8 days ago
ጤና ሚኒስቴር ከጣሊያን ሀገር የመጡ በጎ ፈቃደኛ ሐኪሞች ላከናወኑት የሕፃናት ነጻ የልብ ቀዶ ሕክምና ምስጋናና ዕውቅና ሰጠ
የጤና ሚኒስቴር በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ አማካይነት ከጣልያን ሀገር የመጡ በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች፣ ከኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት 80 የልብ ሕሙማን ሕፃናት በሁለት ጊዜ ምልልስ
በ15 ቀናት ጊዜያት ውስጥ የነጻ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት
በመስጠታቸው የምስጋናና የእውቅና ሠርተፊኬት ሰጠ።
ትላንት ግንቦት 18/2018 ዓ.ም በአራዳ ፓርክ በተከናወነው መርሐግብር ባለሙያዎቹ አገልግሎቱን የሰጡት በሁለት ዙር ተልእኮ መኾኑ የተጠቀሰ ሲሆን 48 ሕፃናት በአዲስ አበባ ኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል፣ 9 ሕፃናት በጂግጂጋ እንዲሁም 23 ሕፃናት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል (በጎንደር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ) የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መኾናቸው ተነግሯል።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለተሰጠው አገልግሎት በጤና ሚኒስቴር፣ በራሳቸው ስምና ከሁሉም በላይ በዚህ ሕክምና ተጠቃሚ በሆነው ማህበረሰብ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ይህ መልካም ተግባር ቀጣይነት እንዲኖረው የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል። በቀጣይም ለሚከናወኑ መሰል ተግባራት ጤና ሚኒስቴርም አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ለዚህ ዓላማ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በተለይም ለኸርት ቱ ኸርት ችልድረን ኤይድ በገንዘብ እና በቴክኒክ ላበረከተው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግከሎት በ45 ቀናት ለ175 ሕፃናት የልብ ቀዶ ሕክምና ለመስጠት በጤና ሚኒስቴር፣ በኸርት ቱ ኸርት ችልድረንስ ኤይድ እና በተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት መካከል የተደረገ ስምምነት አካል ነው።
አቶ ብርሃን ተድላ የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ በበኩላቸው የጤና ሚኒስቴር የተከናወነውን የበጎ ተግባር ትልቅ ዋጋ መስጠቱ ሌሎችም ተመሳሳይ ተልእኮዎች በአርአያነት የሚታይ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኽርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ በገባው ቃል መሰረት ስራዎቹ በአጭር ጊዜያት እንደሚያጠናቅቅም አቶ ብርሃን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ ለስራው የስምምነቱ አካል የኾኑ የመንግስት፣ የግል ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት ያበረከቱት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ መኾኑን በማስታወስ የስራው አጠቃላይ ሪፖርት እኤአ ጁን 10 ከተጠናቀቀ በኋላ ሌላ የምስጋና መርሐግብር እንደሚኖር ዶ/ር አስቻለው ወርቁ የጤና ሚኒስቴር አማካሪ አረጋግጠዋል።

#ethiopia | የጤና ሚኒስቴር በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ አማካይነት ከጣልያን ሀገር የመጡ በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች፣ ከኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት 80 የልብ ሕሙማን ሕፃናት በሁለት ጊዜ ምልልስ በ15 ቀናት ጊዜያት ውስጥ የነጻ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመስጠታቸው የምስጋናና የእውቅና ሠርተፊኬት ሰጠ።

1 month ago
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፈረሙት ለምንድን ነው?
*“ኢትዮጵያን የአፍሪካ የፋሽን ተምሳሌት እናደርጋታለን” — አቶ ዘላለም መራዊ
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት
#ethiopia | በ“ኢትዮጵያ ታምርት” የንግድ ትርኢት ላይ የተሳተፉት የኬሬዠ ኢትዮጵያ መስራች አቶ ዘላለም መራዊ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድርጅታቸውን የፈጠራ ስራዎች መጎብኘታቸውንና ከፍተኛ አድናቆት መቸራቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየዓመቱ በሚያደርጉት ጉብኝት በምርቶቹ ላይ የሚታየው መሻሻልና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች እንዳስደመሟቸው በድርጅቱ የክብር መዝገብ ላይ በፊርማቸው ጭምር አረጋግጠዋል።
በዓለም ላይ ያለው የፋሽን ኢንዱስትሪ እስከ 300 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገቢ እንደሚያንቀሳቅስ የገለጹት አቶ ዘላለም፣ ኢትዮጵያ እንደ ጣልያንና ፈረንሳይ የራሷን የፋሽን “ብራንድ” በመገንባት ከዚህ ገበያ ተጠቃሚ መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል።
ኬሬዠ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከውጭ ይገቡ የነበሩ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የቆዳ ውጤቶች በሀገር ውስጥ በማምረት ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ለተለያዩ የአፍሪካ መሪዎች የሚሰጡ የክብር ስጦታዎችን እያቀረበ ይገኛል።
በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን በፋሽንና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ቦታ ላይ የማድረስ ጉጉት እንዳላቸው ገልጸዋል።
አቶ ዘላለም የኬሬዠ ኢትዮጵያ መስራች ከመሆናቸው ባለፈ፣ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት በመሆን መላው ዘርፍ በቴክኖሎጂ፣ በስልጠናና በጥሬ እቃ አቅርቦት እንዲሻሻል በንቃት እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።
በአጠቃላይ፣ የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት (ቆዳ) እና የሰው ኃይል በመጠቀም ኢትዮጵያን በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በመላው አፍሪካ ገበያዎች ውስጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ ታላቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን የስራ መሪው በኩራት ተናግረዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #amn
#የኢትዮጵያታምርት #ቆዳናየቆዳውጤቶች #ዘላለምመራዊ #ኢትዮጵያ #ፋሽን #የሀገርውስጥምርት #ethiopiatamrit #ethiopianfashion #leatherindustry

''ኢራንን አንተካም!" — ጣልያን
#ethiopia | ፊፋ ኢራንን ከዓለም ዋንጫ አስወግዶ በምትኳ ጣልያንን እንዲያስገባ ያቀረቡት ጥያቄ በራሷ በጣልያን መንግሥትና በስፖርት አመራሮቹ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው።
የጣልያን ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ሉቺያኖ ቦንፊግልዮ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ጠንከር ያለ ምላሽ፣ ጣልያን በሜዳ ላይ ባላሳየችው ውጤት በፖለቲካዊ መንገድ ወደ ዓለም ዋንጫ እንድትገባ የቀረበውን ሐሳብ እንደማይቀበሉት ገልጸዋል።
"ይሄ ከተፈጠረ እንደ ስድብ ነው የምወስደው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ማንኛውም ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማለፍ ያለበት በችሎታውና በጠንካራ ሥራው መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
የሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም የኦሎምፒክ ኮሚቴውን አቋም ተጋርተዋል፦
"ይሄ አስፈላጊ አይደለም፤ ሜዳ ላይ ነው ማለፍ ያለብን" በማለት በጓሮ በር ወደ ውድድሩ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።
የኢኮኖሚ ሚኒስትር ጂዮርጌቲ፦ ዜናው በግላቸው እንዳሳፈራቸው ገልጸው፣ "በዛ መንገድ ከሄድን አፍራለሁ" ሲሉ የሐሳቡን አሳፋሪነት ገልጸዋል።
ምንም እንኳን የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ለ2026ቱ ዓለም ዋንጫ ባለማለፉ ደጋፊዎቿ ቢያዝኑም፣ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ግን ከውጤት ይልቅ ለስፖርታዊ ጨዋነትና ለፍትሐዊ ውድድር ቅድሚያ በመስጠት ዓለም አቀፍ አድናቆትን እያገኙ ይገኛሉ።
ጣልያን "በችሎታችን ካላለፍን በሌላው ስንብት አንገባም" የሚል ጠንካራ መልዕክት ለዓለም አስተላልፋለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#italy #fifa #worldcup2026 #iran #footballnews #sportsmanship #fairplay #azzurri #lucianobonfiglio #andreaabodi #worldcupupdate

ኢራንን በጣልያን ለመተካት እየታሰበ ነወ ተባለ
#ethiopia | በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ዋዜማ፣ የእግር ኳሱን ዓለም የሚያነጋግር አዲስ ውዝግብ ተነስቷል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መልዕክተኛ የሆኑት ፓኦሎ ዛምፖሊ፣ ፊፋ ኢራንን ከውድድሩ ውጪ አድርጎ በምትኳ ጣልያንን እንዲያስገባ መጠየቃቸው ታውቋል።
ምንም እንኳን የጣልያን ብሔራዊ ቡድን በሜዳ ላይ በነበረው የማጣሪያ ጨዋታ ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ማለፍ ባይችልም፣ ዛምፖሊ ግን ፊፋ በኢራን ላይ የቅጣት እርምጃ እንዲወስድና ለጣልያን ድንገተኛ ዕድል እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል። ጥያቄው በዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች የታጀበ እንደሆነ ቢገለጽም፣ በስፖርቱ ማህበረሰብ ዘንድ ግን ግርምትን ፈጥሯል።
ለጣልያን ደጋፊዎች ይህ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ቢመስልም፣ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ግን ከሳምንት በፊት በሰጡት ማረጋገጫ ኢራን በውድድሩ ላይ እንደምትሳተፍ በይፋ መናገራቸው ይታወሳል።
ፊፋ እስካሁን ድረስ በፖለቲካዊ ምክንያቶች ቡድኖችን ከመተካት ይልቅ በሜዳ ላይ ለተመዘገበ ውጤት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ይታወቃል።
ኢራን በፖለቲካዊ ምክንያቶች እንድትታገድና ጣልያን እንድትተካ የቀረበ ጥያቄ።
ቡድኑ በማጣሪያው ወድቆ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን በደብዳቤ የመግባት ዕድል እየተፈለገለት ነው።
ፕሬዝዳንት ኢንፋንቲኖ የኢራንን ተሳትፎ አስቀድመው አረጋግጠዋል።
ይህ ያልተጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ጫና በፊፋ ውሳኔ ላይ ለውጥ ያመጣ ይሆን ወይስ ኢራን በለመደችው መልኩ ጉዞዋን ትቀጥላለች? የሚለው ጉዳይ የብዙዎች መጠባበቂያ ሆኗል። ሆኖም የኳስ ወዳጆች እንደሚሉት "የሜዳ ውጤት በደብዳቤ አይቀየርም"።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #nbc
#fifa2026 #worldcup #italy #iran #gianniinfantino #footballnews #trumpenvoy #worldcupupdate #sportnews

