2 months ago
በኢትዮጵያ የሕጻናት የደም እና የካንሰር ሕክምና ማኅበር ተመሠረተ
#ethiopia | በሀገራችን በየዓመቱ ከ6 ሺህ እስከ 8 ሺህ የሚደርሱ ሕጻናት በካንሰር በሽታ ቢያዙም አስፈላጊውን የሕክምና ዕርዳታ ማግኘት የሚችሉት ከ2 ሺህ የማይበልጡት ብቻ ናቸው።
የቀሩት ሕጻናት ደግሞ ስለ በሽታው በቂ ግንባቤ ባለመኖሩ፣ በቅርበት የሕክምና ተደራሽነት በማጣታቸው፣ የባለሙያ እጥረት በመኖሩ እንዲሁም በዝቅተኛ ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ውስጥ በመገኘታቸው ምክንያት ተገቢውን ዕርዳታ ሳያገኙ ለህልፈተ ሕይወት ይዳረጋሉ።
ይህን አሳሳቢ ችግር ለመቅረፍ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የሕጻናት የደምና የካንሰር ሐኪሞች በመተባበር የኢትዮጵያ የሕጻናት የደምና የካንሰር ማኅበርን ተመስርቷል።
ማኅበሩ በበሽታው ለሚሰቃዩ ሕጻናት ዘላቂ መፍትሔዎችን ለመንደፍ፣ ባለድርሻ አካላትን በጋራ ለማንቀሳቀስ፣ ማኅበረሰቡን ለማንቃት እና የስነ-ልቦና እንዲሁም የማኅበራዊ ድጋፍ ለመስጠት ያለመ ነው።
በተጨማሪም የአገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት እና በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ ዓለም አቀፋዊ ትስስር በመፍጠር፣ በካንሰር ምክንያት የአንድም ሕጻን ሕይወት የማይቀጠፍባትን ሀገር ለመገንባት በቁርጠኝነት ሥራውን ጀምሯል።
ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ከግብ ለማድረስ ማኅበረሰቡን በማንቃት ረገድ የሚዲያ ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ ማኅበሩ ይፋዊ የምስረታ ሥነ ስርዓቱን በሒልተን ሆቴል አካሂዷል።
በዝግጅቱ ላይ ክብርት ሚኒስትሮች፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ከፍተኛ ምሁራን፣ ሕጻናትና ወላጆች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም የድርጅት ሥራ አስኪያጆች ታድመዋል።
በተያያዘ ዜና በጨቅላ ሕጻናት ሰብ-ስፔሻሊስት ሐኪሞች የተመሰረተው የኢትዮጵያ የጨቅላ ሕጻናት ሕክምና ማኅበር ይፋዊ የምስረታ ጉባኤውን በዚሁ ዕለት በሒልተን አዲስ አበባ ሆቴል በደመቀ ሁኔታ አካሂዷል።
ይህ ታሪካዊ የምስረታ በዓል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ደረጄ ዱጉማ፣ የማኅበሩ አመራሮች፣ የጨቅላ ሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪሞች፣ ነርሶች፣ ባለድርሻ አካላት እና ደጋፊ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተገኙበት በይፋ ተከብሯል።
ይህ ማኅበር ከሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪሞች፣ ከጨቅላ ሕጻናት ፌሎው ስፔሻሊስት ተማሪ ሐኪሞች፣ ከጨቅላ ሕጻናት ነርሶች፣ እንዲሁም ማንኛውም በጨቅላ ሕጻናት ጤና ላይ ከሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር በሀገሪቱ የሚወለዱ ጨቅላ ሕጻናትን ሕይወት ለመታደግ በትጋት እንደሚሰራ አስታውቋል።
የዚህ ታላቅ የምስረታ ጉባኤ መሪ ቃል ጤናማ ጅምር ለሁሉም አራስ ልጆች የሚል ነበር።
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ከ5 ዓመት በታች ያሉ ሕጻናትን ሞት በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገበች ቢሆንም፣ የጨቅላ ሕጻናት ማለትም ከተወለዱ ጀምሮ እስከ 28 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ያሉ ሕጻናት ሞት አሁንም ከፍተኛ ሀገራዊ ትኩረት የሚሻ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል።
የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በሀገሪቱ ከሚከሰቱት ከ5 ዓመት በታች ካሉ ሕጻናት ሞት ውስጥ ወደ ግማሽ የሚጠጋው ድርሻ የጨቅላ ሕጻናት ሞት ነው።
በየዓመቱ በሺዎች የሚቆረጠሩ ጨቅላ ሕጻናት ሊከላከሏቸው እና ሊታከሙ በሚችሉ ከመወለጃ ቀናቸው ቀድሞ መወለድ፣ መታፈን እና በኢንፌክሽን ምክንያት ሕይወታቸውን ያጣሉ።
