Logo
Getu Temesgen
በአሰቃቂ አደጋ ለተቀጠፈው የናዖል ገመዳ ቤተሰቦች የገንዘብ ማሰባሰቢያ ጥሪ ቀረበ
#ethiopia | በአሜሪካ ካንሳስ ግዛት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ህይወቱ ለላለፈው ወጣት ናዖል ገመዳ የቀብር ስነ ስርዓት ማስፈጸሚያ እና ለተጎዱ ቤተሰቦቹ መደገፊያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ተጀምሯል።

ወጣት ናዖል ባለፈው አርብ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም (ሜይ 15 ማታ) ከስራ ወደ ቤቱ እየተመለሰ በነበረበት ወቅት በደረሰበት ከባድ የመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል።

ይህ የ31 ዓመት ወጣት ከባለቤቱ ሌንሳ አብዲሳ ጋር ከደንቢዶሎ ኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ አሜሪካ ካንሳስ ካቀና ገና አንድ ዓመት እንኳ ያልሞላው ሲሆን አዲስ ህይወት ለመመስረት እና ኑሮውን ለማስተካከል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ በነበረበት ወቅት ነው ይህ አሳዛኝ አደጋ የገጠመው።

ናዖል በትምህርቱም ሆነ በስራው ጠንካራ፣ ትልቅ ተስፋና ህልም የነበረው እንዲሁም የነርሲንግ ትምህርቱን ለመቀጠል እየተዘጋጀ የነበረ መልካም ወጣት እንደነበር የቅርብ ወዳጆቹ ይመሰክራሉ።

የቀብር ስነ ስርዓቱን ለማስፈጸም እና አስከሬኑን ወደ ሀገር ለመላክ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን የጎፈንድሚ (GoFundMe) የገንዘብ ማሰባሰቢያ ገጽ የተከፈተ ሲሆን ወዳጅ ዘመዶቹ እና የሟች ቤተሰቦች የተቻለዎትን ሁሉ በማድረግ ከጎናቸው እንዲቆሙ እና የበጎ አድራጎት ድጋፍ እንዲያደርጉ በፈጣሪ ስም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

https://gofund.me/21158cd8...
#kansas #gofundme #dembidolo #oromo #ethiopiancommunity #supportnaol #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.