ ያለ እና ከባድ ጉዳት የደረሰበት እጅግ ጀግና ሰው” ብለዋል።
ከ9.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ያለው ቢል አክማን የተባለ አይሁዳዊ ኢንቨስትመንት ባንክ ሰራተኛም የአህመድን ድርጊት አስተውሏል። እሱን መሸለም እንደሚፈልግ ተናግሯል።
“እሱንም ሆነ ቤተሰቡን መሸለም እንድንችል እባክዎን የተረጋገጠ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ሊያዘጋጅልን የሚችል ሰው አለ?” ሲል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ጽፏል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ “የቦንዲ አጥቂን ትጥቅ ላስፈታው ጀግና ድጋፍ” የሚል የ GoFundMe ገጽ ተከፍቷል።
እስከ አሁን ከ320,000 የአውስትራሊያ ዶላር በላይ ተሰብስቧል።

10 months ago
ኢትዮጵያውያን በአሜሪካን ሀገር ነብስ ይማር
መኪናዋ ውስጥ ሞታ የተገኘችው ኢትዮጵያዊት እህታችን
ከዳላስ አሳዛኝ ዜና፡
እህታችን አርሴማ በላይነህ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች 💔
በዳላስ እና አካባቢዋ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣ በድንገተኛ እና አስደንጋጭ ዜና ልብ ተሰብረን የምናሳውቀው፣ የምንወዳት እህታችንና ጓደኛችን ወ/ሪት አርሴማ በላይነህ በአዲሰን (Addison, TX) በሚገኘው መኖሪያ አፓርትመንት ግቢ መኪናዋ ውስጥ ሕይወቷ አልፎ ተገኝታለች።
ይህ ድንገተኛ ሞት በቤተሰቦቿ፣ በጓደኞቿ እና በዳላስ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ዘንድ ከባድ ሐዘንና ድንጋጤን ፈጥሯል። አስከሬኗ ለምርመራ በፖሊስ የተያዘ በመሆኑ፣ አስለቅቆ ሥርዓተ ቀብሯን በአግባቡ ለመፈጸም የቤተሰቧ ኃላፊነት ከባድ ሆኗል።
ለገንዘብ ድጋፍ የተላለፈ ልባዊ ጥሪ
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ቤተሰቦቿ ያለባቸውን የገንዘብ ጫና ለማቃለል እና አርሴማን በክብር እንድትቀበር ለመርዳት የሁሉም ወገኖች ድጋፍ በአስቸኳይ ያስፈልጋል።
የተከበራችሁ ወገኖች፣ በዚህ ከዚህ በታች በተዘጋጀው GoFundMe ሊንክ በመጠቀም፣ የቻላችሁትን ያህል የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰቦቿ ጎን እንድትቆሙ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
እህታችን አርሴማ በልባችን ውስጥ ለዘላለም ትኖራለች። ነፍሷን በአብርሃም፣ በይስሐቅ፣ በያዕቆብ እቅፍ ያኑርልን።
Gursha