ይህ አሃዝ እንደሚያሳየው የማኅበሩ መመስረት እና የባለሙያዎች ቅንጅት በሀገሪቱ የእንክብካቤ ጥራትን ለማሻሻል እና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢትዮጵያ የጨቅላ ሕጻናት ሕክምና ማኅበር መመስረት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጨቅላ ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ ለሚያደርገው አገራዊ ጥረት ታላቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
መንግስት የጨቅላ ሕጻናትን የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነት እና ጥራት ለማሻሻል የፖሊሲ እና የስትራቴጂ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝና ይህ ማኅበር በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ የሕክምና አሰራሮችን በመዘርጋት እና የባለሙያዎችን አቅም በመገንባት ረገድ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስራት ድምፀ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፣ ማኅበሩ ጤናማ ጅምር ለሁሉም ጨቅላ ሕጻን በሚል መሪ ቃል የተመሰረተ መሆኑን ጠቅሰው፣ ዋነኛ ዓላማቸው በኢትዮጵያ የሚወለድ እያንዳንዱ ጨቅላ ሕጻን በወቅቱ የሚገኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትሀዊ፣ በሳይንሳዊ ማስረጃ የተደገፈ፣ ከፍተኛ ጥራት ያለውና ርህራሄ የተሞላበት የጨቅላ ሕጻናት ሕክምናና እንክብካቤ እንዲያገኝ ማስቻል እንደሆነ አስረድተዋል።
ዛሬ በይፋ ሥራ ሲጀመር ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተተ ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር የሕጻናትን ሞት ለመቀነስ መቁረጣቸውን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ የጨቅላ ሕጻናት ሕክምና ማኅበር በሀገሪቱ የሕክምና ሥርዓት ውስጥ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት አራት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
እነሱም በጨቅላ ሕጻናት ሕክምና ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎችን አቅም በስልጠና እና በትምህርት ማሳደግ፣ በሳይንሳዊ ማስረጃዎችና ምርምሮች ላይ የተመሰረቱ የሕክምና አሰራሮችን መዘርጋትና ማሻሻል፣ ለጨቅላ ሕጻናት ጤናና ደህንነት ምቹ የሆኑ ሀገራዊ የጤና ፖሊሲዎች እንዲቀረፁና እንዲሻሻሉ ተፅዕኖ መፍጠር እንዲሁም የጨቅላ ሕጻናትን ጤና በተመለከተ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ማድረግ እና ሰፊ የሕብረተሰብና የሙያተኞች ቅስቀሳ ማካሄድ ናቸው።
ማኅበሩ በሀገሪቱ የጨቅላ ሕጻናትን የጤና ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ ከመንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ሁልጊዜም በሩ ክፍት መሆኑን እያስታወሰ፣ ሕብረተሰቡና የጤና ባለሙያዎች ለዚህ ቅዱስ ዓላማ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪውን አቅርቧል።
#espho #childhoodcancer #esn #neonatology #healthcareethiopia #pediatriconcology #communityawareness #newbornhealth #ethiopiandoctors #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምረቃ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
#ethiopia #laftohospital #ethiopiainnovation #pmabiy #digitalethiopia #healthcareethiopia #addisababa
2 months ago
