ኢትዮጵያውያን በአሜሪካን ሀገር ነብስ ይማር
መኪናዋ ውስጥ ሞታ የተገኘችው ኢትዮጵያዊት እህታችን
ከዳላስ አሳዛኝ ዜና፡
እህታችን አርሴማ በላይነህ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች 💔
በዳላስ እና አካባቢዋ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣ በድንገተኛ እና አስደንጋጭ ዜና ልብ ተሰብረን የምናሳውቀው፣ የምንወዳት እህታችንና ጓደኛችን ወ/ሪት አርሴማ በላይነህ በአዲሰን (Addison, TX) በሚገኘው መኖሪያ አፓርትመንት ግቢ መኪናዋ ውስጥ ሕይወቷ አልፎ ተገኝታለች።
ይህ ድንገተኛ ሞት በቤተሰቦቿ፣ በጓደኞቿ እና በዳላስ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ዘንድ ከባድ ሐዘንና ድንጋጤን ፈጥሯል። አስከሬኗ ለምርመራ በፖሊስ የተያዘ በመሆኑ፣ አስለቅቆ ሥርዓተ ቀብሯን በአግባቡ ለመፈጸም የቤተሰቧ ኃላፊነት ከባድ ሆኗል።
ለገንዘብ ድጋፍ የተላለፈ ልባዊ ጥሪ
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ቤተሰቦቿ ያለባቸውን የገንዘብ ጫና ለማቃለል እና አርሴማን በክብር እንድትቀበር ለመርዳት የሁሉም ወገኖች ድጋፍ በአስቸኳይ ያስፈልጋል።
የተከበራችሁ ወገኖች፣ በዚህ ከዚህ በታች በተዘጋጀው GoFundMe ሊንክ በመጠቀም፣ የቻላችሁትን ያህል የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰቦቿ ጎን እንድትቆሙ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
እህታችን አርሴማ በልባችን ውስጥ ለዘላለም ትኖራለች። ነፍሷን በአብርሃም፣ በይስሐቅ፣ በያዕቆብ እቅፍ ያኑርልን።
Gursha

12 months ago