Logo
Getu Temesgen
የእርዳታ ተማጽኖ
#ethiopia | ለወጣቷ ሰብለ አሰፋ የህይወት አድን ጥሪ
ከካንሰር ጋር የምታደርገውን ትግል እንድታሸንፍ እንርዳት
#ethiopia | ​የደቡብ ጎንደር የወረታ ከተማ ተወላጅ የሆነችው የ21 ዓመቷ ወጣት ሰብለ አሰፋ፣ የትዳር ህይወቷን በደስታ ጀምራ ነበር።

ነገር ግን ይህ የደስታ ጊዜዋ ብዙም ሳይቆይ በአስደንጋጭ የጤና እክል ተተካ። መጀመሪያ ላይ የእርግዝና ምልክት መስሏት የነበረው ድካምና የትንፋሽ መቆራረጥ፣ ምርመራ ሲደረግላት ግን "አኪውት ማይሎብላስቲክ ሌውኬሚያ" (Acute Myeloblastic Leukemia) የተሰኘ ፈጣንና አስከፊ የደም ካንሰር መሆኑ ታወቀ።

​ሰብለ ካንሰሩ ሲታወቅባት የ24 ሳምንት ነፍሰ ጡር ነበረች።

ዶክተሮች ካንሰሩን እያከሙ ፅንሱን ለማዳን ጥረት ቢያደርጉም፣ በህመሙ መፅናት ምክንያት ልጇ በማህፀን ውስጥ ሊሞት ችሏል።

በጥቂት ወራት ውስጥ የትዳር ደስታዋን፣ ልጇን እና ጤናዋን ያጣችው ሰብለ፣ አሁን ከሞት ጋር ብርቱ ትግል እያደረገች ትገኛለች።

​በደጋፊዎች እርዳታ ወደ ህንድ ሀገር ለህክምና ያመራችው ሰብለ፣ ባለፉት ሦስት ወራት ሁለት ዙር የኬሞቴራፒ ህክምና ብታደርግም ካንሰሩ ሊጠፋላት አልቻለም።

አሁን ዶክተሮች ብቸኛው የህይወት ማዳኛ አማራጭ "የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ" (Bone Marrow Transplant) መሆኑን ገልጸዋል።

​ይህንን የህይወት አድን ህክምና ለማድረግ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎችን ለመሸፈን 20,000 የአሜሪካ ዶላር በአስቸኳይ ያስፈልጋታል።

ሰብለ ገና 21 ዓመቷ ነው፤ መኖር ትፈልጋለች። ይህንን የገንዘብ አቅም ብቻዋን መቋቋም ስለማትችል ሁላችንም ከጎኗ እንቁም።

(የጎፈንድሚ (GoFundMe) ሊንክ : https://gofund.me/905858c8...

CBE: 1000220940121
Abay Bank: 2081011096364019

Telebirr: 0918094300
Tewodros Wondimu

ሰብለና ቤተሰቦቿ ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ እንዲያልፉ በጸሎታችሁ አስቧቸው።

​ለሰብለ የምናደርገው እያንዳንዷ በጎነት ለህይወቷ ትልቅ ተስፋ ናት። ዛሬ ለወገን ደራሽ እንሁን።

​#ሰብለአሰፋ #ለወገንደራሽ #ኢትዮጵያ #የደምካንሰር #እርዳታ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.