2 months ago
🇮🇹 የጣልያን እግር ኳስ መርዶ
አዙሪዎቹ ለ16 ዓመታት ከዓለም ዋንጫ ተለዩ
#ethiopia | በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ስሟ በወርቅ የተጻፈው ጣልያን፣ ዛሬ የቀራት የትዝታ ማዕበል ብቻ ሆኗል።
እነ ማልዲኒ፣ ፒርሎ፣ ቡፎንና ባጂዮን ያፈራው የጣልያን ማህፀን፣ ዛሬ በታሪኩ አስከፊ የሚባለውን የውድቀት ዘመን እያሳለፈ ይገኛል።
ጣልያን ከ2018 እና ከ2022 በመቀጠል፣ አሁን ደግሞ ከ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውጪ ሆናለች። ይህም ለአንድ ትልቅ ሀገር ለ16 ዓመታት (አራት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች) ከመድረኩ መራቅ በታሪክ የመጀመሪያዋ ያደርጋታል።
በትናንትናው ወሳኝ የጥሎ ማለፍ ፍልሚያ፣ በፊፋ 71ኛ ደረጃ ላይ በምትገኘው ቦስኒያ ሄርዞጎቪና በመለያ ምት 4 ለ 1 ተሸንፋ ተሰናብታለች።
ሞይስ ኬን ጣልያንን መሪ ቢያደርግም፣ የባስቶኒ ቀይ ካርድና የቦስኒያ የአቻነት ግብ ጨዋታውን ወደ መለያ ምት ወስዶታል።
የጣልያን የመጨረሻው የዓለም ዋንጫ ትዝታ በ2014 ብራዚል ላይ ሱዋሬዝ ቺሊኒን የነከሰበትና ጣልያን በኡራጓይ ተሸንፋ ከምድብ የቀረችበት መራራ ምሽት ሆኖ ቀርቷል።
ከ2006ቱ ድል በኋላ ጣልያን በዓለም ዋንጫ መድረክ አንድም ስኬታማ ጉዞ ማድረግ አልቻለችም።
ጂናሮ ጋቱሶ የሉቺያኖ ስፓሌቲን መንበር ተረክቦ ሊታደጋት ቢሞክርም፣ እሱም እንደ ማንቺኒና ኮንቴ ሁሉ የአዙሪዎቹን ክብር ሳይመልስ አንገቱን ደፍቶ ወጥቷል።
ኩራሳኦና ጆርዳን ወደ አሜሪካ ሲያመሩ፣ አዙሪዎቹ ግን አሁንም ቤታቸው እንዲቀሩ ተፈርዶባቸዋል።
#getu #italyfootball #azzurri #worldcup2026 #gattuso #footballnews #worldcupqualifiers #italyvsbosnia #footballhistory #ጣልያን #እግርኳስ #ዓለምዋንጫ #መርዶ #ትዝታ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
2 months ago
የልብ ሕሙማን ሕፃናት ተስፋ
170 ሕፃናት በ45 ቀናት ውስጥ ነፃ ሕክምና ሊያገኙ ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ በልብ ሕመም ሳቢያ በሕክምና ወረፋ ላይ ላሉና ለከፋ ችግር ለተጋለጡ ሕፃናት ትልቅ የምስራች ተሰምቷል።
የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ (Heart to Heart Children's Aid) ፋውንዴሽን "በኢትዮጵያውያን የልብ ሐኪሞች - ለኢትዮጵያውያን ሕጻናት ልብ ጤና!!" በሚል መሪ ቃል፣ 170 ሕፃናትን በ45 ቀናት ውስጥ ለማከም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት መጋቢት 20/2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ፈጽሟል።
የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ሕክምናው ከሚያዝያ 12/2018 (April 20) ጀምሮ ባሉት 45 ቀናት ውስጥ ተጠናቆ ለሕፃናቱ ይደርሳል።
በስምምነቱ ላይ የጤና ሚኒስቴር፣ የጥቁር አንበሳና የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች፣ የኢትዮ ኢስታንቡል፣ ጣዝማና ኤሊዘር የልብ ሕክምና ማዕከላት እንዲሁም የዘርፉ ማህበራት በጋራ ለመሥራት ቃል ገብተዋል።
አቶ ብርሃን ተድላ (የፋውንዴሽኑ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ) እንደገለጹት፣ ፋውንዴሽኑ አስፈላጊውን የሕክምና ግብዓትና ወጪ በመሸፈን ተልዕኮውን ይመራል።
ከጣልያን አገር የሚመጣ የሕክምና ቡድንም የዚሁ ጥረት አካል ሲሆን፣ ለ50 ሕፃናት ሕክምና ይሰጣል።
ይህ ትብብር በሕክምና ወረፋ ብዛት ሕይወታቸው የሚያልፍ ሕፃናትን ለመታደግ ከመጣጣሩም በላይ፣ የሀገር ውስጥ የሕክምና ባለሙያዎችና ተቋማት ተቀናጅተው ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየ ነው።
#getu #hearttoheart #childrenshealth #cardiacsurgery #ethiopiahealth #humanitarianaid #ethioistanbulhospital #ministryofhealth #savinglives #addisababa #የልብሕክምና #ሕፃናት #በጎአድራጎት #ጤና #ጌጡተመስገን #getutemesgen

170 የልብ ሕሙማን ሕፃናትን በ45 ቀናት ውስጥ ነፃ ሕክምና ለመስጠት ስምምነት ተደረገ
የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ/ ፋውንዴሽን
"በኢትዮጵያውያን የልብ ሐኪሞች - ለኢትዮጵያውያን ሕጻናት ልብ ጤና!!" በሚል መሪ ቃል
በቅርቡ በአሜሪካን ሀገር ባሰባሰበው የገንዘብ ድጋፍ 170 የልብ ሕሙማን ሕፃናት ከሚያዝያ 12/2018 (April 20) ጀምሮ በ45 ቀናት ጊዜ ውስጥ ሕክምና ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት መጋቢት 20/2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ፈጸመ። በስምምነቱ የተሳተፉት:-
1.የጤና ሚኒስቴር፣
2.የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣
3. የቅዱስ ጻውሎስ ሆስፒታል፣
4. የኢትዮጵያ ልብ ማኀበር፣
5.የኢትዮጵያ የልብ ሕክምና ባለሙያዎች ማኀበር፣
6. የኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል፣
7.ጣዝማ ሜዲካል ኤንድ ሰርጂካል ስፔሻላይዝድ ሴንተር፣
8.ኤሊዘር የልብ ሕክምና፣ እንዲሁም የልብ ሐኪሞች ናቸው።
አቶ ብርሃን ተድላ የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ/ ፋውንዴሽን መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ እና የኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ባለቤት እንደተናገሩት ስምምነት ለፈፀሙ የጤና ተቋማት፣ ማኀበራትና ባለሙያዎች ያላቸውን አድናቆትና ክብር በመግለፅ ቀደም ሲል በኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ተጀምሮ የነበረው የልብ ሕሙማን ሕፃናትን የማከምና የመደገፍ ሥራ በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንሰ ኤይድ በኩል ተደራሽነቱን ለማስፋትና በሕክምና ተቋማት ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል የጋራ ስምምነት በመፈፀሙ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ስምምነቱ በሕክምና ወረፋ ረዥም ጊዜ ከማሳለፋቸው ጋር ተያይዞ ለሞት ጭምር የሚዳረጉ የልብ ሕሙማን ሕጻናትን ከመታደግ አንጻር የሚኖረው ትርጉም ላቅ ያለ መሆኑን እንዲሁም የኢትዮጵያ ጤና ተቋማትና ባለሙያዎች በትብብር እንዲህ አይነት ትልቅ ተልእኮ መወጣት እንደሚችሉ ምሳሌ የሆነ በመሆኑ ትብብሩን ልዩ እንደሚያደርገው ጠቅሰዋል።
በስምምነቱ መሰረት በ45 ቀናት ጊዜ ውስጥ 170 ሕፃናት ሕክምናውን የሚያገኙ ሲሆን ፋውንዴሽኑ አስፈላጊውን ግብዐቶችና ወጪ በመሸፈን እንዲሁም የዚህን ተልእኮ በመምራትና በማስተባበር ሥራዎችን የሚያከናውን ሲሆን በመንግስትና የግል ሆስፒታሎቹ በኩል እንደአቅማቸው ያሏቸውን ባለሙያዎች በማስተባበር ሕክምናው በመስጠት፣ የታካሚዎች የቆይታ ጊዜ አስፈላጊውን እንክብካቤና ክትትል ያደርጋሉ።
ኸርት ቱ ኸርት በተጨማሪም ለዚሁ ሰብዓዊ ስራ ከጣልያን ሀገር የሚመጣው የሕክምና ቡድን የዚሁ ስራ አካል ሲሆን በቡድኑ ከሚታከሙ 50 ሕፃናት መካከል ግማሹ በፋውንዴሽኑ በኩል የሕክምና ግብዐት ወጪን ጨምሮ የቡድኑ የኢትዮጵያ የሆቴል ቆይታ ወጪ እንደሚሸፈን ተናግረዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ተወካይ ዶ/ር አስቻለው ወርቁ በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ የመሰረተው በጋራ የመሥራት ትብብር በአርአያነት የሚታይና ሚኒስቴሩም አቅም በፈቀደ ሁሉ የሚደግፈው መሆኑን በመጥቀስ አበረታተዋል።
ዶ/ር አስቻለው አያይዘውም ጤና ሚኒስቴር አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
በስምምነቱ ላይ የተገኙ የረዥም ጊዜ ልምድ ያላቸው የሆስፒታል ሥራ አስፈፃሚዎች፣ ዳይሬክተሮች እና የሕክምና ባለሙያዎች በበኩላቸው የልብ ሕሙማን ሕጻናትን ለመታደግ በተፈጠረውና በጤና ዘርፍ በአርአያነት ጭምር ሊጠቀስ በሚችለው በዚህ ትብብር መደሰታቸውንና ለተፈጻሚነቱም የአቅማቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
አቶ ብርሃን ተድላ በመጨረሻም ለዚህ ታሪካዊ ትብብር ስኬት ከፍተኛ ድርሻ ላላቸው ሆስፒታሎች፣ የዘርፉ ማኀበራትና ባለሙያዎች ያላቸውን አድናቆትና ክብር በመግለፅ በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ ቦርድ እና በታካሚ ሕጻናቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

#fastmereja I የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ/ ፋውንዴሽን "በኢትዮጵያውያን የልብ ሐኪሞች - ለኢትዮጵያውያን ሕጻናት ልብ ጤና!!" በሚል መሪ ቃል በቅርቡ በአሜሪካን ሀገር ባሰባሰበው የገንዘብ ድጋፍ 170 የልብ ሕሙማን ሕፃናት ከሚያዝያ 12/2018 (April 20) ጀምሮ በ45 ቀናት ጊዜ ውስጥ ሕክምና ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት መጋቢት 20/2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ፈጸመ። በስምምነቱ የተሳተፉት:-

የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ድርጊት በቦስኒያ ቁጣን ቀሰቀሰ
የ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያን ተከትሎ የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ያሳዩት ደስታ በቦስኒያ ደጋፊዎችና ተጫዋቾች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቷል።
የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የሆኑት ዲማርኮ፣ ፒዮ ኤስፖዚቶ እና ቪካሪዮ የቦስኒያና ዌልስን የፍጹም ቅጣት ምት ውጤት ሲመለከቱ የነበረው ምስል በቪዲዮ ተቀርጾ ወጥቷል።
ተጫዋቾቹ ቦስኒያ ስታሸንፍ ያሳዩት ከመጠን ያለፈ ደስታ "ንቀትና እብሪት" ተብሎ ተፈርጇል።
የተጫዋቾቹ የመነጨው ከዌልስ ቦስኒያ ትቀለናለች የሚል መልዕክት አለው የሚል ትችት ተሰንዝሮበታል።
የቦስኒያ ደጋፊዎች በማህበራዊ ሚዲያ "ይህንን ንቀት በዜኒካ ሜዳ ላይ እናሳያችኋለን" ሲሉ ዝተዋል። ድርጊቱ የቀድሞው ተጫዋች ሌሌ አዳኒን ጨምሮ ብዙዎችን ያስገረመ ሲሆን፣ የጣሊያኑ አሰልጣኝ ጋቱሶም በጉዳዩ ዙሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።
ጣሊያን በቀጣይ ማክሰኞ ከቦስኒያ ጋር ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ለምታደርገው ጨዋታ ይህ ክስተት ጨዋታውን ከወዲው አነጋጋሪ አድርጎታል።

ዌልስ በታሪካዊ ሽንፈት ከዓለም ዋንጫ ውጪ ሆነች
በካርዲፍ ሲቲ ስታዲየም በተደረገው ወሳኝ ጨዋታ ዌልስ በቦስኒያ ሄርዞጎቪና በመለያ ምት ተሸንፋ የዓለም ዋንጫ ህልሟ ከሽፏል።
ዌልስ በዳንኤል ጀምስ ድንቅ የ51ኛው ደቂቃ ጎል መሪነትን ብትይዝም፣ ኤዲን ዜኮ በ86ኛው ደቂቃ በግንባር በመግጨት ቦስኒያን አቻ አድርጓል።
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እና ጭማሪው 30 ደቂቃ 1-1 በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት ተገብቷል።
በመለያ ምቱም ብሬናን ጆንሰን እና ኔኮ ዊሊያምስ መሳታቸውን ተከትሎ ቦስኒያ 4-2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
ይህ ውጤት ለአሰልጣኝ ክሬግ ቤላሚ እና ለደጋፊዎች ከፍተኛ የልብ ስብራት ሆኗል።
ቦሲኒያ በመጪው ማክሰኞ የአለም ዋንጫ ትኬትን ለመቁረጥ ጣልያንን በሜዳዋ ትገጥማለች።

3 months ago
ከ30 አመት በኃላ ሊደገም ነው ከ30 አመት በኃላ ህዝብ ለህዝብ ድንቅ ነሽ ኢትዯጵያ ሉሲን ለመስራት ዝግጅታቸውን አጠናቀው የበላይ ኮሚቴዎች ተፈራረሙ በተላያየ ምክንያት ተቋርጦ
የነበረውን የህዝብ ለህዝብ ድንቅነሽ ኢትዯጵያ (ሉሲ) እነደሚታወቀው የዛሬ ሰላሳ አመት በፊት በመላው አለም የሀገሪቱ ክፍል እነደታየ ይታወቃል አሁን ደግሞ ከሰላሳ አመት በኌላ በአሜሪካ የተለያዩ ስቴቶች እንዲሁም በካናዳ በአውስትራልያ በ እንግሊዝ በፈረንሳይ በ ጣልያን በመሳሰሉት የአለም ክፈሎች የሚታይ ሲሆን ይሄን ስራ በ አጭር ግዜ ውስጥ አጠናቀው ለህዝቡ ለማድረስ የበላይ ኮሚቴዎች የስምምነት ፊራማቸውን አስቀምጠዋል ።
የ ህዝብ ለህዝብ የበላይ ኮሚቴዎች
1 ኛ ሎሬት አያልነህ ሙላቱ የድርሰቱ ባለቤት
2 ኛ ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ የሙዚቃው አቀናባሪ
3 ኛ ርቲስት ተስፋየ ታየ የኪነ ጥበብ አስተባባሪ
4 ኛ አርቲስት ቴዎድሮስ ዘዋለ (ቴዲ ማቲ) የፕሮጀክቱ ዋና አሰረተባባሪ (ማናጀር ) ፕሮጀክቱ በጥበብ አደቨርታይዚንግ እና አኢቨንት የሚዘጋጅ ሲሆን ዝግጅቱ አጠናቆ ለመጨረስ ከ 4 ወር- 5 ግዜ የሚዎስድ ሲሆን በውስጡ የሚሳተፉ የኪነ ጥብበ ሰዎች (አርቲሰረቶች ከ 55-60 ሰዎች የሚሳተፉ ይሆናል
በቅርቡም ከ አጋር ድርጅቶቻቸው ጋር በመሆን ይፋዊ ጋዜጣዊይ መግልጫ የሚሰጡ ይሆናል::

