Logo
Getu Temesgen
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ
የእህታችንን የሎዛ በዛብህን ሕይወት እንታደግ!
#ethiopia | ​በላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል በከፍተኛ የጉበት ህመም (Liver Cirrhosis) ምክንያት በህክምና ላይ የምትገኘው የ40 ዓመቷ ሎዛ በዛብህ፣ ሕይወቷን ለማዳን አፋጣኝ የጉበት ንቅለ ተከላ (Liver Transplant) ህክምና ያስፈልጋታል።

ሎዛ አገር ውስጥ ሊሰጥ የማይችል ከፍተኛ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋት ሲሆን፣ ዶክተሮች በሰጡት ምክር መሠረት በአፋጣኝ ወደ ውጭ አገር ሄዳ መታከም ይኖርባታል።

ጉበት የሚለግሳት ታናሽ ወንድሟ አስፈላጊውን ምርመራ ሁሉ አጠናቆ ዝግጁ ቢሆንም፣ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ብቻ ጉዞውና ህክምናው ተጓትቷል።

ለህክምና፣ ለጉዞ እና ለተያያዥ ወጪዎች በጠቅላላው 37,000 (ሠላሳ ሰባት ሺህ) ዶላር ተጠይቋል። ይህ መጠን ከቤተሰቧ አቅም በላይ በመሆኑና እስካሁንም ለነበረው የህክምና ቆይታ ከፍተኛ ወጪ ስለወጣ፣ ቤተሰቧ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የርዳታ እጃችሁን ዘርጉልን ሲሉ ተማጽነዋል።
​🙏
"የወገን ደራሽ ወገን ነው"ና እህታችን ወደ ቀድሞ ጤናዋ ተመልሳ ለቤተሰቧ እንድትበቃ በአቅማችን ያለውን ድጋፍ እናድርግላት።

​የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000492987755
​ስም፦ ፀሐይ በዛብህ (Tsehay Bezabeh)
​ጎፈንድሚ (GoFundMe)፦ https://gofund.me/3e76bea4...

​ስልክ ቁጥሮች፦
0939 66 53 59 (ሎዛ በዛብህ)
​0911 21 61 23 (ፀሐይ በዛብህ)

​ዛሬ የምናደርገው ጥቂት እርዳታ የአንድን እናትና እህት ሕይወት ይታደጋል!

​እባክዎን ይህንን መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን።

​#የእርዳታጥሪ #ሎዛበዛብህ #የጉበትንቅለተከላ #ኢትዮጵያ #livertransplant #medicalhelp #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.