ከአይቻልም ወደ ምን እንርዳዎት ➡️ https://youtu.be/AKoFF96F4... #pmabiyahmed #ethiopia #laftohospital #ethiopiainnovation #healthcareethiopia
2 months ago
2 months ago
2 months ago
ማዕድ ማጋራት አሁን ምን ያደርጋል? ለሚሉ...የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ➡️ https://youtu.be/AKoFF96F4... #pmabiyahmed #ethiopia #laftohospital #ethiopiainnovation #healthcareethiopia
2 months ago
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ለአዲስ አበባ አስተዳደር ➡️ https://youtu.be/AKoFF96F4... #pmabiyahmed #ethiopia #laftohospital #ethiopiainnovation #healthcareethiopia
2 months ago
በሽታ ልክ እንደጦር ውጊያ ይፈልጋል ➡️ https://youtu.be/AKoFF96F4... #pmabiyahmed #ethiopia #laftohospital #ethiopiainnovation #healthcareethiopia
Sponsored by
Surafel
2 months ago
u1320u1245u120bu12ed u121au1292u1235u1275u122d u12d0u1262u12ed u12a0u1215u1218u12f5 (u12f6/u122d) u12e8u120bu134du1276 u1235u1354u123bu120bu12edu12ddu12f5 u1206u1235u1352u1273u120d u121du122du1243 u120bu12ed u12ebu1235u1270u120bu1208u1349u1275 u1218u120du12d5u12adu1275
#abiyahmed #ethiopia #laftohospital #ethiopiainnovation #pmabiy #digitalethiopia #healthcareethiopia #addisababa ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምርቃ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
#abiyahmed #ethiopia #laftohospital #ethiopiainnovation #pmabiy #digitalethiopia #healthcareethiopia #addisababa
3 months ago
የወጣቱን እስጢፋኖስ አምሃን ሕይወት እንታደግ
#ethiopia | የ17 ዓመቱ ወጣትና የ11ኛ ክፍል ተማሪው እስጢፋኖስ አምሃ፣ በደም ካንሰር (Leukemia) ህመም ምክንያት በከባድ ፈተና ውስጥ ይገኛል።
ለ6 ወራት በኬሞቴራፒ ታክሞ ወደ ጤናው ተመልሶ የነበረ ቢሆንም፣ በሽታው በድጋሜ በማገርሸቱ በአስቸኳይ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ መታከም እንዳለበት ሐኪሞች አዝዘዋል።
የህክምና ወጪ
ለህክምናው ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል። ይህ መጠን ለቤተሰቡ ከአቅም በላይ በመሆኑ የእናንተን የደጋግ ወገኖቹን እገዛ ይፈልጋል።
እናቱ ዝናሽ ተፈራ እንዲህ ይላሉ
"የልጄን ህይወት ለመታደግ የእናንተን እገዛ እፈልጋለሁ... በሃገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር የምትገኙ ደጋግ ወገኖቼ በቻላችሁት ሁሉ እንድታግዙኝ በፈጣሪ ስም እጠይቃችኋለሁ።"
ድጋፍ ለማድረግ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000760949918
GoFundMe: https://gofund.me/47505f93...
ለተጨማሪ መረጃ፦
0968 881906
0930 288790
0923 669504
0911 158119
ወገኖቼ፣
ዛሬ የቡና ደጋፊዎች ደም በመለገስና ዮሚፍ ለንደን ላይ ታሪክ በመስራት ያስደሰቱን ቀን ነው። ይህንን ደስታችንን ሙሉ የምናደርገው ደግሞ እንደ እስጢፋኖስ ያሉ ተስፋ ያላቸው ወጣቶችን ከሞት አፋፍ ስንታደግ ነው።
7 ሚሊዮን ብር ለቤተሰቡ ትልቅ ቢሆንም፣ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ግን ተባብረን የማናሸንፈው ቁጥር አይደለም።
እባካችሁ በጸሎትም በገንዘብም ከጎኑ እንቁም!"
አንድ ሰው ለብዙዎች፣ ብዙዎች ለአንድ ሰው!