የአድዋ ድል ጥያቄዎች። መልሳቹን ኮመንት ላይ አስቀምጡልን
1. እ.አ.አ በ1885 የተጠናቀቀውና አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት የተስማሙበት ታሪካዊ ጉባዔ ምን ይባላል?
ሀ) የፓሪስ ስምምነት
ለ) የበርሊን ጉባዔ
ሐ) የአድዋ ውል
መ) የለንደን ስብሰባ
2. የታሪክ ተመራማሪው ፖል ሄንዝ የአድዋን ድል ከአውሮፓ ተሰሚነት አንጻር እንዴት ይገልጹታል?
ሀ) ለአውሮፓውያን ተጨማሪ ኃይል የሰጠ ክስተት
ለ) የአውሮፓ ተሰሚነት የቁልቁለት ጉዞ መነሻ
ሐ) በኢትዮጵያና ጣልያን መካከል የተደረገ ቀላል ግጭት
መ) ለአውሮፓውያን የባህር በር የከፈተ ድል
3. "ቪቫ ምኒልክ! ቪቫ ኢትዮጵያ!" በማለት የኢትዮጵያን ድል ያወደሰው ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ ማን ይባላል?
ሀ) ኦቶ ቫን ቢስማርክ
ለ) ሪቻርድ ፓንክረስት
ሐ) ፊሊፖ ቱራቲ
መ) ሬይመንድ ጆናስ
4. ለአድዋ ድል ክብር ሲሉ 17 የአፍሪካ አገራት ያደረጉት ተግባር ምንድን ነው?
ሀ) የኢትዮጵያን የጦር ስልት መቅዳት
ለ) የሰንደቅ ዓላማ ቀለማቸውን ከኢትዮጵያ መውሰድ
ሐ) ዋና ከተማቸውን አዲስ አበባ ብለው መሰየም
መ) ለዳግማዊ ምኒልክ ሀውልት ማቆም
5. ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ በበርሊን ጉባዔ አፍሪካን ለመቀራመት ለተስማሙት ሦስት አገራት (ብሪታንያ፣ ፈረንሳይና ጣልያን) ለላኩላቸው "የሦስትዮሽ ስምምነት" የሰጡት ምላሽ ምን ነበር?
ሀ) ስምምነቱን በደስታ መቀበል
ለ) "እኔ በሌለሁበት የተወሰነውን አላውቅም" በማለት ውድቅ ማድረግ
ሐ) የተወሰነውን መሬት ለጣልያን አሳልፎ መስጠት
መ) ከአውሮፓውያን ጋር አብሮ ለመቀራመት ጥያቄ ማቅረብ
6. ስለ ዓፄ ምኒልክ ጀግንነት "በምድር ላይ ጀግና ጥራ ብትሉኝ ቀድሜ የምጠራው የንጉሥ ምኒልክን ነው" በማለት ምስክርነት የሰጡት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ማን ናቸው?
ሀ) አብርሃም ሊንከን
ለ) ጆን ኤፍ ኬኔዲ
ሐ) ባራክ ኦባማ
መ) ፍራንክሊን ሮዝቬልት
7. የናይጄሪያ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ናምዲ አዚኪዊ ስለ ኢትዮጵያ የሰጡት ትርጓሜ ምንድን ነው?
ሀ) ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት የተያዘች አገር ነች
ለ) ኢትዮጵያ ጥቁር ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርባት የታሪክ ዋቢ ነች
ሐ) ኢትዮጵያ የአውሮፓ አጋር ነች
መ) ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት ደካማ አገር ነች
8. ዓፄ ምኒልክ በኢትዮጵያ ካስተዋወቋቸው ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች መካከል የማይመደበው የቱ ነው?
ሀ) የመጀመሪያው ባንክ (አቢሲኒያ ባንክ)
ለ) የመጀመሪያው የባቡር መንገድ
ሐ) የመጀመሪያው የአውሮፕላን በረራ
መ) የመጀመሪያው ፖስታ ቤትና ስልክ
9. እንግሊዛዊው መሪ ዊንስተን ቸርችል የአድዋ ጦርነት በአውሮፓ ፖለቲካ ላይ ያመጣው ተጽዕኖ ምንድን ነው ይላሉ?
ሀ) የአውሮፓን ክብር ከፍ አደረገው
ለ) የጣልያን ዋጋ በዓለም ፖለቲካ ረገድ ወደ ታች እንዲወርድ አደረገ
ሐ) ለጣልያን ትልቅ ድል አስገኘ
መ) የቅኝ ግዛት መስፋፋትን አፋጠነ
10. ዓፄ ምኒልክን "ነገር ከዓይነ-ውኃ የሚያውቅ ብልህ ፖለቲከኛ (ዲፕሎማት)" ሲል የገለጻቸው የታሪክ ጸሐፊ ማን ነው?
ሀ) ፖል ሄንዝ
ለ) ሬይመንድ ጆናስ
ሐ) ሪቻርድ ግሪንፊልድ
መ) ፊሊፖ ቱራቲ

ቪቫ ምኒልክ! ቪቫ ጣይቱ!"
ከአድዋ ድል በኋላ የጣልያን ጋዜጦች ያሰፈሩት የውርደት ማስታወሻ
እንደሌላው ጥቁር ህዝብ ኋላ ቀር እና ቶሎ ይሸነፋል የተባለው የኢትዮጵያ ጦር ነጭን አሸነፈ ከሚባል የላም ወተት ነጭ ሳይሆን ጥቁር ነው ቢባል ብዙ ሰው ያምን ነበር።
ግን ሆነ ወተቱም ነጭ አይደለም ።ኢትዮጵያም ሊገዛት የመጣውን የጣልያን ጦርን አሸነፈች።
የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. የፀሐይ ጮራ የኤርትራን ተራሮች ተሻግሮ የአድዋን የምድር ገጽ ሲያሞቀው፣ በአውሮፓ ምድር “የማይሸነፍ” ተብሎ የሚታመነው የጄነራል ኦሬስቴ ባራቲዬሪ ጦር እንዲህ ባለ አሳፋሪ ሁኔታ ይበተናል ብሎ ያሰበ አልነበረም።
ነገር ግን ድል በኢትዮጵያ እጅ ነበረች። አድዋ ላይ የፈነዳው መድፍ አፍሪካን ብቻ ሳይሆን አውሮፓን በተለይም ጣልያንን ከእነ መሠረቷ አናወጣት።
ዜናው ሮም የደረሰው ዘግይቶ ቢሆንም፣ የደረሰበት ፍጥነትና ያስከተለው ድንጋጤ ግን በጣልያን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነበር። የሮም መንገዶች በለቅሶ፣ በቁጣና በጩኸት ተሞሉ፤ ጋዜጦችም የቀለም እንባ አነቡ።
የመጀመሪያዎቹ የቴሌግራም መልእክቶች ሮም ሲደርሱ የጣሊያን ጋዜጦችና ሕዝቡ ለማመን ተቸግረው ነበር። "እንዴት?" የሚለው ጥያቄ በየአምደ-ጋዜጣው ሰፈረ።
Il Corriere della Sera እና ሌሎች ታዋቂ ጋዜጦች በድንጋጤ ተዋጡ። ለአመታት "ኋላ ቀር" እና "ያልሰለጠነ" ተብሎ ሲሰበክለት የነበረው የአፍሪካ ጦር፣ የአውሮፓን ዘመናዊ ጦር አሳዶ መምታቱ የብሔራዊ ኩራት ውድቀት ሆነ።
የጣልያን ጋዜጦች እንደዘገቡት፣ ጦርነቱ የተጠናቀቀው በሽንፈት ብቻ ሳይሆን በውርደት ነበር። ከ70% በላይ የሚሆነው የጣልያን ጦር ተደምስሷል። 289 ከፍተኛ መኮንኖች፣ ብርጋዴር ጄነራል ዳቦርሚዳ እና አሪሞንዲን ጨምሮ በጦር ሜዳ ወድቀዋል። 6,000 የሚጠጉ የጣልያን ወታደሮች ሲገደሉ፣ 3,000 የሚሆኑት ደግሞ በምኒልክ እጅ ተማረኩ። ይህ አሃዝ ለጣልያን ጋዜጠኞች "የማይዋጥ መራራ ጽዋ" ሆነ ። አይክዱት ነገር ምን ያድርጉት። ያፈጠጠ እውነት ሆነ።
የድሉ ዜና ጣልያን ሲደርስ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ፍራንቸስኮ ክሪስፒ መንግሥት መረጋጋት ተሳነው። ሕዝቡ ወደ አደባባይ ወጣ። የሚገርመው ግን፣ ሕዝቡ የገዛ መንግሥቱን እየረገመ፣ የድል አድራጊዎቹን የምኒልክንና የጣይቱን ስም መጥራት መጀመሩ ነበር።
በሮም፣ በሚላን፣ በናፖሊና በፓቪያ ጎዳናዎች ላይ "Viva Menelik! Viva Taytu!" (ምኒልክ ይኑር! ጣይቱ ትኑር!) የሚሉ ድምፆች አስተጋቡ።
ይህ ጩኸት ለንጉሠ ነገሥቱ ካላቸው ፍቅር የመነጨ ሳይሆን፣ ልጆቻቸውን ለማይረባ ጦርነት ወደ ማገዶነት በላከው የክሪስፒ መንግሥት ላይ ያላቸውን ጥሪት ጥላቻ ለመግለጽ ነበር።
ጋዜጦች አንደፃፉት የባቡር ሐዲዶች ተነቃቅለዋል፣ የቴሌግራፍ ሽቦዎች ተቆርጠዋል። በተለይም ሴቶች "ልጆቻችንንና ባሎቻችንን አትውሰዱብን" በሚል በባቡር ሐዲድ ላይ በመጋደም ወታደሮች ወደ አፍሪካ እንዳይጓዙ አግደዋል።
L'Italia የተሰኘው ጋዜጣ እንዲህ ሲል ዘግቧል፦
"በፓቪያ የሚገኙ እናቶችና ሚስቶች ባቡር ጣቢያውን በመውረር ወታደሮችን ከባቡር ላይ ጎትተው አውርደዋል። ሐዲዱን ነቃቅለውታል። ፖሊሶችና ወታደሮች ቁጣውን መቆጣጠር አልቻሉም።"
የጣልያን ጋዜጦች ጄነራል ባራቲዬሪን "ከዳተኛ" እና "ደካማ" እያሉ መክሰስ ጀመሩ። Della Tribuna Illustrata የተሰኘው መጽሔት በወቅቱ በነበሩ ስዕላዊ መግለጫዎች የጦርነቱን አስከፊነትና የጣልያንን ሠራዊት መበተን ለሕዝቡ አሳይቷል። "የአቢሲኒያ ጀግኖች የጣልያንን ጦር እንደ ቅጠል አረገፉት" የሚሉ ዘገባዎች የአውሮፓን የበላይነት ስነ-ልቦና ሰባበሩት።
ንጉሥ ኡምቤርቶ ቀዳማዊ ልደታቸው ሊከበር ጥቂት ቀናት ሲቀሩት፣ አገሪቱ በሐዘን እንድትዋጥና የልደት በዓሉ እንዲሰረዝ አዘዙ። ጋዜጦች "ብሔራዊ የሐዘን ቀን" በማለት የፊት ገጻቸውን በበቀልና በውርደት ስሜት ሞሉት።
የእቴጌ ጣይቱ ሚና በጣልያን ጋዜጦች ዓይን
ለጣልያን ጋዜጠኞችና የታሪክ ጸሐፊዎች እጅግ አስገራሚው ነገር የሴት መሪ (የእቴጌ ጣይቱ ብጡል) በጦር ሜዳ መገኘት ነበር።
ጣይቱ ወታደሮቻቸውን እየመሩ፣ የመድፍ ተኩስ እየመጠኑና የውሃ መገናኛዎችን በመዝጋት የጣልያንን ጦር ለጥም መዳረጋቸው በጋዜጦች ላይ እንደ ትልቅ ተዓምር ተወርቷል።
"ይህች ሴት የጦር ጥበብን ከየት አመጣችው?" የሚሉ ጥያቄዎች በጋዜጦች አምዶች ላይ ተስተውለዋል።
የአድዋ ሽንፈት የክሪስፒን መንግሥት ጠራርጎ ወሰደው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዱ። ጣልያን በታሪኳ አይታው የማታውቀውን የዲፕሎማሲ ውርደት ተከናነበች። ጥቅምት 1889 ዓ.ም. የተፈረመው የአዲስ አበባ ውል፣ ጣልያን የኢትዮጵያን ሙሉ ነፃነት እንድታውቅና የወጫሌን ውል እንድትሰርዝ አስገደዳት።
የብሪታኒያው ጦር ዘጋቢ አውገስተስ ዊልዴ በወቅቱ እንደጻፈው፦
"ከቀትር በኋላ የአድዋ ጦርነት ድምፅ ሲጠፋ፣ የጣልያን ጦር ተስፋ ቆርጦ ይሸሽ ነበር። ሽብር በኤርትራ ምድር ነገሠ። በዕለቱ ማብቂያ ላይ የኢትዮጵያ ጦር አሁንም 3 ሚሊዮን ጥይት በእጁ ይዞ ነበር። ጣልያኖች ግን አንድም ቀን ለመዋጋት የሚያስችል አቅም አልነበራቸውም።"
የአድዋ ድል በጣልያን ጋዜጦች ላይ የታተመው በውርደት፣ በለቅሶና በቁጣ ቢሆንም፣ ለቀሪው ዓለም ግን የነፃነት ብርሃን ነበር። የአድዋ ድል የአውሮፓውያንን "የማይሸነፍነት" ተረት ሰባብሮ፣ የፓን-አፍሪካኒዝም እና የጥቁር ሕዝቦች ኩራት መሠረት ሆኗል።
ዛሬም ድረስ አድዋ ሲነሳ፣ የሮም ጋዜጦች የፈሰሰው እንባና የኢትዮጵያ ጀግኖች ያንጸባረቁት ድል በታሪክ ገጾች ላይ በደመቀ ቀለም ተጽፎ ይገኛል።

