8 months ago
#ethiopia | የናፖሊው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በጣሊያን ሴሪአ እና በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መካከል ያለውን የፋይናንስ ልዩነት የሚያሳይ ግልጽ አስተያየት ሰጥተዋል።
ኮንቴ በተለይ የቀድሞ ክለቡ ቼልሲ ለወጣት ተጫዋቾች የሚያወጣውን እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ በማንሳት የጣሊያንን የገበያ እውነታ አብራርተዋል።
"የገንዘብ ጉልበት እና የጣሊያን እውነታ"
ኮንቴ ሲናገሩ፦ "እኔም ናፖሊ እንደ ካይሴዶ ወይም ኢንዞ ፈርናንዴዝ ያለ ወጣት ተጫዋች በ120 ወይም 130 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲገዛልኝ መጠየቅ ብችል ደስ ይለኝ ነበር። ነገር ግን ጣልያን ውስጥ ማንም ሰው ያንን ማድረግ አይችልም፤" ሲሉ በቁጭት ተናግረዋል።
"ለቼልሲ ያለ ክብር"
ስለ ቀድሞ ክለባቸው ሲጠየቁም፦ "ቼልሲን ለሁለት ዓመታት ማሰልጠን ትልቅ ክብር ነበር፤ የክለቡን ፍልስፍና እና የገበያ አቅም በሚገባ አውቀዋለሁ" ሲሉ የቀድሞ ቤታቸውን አስታውሰዋል።
ኮንቴ ይህንን ያሉት ናፖሊ በገበያው ላይ ያለውን አቅም ከእንግሊዝ ሀብታም ክለቦች ጋር በማነጻጸር ሲሆን፣ በጣሊያን ክለቦች ዘንድ ያለውን የፋይናንስ ውስንነትም አመላክተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #napoli #chelsea #antonioconte #transfernews #enzofernandez #caicedo #seriea #premierleague #footballnews #ethiopia
Comments