Logo
FIDEL POST NEWS
በጣሊያን በቲቪ እግር ኳስ ሲያይ የነበረው ባል በገዛ ሚስቱ በቢላ ተወጋ

​በጣሊያን ኔፕልስ ከተማ አንድ የ40 ዓመት የናፖሊ ደጋፊ በገዛ ሚስቱ ተወግቶ ሆስፒታል ገባ።

ግጭቱ የተነሳው ባለፈው እሁድ ናፖሊ ከአታላንታ ጋር ሲጫወቱ ባልየው በዳኛው ውሳኔ ተበሳጭቶ በከፍተኛ ድምጽ ሲሳደብ ነበር።

​ሚስትየው ግን ስድቡ ለእሷ የተሰነዘረ መስሏት በመሳሳቷ በመጀመሪያ መቀስ፣ በመቀጠልም የወጥ ቤት ቢላ በመጠቀም ባሏን ወግታዋለች።

ግለሰቡ በደረሰበት ጉዳት ሆስፒታል ገብቶ ህክምና እየረደረገለት እና በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የ35 ዓመቷ ሚስት ደግሞ በቁጥጥር ስር ውላለች ሲሉ የጣልያን መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑ ዘግበዋል።
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.