ከቤተ መንግስት ዘበኝነት እስከ አድዋ ድል የጥበብ ማማ ፡ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (አባ መላ)
ይህ ታሪክ ስለ አንድ ተራ ሰው አይደለም፤ ይህ ታሪክ ስለ አንዲት ሀገር ትንሳኤ፣ ስለ አንድ ምርኮኛ ጀግንነት እና ስለ አንዲት ነፍስ ፍጹም ታማኝነት የሚተርክ የኢትዮጵያዊነት ማህተም ያለው ዛሬ አድዋ ድልን ስናከብር በፍፁም የማንረሳው ለወደፊትም የምንዘክረው ሰው ታሪክ ነው።
ላለፉት 130 አመታት እንዲሁም ዛሬም ድረስ በአድዋ ተራሮች ላይ የሚስተጋባው የድል ዝማሬ የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ የጥበብና የደም ውጤት አለበት። ይህን በኩራት እንናገራለን።
በ1840ዎቹ አጋማሽ በደቡብ ሸዋ ጨቦ ምድር ወጣቱ ሀብተ ጊዮርጊስ በጦርነት ተማርኮ ወደ አፄ ምኒልክ ግቢ ሲመጣ፣ እግሩ ላይ የነበረው ሰንሰለት እንጂ ልቡ ውስጥ ያለው እሳት አልታየም ነበር።
ምርኮኛ ሆኖ የገባው ወጣት፣ በቤተመንግስት ዘበኝነት ተመደበ።
አንድ ምሽት አፄ ምኒልክ በቤተመንግስቱ ቅጥር ግቢ ሲዘዋወሩ፣ ይህ ወጣት ዘበኛ በብርድ እየተገረፈ ግን ደግሞ እንደ ቋጥኝ ጸንቶ በንቃት ሲጠብቅ አዩት። ንጉሡ ቀርበው "አንተ ልጅ፣ አይበርድህም ወይ?" ሲሉ ጠየቁት። ወጣቱም ቀና ብሎ "የንጉሡ ትዕዛዝ ከብርዱ በላይ ያሞቀኛል" ብሎ መለሰ።
ምኒልክ በዚያች ቅጽበት በወጣቱ አይን ውስጥ የታማኝነትን ጥልቅ ባህር አዩ። ከዚያ ቀን ጀምሮ ሀብተ ጊዮርጊስ ከዘበኝነት ወደ ቅርብ አሽከርነት፣ ከቅርብ አሽከርነት ወደ መላተኛ መካሪነት ተሸጋገረ።
ባለማወቅ እና በትዕቢት ጣልያን 1888 ዓ.ም ኢትዮጵያ ለመግዛት መጣች። በዚህም ኢትዮጵያ በታሪኳ ታይቶ የማይታወቅ የህልውና አደጋ ተደቀነባት። የጣሊያን ጦር ዘመናዊ መሣሪያ ታጥቆ፣ የአፍሪካን ኩራት ለመቅበር ወደ አድዋ መጣ። በዚህ ጊዜ ነበር ሀብተ ጊዮርጊስ "አባ መላ" የሚለውን ስም በታሪክ መዝገብ ላይ በደማቅ ቀለም የጻፉት።
አባ መላ ከመቶ ሺህ በላይ የሚሆን ሰራዊት፣ አዝማቾችና ፈረሶች ከሸዋ እስከ አድዋ ሲጓዙ ሳይራቡና ሳይጠሙ እንዲደርሱ ማድረግ ከጦርነቱ በላይ ከባድ ነበር። ሀብተ ጊዮርጊስ ግን በየመንገዱ ስንቅ የሚያከማቹ "ጎተራዎችን" በማዘጋጀት፣ ሰራዊቱ በረሃብ ተዳክሞ ለጠላት እጅ እንዳይሰጥ አደረጉ።
ይህ ብርቱ ሰው ጣሊያኖች የኢትዮጵያን ሰራዊት ቁጥርና አቅጣጫ ለማወቅ ደፋ ቀና ሲሉ አባ መላ ግን የራሳቸውን ሰላዮች ወደ ጣሊያን ምሽግ በመላክ፣ የሀሰት መረጃ እንዲደርሳቸው አደረጉ። ጣሊያኖች "የኢትዮጵያ ጦር ተራርቋል፣ ተጣልቷል፣ ስንቅ አልቆበታል" የሚል የሀሰት መረጃ እንዲያምኑ በማድረግ ወደ ወጥመዱ እንዲገቡ መሯቸው።
በዚህም አላበቁም ጦርነቱ ሲለኮስ ሀብተ ጊዮርጊስ በስተጀርባ የሚመክሩ ብቻ አልነበሩም። "ፊታውራሪ" ማለት የጦር ግንባር ቀደም መሪ ማለት ነው። ጥይት እንደ በረዶ በሚዘንብበት፣ መድፍ ምድሩን በሚያናውጥበት በዚያ አስፈሪ ሰዓት፣ ሀብተ ጊዮርጊስ በፈረሳቸው ላይ ሆነው "ለሀገራችሁ! ለክብራችሁ!" እያሉ ሰራዊቱን በመምራት የጠላትን ምሽግ ሰባበሩ።
በአድዋ ድል ኢትዮጵያ ተቀዳጀች። ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ከፍ አለች። ሀብተ ጊዮርጊስም የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጦር ሚኒስትር ሆኑ።
ከታሪካቸው መሀል እጅግ ልብ የሚነካ የሚሆነው ከአፄ ምኒልክ ጋር የነበራቸው ቁርኝት ነው።
አፄ ምኒልክ በታመሙበትና አልጋ ላይ በዋሉበት አስቸጋሪ ወቅት፣ ቤተመንግስቱ በሴራና በፖለቲካ ትኩሳት ሲናጥ፣ ሀብተ ጊዮርጊስ እንደ አጥንት ለምኒልክ ጸኑ። ንጉሡ መናገር ባቃታቸው ጊዜ እንኳን፣ የሀብተ ጊዮርጊስን እጅ ይዘው አይን አይናቸውን እያዩ ይጽናኑ ነበር።
ታኅሣሥ 3 ቀን 1906 ዓ.ም. ታላቁ ንጉሥ አፄ ምኒልክ አረፉ። ሀብተ ጊዮርጊስ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ፣ ግን አልደከሙም። "ንጉሡ ቢሞቱም ሀገር መሞት የለባትም" ብለው ለ13 ዓመታት ኢትዮጵያን ጠበቁ። ንግሥት ዘውዲቱና አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን (ኃይለ ሥላሴ) በሰላም ሀገሪቱን እንዲመሩ የጀርባ አጥንት ሆኑ።
ታኅሣሥ 3 ቀን 1919 ዓ.ም.። አፄ ምኒልክ ካረፉ ልክ በ13ኛው ዓመት፣ በዚያችው ቀንና በዚያችው ሰዓት ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስም አረፉ። ይህ የአጋጣሚ ጉዳይ ሳይሆን፣ የፍጹም ታማኝነት መንፈሳዊ ትስስር እንደሆነ የታሪክ ጸሐፊዎች ይገልጻሉ።
በቀብራቸው ቀን በአዲስ አበባ ታይቶ የማይታወቅ የልቅሶ ድምፅ ተሰማ። የጦር ሰራዊቱ፣ ድሆች፣ እናቶችና ህፃናት "አባ መላ ወዴት ሄዱ?" እያሉ ምድሩን በእንባቸው አጠቡት።
ባለቤታቸው ወይዘሮ አልታየ ወርቅ፣ የባላቸውን ራስ ወርቅና የክብር ልብስ ይዘው በሀዘን ሲንሰቀሰቁ፣ የኢትዮጵያ ትልቅ ተራራ የተናደ መሰለ።
ታላቁ የቅኔ አዋቂ ተሰማ እሸቴ እንዲህ ብሎ ተቀኘ፦
"ከምኒልክ ይዞ እስካሁን ድረስ፣
የአልታየ ሞት ሆነ የሀብተ ጊዮርጊስ።"
(ትርጉሙ፡- ሀብተ ጊዮርጊስ ምኒልክ ከሞቱበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በቁም ሞተው ነበር፤ ዛሬ ግን ያ የታየው ሞታቸው እውነት ሆነ።)
ማንነትና መነሻ ስኬትን አይወስነውም። ታማኝነትና ብልህነት ካለ፣ ከዝቅተኛው ስፍራ ተነስተን የሀገር መሪ መሆን እንደምንችል አባ መላ ትልቅ ምስክር ናቸው።
በ"አባ መላ" ጥበብ ጦርነትና ግጭት ሁልጊዜ በጉልበት አይፈታም የሚል ፍልስፍና ተምረናል። ብልሃትና ማስተዋል ለአባ መላ ከሺህ መድፎች በላይ ኃይል ነበራቸው።
ሀብተ ጊዮርጊስ የኦሮሞና የጉራጌ ደም ቢኖራቸውም፣ ህይወታቸውን የሰጡት ግን ለኢትዮጵያ አንድነት ነው። ዘር ሳይለዩ፣ ሃይማኖት ሳይከፍሉ ለጥቁር ህዝብ ነፃነት ቆሙ።
ዛሬ በአዲስ አበባ "ሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ" ላይ ስትቆም፣ ያ ድልድይ በድንጋይ ብቻ የተገነባ እንዳይመስልህ። ያ ድልድይ የተገነባው በአባ መላ አጥንት፣ በደምና በጽኑ ታማኝነት ላይ ነው።
ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ፤ አንተ የጥበብ ማማ፣ አንተ የታማኝነት መዝገብ፣ አንተ የአድዋ ድል ቀኝ እጅ! ስምህ ለዘላለም በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ህያው ሆኖ ይኖራል።

በጣሊያን በቲቪ እግር ኳስ ሲያይ የነበረው ባል በገዛ ሚስቱ በቢላ ተወጋ
በጣሊያን ኔፕልስ ከተማ አንድ የ40 ዓመት የናፖሊ ደጋፊ በገዛ ሚስቱ ተወግቶ ሆስፒታል ገባ።
ግጭቱ የተነሳው ባለፈው እሁድ ናፖሊ ከአታላንታ ጋር ሲጫወቱ ባልየው በዳኛው ውሳኔ ተበሳጭቶ በከፍተኛ ድምጽ ሲሳደብ ነበር።
ሚስትየው ግን ስድቡ ለእሷ የተሰነዘረ መስሏት በመሳሳቷ በመጀመሪያ መቀስ፣ በመቀጠልም የወጥ ቤት ቢላ በመጠቀም ባሏን ወግታዋለች።
ግለሰቡ በደረሰበት ጉዳት ሆስፒታል ገብቶ ህክምና እየረደረገለት እና በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የ35 ዓመቷ ሚስት ደግሞ በቁጥጥር ስር ውላለች ሲሉ የጣልያን መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑ ዘግበዋል።

