በአውስትራሊያ የ43 አመቱ ሙስሊም ከጥቃት ፈፃሚው ጠመንጃ ነጥቆ የብዙ ሰው ህይወት በማትረፉ ከፍተኛ አድናቆት ተቸረው
ለዚህ ተግባሩ አንድ ባለሀብት ከፍተኛ ብር እሸልመዋለው ብለዋል።
እሁድ ምሽት አህመድ ኤል አህመድ በቦንዲ ባህር ዳርቻ በደረሰው አስከፊ የጅምላ ተኩስ ወቅት ከተኳሾች አንዱን ተጋፍጦ ጠመንጃውን ትጥቅ በማስፈታቱ ጀግና ተብሏል።
ይህ የሁለት ልጆች አባትየፍራፍሬ ነጋዴ የሆነው ።
አህመድ የ50 ዓመቱን ሽብር ፈጻሚ ተጋፍጦ በቀኝ እጁ ገዳዩን ትከሻ ላይ አድርጎ በሌላኛው እጁ ጥይት የሚተኩሰውን መሳሪያ ከእጁ ሊነጥቅ ችሏል።
አህመድ ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሁለት ጊዜ በጥይት ተመቶ በሴንት ጆርጅ ሆስፒታል ቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል። ደህና እንደሆነም ተነግሯል።
“ትልቅ ጀግንነት” ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአህመድን ጀግንነት አድነቀዋል።
ትራምፕ “አንድ እጅግ በጣም ጀግና የሆነ ሰው በእርግጥም ሄዶ ከተኳሾቹ አንዱን ፊት ለፊት በማጥቃት ብዙ ሕይወትን አድኗል። አሁን ሆስፒታል ውስጥ ያለ እና ከባድ ጉዳት የደረሰበት እጅግ ጀግና ሰው” ብለዋል።
ከ9.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ያለው ቢል አክማን የተባለ አይሁዳዊ ኢንቨስትመንት ባንክ ሰራተኛም የአህመድን ድርጊት አስተውሏል። እሱን መሸለም እንደሚፈልግ ተናግሯል።
“እሱንም ሆነ ቤተሰቡን መሸለም እንድንችል እባክዎን የተረጋገጠ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ሊያዘጋጅልን የሚችል ሰው አለ?” ሲል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ጽፏል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ “የቦንዲ አጥቂን ትጥቅ ላስፈታው ጀግና ድጋፍ” የሚል የ GoFundMe ገጽ ተከፍቷል።
እስከ አሁን ከ320,000 የአውስትራሊያ ዶላር በላይ ተሰብስቧል።

8 months ago