1 year ago
ለዩኒቨርሲቲ መምህሩ አስናቀ ብርሃኑ እንድረስለት
Lets support Our Teacher
Yilkal Andualem is organizing this fundraiser.
Donation protected
መምህራችን_ታሞብናል
ወደ ካንሰር ሊቀየር ይችላል....ሀኪሞች
ወጣት መ/ር አስናቀ ብርሃኑ አላምነህ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቅንነትና በታማኝነት እያገለገለ ያለ በሙያውም አንቱታን ያተረፈ በሥነ ምግባሩ ምስጉን ሰው አክባሪ፣ ለተቸገሩ ፈጥኖ ደራሽ ወንድማችን ነው::
በሒሳብ ትምህርት ክፍል የኑሜሪካል አናላይሲስ መምህር ሲሆን በዩኒቨርሲቲ ቆይታውም ከማስተማር ስራው ጎን ለጎን በጥናትና ምርምር ዘርፍ በሙያው አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው 6 (ስድስት) ጥናትና ምርምሮችን በማሳተም ለአንባቢያን አድርሷል::
ወንድማችን መ/ር አስናቀ ድንገት በገጠመው የጤና እክል በህይወት እና በሞት መካከል ሆኖ የድረሱልኝ ተማፅኖውን እያሰማ ይገኛል:: በገጠመው የጤና ዕክል በተለያዩ ስድስት (6) ሆስፒታሎች ህክምና ሲያደርግ ቆይቷል::
ከነዚህም ውስጥ በአንዱ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ሰርጀሪ ተሰርቶ ሊሻለው ባለመቻሉ ወደ አዲስ አበባ አለርት ኮምፕርሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎለት ክትትል እያደረገ ይገኛል::
በመሆኑም የአለርት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ቦርድ 30% አጠቃላይ ቋሚ የአካል ጉዳተኛ እንደሆነና የሚከተሉትን ውሳኔዎችን ወስኗል::
1ኛ. በግራ እግሩ ላይ ስድስት (6) ዓመት የቆየ ከባድ ቁስለት ወደ ካንሰር የመቀየር እድሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑን፣
2ኛ. ሁለቱም እግሮቹ ነርቫቸው የተጎዳና ስሜት አልባ መሆናቸውን፣
3ኛ. የግራ እግሩ ሙሉ አጥንቶቹ የተጎዱና ይዘታቸውን የቀየሩ መሆናቸውን
4ኛ. ቁሞ ማስተማርም ሆነ በእግሩ መንቀሳቀስ እንደማይችል የአለርት ሆስፒታል ሜዲካል ቦርዱ አረጋግጧል
መምህር አስናቀ ባለብዙ ተስፋና ብዙ ህልም የነበረዉ ሩጦ ያልጠገበ ወንድማችን እግሮቹ ደክመው እቤት እንዲውል ተገዷል::
የህመሙ ሁኔታ አሳሳቢ እና ለህይወቱም አስጊ ደረጃ ላይ በመድረሱ ወደ ህንድ አገር ሂዶ ህክምና እንዲያደርግ ሪፈር ተፅፎለታል:: የህክምና ወጭውም ከሁለት ሚሊየን (2,000,000) ብር በላይ እንደሚያስፈልገው ተነግሮታል::
ወንድማችንን ለማገዝ አነሰ በዛ ሳንል በአገር ውስጥና በውጭ ያላችሁ ትዉልደ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የእርዳታ እጃችሁን ትዘርጉ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን::
Asinake Birihanu Alamneh
ስልክ_ቁጥር 09 23 53 45 01
Lecturer Asnake Berhanu, who has been serving Hawassa University with integrity and honesty, is a respected, respectful, and helpful person who has earned a reputation in his profession.
He is a Numerical Analysis Lecturer in the Department of Mathematics.
During his time at the university, he has published 6 (six) internationally recognized studies and research papers in his field, and has reached readers.
Our brother,Teacher Asnake is suddenly in the middle of life and death due to a health problem he encountered.
He has been receiving treatment in six (6) different hospitals for his health problem. In one of them, he underwent surgery at Hawassa University Referral Hospital and was referred to Addis Ababa Alert Compressive Specialized Hospital for follow-up.
Therefore, the Alert Specialized Hospital Medical Board has determined that he is 30% permanently disabled and has made the following decisions:
1st. The six (6) year old severe ulcer on his left leg has a very high chance of turning into cancer,
2nd. Both his legs are nerve damaged and numb,
3rd. The entire bones of his left leg are damaged and their contents have changed,
4th. The Alert Hospital Medical Board has confirmed that he cannot stand or walk.
Our brother, Teacher Asnake, who had many hopes and dreams, has been forced to stay home due to tired legs. His condition is serious and life-threatening, so he has been referred to India for treatment. He has been told that the medical expenses will cost more than $15000 .
Please help support this visionary teacher as they navigate through an incredibly difficult time. The funds raised will go towards the cost of surgical treatment , and to help to cover the loss of income while taking some much needed time to recover.
Thank you for your generosity.
I am grateful for your help and wishes.
Thank you
"Let's save the life of the visionary teacher with sincere hearts and united hands!
Show your support for this GoFundMe

Comments