#getu #saveestifanos #helpestifanos #leukemiaawareness #ethiopianhumanity #emergencyappeal #healthcareethiopia #ድረሱልን #እስጢፋኖስአምሃ #ሰብአዊነት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago
በታዝማ ልዩ የሕክምና ማዕከል ሌላኛው አስደናቂ ስኬት!
በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተከናወነ እጅግ ውስብስብ የቤንታል (Bentall) የልብ ቀዶ ሕክምና!
በሀገራችን እጅግ ውስብስብና የመጀመሪያ የተባሉ የልብ ቀዶ ሕክምናዎችን በማከናወን ግንባር ቀደም የሆነው ታዝማ የውስጥ ደዌ እና የቀዶ ህክምና ልዩ ማዕከል፤ ዛሬም እንደተለመደው በስኬት የታጀበ የምስራች ይዞላችሁ ቀርቧል።
የህክምናው ሂደት በአጭሩ
የ50 ዓመት ጎልማሳ የሆኑት ታካሚው፦
* የልብ ደም ወሳጅ ቧንቧ እብጠት (Aortic Aneurysm) እና
* የደም ቧንቧ መሰንጠቅ (Type A Aortic Dissection) አጋጥሟቸው ለሕይወት አስጊ በሆነ ደረጃ ላይ ነበሩ።
በታዋቂው የልብ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ብርሃኑ ኃይለማርያም በሚመራው የሕክምና ቡድናችን በተደረገ ከፍተኛ ርብርብ፤ እጅግ ውስብስብ የሆነው የቤንታል (Bentall) ቀዶ ሕክምና በጥንቃቄ ተከናውኖ የታካሚውን ሕይወት መታደግ ተችሏል።
በአሁኑ ወቅት ታካሚው ሙሉ በሙሉ አገግመው በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።
የልብ ህክምና ፍለጋ ወደ ውጭ ሀገር መሄድ የቀረበት ዘመን!
ይህ ስኬት በራሳችን ልጆች፣ በኢትዮጵያውያን ሐኪሞች በአገር ውስጥ መከናወኑ፤ ማዕከላችን ለኢትዮጵያውያን ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሕያው ምስክር ነው።
ታዝማ - የጤናማ ልብ አርማ! 💙
#tazmamedicalcenter #heartsurgery #bentallprocedure #ethiopiandoctors #healthcareethiopia #savinglives

5 months ago
10ኛው የኢትዮ ሄልዝ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽንና ጉባኤ ሊካሄድ ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ የጤናውን ዘርፍ ለማዘመንና የሕክምና ግብዓቶችን አቅርቦት ለማሳለጥ ያለመው 10ኛው የኢትዮ ሄልዝ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽንና ጉባኤ፣ እንዲሁም 2ኛው የአገር ውስጥ የሕክምና ግብዓቶች ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን ከመጋቢት 24 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል።
በዚህ መድረክ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እና በፕራና ኤቨንትስ አዘጋጅነት የሚቀርብ ሲሆን፣ ከስምንት አገራት የተውጣጡ ከ90 በላይ ዓለም አቀፍና አገር በቀል ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ለታዳሚዎች ያቀርባሉ።
በኤግዚቢሽኑ ላይ ከእንግሊዝ፣ ከቻይና፣ ከህንድ፣ ከቱርክ፣ ከታይላንድ፣ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስና ከአሜሪካ የመጡ ታዋቂ ድርጅቶች የሚሳተፉ በመሆኑ፣ የውጭውን ቴክኖሎጂ ከአገር ውስጥ አምራቾች ጋር ለማስተሳሰርና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
ከንግድ ትርኢቱ ጎን ለጎን የጤና ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ የሚረዱ ከ40 በላይ ቀጣይነት ያለው የሙያ ማሳደጊያ (CPD) ስልጠናዎች የሚሰጡ ሲሆን፣ ከ20 በላይ የሚሆኑ የዘርፉ የሙያ ማህበራትም በዝግጅቱ ላይ የነቃ ተሳትፎ ያደርጋሉ።
በተጨማሪም የጤና አመራር ጉባኤ፣ የዲጂታል ሄልዝ ፎረም እና የሳይንሳዊ መድረኮች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በጤናው ዘርፍ ያሉ ችግሮችን በምርምርና በቴክኖሎጂ ለመፍታት የሚያስችሉ ምክክሮች የሚደረጉባቸው መድረኮች ይሆናሉ።
ይህ ዝግጅት በተለይም የሀገር ውስጥ የሕክምና መሣሪያዎችና የመድኃኒት አምራቾች ምርቶቻቸውን ለገበያ በማቅረብ በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ድርሻ እንዲያሳድጉና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን (EFDA) እና በሌሎችም መንግስታዊ ተቋማት ሙሉ እውቅናና ድጋፍ የሚደረግለት ይህ ጉባኤ፣ የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ሚና ይጫወታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiohealth2026 #healthcareethiopia #medicalexhibition #pranaevents #ahri #digitalhealth #medicalinnovation #ethiopiahealthconference

