የካቲት 12, ለምን ይከበራል?
•+============+.
በ1929 ዓ ም የጣልያን ወረራ ገነተ ልዑል ተብሎ በሚታወቀው የንጉሱ ቤተመንግስት (የዛሬው 6ኪሎ ዋና የዩኒቨርስቲ ግቢ) የተነሳው አመጽ ለብዙ ኢትዮጵያውያን እልቂት ምክንያት በመሆኑና በአካፋ በመትረየስ በሳንጃ የብዙ ሰው ህይወትን ያለቀበት እለት ስለሆነ በዚህም ዙሪያ ለመታሰቢያ የካቲት 12 ሆስፒታል እንዲሁም የካቲት 12 ትምህርትቤት መኖሩ ይታወቃል:: ቤተክርስቲያንም በዚህች እለት ጸሎተ ምህላ እና ጸሎተ ፍትሐት በማድረግ በታቦተ ንግስ ቀኑን ትዘክረዋለች::
ከ71 ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ቤተመዘክር ውስጥ ለዘመናት በሙዚየሙ ሲኖር የነበረው የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ከገባ እለት ጀምሮ ማለትም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በምዕመናኑ እና በካህናቱ ጥያቄ ለዘጠነኛ ጊዜ ዘንድሮ በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ወቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ይከበራል:: የንጹሃንን ነፍስ አምላከ አበው እግዚአብሔር ይማርልን::
በዚሁ ሳምንት የፊታችን የካቲት 14 ቅዳሜ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ደግሞ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ የማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም ገዳም አጭር ዶክመንተሪ ምርቃትና በአበው መነኮሳት ጥሪ ሰፊ ጉባኤ ተዘጋጅቷል::
በመርሐ ግብሩ መነኮሳቱ ከሚያገለግሉበት አፄ ፋሲለደስ ካሰራው የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በተጨማሪ ወደ ገዳሙ የሚመጡ ምእመናን/ት በተለይ ወደ ግዝት ቅፅር የማይገቡ ሴቶች የሚገለገሉበት በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና በአቡነ ያሳይ ስም የቤተ ክርስቲያን ግንባታ እንዲሁም ለሚከናወኑት የልማት ሥራዎ ፍኖተ ካርታ ይፋ ይደረጋል።
ለአገልግሎቱ መሳካት ማኅበረ መነኲሳቱ ዘወትር እግዚአብሔር አምላካችንን በጸሎት እያሳሰቡ ሲሆን ፤ እርስዎ በመርሐ ግብሩ እንዲሳተፉ እና በረከት እንዲያገኙ በማሰብ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በማኅበረ መነኲሳት እና በገዳሙ ስም እናቀርባለን::
ድጋፍ ለማድረግ:
ንግድ ባንክ: 1000731553134
ስልክ: -
0918240454
0906632367
0921612653
Website: www.abuneyasay.com
Online Donation link: https://chapa.link/donatio...
አምላከ አቡነ ያሳይ ኢትዮጵያን ይባርክ!
8 months ago