6 months ago
አዙሪዎቹ ለ16 ዓመታት ከዓለም ዋንጫ ተለዩ
#ethiopia | በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ስሟ በወርቅ የተጻፈው ጣልያን፣ ዛሬ የቀራት የትዝታ ማዕበል ብቻ ሆኗል።
እነ ማልዲኒ፣ ፒርሎ፣ ቡፎንና ባጂዮን ያፈራው የጣልያን ማህፀን፣ ዛሬ በታሪኩ አስከፊ የሚባለውን የውድቀት ዘመን እያሳለፈ ይገኛል።
ጣልያን ከ2018 እና ከ2022 በመቀጠል፣ አሁን ደግሞ ከ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውጪ ሆናለች። ይህም ለአንድ ትልቅ ሀገር ለ16 ዓመታት (አራት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች) ከመድረኩ መራቅ በታሪክ የመጀመሪያዋ ያደርጋታል።
በትናንትናው ወሳኝ የጥሎ ማለፍ ፍልሚያ፣ በፊፋ 71ኛ ደረጃ ላይ በምትገኘው ቦስኒያ ሄርዞጎቪና በመለያ ምት 4 ለ 1 ተሸንፋ ተሰናብታለች።
ሞይስ ኬን ጣልያንን መሪ ቢያደርግም፣ የባስቶኒ ቀይ ካርድና የቦስኒያ የአቻነት ግብ ጨዋታውን ወደ መለያ ምት ወስዶታል።
የጣልያን የመጨረሻው የዓለም ዋንጫ ትዝታ በ2014 ብራዚል ላይ ሱዋሬዝ ቺሊኒን የነከሰበትና ጣልያን በኡራጓይ ተሸንፋ ከምድብ የቀረችበት መራራ ምሽት ሆኖ ቀርቷል።
ከ2006ቱ ድል በኋላ ጣልያን በዓለም ዋንጫ መድረክ አንድም ስኬታማ ጉዞ ማድረግ አልቻለችም።
ጂናሮ ጋቱሶ የሉቺያኖ ስፓሌቲን መንበር ተረክቦ ሊታደጋት ቢሞክርም፣ እሱም እንደ ማንቺኒና ኮንቴ ሁሉ የአዙሪዎቹን ክብር ሳይመልስ አንገቱን ደፍቶ ወጥቷል።
ኩራሳኦና ጆርዳን ወደ አሜሪካ ሲያመሩ፣ አዙሪዎቹ ግን አሁንም ቤታቸው እንዲቀሩ ተፈርዶባቸዋል።
#getu #italyfootball #azzurri #worldcup2026 #gattuso #footballnews #worldcupqualifiers #italyvsbosnia #footballhistory #ጣልያን #እግርኳስ #ዓለምዋንጫ #መርዶ #ትዝታ #ጌጡተመስገን #getutemesgen
1 year ago
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፊፋ ይፋዊ ቅሬታውን አቀረበ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዓርብ ዕለት ከግብጽ ጋር ባደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ የግብጽ ደጋፊዎች የፈፀሙትን ያልተገባ ተግባር ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፊፋ ይፋዊ ቅሬታውን አቅርቧል።
ፌዴሬሽኑ ለፊፋ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በላከው ደብዳቤ፣ ተፈፅመዋል ያላቸው ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳለው ገልጿል።
የመጀመርያው ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በሚዘመርበት ወቅት የግብፅ ደጋፊዎች ክብረ ነክ በሆነ መልኩ ጩህት እና ረብሻ ሲያሰሙ እንደነበር አሳውቋል፡፡
በተጨማሪም ደጋፊዎች በፊፋ በፍጹም ክልክል የሆነውን የሌዘር ጠቋሚ በማንጸባረቅ ተጫዋቾች ላይ በተለይ ደግሞ ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ ፍጹም ቅጣት ምቶቹ ሲመቱ ትኩረቱን እንዲያጣ አድርገዋል በማለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ቅሬታውን አቅርቧል፡፡
የተፈጸሙት ሁለቱም ጉዳዮች በፊፋ የስነ ምግባር ደንብ መሰረት በአባል ሀገራቱ ፈጽሞ የተከለከሉ በመሆናቸው ክስተቶች ላይ ግልጽ ምርመራ እንዲያደርግ እና ፊፋ ባስቀመጣቸው የዲሲፕሊን ደንቦች መሠረት የግብጽ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደጋፊዎቹ ላሳዩት ያልተገባ ባህሪ ተጠያቂ እንዲሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በይፋ ጠይቋል።
#ebc #ethiopia #egypt #worldcup #worldcupqualifiers #fifa

Comments