የነገው የጤና ተስፋዎች
📌የዶ/ር መቅደስ ዳባ መልዕክት ለተመራቂዎች
#ethiopia | የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚንስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ትምህርት ቤት የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ለተመራቂ ተማሪዎች ደማቅ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዶ/ር መቅደስ በንግግራቸው ወቅት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለጤናው ዘርፍ ጥራትና ለባለሙያዎች ደህንነት የሰጠውን ትኩረት አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል። ሚኒስትሯ በዋናነት የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፡-
* የትምህርት ጥራትና ማሻሻያ፡ ከአካዳሚክ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የህክምና ትምህርትን የማዘመንና የሬዚደንሲ ፕሮግራሞችን የማጠናከር ስራ እየተሰራ መሆኑን።
* የሆስፒታል ሪፎርም፡ በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማሻሻልና የስፔሻሊቲ እንዲሁም የሰብ-ስፔሻሊቲ ስልጠናዎችን ተደራሽ ለማድረግ በትጋት እየተሰራ እንደሚገኝ።
* የባለሙያዎች ደህንነት፡ በተለይም የሬዚደንቶችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻልና አበረታች የስራ ሁኔታን ለመፍጠር ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።
ይህ ምርቃት በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ላይ አዳዲስ አቅሞችን እንደሚጨምር የታመነ ሲሆን፣ ተመራቂዎችም በታማኝነትና በሙያ ስነ-ምግባር ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ ቀርቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #healthministry #aau #medicalgraduation #doctormekdesdaba #healthcareethiopia #futuredoctors

6 months ago
💎 ቪዥን የጤና አገልግሎት የ"ዳይመንድ ደረጃ" የክብር ዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! 🇪🇹🏥
#ethiopia | "ለዚህ ሁሉ ዓመት ስኬት ያበቃን ሙያችንንና ሕሙማንን ማስቀደማችን ነው" — ቪዥን የጤና አገልግሎት
ባለፉት 15 ዓመታት በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ በምሳሌነት የሚጠቀስ ሥራ ሲያከናውን የቆየው ቪዥን የጤና አገልግሎት፣ በግራንድ አፍሪካ ሽልማት ከፍተኛው የዳይመንድ ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
ተቋሙ ለሽልማት የበቃባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች፦
⭐ ልዩ ትኩረት፦
ለታካሚዎች ለሚሰጠው ልዩ እንክብካቤ እና ለአገልግሎት ጥራት ያለው ጽኑ አቋም።
💻 ዲጂታል ጤና (Digital Healthcare)፦
አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ሲስተም በመደገፍ፣ የታካሚዎችን መረጃ በአስተማማኝ ሁኔታ መያዝ እና የጥበቃ ጊዜን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ በመቻሉ።
🤝 ማህበራዊ ኃላፊነት፦
አቅም ለሌላቸው ዜጎች በሚያደርገው የዋጋ ቅናሽ እና በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ተሳትፎ።
🚀 የሥራ ዕድል፦
በአሁኑ ወቅት ከ70 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር የክሊኒካል፣ የፋርማሲ፣ የማማከርና የላቀ የላብራቶሪ ምርመራዎችን እየሰጠ ይገኛል።
የወደፊት ራዕይ፦
የድርጅቱ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ስምዖን ሀብተአብ እንደገለጹት፤ ተቋሙ ወደፊት የተቀናጀ የቴሌ-መድኃኒት (Telemedicine) ኔትወርክን እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፉ የሕክምና ውሳኔ ረዳት ሥርዓቶችን ለመዘርጋት እየሰራ ይገኛል።
በ2011 (እ.ኤ.አ) የተመሰረተው ይህ ተቋም ለደረሰበት ከፍተኛ ደረጃ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!