አድዋ የሚያስደንቀኝ ድልና ገድል ነው
ዓድዋ የዳዊትና ጎልያድ ተረክ ዳግም የተኖረበት የታሪክ እጥፋትም ነው፡፡ በመውረርና መዝረፍ፣ በቴክኖሎጂና ሴራ፣ በዓለማቀፍ ልማዶችና ዲፕሎማሲ የጠበደለችው ጣልያን በገዛ ሜዳዋ ላይ፣ ሀገራቸውን በሚወዱና በተለይም በጨበጣ ውጊያ እጅግ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የአቢሲኒያ ጀግኖች ጉድ ሆነች፡፡
ብዙ ጊዜ “በጦርነቱ ብንሸነፍስ ኖሮ?” ብዬ እጠይቅና የእነዚያ ጀግኖች ውለታ ልክ ያጣብኛል፡፡
እውነት ግን ብንሸነፍስ ኖሮ?
ሬሞን ጄናስ የተባለ ፃሐፊ “የአድዋ ድል የአፍሪካን ቀለም የወሠነ ድል ነው” ያለው በትክክል ድሉን ሳይገልፀው አይቀርም፡፡
አድዋ ላይ እነዚያ የአፍሪካ አንበሶች የነጭ ወራሪዎችን ማሸነፍ ቢሳናቸው ኖሮ እንደህንድና ሞዛምቢክ ሁሉ የመላው አፍሪካ ቅኝ ግዢ በ40 እና በ80 ዓመታት ተጠቃልሎ በነፃነት ባልተተካ ነበር፡፡ የማሸነፍ ተምሳሌት የሌለው የቅድመ አድዋ አፍሪካዊ በፍፁማዊ የበታችነት ተንበርክኮ ነበር፡፡
እነኮንጎና መሠል የምዕራብ አፍሪካ ሐገራትማ የነጠረ የዘር ጭፍጨፋን አስተናግደውም ኮሽታን ማሠማትም ተስኗቸው ነበር፡፡
የአድዋ ድል የጥቁሮችን የዓለም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ተካፋይና ባለቤትነት ጮሆ መናገር ባይችል ኖሮ በካሪቢያን የሚገኘው የጥቁር ማሕበረሠብ ማርከስ ጋርቬይን መውለድ የሚያስችል ማሕፀን ባልነበረው ነበር፡፡
የማርከስ ጋርቬይም ሆነ ቀጥሎ የመጡት የፓን አፍሪካን ንቅናቄዎች ሁሉ የጉልበትና የተስፋ ምንጭ የአድዋ ድል ነበር፡፡
የአብዛኞቹን የአፍሪካ ሐገራት ሠንደቅ ዓላማዎችን ተመልከቱ …..
ምንጫቸው በቀጥታ የአድዋ ድል እናቷ ኢትዮጵያ ነች!
የነጻነትና ፍቅር መቀንቀኛ ሬጌም ሆነ የጥበብ ባለሟሎቿ የሐሳብ ምንጭ ኢትዮጵያችን የመሆኗ ብቸኛ ሚስጥር የአድዋው ድል ነው፡፡
ቦብ ማርሌይ፣ ቡጁባንታን፣ ካፕልተንና ፒተር ቶሽ፣ በርኒንግ ስፒርና ሲዝላ ካላንጄን የመሳሰሉት ከባባድ ሚዛን የሬጌ ሙዚቀኖች ሁሉ የታላቅነታቸው ምንጭ ኢትዮጵያ ትመስል ሁሉም አቀንቅነውላታል፡፡
በተለይ በተለይ ቦብ ማርሌይ exodus (ወደሐገር መመለስ) የተሠኘውን ሙዚቃውን መነሻው ያደረገው ኢትዮጵያን ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር የፊደላት አጣጣሉን በኢትጵያ ፊደሎች ዲዛይን አሠርቶም ነበር ለገበያ ያቀረበው፡፡
እንዲሁም እጅግ ዝነኛ ስራው የሆነውን “ዋር” የተሠኘ ሙዚቃ የሠራው ቀዳማዊ ሃይለስላሴ በተባበሩት መንግስታት ያደረጉትን ንግግር ወደ ግጥም በመቀየር ነበር ፡፡
በአድዋ ተራሮች ሽንፈትን ቀምሠን ቢሆን ኖሮ የማታ የማታ እንኳን ነፃነቱ ቢገኝ ገዥዎቻችን ጥለውልን በሚሄዱት የብሄር መርዝ እንደሶማሊያና ሱዳን፣ እንደሁቱና ቱትሲ፣ እንደኮጎ ጦርነቶች እርስበርስ በተፋጀን ነበር፡፡ (ገባ ብለው ወጣ ላሉት እንኳን ስንት የጨቋን ተጨቋኝ ተረኮችን ቀብረው እስካሁን ደም ይፈሳል)
በሌላ በኩል እንደምዕራብ አፍሪካውን የኢኮኒሚ ስሪታችንን “ጥሬ እቃን መላክ ብቻ” ላይ እንዲወሠን በማድረግ መከራ ያበሉን ነበር፡፡ ወታደራዊ ጣልቃገብነት፣ የመንግስት ግልበጣ ሴራዎች፣ የእጅ አዙር ጫናዎች ሁሉ ተረባርበው ባደቀቁን ነበር፡፡
የኔ የምንለውን ባሕል አራግፈው በ“ፍራንቻይዜሽን” ማዕበል በ”ኢስት አፍሪካን ኢታሊ” ቅኝት አፍርሠው በገነቡንም ነበር፡፡
“አበበ” መባል፣ “ትርሐስ” መሠኘት፣ “ኩርፋ” ተብሎ መጠራት የነፃነታችን ትሩፋት ነው
“ጥምቀትን” ማክበር፣ በ“አሸንዳ” መተጫጨት፣ “ጀፎረ” ላይ መምከር የአድዋ ድል ውለታ ነው በአማርኛ መዝፈን፣ በኦሮምኛ ማስታረቅ፣ በወላይትኛ መማር የአድዋ ድል ያስቀረልን ንዋያችን ነው ።
ዝዋይ ላይ አሳ እንድናሰግር፣ ድሬ ሺቲ እንድንገዛ፣ መቀሌ ቤት እንድንሠራ ….. የጀግኖች አባቶቻችንን ድል አስፈልጎት ያውቃል!
አሸናፊ መለሠ
ደራሲና የኮሙኒኬሽን ባለሙያ

አድዋ፡ የነፃነት ማማ ወይስ የድህነት ጥላ? — የጀግኖች አጥንትና የትውልዱ ቁርሾ
የካቲት 23 ቀን፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ተራሮች በባሩድ ጭስ ተሸፍነው የጥቁር ሕዝብን የነፃነት ፋና ባበሩበት በዚያ ታሪካዊ ስፍራ፣ ዛሬም የድል በዓል ይከበራል። ነገር ግን የዘመናት የአድዋ አከባበራችን ላይ ኩራት ብቻ ሳይሆን የሚፋጅ "ቁጭት" አለበት።
ነጭ ጋቢ ለብሰው፣ በገንቦ ፀጉራቸው ላይ ሰንደቅ ዓላማ አስረው የመጡት አባቶች አይን ውስጥ የሚታየው የታሪክ ድል ሳይሆን፣ "ለዚህ ነበር የሞቱት?" የሚል መሪር ጥያቄ ነው።
1. የቬትናም ትንሣኤና የእኛ "የቆመ ሰዓት"
የታሪክ ምሁሩ ኤሪክ ሆብስባውም እንደሚለው፣ "ብሔርተኝነት ያለ ኢኮኖሚ ግንባታ ባዶ ቤት ነው"። ቬትናም በፈረንሳይና በአሜሪካ የቦምብ ናዳ ስትታመስ፣ ኢትዮጵያ በነፃነት አየር ትተነፍስ ነበር። ቬትናሞች እንደ እኛ "አልገዛም" ብለው ተዋግተዋል፤ መሬታቸውን በደማቸው አጥበዋል።
ልዩነቱ ግን እዚህ ላይ ነው፦ ቬትናም ከጦርነቱ ማግስት "ዶይ ሞይ" (Doi Moi) የተሰኘ የኢኮኖሚ ተሃድሶ አውጃ፣ ጠመንጃዋን አውርዳ ማረሻና ማሽን ጨበጠች። ዛሬ ቬትናም የዓለም የንግድ ማዕከል ስትሆን፣ የአድዋ ጀግኖች የልጅ ልጆች ግን አሁንም በድህነት አዙሪት ውስጥ ናቸው። አድዋ ላይ ቆመው የሚቆጩት አባቶች "እኛ ቀድመን ነፃ ወጣን፣ እነሱ ግን ቀድመው ከረሃብ ወጡ" እያሉ በትር የማያውቅ ቁጭት ውስጥ ይገባሉ።
2. የቻይናው ተአምርና የ"ማኪያቬሊ" ምፀት
የፖለቲካ ሳይንስ ፈላስፋው ኒኮሎ ማኪያቬሊ "ታላቅነት የሚለካው በድል ሳይሆን ድሉን ተከትሎ በሚመጣው ሰላምና ብልጽግና ነው" ይላል። ቻይና በ1970ዎቹ መጨረሻ ላይ የነበረችበት የድህነት ደረጃ ከኢትዮጵያ የባሰ ነበር። ነገር ግን ቻይና በአንድ ትውልድ ውስጥ 800 ሚሊዮን ሕዝቧን ከድህነት አወጣች።
እኛ ግን በአድዋ ድል ማግስት የነበረንን የአንድነት መንፈስ በውስጥ ሽኩቻና በስልጣን ጥመኝነት አበላሸነው። ፈላስፋው ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚለው፣ ለሀገር እድገት "ጠንካራ መንግሥት፣ የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት" ያስፈልጋሉ። ኢትዮጵያ ግን ድሏን ወደ ተቋማዊ ግንባታ መለወጥ አቃታት። ቻይና ታሪኳን ለነገ መወርወሪያ (Springboard) አደረገችው፤ እኛ ግን ታሪካችን ላይ ተኝተን መቃዠትን መረጥን።
3. የነፃነት ትርጉም ሲፈተሽ
ፍሬንዝ ፋኖን "The Wretched of the Earth" በሚለው መጽሐፉ፣ ነፃነት ማለት ባንዲራ መቀየር ብቻ ሳይሆን፣ የሰውን ልጅ አእምሮ ከባርነትና ከድህነት ማላቀቅ እንደሆነ ያስጠነቅቃል። አድዋ ያመጣልን ነፃነት "መሬትን" እንጂ "ሰውን" አላበለፀገም የምንለው ለዚህ ነው።
ታዋቂው ፈላስፋ ዣን ዣክ ሩሶ "ሰው ነፃ ሆኖ ይወለዳል፣ ነገር ግን በየቦታው በሰንሰለት ታስሯል" ይላል። ዛሬ ኢትዮጵያዊያን ከቅኝ ግዛት ነፃ ብንሆንም፣ በድህነት፣ በበሽታና በስደት ሰንሰለት ታስረናል። አድዋ ላይ የወደቁት ጀግኖች አጥንት የሚጮኸው ለዚህ ነው። እነሱ የሞቱት ልጆቻቸው በዓለም ፊት አንገታቸውን ደፍተው እንዲለምኑ አልነበረም።
4. የሽማግሌዎች ቁርሾ፡ "ሰው ለሰው ተኩላ..."
በአድዋ በዓል ላይ የሚገኙት እነዚያ አዛውንቶች ድምፃቸው እየተንቀጠቀጠ የሚናገሩት አንድ መሪር እውነት አለ። "ልጆቻችን እርስ በርሳችሁ ተላለቃችሁ፣ ሀገሪቱን አደከማችኋት" የሚል ወቀሳ። ፈላስፋው ቶማስ ሆብስ እንደሚለው "ሰው ለሰው ተኩላ ነው" የሚለው አባባል ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ነግሷል።
አያቶቻችን ጣልያንን ድል ያደረጉበትን መሣሪያ፣ ዛሬ እኛ እርስ በርሳችን ለመጨራረስ እንጠቀምበታለን። ይህ ነው እንግዲህ ለጀግኖቻችን የምንሰጠው ክብር? ቻይናና ቬትናም ልዩነቶቻቸውን በብሔራዊ ዓላማ ስር ሲያቀልጡ፣ እኛ ግን ልዩነቶቻችንን መሣሪያ አድርገን ድህነታችንን አራዘምን።
5. ያልተቋጨው የቤት ሥራና የመፍትሔ አቅጣጫ
አድዋ "ያልተበላ የድግስ ማዕድ" ነው። አያቶቻችን ማዕዱን አዘጋጅተውልን አለፉ፤ እኛ ግን በጠረጴዛው ዙሪያ ስንጣላ ማዕዱ ተበላሸ። የታሪክ ምሁራንና ፈላስፎች እንደሚስማሙት፣ የኢትዮጵያ እውነተኛ ነፃነት የሚታወጀው ዜጎቿ ከራብና ከስደት ሲላቀቁ ብቻ ነው።
የኢኮኖሚ ክተት፡ ልክ እንደ ቬትናም "ዶይ ሞይ"፣ እኛም ከጦርነት ይልቅ የኢኮኖሚ ነፃነት አዋጅ ማወጅ አለብን።
ብሔራዊ እርቅ፡ በአድዋ የታየውን "የአንድነት መንፈስ" በዘመናዊ ፖለቲካ ውስጥ መተግበር።
የጀግኖች አጥንት ዕረፍት
የአድዋ ጀግኖች አጥንት ዛሬም ድረስ በሰሜኑ ተራሮች ላይ ይጮኻል። "እኛ አንድ ሆነን ወራሪን አሸነፍን፤ እናንተ ግን አንድ ሆናችሁ ድህነትን ማሸነፍ አቃታችሁ?" የሚሉ ይመስላል።
ሽማግሌዎቹ ከአድዋ ተራራ ሲወርዱ አይናቸው በእንባ ይሞላል። ያ እንባ የደስታ ብቻ ሳይሆን፣ "ሀገሬ መቼ ነው ከድህነት ነፃ የምትወጣው?" የሚል የናፍቆት እንባ ነው።
ታሪክን ማክበር ያለብን በበዓል ድምቀት ብቻ ሳይሆን፣ የታሪክን ስህተት በማረም መሆን አለበት። ከአድዋ የተረከብነውን ነፃነት ወደ ዳቦ፣ ሰላምና ብልጽግና መለወጥ ካልቻልን፣ ድሉ ለእኛ "የታሪክ ሸክም" ከመሆን አያልፍም።

4 months ago
የካቲት 12, ለምን ይከበራል?
•+============+.
በ1929 ዓ ም የጣልያን ወረራ ገነተ ልዑል ተብሎ በሚታወቀው የንጉሱ ቤተመንግስት (የዛሬው 6ኪሎ ዋና የዩኒቨርስቲ ግቢ) የተነሳው አመጽ ለብዙ ኢትዮጵያውያን እልቂት ምክንያት በመሆኑና በአካፋ በመትረየስ በሳንጃ የብዙ ሰው ህይወትን ያለቀበት እለት ስለሆነ በዚህም ዙሪያ ለመታሰቢያ የካቲት 12 ሆስፒታል እንዲሁም የካቲት 12 ትምህርትቤት መኖሩ ይታወቃል:: ቤተክርስቲያንም በዚህች እለት ጸሎተ ምህላ እና ጸሎተ ፍትሐት በማድረግ በታቦተ ንግስ ቀኑን ትዘክረዋለች::
ከ71 ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ቤተመዘክር ውስጥ ለዘመናት በሙዚየሙ ሲኖር የነበረው የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ከገባ እለት ጀምሮ ማለትም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በምዕመናኑ እና በካህናቱ ጥያቄ ለዘጠነኛ ጊዜ ዘንድሮ በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ወቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ይከበራል:: የንጹሃንን ነፍስ አምላከ አበው እግዚአብሔር ይማርልን::
በዚሁ ሳምንት የፊታችን የካቲት 14 ቅዳሜ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ደግሞ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ የማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም ገዳም አጭር ዶክመንተሪ ምርቃትና በአበው መነኮሳት ጥሪ ሰፊ ጉባኤ ተዘጋጅቷል::
በመርሐ ግብሩ መነኮሳቱ ከሚያገለግሉበት አፄ ፋሲለደስ ካሰራው የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በተጨማሪ ወደ ገዳሙ የሚመጡ ምእመናን/ት በተለይ ወደ ግዝት ቅፅር የማይገቡ ሴቶች የሚገለገሉበት በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና በአቡነ ያሳይ ስም የቤተ ክርስቲያን ግንባታ እንዲሁም ለሚከናወኑት የልማት ሥራዎ ፍኖተ ካርታ ይፋ ይደረጋል።
ለአገልግሎቱ መሳካት ማኅበረ መነኲሳቱ ዘወትር እግዚአብሔር አምላካችንን በጸሎት እያሳሰቡ ሲሆን ፤ እርስዎ በመርሐ ግብሩ እንዲሳተፉ እና በረከት እንዲያገኙ በማሰብ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በማኅበረ መነኲሳት እና በገዳሙ ስም እናቀርባለን::
ድጋፍ ለማድረግ:
ንግድ ባንክ: 1000731553134
ስልክ: -
0918240454
0906632367
0921612653
Website: www.abuneyasay.com
Online Donation link: https://chapa.link/donatio...
አምላከ አቡነ ያሳይ ኢትዮጵያን ይባርክ!
4 months ago
🌿 እንኳን ወደ ጋርደን ሒልስ በደህና መጡ
Escape to the Extraordinary ✨
#ethiopia | በአዲስ አበባ እምብርት፣ የካ ኮረብታን ተንተርሶ የተገነባው ጋርደን ሒልስ ሆቴል እና ስፓ፤ ከተፈጥሮ ጋር የተሳሰረ ቅንጦትን ሊያስተዋውቅዎ ዝግጅቱን ጨርሷል።
የምሥራች ✨
በዓለም አቀፍ ባለሙያዎች የተደራጀ - ከከተማው ግርግር ተነጥለው፣ በንጹህ አየር እና በወፍ ዝማሬ ታጅበው መንፈስዎን የሚያድሱበት አዲሱ "የአዲስ አበባ ማረፊያዎ"ነ አዘጋጅተናል።
🍽 Culinary Excellence ✨
በታዋቂው "La Tavola" ሬስቶራንታችን የጣልያን የምግብ ጥበብን (Authentic Italian Cuisine) ከልዩ የቡና እና ኬክ ያጣጥማሉ።
🛏 Luxury Living ✨
የከተማዋን እና የተፈጥሮን እይታ የሚሰጡ 40 ዘመናዊ እና ምቹ የመኝታ ክፍሎች (Suites)።
bi Rejuvenation:
አካልና መንፈስን የሚያድስ ስፓ እና ዌልነስ ማዕከል።
🎉 Grand Events ✨
ከ10 እስከ 300 እንግዶችን ማስተናገድ የሚችሉ፣ ለሰርግም ሆነ ለኮርፖሬት ስብሰባዎች የተዘጋጁ ዘመናዊ አዳራሾች።
🥂 You Are Invited!
( በክብር ተጋብዘዋል!)
ለሆቴል ኢንዱስትሪው፣ ለቱሪዝም፣ ለኪነ-ጥበብ እና ለሚዲያ ቤተሰቦች እንዲሁም ለክቡራት ደንበኞቻችን በሙሉ፤ በዚህ ታሪካዊ የምርቃት በዓል ላይ ተገኝተው የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ በአክብሮት ጠርተናል።
📅 ቅዳሜ ጥር 30 እና እሁድ የካቲት 1 ቀን 2018 (Feb 7 & 8, 2026)
📍 ሾላ፣ ከእንግሊዝ ኤምባሲ አጠገብ፣ ሚናሮል ሕንፃ ጀርባ።
ለቦታ ማስያዝ እና ለበለጠ መረጃ (RSVP):
📞 +251-990-41-87-12
📞 +2519-29906490
🌐 www.gardenhillshotel.com
📧 infogardenhillshotel.com
#gardenhills #luxurylifestyle #addisababa #grandopening #urbanoasis #ethiopia #boutiquehotel #latavola #spaday #getutemesgen

🇮🇹 አንቶኒዮ ኮንቴ፦ "እኔም እንደ ቼልሲ በ120 ሚሊዮን ተጫዋች ቢገዛልኝ ደስ ይለኝ ነበር!"
#ethiopia | የናፖሊው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በጣሊያን ሴሪአ እና በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መካከል ያለውን የፋይናንስ ልዩነት የሚያሳይ ግልጽ አስተያየት ሰጥተዋል።
ኮንቴ በተለይ የቀድሞ ክለቡ ቼልሲ ለወጣት ተጫዋቾች የሚያወጣውን እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ በማንሳት የጣሊያንን የገበያ እውነታ አብራርተዋል።
"የገንዘብ ጉልበት እና የጣሊያን እውነታ"
ኮንቴ ሲናገሩ፦ "እኔም ናፖሊ እንደ ካይሴዶ ወይም ኢንዞ ፈርናንዴዝ ያለ ወጣት ተጫዋች በ120 ወይም 130 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲገዛልኝ መጠየቅ ብችል ደስ ይለኝ ነበር። ነገር ግን ጣልያን ውስጥ ማንም ሰው ያንን ማድረግ አይችልም፤" ሲሉ በቁጭት ተናግረዋል።
"ለቼልሲ ያለ ክብር"
ስለ ቀድሞ ክለባቸው ሲጠየቁም፦ "ቼልሲን ለሁለት ዓመታት ማሰልጠን ትልቅ ክብር ነበር፤ የክለቡን ፍልስፍና እና የገበያ አቅም በሚገባ አውቀዋለሁ" ሲሉ የቀድሞ ቤታቸውን አስታውሰዋል።
ኮንቴ ይህንን ያሉት ናፖሊ በገበያው ላይ ያለውን አቅም ከእንግሊዝ ሀብታም ክለቦች ጋር በማነጻጸር ሲሆን፣ በጣሊያን ክለቦች ዘንድ ያለውን የፋይናንስ ውስንነትም አመላክተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #napoli #chelsea #antonioconte #transfernews #enzofernandez #caicedo #seriea #premierleague #footballnews #ethiopia

5 months ago
በናዚ መሰል አለባበስ የተገኙት የትራምፕ የድንበር ጥበቃ ሹም ከፍተኛ ቁጣ ቀሰቀሱ
የዶናልድ ትራምፕ የቀኝ እጅ እና የሕገ-ወጥ ስደተኞች አደን ዋና አስፈጻሚ ተደርገው የሚታዩት ግሬጎሪ ቦቪኖ በሚኒያፖሊስ ጎዳናዎች ላይ በታዩበት ወቅት በለበሱት "አወዛጋቢ" ልብስ ምክንያት ከፍተኛ ትችት እየቀረበባቸው ይገኛል።
የናዚ ዩኒፎርም ንፅፅር፦ ቦቪኖ በሚኒያፖሊስ የኦፕሬሽን ጉብኝት ወቅት የለበሱት ረጅም የወይራ ቀለም ያለው ኮት፣ የወርቅ ቁልፎች እና ጥቁር ስካርፍ በናዚ ዘመን የነበሩ ባለሥልጣናት ይለብሱት ከነበረው ዩኒፎርም ጋር እንደሚመሳሰል ተገልጿል። በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድም "የናዚ ማስመሰል" (Nazi Cosplay) በሚል ተወግዟል።
የሚኒያፖሊስ ግጭት፦ በአሁኑ ወቅት ከተማዋ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ትገኛለች። በአንድ በኩል ስደተኞችን ለማደን የተሰማሩ 3,000 የፌዴራል ወኪሎች፣ በሌላ በኩል ደግሞ ድርጊቱን የሚቃወሙ ዜጎች በየቀኑ እየተጋጩ ይገኛሉ።
የቦቪኖ ጠንካራ አቋም፦ የጣልያን ስደተኞች ልጅ የሆኑት ቦቪኖ፣ በትራምፕ ትዕዛዝ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን "በብረት እጅ" በመቅጣት ይታወቃሉ። ተቃዋሚዎች "ብራውን ሸርት" (የናዚ ወታደራዊ ቡድን) እያሉ ቢጠሯቸውም፣ እሳቸው ግን ፊታቸውን በኩራት ገልጠው ተቃዋሚዎችን ከጎዳና ሲያባርሩ ታይተዋል።
ልዩነቱ፦ አብረዋቸው ያሉት ወኪሎች በሙሉ የጥይት መከላከያ እና ጭንብል አድርገው ሳለ፣ ቦቪኖ ግን ይህንን ረጅም ኮት ለብሰው ብቻቸውን ለየት ብለው መታየታቸው ልብሱን "ሆን ብለው የመረጡት ነው" የሚል ጥርጣሬ ፈጥሯል።
ይህ አጋጣሚ በአሜሪካ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ በዘር እና በስደት ጉዳይ ላይ ያለውን ከፍተኛ መከፋፈል ይበልጥ እንዲባባስ አድርጎታል ተብሏል።

በጣልያን ለ30 አመት ህፃን ያልተወለደባት መንደር በቅርቡ አንዲት ህፃን ተወለደችባት
👉ህፃኗ በመወለዷ የመንደሩ ህዝብ ብዛት ወደ 20 ከፍ ብሏል።
ዘ ጋርዲያን አንደዘገበው በፓሊያራ ዴይ ማርሲ መንደር ላለፉት 30 ዓመታት ገደማ አንድም ልጅ ያልተወለደ ሲሆን ላራ ቡሲ ትራቡኮ የተባለቸው ህፃን በመንደሩ ከ 30 አመት በኋላ የተወለደች የመጀመሪያዋ ህፃን ሆናለች፤ ይህም የመንደሯን የህዝብ ቁጥር ወደ 20 አድርሶታል።
የህፃኗ ወላጆች ልጅ በዚህች መንደር በመውለዳቸው አንድ ሺ ዮሮ በቦነስ መልኩ የተሰጣቸው ሲሆን 370 ዩሮ በየወሩ ይከፈላቸዋል ተብሏል።
ይህ ክፍያ የተደረገው ሌሎችም ተመሳሳይ ነገር አድርገው የመንደሯን ህዝብ እንዲጨምሩት በማሰብ ነው።
seledadotio

ከኢትዮጵያ ያመለጠው በሕገ ወጥ የሰው ዝውውር የተከሰሰው ኤርትራዊ ለኔዘርላንድስ ተላልፎ ተሰጠ
ሰዎችን በሕገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር የተከሰሰው ኤርትራዊ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለኔዘርላንድስ ተላልፎ መሰጠቱ ተገለጸ።
የ41 ዓመቱ ኪዳኔ ዘካርያስ ሃብተማርያም በኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ የአገሪቱ ዐቃቤ ሕግ በድረ ገጹ ያወጣው መግለጫ ይጠቁማል።
በኢትዮጵያ በፍርድ ሒደት ላይ ሳለ ካመለጠ በኋላ ላለፉት አምስት ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ ገብቶ ነበር።
በኔዘርላንድስ ወታደራዊ ፖሊስ ታጅቦ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ወደ አምስተርዳም መወሰዱም ተገልጿል።
ኪዳኔ በወንጀል ቡድን ውስጥ በመሳተፍ፣ ስደተኞችን በሕገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር፣ ሰዎችን በማገት፣ በብዝበዛ፣ አካላዊ ጥቃት በማድረስ እንዲሁም ወሲባዊ ጥቃት በመፈጸም በኔዘርላንድስ ሲፈለግ ነበር።
የኪዳኔ ጉዳይ ከሌላው ኤርትራዊ ተወልደ ጎይቶም ጋር የሚተሳሰር ሲሆን፤ ጎይቶም ባለፈው ወር በኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት ቀርቧል።
ዐቃቤ ሕግ ጎይቶም በ20 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ጠይቋል።
የጎይቶም ጠበቆች ኪዳኔን እንደ ምስክር ማቅረብ ይፈልጋሉ። ዐቃቤ ሕግ ባወጣው መረጃ መሠረት በሕገ ወጥ የሰው ዝውውር ትልቅ ከሚባሉ የፍርድ ሒደቶች አንዱ ነው።
እአአ በ2022 ከኢትዮጵያ ለኔዘርላንድስ ተላልፎ የተሰጠው ጎይቶም ለፍርድ ቤት በሰጠው ቃል በቁጥጥር ሥር የዋለው በተሳሳተ ማንነት እንደሆነ ገልጿል።
ጎይቶም በኢትዮጵያም በሕገ ወጥ የሰው ዝውውር ተከስሶ እንደነበር ይታወሳል።
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የተመራ ዓለም አቀፍ አሰሳ ተካሂዶ ኪዳኔ በ2023 በሱዳን ተይዞ ነበር።
የፊታችን ቅዳሜ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብም የኔዘርላንድስ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።
"ሁለቱ ኤርትራውያን አብረው በመሥራት ከፍተኛ ገንዘብ አግኝተዋል። በዋናነት ኤርትራውያን ስደተኞችን ያንገላቱ እና ገንዘባቸውን ይበዘብዙ ነበር። ጥቃት ያደርሱ የነበረው በሊቢያ ነው። ኔዘርላንድስ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ በመጠየቅ ብዝበዛውን ፈጽመዋል" ሲል ዐቃቤ ሕግ መግለጫ አውጥቷል።
በሊቢያ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የሚያደርሱት ስቅይት "ይቆም የነበረው ቤተሰቦቻቸው ከከፈሉ ብቻ ነው" ሲል ዐቃቤ ሕግ ገልጿል።
የስደተኞቹ ቤተሰቦች ገንዘብ ከከፈሉ በኋላ ስደተኞቹ የሚደርስባቸው ስቃይ ተገትቶ ወደ አውሮፓ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ እንደሚፈቀድላቸውም ተገልጿል።
ኪዳኔ ከኢትዮጵያ ካመለጠ በኋላ በሌለበት የዕድሜ ልክ እስራት ተፍርዶበት ነበር።
የኔዘርላንድስ ዐቃቤ ሕግ ኪዳኔ ላይ የሚያቀርበው ክስ ከሊቢያ ወደ አውሮፓ የሚጓዙ ስደተኞች ላይ ከተፈጸመ ጥቃት እና ብዝበዛ ጋር ይገናኛል።
ጥር 1/2023 በሱዳን በቁጥጥር ሥር የዋለው ኪዳኔ በኔዘርላንድስ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ ነበር።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሕገ ወጥ ገንዘብን ሕጋዊ መስመር ውስጥ በማስገባት ላይ ምርመራ ስታደርግ ኪዳኔ እንደተያዘ የዐቃቤ ሕግ መግለጫ ይጠቁማል።
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በቀረበበት ክስ ታስሮ ከቆየ በኋላ ለኔዘርላንድስ ተላልፎ ተሰጥቷል።
ከሁለቱ ኤርትራውያን በተጨማሪ ሌሎች አምስት ተጠርጣሪዎች ለወንጀል ቡድን ገንዘብ በመሰብሰብ እና በማስተላለፍ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተገልጿል።
የኔዘርላንድስ ዐቃቤ ሕግ እንዳለው ምርመራ እየተካሄደ ያለው እአአ ከ2014 እስከ 2020 ድረስ በተፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች ነው።
በዚህም ጣልያን፣ ዩሮፖል፣ ኢንተርፖል እና ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
BBC

6 months ago
የቀይ ባህር እንቁ አሥመራ ሽኮሪና
የአለማችን የመጀመርያዋ የቅርስ ከተማ!
( በታዴ የማመይ ልጅ )
#ethiopia | በእርግጥም በምስራቅ በፅሎትና ቤተ ጊዮርጊስ ፣ በምዕራብ በፀራራት ፣በሰሜን በአክሪያና ባዕታ አስመራ፣ በደቡብ አዲ ጓእዳ ኮረብታዎች ደጀን የሆኗት በፅዳቷ ፣ በእርጋታዋ ፣ እንደሚፈርጥ እንቁላል በጥንቃቄ በተደረደሩት እፁብ ህንፃዎቿ በተንዠረገጉት ዘንባባዎቿ፣ የአፍሪካ ዘመናዊ ከተማ ፣የቀይ ባህር እንቁ ትመስላለች ።
በዛሬዉ የአፍታ ቱሪዝም ጉብኝታችን ባለፉት ሦስት አስርት አመታት ክፉ ክፉዉን አግዝፈው የሚነግሩን ቤኒቶ ሙሶሊኒም “ፒኮላ ሮማ” ወይም “ትንሿ ሮም” ሲል ያሞካሻት የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ገብተናል ።
በቆይታችን ደግነትና ባህል አክባሪነት መገለጫው ሰዉን ያለልዩነት የሚወደው ቸርነት ከባህሪዉ የሆነው የአስመራ ህዝብ አለና ወደኋላም ከመነሻዋ ወደፊትም ከገፅታዋ መለስ ቀለስ እያልን በጎዳናዎቿ ሸር ብትን እንላለንና አብራችሁን ዝለቁ ።
ጥንት ከሁለት ሺህ ዓመት በላይ ታሪክ ያለዉ አዶሊስ በዝያን ጊዜ ከነበሩ ከታወቁ የተለያዩ ሃገሮች ጋር ትልቅ የንግድ ግንኙነት የነበረዉ፤ አዶላዉያን በዝያን ጊዜ እስከ ሕንድ አልፈዉ እስከ ቻይና ግንኙነት ያደርጉባት የነበረዉ የወደብ ከተማ ናት የሰሜን ፈርጧ አስመራ።
በአሥመራ በሠምበል አካባቢ የተገኘው የአርኪዮሎጂ ማስረጃ ከተማዋ ስያሜ በ 800 ዓ.ዓ. ይወስደናል ።
የኦና ባህል ተብሎ የሚጠራውን የአሥመራ ታሪክ በ 800 ዓ.ዓ. እና በኤርትራ ትግሪኛ ቃል ባሕላዊ ታሪክ መሠረት፣ በቀበሳ አምባ ላይ በአስመራ አካባቢ አራት ጎሳዎች ይኖሩ ነበር።
በዘመኑ ተበታትነው የነበሩት ገዛ ጉርቶም። ገዛ ሽሌሌ፣ ገዛ ሴሬንሰር እና ገዛ አስመኤ የተባሉ ግዛቶች ጎሳዎች በአንድነት በመሆን ከተማ በመመስረት "አርባተ አስመራ" የሚል ስም ሰጧት ይባላል ይህም አርባተ አስመራ ማለት በትግርኛ ቋንቋ 'አራቱ ጎሳዎች' ማለት ነው።
ከባህር ጠለል በላይ ከ2,300 ሜትር በላይ ከፍታ ላይ የምትገኝ ሲሆን ከአካባቢው ዝቅተኛ ቦታዎች ሙቀት ጋር የሚቃረን መለስተኛ የአየር ንብረት ያላት አስመራ ግብፆች፤ ቱርኮች፤ጣልያኖች እንጊሊዞች ተዋግተዉባታል። ከተማዋን የጎዳ ማንም ኃይል ግን አልነበረም ወዘናዋ ዛሬም በእርጋታ ተዉቦ ይገኛል ።
ከተማዋና ዙርያዋ ታሪክ ከ 2000 ዓመት ወደኋላ ይወስደናል 2000 አመታት በላይ ስልጣኔ የነበረዉ ታሪካዉ" መጠራ በለዉ ከለዉ" የተባለ በአፍሪቃዉ ቀንድ ላይ ለሚገኙ ሁለቱም ሃገሮች የሥነ-ጽሑፍ የተከሰተበት ታሪካዊ ቦታ ሲሆን በሃዉልቱ ላይ አናባቢ የሌለዉ የግዕዝ ጽሑፍ ሰፍሮ ይገኛል ።
ሰፊ ከተማ የነበረችዉ 17 ኪሎሜትር ስፋት የነበራት ቆሃይቶ እስከ ትልቅ የአፍሪቃ ከተማ ያደርጋታል። ከዚህም ባሻገር በአፍሪቃ እስልምናን ከተቀበሉት አካባቢዎች የመጀመርያዉ የሆነው ዳህላክኬሪስ
ጥንታዊ መቃብሮች ጥንታዊ የዉኃ ማጠራቀምያ ገንዳዎች መገልገያዎች አስመራና ዙርያዋ የረጂም ታሪክ እንዳላት ህያው እማኝ ይሆናሉ ።
ይሁንና የዛሬውን ገፅታ የያዘችው በጎርጎረሳዉያኑ 1930ዎቹ በቅኝ ግዛት ኤርትራን የያዘዉ ኢጣልያዊዉ ፋሺስት ሞሶሎኒ በምስራቅ አፍሪቃ ለሚያካሂደዉ የቅኝ ግዛት ዘመቻ ማዕከል እና መነሻ እንድትሆነዉ ዓይኑን ከጣለባት በኋላ ነበር ።
የጣልያንን መምጣት ተከትሎም አስመራ የምትባለዉ ትንሽ መንደር ሞቅ ደምቅ ማለት ጀመረች ። በአፍሪካ የመጀመሪያው የቴሌቪዥን ስርጭት ፣ የመጀመሪያው Am FM አጭር መካከለኛ ረጂም ሞገድ ራዲዮ ፣
የኤርትራ የባቡር መስመር በጊንዳ ከተማ በኩል በካርሎ ካቫና መሪነት ወደ ምጽዋ የባህር ዳርቻ የሚያመራ ሀዲድ ፣ ሲኒማ
ፋብሪካዎች በብዛት ተገንብተው በአፍሪካ ምድር ላይ የአውሮፓ ዘመናዊነት እውነተኛ ማሳያ ያደርጋታል ።
ሲኒማ ኢምፔሮ፣ የፊያት ታግሊየሮ አገልግሎት ጣቢያ እና የቅዱስ ጆሴፍ ካቴድራል ያሉ ታዋቂ ሕንፃዎች ለዚህ የፈጠራ ኃይል ምስክር ናቸው። ፊያት ታግሊየሮ፣ እንደ አውሮፕላን ለመነሳት ዝግጁ የሆነ አውሮፕላን ቅርጽ ያላቸው የተጠናከረ የኮንክሪት ክንፎቹ ያሉት፣ የዘመኑን የቴክኖሎጂ፣ የእድገት እና የፍጥነት ውበት ያለውን ማራኪነት መገለጫዎች ናቸው ።
ጋዜጠኛ ጆን ጉንተር እ.ኤ.አ. በ 1955 እንደገለጸው "ጣሊያኖች [አስመራን] እንደ ትሪፖሊ በጥሩ ሁኔታ እንደገነቧት ጽፏል።
በሚያማምሩ ሰፊ ጎዳናዎች ፣ ያጌጡ የህዝብ መገልገያ ሕንፃዎች እና የሥልጣኔ ምልክት የሆነው በከተማዋ የተገነባው ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት ... የጣልያኖች የስራ ውጤት መሆኑን ጽፏል።
የኢጣሊያ መንግሥት በአስመራ እና በአስመራ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በኢንዱስትሪ ልማት ላይ ኢንቨስት አድርጓል ።
ከሥነ ሕንፃዋ ባሻገር፣የጂኦሜትሪክ ዲሲፕሊን እና የሜዲትራኒያን ጸጋ ድብልቅ አሰራሯ አስመራን ልዩ ውበት ይሰጣታል ።
አስመራ ሙሉ በሙሉ በዘመናዊነት ሀሳብ ዙሪያ ለተቀረፀ የከተማ ፕላን ትታወቃለች፤ ሰፊ አውራ ጎዳናዎች፣ ሥርዓታማ ሰፈሮች፣ ለጋስ የሕዝብ ቦታዎች እና ቀልጣፋ መሠረተ ልማቶች የጣልያኖች የስራ ዉጤት የተመለከተው ፋሽስት ሞሶሎኒም በዝያን ጊዜ አስመራን አፍሪቃዊትዋ ትንሽዋ የሮም ከተማ ሲል አንቆለጳጽሷታል።
ሲኒማ ቤቶቹ ራሳቸዉ ድንቅ ናቸዉ ሲኒማ ኤንፔሮ፤ ሲኒማ ዳንቴ፤ ሲኒማ ካፒቶል፤ ሲኒማ ሮማ፤ ሲኒማ ኦዲዎን የሚባሉ ሲኒማ ቤቶች አሉ።ሁሉም ሲኒማ ቤቶች የተሰሩት በአዉሮጳ ደረጃ ነዉ። ሌሎቹ ሕንጻዎች ቡናማ ሰማያዊ አረንጓዴ ቀለም ያላቸዉ ሲሆኑ የአስመራ ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስትያን ዉብ ቪላ ቤቶች ፤ ፋብሪካዎች አስመራ የሚገኘዉ ትልቁ መስጊድ የመሳሰሉት ሁሉ የሚያማልሉ ናቸዉ።
ከተማዋ እድለኛ ከተማም ናት 30 እና 40 ዓመት ጦርነት ተካሂዶ ከተማዋ ምንም አልተጎዳችም ከተማዋን የጎዳ ኃይል የለም። በመጀመርያ ከተማ አስመራን በኦቶማን ኤምፓየር በሚባለዉ ዘመን ቱርኩች ያዙ፤ ከዝያ በኋላ ግብጾች ያዙ ከዝያ በኋላ ጣልያኖች ያዙ ከዝያ በኋላ እንጊሊዞች ያዙ። ይህ ሁሉ ትርምስ ሲካሄድ ግን ከተማዋ አልተጎዳችም ።
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት አስመራ የዓለም ቅርስ ሆና እንድትመዘገብ በፖላንድ ዋርሶ ባካሔደው ጉባዔ ላይ የአለማችን የመጀመርያዋ የቅርስ ከተማ ክብር መዝገብ አስፍሯታል ።
በአስመራ የሚገኙትና ቅኝ ግዛቱ ዘመን የተሰሩት ከ 50 በላይ ሕንፃዎች በሙሉ በዓለሙ መንግሥታት የቅርስ መዝገብ በመስፈራቸዉ ኤርትራ ጥንታዊና የባህል ቅሪቶች በሙሉ የተመዘገበላት ቀዳሚዋ የዓለም ሀገር ያደርጋታል ።
UNESCO ስለ ከተማዋ ሲገልፅ
«አስመራ በጣም ዉብ የሆነች ከተማ ናት። ከሁሉ ደግሞ ሕዝብዋ በዉስጥዋ እየኖረ ባህሉን እየጠበቀ ሥነ ሕንጻዉን እየጠበቀ በመሆኑ ነዉ። የአስመራ ሕንጻዎች ለየት ያለ ንድፍና ቅርስ የያዙ ናቸዉ። ጣልያኖቹ በቅኝ ግዛት ወቅት ሃገራቸዉ ዉስጥ የሌለ ነጻነት አስመራ ዉስጥ፤ ቅኝ ሃገር ዉስጥ ነጻነት ተሰምቶአቸዉ ፤ በምህንድስናዉ ረገድ አብዮት ያካሄዱ ይመስላል። ምክንያቱም ኢጣልያ ዉስጥ የማይገኘዉ ሕንጻ አስመራ ዉስጥ አለ።» ሲል ገልጿል ።
አስመራ ከተማ በኪነ ሕንጻ ብቻ ሳይሆን በጽዳትዋ ፤ በአየር ፀባይዋና በተለያዩ ሁኔታዎች ከአፍሪቃ የታወቁ ከተማ በመሆንዋ አስመራ በዓለሙ የቅርስ መዝገብ መመዝገብዋ ለኛ ለኢትዮጵያዉያን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ኩራት ነዉ ሲሉ የወቅቱ የበኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ገልጿል ።
አስመራ ሕያው ሙዚየም እና ሕያው የስልጣኔ ከተማ የአፍሪካን ዘመናዊነት ማሳያ የተረጋጋች እጅግ ማራኪ ብትሆንም ከተማዋ ከቱሪዝም ዘርፉ ተጠቃሚ አልሆነችም።
ሜሳረጊያዉን የባለቅኔዉን የሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ግጥም እንገባበዝና ለዛሬው ይብቃን ።
አስመራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ
ያውራ ጎዳናሽ ጠለላ ፡
ሁሉን በአክናፉ እየጠራ
አስር ሰዓት ላይ ሲደራ
ለመንገደኛሽ መዝናኛ ፣ሲያጠላ ሲያብብ ሲያፈራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
አደባባይ ሲያነጥፉ
አድባራትና መስኪዱን ፣ ካቴድራሉን በየረድፉ
ገበያውን በየመልኩ ፣ እንደ አውታር እያሰለፉ
በወግ እየደረደሩ ፣በስምረት እያሰመሩ
በውበት እያዳበሩ ፣እያሳመሩ ቢያደሩ
በየክፍሉ በየበሩ በየመልኩ በየተራ
ፋኖሱን እንደ ደመራ
ቡና ቤቱን እንደ ሦራ
ምነው ሁሉ እንደ አንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ፡፡
እሳት ወይ አበባ (ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን )

ፖርቹጋል ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫን አሸነፈች
#ethiopia | በኳታር አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ፖርቹጋል ኦስትሪያን 1 ለ 0 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆናለች።
በካሊፋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አኒሲዮ የፖርቹጋለን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል፡፡
48 ሀገራት በተሳተፉት እና ለ20ኛ ጊዜ በተደረገው ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ፖርቹጋል ለመጀመርያ ጊዜ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡
ለደረጃ በተደረገ ጨዋታ ጣልያን በመለያ ምት ብራዚልን 4 ለ 2 በማሸነፍ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡
በአንተነህ ሲሳይ

የእንግሊዟ ንግሥት ኤልሳቤጥ የጎበኙት ኮሶዬ
#ethiopia | ኮሶዬ ከጎንደር ከተማ በሰሜን አቅጣጫ 3ዐ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ የሚገኝ ሥፍራ ነው። ቦታው ከባሕር ወለል በላይ 3 ሺህ ሜትር ከፍታ ላይ እንደሚገኝም ይገለጻል።
ኮሶዬ የሚገኝበት አካባቢ ከፍተኛ ቦታ ወይም ተራራማ በመኾኑ "ኮሶዬ አምባራስ" የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል፡፡ በተጨማሪም ስያሜው የተሰጠው በአካባቢው በርካታ የኮሶ ዛፍ ስለሚገኝ እንደኾነ ከወገራ ወረዳ ባሕል እና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።
ቦታው በዓለም ቅርስነት ከተመዘገበው የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ጋር የተያያዘ ሰንሰለታማ ውብ፣ ለዓይን የሚማርኩ የመሬት ገጽታዎች፤ ዋሻዎች፣ ተራራዎች፣ ሸለቆዎች፤ ኮረብታዎች መገኛም ነው። በውስጡ እንደ ጅብ፣ አቦ ሸማኔ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ፣ ድኩላ፣ ሚዳቋ፣ ጦጣ፣ ጉሬዛ እና የመሳሰሉ የዱር እንስሳትና አዕዋፋት መገኛም ጭምር ነው።
አካባቢውን ነገሥታት ይጎበኙት፤ በውበቱም ይደነቁበት እንደነበር ይነገራል። አጼ ኃይለ ሥላሴ የእንግሊዟን ንግሥት ኤልሳቤጥ ጥር 11 ቀን 1957 ዓ.ም ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜም ካስጎበኟቸው ዋና ዋና የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል አንዱ እንደኾነም በታሪክ ተቀምጧል።
በወቅቱ ንግሥቷ ከመጡበት ሀገር የአየር ንብረት ጋር ተመሳሳይና ምቹ ኾኖ እንዳገኙት ለንጉሡ መግለጻቸውም ይነገራል። ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴም በቦታው ተፈጥሯዊ ውበት ከመማረካቸው የተነሳ ወደ ጎንደር ከተማ በሄዱ ቁጥር ሳይጎበኙት አይመለሱም ነበር ይባላል።
በኮሶዬ ጅብ ዋሻ በተባለ አካባቢ የጎንደር አብያተ መንግሥታት ሲገነቡ ለግንባታ አገልግሎት የሚውል ቀይ አፈር በብዛት ይጓጓዝበት እንደነበረም ይነገራል። አካባቢው በጣልያን ወረራ ጊዜ ለአባት አርበኞች እንደ መጠለያ ኾኖ ማገልገሉም ይጠቀሳል። በደርግ ዘመነ መንግሥትም የሎጀስቲክስ ማከማቻና መምሪያ ኾኖ ያገለግል ነበር።
የወገራ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አረፈዓይኔ ካሴ፣ ቦታውን ለማስተዋወቅና የቱሪስት መዳረሻነቱን ለማሳደግ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሁለት የእንግዳ ማረፊያ ሎጅዎች በግንባታ ላይ እንደሚገኙም አንስተዋል።
ከ28 በላይ የሚኾኑ የአካባቢው ወጣቶችን በማሥተባበርና የስካውት ቡድን በማቋቋም አካባቢውን ለማስተዋወቅና ለመጠበቅ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ቦታው ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኝ መኾኑ ለጎብኝዎች ተመራጭ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ከ35 በላይ ለሚኾኑ ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም አንስተዋል።#አሚኮ

ሴኔጋላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሙሉ
መንደር ዳግም እየገነባ ነው
#ethiopia | ታዋቂው የጣልያን የስፖርት ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንደተናገረው፤ ሴኔጋላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሳድዮ ማኔ፣ በሴዲዮ ክልል ውስጥ የምትገኘውን የትውልድ ቀዬውን - ባምባሊን - እየቀየራት ነው፡፡
በእቅዱ መሰረት በቀዬው ከሚገነባቸው መሰረተ ልማቶች መካከል፡-
- አዲስ ሆስፒታል
- ትምህርት ቤት
- ሙሉ 4G ኔትዎርክ
- ፖስታ ቤት
- ነዳጅ ማደያ
- ስታዲየም --- ይገኙባቸዋል፡፡
በተጨማሪም ሳድዮ ማኔ ለእያንዳንዱ ነዋሪ በየወሩ 70 ዩሮ እንደሚሰጥ ተዘግቧል፡፡ በዚህም ሴኔጋላዊው የእግር ኳስ ኮከብ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ህይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ እንደሚፈጥር ነው የስፖርት ጋዜጠኛው የገለጸው፡፡#አዲስ አድማስ

7 months ago
44 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን የንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት እንደሌላቸው ተገለጸ።
"World Population Review" በ2025 ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የመጠጥ ውሃ ጥራት ካላቸው ሃገራት መካከል አንዷ ነች ብሏል። በዚህም ለኢትዮጵያ 19.2/100 ውጤት ተሰጥቷታል።
ንፁህ ያልሆነን ውሃ ከሚጠጡ 100,000 ሰዎች ውስጥ ምን ያህሉ ዕድሜውን ከውሃው ጋር በተያያዘ እንደሚያጣ መሰረት በማድረግ መለኪያው የተሰራ ሲሆን እንደ ጀርመን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጣልያንና ግሪክ ያሉ ሃገራት 100 ተሰጥቷቸው፥ ዜጎቻቸው ንፁህ ውሃ የሚጠጡባቸው ሀገራት ተብለዋል።
በዝርዝሩ ዝቅተኛው ነጥብ የተሰጣቸው 10 ሃገራት ሙሉ ለሙሉ ከአኅጉራችን አፍሪካ ናቸው።
ኢትዮጵያ አሁንም 44 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንደሌላቸው በዝርዝሩ ሲመላከት ይህም 42.7% ህዝቧን መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪ የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩ ሰዎች ከመጠጥ ውሃ ጋር በተያያዘ ለሚፈጠሩ በሽታዎች የሚጋለጡባትም ነች ተብሏል።
44 ሚሊየን ዜጎቿ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አያገኙባትም የተባለችው ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ 60.1 ሚሊየን ህዝብ በመቀጠልም ብዙ ሰዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የማያገኙባት አፍሪካዊ ሀገር ነች።
Tikvah