#visionhealth #healthcareethiopia #awardwinning #digitalhealth #grandafricaaward #medicalexcellence #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

👶 አዲስ ተስፋ ለጥንዶች ✨
#ethiopia | አዶ የስነ ተዋልዶ ማእከል" (Ado Fertility Center) በአዲስ አበባ ስራ ጀመረ! 🏥✨
በመቐለ ከተማ ስኬታማ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው "አዶ የእናቶችና ሕፃናት እንዲሁም የስነ ተዋልዶ ሕክምና ማእከል"፤ አሁን ደግሞ በ60 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት በአዲስ አበባ ዘመናዊ የIVF እና የመኻንነት ሕክምና ማዕከሉን በይፋ መርቋል።
ቁልፍ መረጃዎች፦
👨⚕️ የባለሙያዎች ጥምረት፦
ዶ/ር ሳምሶን ሙሉጌታ ከታዋቂው የዘርፉ ባለሙያዎች (ዶ/ር ማንደፍሮ ደለለኝ፣ ዶ/ር እያሱ መኮንን፣ አቶ ጤናው ሲሳይ እና ዶ/ር አቤል ተሾመ) ጋር በመሆን ማዕከሉን አደራጅተዋል።
📉 የተደራሽነት ክፍተት፦
በኢትዮጵያ በአመት ሕክምና የሚያገኙት 1000 ጥንዶች ብቻ ሲሆኑ (0.007%)፣ ይህ ማዕከል ይህንን ከፍተኛ ክፍተት ለመሙላት አልሟል።
🔬 የቴክኖሎጂ ሽግግር፦
በቅርብ ወራት ውስጥ የStem cell treatment እና ሌሎች የተራቀቁ ሕክምናዎችን ለመጀመር ዝግጅት ተጠናቋል። በተጨማሪም በህንድ ሀገር ከሚገኙ አጋሮች ጋር በመሆን ውስብስብ ሕክምናዎችን (PGT, Micro-TESE) ለመስጠት ታቅዷል።
🎓 ስልጠና፦
የሰው ኃይል እጥረቱን ለመቅረፍ ከጤና ሚኒስቴር እና ከህንድ የEmbryology አካዳሚ ጋር በመሆን በART እና Embryology እውቅና ያለው ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።
🎁 የደስታ ብስራት፦
ማዕከሉ ማህበራዊ ግዴታውን ለመወጣት መስፈርቱን ለሚያሟሉ 2 ተመረጡ ባለትዳሮች የ2 ሚሊዮን ብር ነፃ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ በደስታ አስታውቋል።
ለዚህ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉት ንብ፣ አቢሲኒያ እና እናት ባንኮች እንዲሁም ሌሎች አጋሮች ምስጋና ቀርቧል።
የመኻንነት ችግር ለሚፈታተናቸው ብዙዎች ይህ ማዕከል ትልቅ የምስራች ነው!
✨ "የአገራችንን የስነ-ተዋልዶ ሕክምና ተደራሽነት ለማሳደግ ቁርጠኛ ነን" — ዶ/ር ሳምሶን ሙሉጌታ
#adofertilitycenter #ivfethiopia #healthcareethiopia #infertilitysupport #addisababa #medicalinnovation #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments