19 days ago
ከአቧራ ወደ ዐሻራ፤ ከቅርስ ወደ ቁርስ
*************
በቅርብ ዓመታት ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍን ከተራ የኢኮኖሚ ምንጭነት ባለፈ ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላም፣ ለብዝኃነትና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገንቢያ ስትራቴጂካዊ መሣሪያ አድርጋ በመውሰድ ላይ ትገኛለች።
ሀገራችን በታሪክ፣ በባሕልና በተፈጥሮ ያላትን እምቅ ባለጠግነት ለመጠቀም ቱሪዝምን ዋነኛ የኢኮኖሚ ምሰሶ ያደረገች ሲሆን፣ ይህም መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት፣ ገቢን ለማሳደግና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር መሠረት ሆኗል።
መንግሥት የመንግሥትና የግል ዘርፍ ቅንጅትን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በመምራት፣ ቱሪዝም የጋራ ታሪክን የሚያሳይና ብሔራዊ ማንነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እንዲሆን እያደረገ ነው።
ይህን ዘርፍ ለማሳደግ ለ16 ዓመታት ሳይሻሻል የቆየው የቱሪዝም ፖሊሲ በአዲስ መልክ ተሻሽሎ በሚኒስቴር ደረጃ እንዲደራጅ መደረጉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን አሳድጎታል።
በተጨማሪም የስብሰባ፣ የጉዞ፣ የኮንፍረንስና የኤግዚቢሽን (MICE) ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ወደ ተግባር የገቡ ሲሆን፣ የአሠራር ሥርዓቱን ለማዘመን የኢ-ቪዛና የዲጂታል አሠራሮች ተዘርግተው የቱሪስት ፍሰቱን አቀላጥፈዋል።
እንደ “ገበታ ለሀገር”፣ “ገበታ ለሸገር” እና “ኮሪደር ልማት” ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ ሀብትን ከልማት ጋር በማስተሳሰር ለሀገር ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል።
እነዚህ ተቋማዊ ጥረቶች እንደ እንጦጦ፣ ወንጪ፣ ሃላላ ኬላ እና ኮይሻ ያሉ መዳረሻዎችን ወደ ሥራ በማስገባት የቱሪስቶች ቁጥር ከ781 ሺህ ወደ 1.3 ሚሊዮን እንዲያድግ ማድረጉን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ይህም የውጭ ምንዛሪ ገቢን በከፍተኛ መጠን ከማሳደጉም በላይ በሆቴልና በአስጎብኚ ዘርፎች ለሺዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል። ኢትዮጵያ በዓለም ቱሪዝም ድርጅት እንድትሸለም ከማድረጉም ባሻገር፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሦስት አዳዲስ ቅርሶችን በዩኔስኮ በማስመዝገብ የታሪክ ክብረ-ወሰን እንድታስመዘግብ አስችሏታል።
ኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋናና በዓለም የተመረጠች መዳረሻ በማድረግ የቱሪስት ፍሰቱን እስከ 7.3 ሚሊዮን ለማድረስ ሰፊ ራዕይ ተቀምጧል።
ይህንን ለማሳካት አዳዲስ የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻዎችን ማስፋፋት፣ የታሪካዊ ቅርሶች ጥገናን ማዘመን፣ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ማበረታታትና የመሠረተ ልማት አውታሮችን ማሻሻል በትኩረት እየተከናወነ ነው።
በቀጣይም ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገልግሎቱን ማዘመንና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ተጨማሪ የሥራ ዕድል መፍጠር የመንግሥት ዋነኛ ትኩረት ሲሆን፣ ይህም ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገትና ለዜጎች የኑሮ ደረጃ መሻሻል ጉልህ ሚና ይኖረዋል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopiantourism #landoforigins #visitethiopia #miceethiopia

22 days ago
ለሀገራዊ ምክክሩ ግብዓት የሆነ ሀብት
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በባህላዊ የእርቅ ሥነ ሥርዓት የሚፈቱ፣ ቂም በቀልና ጥላቻን የሚያስቀሩ፣ የሰላምና አብሮነት መሠረት የሆኑ የበርካታ እሴቶች ባለቤት ናት።
ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር እና ብሔራዊ መግባባትን ለማስፈን ምክክር ወርቃማው አማራጭ ነው።
ኢትዮጵያ በልዩነቶች መካከል ድልድይ የሚገነባና ለዘመናት የቆዩ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ቅራኔዎችን መፍታት የሚያስችል ሀገራዊ ምክክር እያደረገች ትገኛለች።
ይህ ታሪካዊ ምክክር ስኬታማ እንዲሆን ሀገር በቀል የውይይትና የምክክር እሴቶች በግብዓትነት ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው።
ብዙ ጊዜ ሰዎች ተጣልተው ወደ ሽምግልና ይመጣሉ። ሽማግሌዎችም በነፍስ የሚፈላለጉ ሰዎችን ጭምር ያስታርቃሉ። ይቅር ያባብላሉ።
አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ባህሎች ሰላምን በሽምግልና የሚያጸኑ እንዲሁም ጥልን በካሳና በግሳጼ የሚያጠፉ ናቸው።
ከእነዚህ ባህሎች መካከል የዘላቂ ሰላም መሰረት የሆነው “ዱቡሻ እና የዱቡሻ ወጋ” ተጠቃሽ ነው።
የጋሞ አባቶች በእጃቸው እርጥብ ሳር ከያዙ ቁጣ ይበርዳል፡፡ ለፀብ ወይም ለበቀል የተነሳ ማንኛውም አካል ጥቃት ለመሰንዘር የያዘውን ቁሳቁስ መሬት ያስቀምጥና ጉዳዩ “በዱቡሻ” ሥርዓት እንዲታይ ይደረጋል፡፡
ጥላቻን በማስወገድ የሰላምና አብሮነት መሠረት የሆነው “ዱቡሻ እና የዱቡሻ ወጋ” በቅንነት ተጀምሮ በእውነት የሚቋጭ ባህላዊ የፍትህ ሥርዓት ነው።
ከግጭት ይልቅ ሰላምን እና ፍቅርን፣ ከመለያየት አንድነትን እና አብሮነትን የሚያስቀድመው ሥርዓቱ በጥንት ጊዜ በጋሞ አባቶች እና እናቶች ይመራ የነበረ ያልተፃፈ ሕግ ነው።
ዱቡሻ የሚለው የጋሞኛ ቃል ትርጉሙ "ባህላዊ የሕዝብ መሰብሰቢያ አደባባይ" ማለት ሲሆን÷ ይህም በሕዝቦች መካከል የአንድነትና የጥንካሬ ምልክት ሆኗል።
በአብዛኛው በዛፎች ሥር፣ በለምለም ሳር አካባቢ፣ በድንጋዮች በተከበበ እና በባህላዊ መቀመጫዎች ባጌጠ ቦታ ላይ ሥርዓቱ ይከናወናል።
ይህ የመሰብሰቢያ ቦታ የጋሞ ሕዝብ ከመሪው ጋር እየተገናኘ በጋሞ ባህላዊ የፖለቲካ ሥርዓት ሕግና ደንብ የሚያወጣበት የተከበረ ስፍራ ነው።
በዚህ ስፍራ መዋሸት ቅጣቱ እርግማን እንዲሁም ከማኅበረሰቡና ከማኅበራዊ አገልግሎቶች መገለል በመሆኑ በዳይም ተበዳይም ለእውነት ተገዢ ይሆናሉ።
"ዱቡሻ እና የዱቡሻ ወጋ" ለዘመናዊ የአስተዳደር ሥርዓት መጎልበት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ፣ የብሔረሰቡ የሰላም ምልክት፣ የሕዝቦችን አንድነት የሚያጠናክር እና የተደበቀውን እውነት የሚገልጥ ታሪካዊ እሴት ነው።
ይህ እሴት በቅርስነት እንዲጠበቅ እና በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
የጋሞ ሕዝብ ባህላዊ የፍትህ ሥርዓትን ለአብነት አነሳን እንጂ በኢትዮጵያ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በባህላዊ ሽምግልና እና እርቅ ሥነ ሥርዓት መፍታት የሚቻልባቸው በርካታ እሴቶች እንዳሉ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተለይ ለምክክር ሒደቱ ጠቃሚ የሆኑ ሀገር በቀል እሴቶችን በግብዓትነት ጥቅም ላይ እያዋለ ይገኛል።
በብርሃኑ አበራ

1 month ago
የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን የፈጠራ መብት ለማስከበር የታለመው የ18 ወራት ፕሮጀክት በስኬት ተጠናቀቀ!
#fastmereja :በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የፈጠራ ውጤቶች ላይየሚታየውን የአእምሯዊ ንብረት ጥሰት ለመከላከልና መብቶቻቸው በሕግ እንዲጠበቁ ለማስቻል ለተከታታይ 18 ወራት ሲተገበር የቆየው ሀገር አቀፍ ፕሮጀክት መጠናቀቁ ተበሰረ።
"በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ የእእምሯዊ ንብረት መብቶችን ማጠናከር" (SIPRE) በሚል መጠሪያ ሲተገበር የቆየው የዚህ ፕሮጀክት ማጠቃለያና የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የምክክር መድረክ በዛሬዉ እለት ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሞናርክ ሆቴል ተካሂዷል።
በሰላም ኢትዮጵያ አዘጋጅነት በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ እንደተገለጸው፤ ፕሮጀክቱ በዩኔስኮ የባህል ብዝኃነት ዓለም አቀፍ ፈንድ (IFCD) የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ሲሆን፣ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን እና በኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማኅበራት ሕብረት አማካኝነት በጋራ ሲተገበር ቆይቷል።
ባለፉት 18 ወራት ፕሮጀክቱ በስነ-ስዕል፣ በቅርጻ ቅርፅ፣ በፊልም፣ በቲያትር፣ በሙዚቃና በውዝዋዜ ዘርፎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሲንቀሳቀስ የቆየ ሲሆን፤ በዋናነት በግንዛቤ ማስጨበጫ፣በክህሎት ማሳደጊያ እና በስራ ትስስር በእነዚህ በሦስት ዘርፎች ስኬቶች መመዝገባቸው ተገልጿል።
በማጠናቀቂያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ተወካዮች እንደገለጹት፤ ምንም እንኳ የኪነ-ጥበብ ዘርፉ እያደገ ቢመጣም፣ የፈጠራ ውጤቶች ያለፈቃድ ጥቅም ላይ መዋልና የቅጂ መብት ጥሰት አሁንም በዘርፉ ላይ ትልቅ ስጋት እንደሆነ ገልፀዋል።
በመሆኑም የSIPRE ፕሮጀክት ቢጠናቀቅም፣ የተጀመሩ የንቅናቄ ስራዎች ከመንግስትና ከክልል የባህል መዋቅሮች ጋር በዘላቂነት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የሰላም ኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ መንግስቴ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቱ በኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት መካከል የነበረውን የግንኙነት ክፍተት ለመሙላት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን ገልፀዉ የኪነ-ጥበብ ስራዎች የሀገር ገጽታን ከመገንባት ባለፈ ለኢኮኖሚ እድገት ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ወሳኝ መሆኑንም አቶ ሲሳይ አክለው ገልጸዋል።
ይህ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለፈጠራ ባለቤቶች ተገቢው ክብርና ክፍያ እንዲሰጥ እንዲሁም ለዘርፉ እድገት ምቹ የሕግ ከባቢ እንዲፈጠር መሰረት ጥሎ እንደሚያልፍ ይጠበቃል።

2 months ago
የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የምስራቅ ኢትዮጵያን የቱሪስት መስህቦች ጎበኙ
#fastmereja I በ"ቅን ልቦች" የበጎ አድራጎት ድርጅት የተዘጋጀውና በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ያሳተፈው «የሰላም ቱሪዝም ለሀገር ግንባታ» የጉብኝት መርሃ ግብር በድሬዳዋ፣ በማያ ከተማና በሐረሪ ክልል በድምቀት ተካሂዷል። ይህ ጉብኝት የሀገሪቱን የቱሪዝም ሀብቶች በማስተዋወቅና ሰላምን በመገንባት ረገድ ያለውን ፋይዳ ለማጎልበት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በጉዞው መጀመሪያ የቡድኑ አባላት በድሬዳዋ ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በንግድና በኢንዱስትሪ የምትታወቀው ድሬዳዋ፣ በዘመናዊ የከተማ ውበትና ለመንገደኞች ምቹ በሆኑ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ተገቢውን የቱሪስት መዳረሻነት እየተቀዳጀች መሆኑን ታዝበዋል። ተፅዕኖ ፈጣሪዎቹ በቆይታቸው የከተማዋን የቀድሞ ለውጥና የአሁኑን ገጽታ በማነጻጸር የተሰሩ ስራዎች ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ዕድገት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።
የጉዞው ቀጣይ መዳረሻ የነበረችው የማያ ከተማ ሲሆን፣ በዚያም በአንድ ወቅት ደርቆ የነበረውና በአሁኑ ወቅት በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ጥበቃ ዳግም ህይወት የዘራው የሐረማያ ሐይቅ ተጎብኝቷል። የሐይቁ መመለስ ለአካባቢው ስነ-ምህዳርና ለቱሪስት መስህብነት ያለውን ሚና የተረዱት ተሳታፊዎቹ፣ የተፈጥሮ ሀብትን መጠበቅ ለሀገር ግንባታ ያለውን ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተውበታል። ይህ የሐይቁ መመለስ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ የፈጠረው ተስፋና ደስታም የጉብኝቱ ልዩ ትኩረት ነበር።
በሐረሪ ክልል በተደረገው ጉብኝት ደግሞ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦድሪ በድሪ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ ተፅኖ ፈጣሪዎቹ በዩኔስኮ የተመዘገበውን ታሪካዊ የጀጎል ግንብን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የሐረር የቆየ የመቻቻልና የፍቅር እሴት ለሰላም ቱሪዝም ግንባታ እንደ ምሳሌ የሚጠቀስ መሆኑ ተመላክቷል። ክልሉ ያለውን ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በስፋት ማስተዋወቅ እንደሚገባም በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።
«የሰላም ቱሪዝም ለሀገር ግንባታ» የሚለው ጽንሰ-ሃሳብ በዋናነት ቱሪዝምን እንደ አንድ የዲፕሎማሲና የሰላም ግንባታ መሳሪያ መጠቀም ላይ ያተኩራል። ሰዎች ከተለያዩ አካባቢዎች በመነሳት የሌላውን ባህል፣ ታሪክና እሴት ሲጎበኙ በመካከላቸው ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ ጥላቻንና ጥርጣሬን ያስወግዳሉ። ይህም በተራው ለሀገራዊ አንድነትና ለጋራ ግንባታ መሰረት የሚጥል ሲሆን፣ ቱሪዝም በኢኮኖሚ ከሚያስገኘው ገቢ ባለፈ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን በማጠናከር ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ያለውን ከፍተኛ ሚና ያመላክታል። ተጽዕኖ ፈጣሪዎቹም ይህንኑ እውነት በማህበራዊ ገጾቻቸው በማጋራት የሀገርን ገጽታ የመገንባት ሃላፊነት እንዳለባቸው ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
📷 Visit Oromia

ፍቼ ጫምበላላ በዓል በአዲስ አበባ ተከበረ
የሰላም፣ የመከባበርና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነው የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፍቼ ጫምበላላ ዛሬ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ለሰባተኛ ጊዜ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
በበዓሉ አከባበር ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በምርቃት ተጀምሯል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፍቼ ጫምበላላ የፍቅርና የአዲስ ተስፋ መገለጫ ከመሆኑም ባለፈ የጨረቃንና የከዋክብትን ዑደት የቀመረ ጥልቅ ሀገር በቀል እውቀት የሚታይበት የአለም ህዝብ ቅርስ ነው ብለዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዓሉ የሲዳማ አባቶች ያላቸውን ጥልቅ የሥነ-ፈለክ ዕውቀት ለዓለም ያስተዋወቀ የታሪክና የባህል ማንነት መገለጫ መሆኑን በንግግራቸው አንስተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ በዓሉ በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበና የከተማዋን ብዝኀነት ይበልጥ የሚያጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ይህ በዓል እሴቱ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍና የቱሪዝም ዘርፉን እንዲያነቃቃ ከክልሉ መንግሥት ጋር በትኩረት እንደሚሠራ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

የፊቼ ጫምባላላ በዓል በአዲስ አበባ በልዩ ድምቀት ተከበረ!
#fastmereja I የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫና በዩኔስኮ (UNESCO) በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የፊቼ ጫምባላላ በዓል በዛሬዉ እለት በወዳጅነት አደባባይ በድምቀት ተከበረ።
በዓሉ በመዲናዋ ለ7ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን ዋና ዓላማውም የሰላም፣ የእርቅና የአንድነት እሴቶችን ለሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ማጋራት እንደሆነ ተገልፆ በዓሉ ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትና ለተፈጥሮም ጭምር ሰላምን የሚመኝ ጥልቅ ባህላዊ ትርጉም ያለው መሆኑም ተመላክቷል።
ፊቼ ጨምበላላ ትልቅ የመንፈሳዊና የቁሳዊ ባህል እሴት የሚታይበት በዓል መሆኑን እና፤ የጨረቃንና የከዋክብትን ፈለግና ዑደት ለዘመናት የቀመረ ነባር ሀገር በቀል የእውቀት መገለጫ መሆኑን አስረድተዉ በበዓሉ ላይ የሚታየው የባህሎች መስተጋብርም ኢትዮጵያ የምታልማትን የጋራና ማንነት የሚያንፀባርቅ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትርዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ገልፀዋል።
በዓሉ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ መሪነትና ድጋፍ በየዓመቱ እየተከበረ የቆየ ሲሆን፣ አሁን ላይ ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት የሚሰጥ ትልቅ ህዝባዊ ፌስቲቫል ለመሆን መብቃቱ ነዉ የተገለፀዉ።
በዛሬዉ እለት በተከናወነዉ መርሀ-ግብር ላይ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሲዳማ ማህበረሰብ አባቶች፣ አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም በርካታ የሲዳማ ተወላጆች ታድመዋል።
#ኹነት

Sponsored by
Surafel
2 months ago
የፊቼ ጨምበላላ በዓል ነገ በአዲስ አበባ በድምቀት ይከበራል! 🌿✨
#ethiopia | በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበው የሲዳማ ዘመን መለወጫ — ፊቼ ጨምበላላ — ነገ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ይከበራል።
የአዲስ አበባ የሲዳማ ኮሚኒቲ ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ እሥራኤል መሐመድ እንዳስታወቀው፣ በዓሉ ለ7ኛ ጊዜ በመዲናዋ የሚከበር ሲሆን ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።
የሰላምና የእርቅ ተምሳሌት፦
በዓሉ ከመከበሩ በፊት "አራራ ካራ" (እርቅ እናውርድ) በሚባለው ስርዓት በሰዎች መካከል ሰላም መውረድ አለበት።
ሁለንተናዊ እሴት፦
ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትና ለተፈጥሮም ሰላምን የሚመኝ ጥልቅ ባህላዊ እሴት አለው።
ቱሪዝም፦
የሀገራችንን የባህል ሀብት ለዓለም የሚያስተዋውቅ ታላቅ ክስተት ነው።
ወዳጅነት አደባባይ (Friendship Park)
ነገ ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት ጀምሮ
ሁላችሁም በዚህ ውብ ባህላዊ በዓል ላይ እንድትታደሙ ተጋብዛችኋል።
መልካም የፊቼ ጨምበላላ በዓል! 🌼
#ፊቼጨምበላላ #ሲዳማ #አዲስአበባ #ኢትዮጵያ #ባህል #ወዳጅነትአደባባይ #ficheechambalaalla #sidama #addisababa #ethiopia #culture #unescoheritage #getutemesgen

የፊቼ ጨምበላላ በዓል በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በድምቀት ይከበራል
#fastmereja I አዲስ አበባ
በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበው የሲዳማ ዘመን መለወጫ የፊቼ ጨምበላላ በዓል ነገ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ እንደሚከበር ተገለጸ። የሲዳማ ኮሚኒቲ ማህበር ለበዓሉ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቋል።
የማህበሩ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሚኤሶ እርቤሳ በሰጡት መግለጫ፣ በዓሉ በመዲናዋ ለ7ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን፣ የሰላም፣ የእርቅና የአንድነት እሴቶችን ለሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ለማጋራት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። በዓሉ የሰው ልጅን ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትም ጭምር ሰላምን የሚመኝ ጥልቅ ባህላዊ ትርጉም እንዳለው ተመላክቷል።
የባህል ጥናት ባለሙያው አቶ ስለሺ ወርቅነህ በበኩላቸው፣ ከበዓሉ ቀደም ብሎ “አራራ ካራ” በሚባለው ስርዓት በሰዎች መካከል እርቅ እንደሚወርድና ሰላም ሳይሰፍን በዓሉ እንደማይከበር አስረድተዋል። ይህም ለቱሪዝም ዕድገትና ለሀገራዊ መግባባት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል።
መርሃ ግብሩ ነገ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ ባህላዊ ክነቶች እንደሚከበር ይጠበቃል።
መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

የፊቼ ጨምበላላ በዓል በነገው እለት በአዲስ አበባ ይከበራል
የፊቼ ጨምበላላ በዓል በነገው እለት በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ በድምቀት እንደሚከበር የሲዳማ ኮሚኒቲ ማህበር አስታወቀ።
የአዲስ አበባ የሲዳማ ኮሚኒቲ ማህበር ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ፕሬዚዳንት አቶ ሚኤሶ እርቤሳ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንዳብራሩት፤ ማህበሩ በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበውን የፊቼ ጨምበላላ በዓል ለሰባተኛ ጊዜ እያከበረ ይገኛል።
በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች ከተመዘገበ 11ኛ ዓመት የሆነውን ይህን በዓል ከሌሎች ወንድም ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በመዲናዋ በጋራ ለማክበር ዝግጅቱ መጠናቀቁንም ተናግረዋል።
በዓሉ የሰላም እና የእርቅ ነው ያሉት አቶ ሚኤሶ፤ ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትም ጭምር ሰላምን የሚመኝ እሴት ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል።
በመግለጫው ላይ ንግግር ያደረጉት የባህል ጥናት ባለሙያው አቶ ስለሺ ወርቅነህ በበኩላቸው፤ የፊቼ ጨምበላላ በዓል ከዘመን መለወጫነቱ ባለፈ ጥልቅ የሆኑ የሲዳማ ነባር እውቀቶችና እሴቶች መገለጫ መሆኑን አስረድተዋል።
“ፊቼ ጨምበላላ የሰላም፣ የእርቅና የአንድነት ተምሳሌት ነው” ያሉት ባለሙያው፣ በዓሉ ከመከበሩ በፊት “አራራ ካራ” (እርቅ እናውርድ) በሚባለው ስርዓት በሰዎች መካከል እርቅ መውረድ እንዳለበትና ሰላም ሳይሰፍን በዓሉ እንደማይከበር ገልጸዋል።
በዓሉ ቱሪዝምን ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም አቶ ስለሺ ገልጸዋል።
በዓሉ ነገ በዕለተ አርብ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በወዳጅነት አደባባይ እንደሚከበር ተመላክቷል።
በዮሐንስ መልካሙ

የሹዋሊድ በዓል
በፍቅር ከተማ ሐረር
#ethiopia | ለዘመናት በኩራት ለዘለቀውና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የሹዋሊድ በዓል ተከብሯል።
የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እንደተናገሩት የሐረሪ ሕዝብ ካሉት በርካታ ድንቅ ባህላዊ እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው ብለዋል።
ሹዋሊድ ከረመዳን ጾም መጠናቀቅ በኋላ የሚከበር የደስታ፣ የፍቅር እና የማኅበራዊ ትስስር መገለጫ ነው።
ሚኒስትሯ በዓሉ ኢትዮጵያ ያላትን ጥንታዊ ሥልጣኔና ለዓለም ያበረከተችውን ድንቅ የባህል ሀብት በኩራት ያስታወሰ ነውም ሲሉ ተናግረዋል።
የሹዋሊድ በዓል ለቱሪዝም ዘርፋችን ትልቅ አቅም ይዞ የመጣ ብርቅዬ ሀብታችን ነው።
በታሪካዊቷ የሐረር ጀጎል ግንብ ውስጥ የተከበረው ይህ ደማቅ በዓል፣ በባህላዊ ጭፈራዎች፣ ውብ በሆኑ አልባሳትና የሐረሪ ሕዝብ የእንግዳ ተቀባይነት ሥነ-ሥርዓቶች የታጀበ በመሆኑ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቀልብ የሳበ ነበር።
የቱሪዝም ሚኒስትር ይህንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያገኘ ቅርስ ለዓለም በማስተዋወቅ፣ ሐረርን ዋነኛ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ተብሏል።
በመጨረሻም፣ ይህንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያገኘ ታላቅ ቅርስ የመጠበቅ፣ የመንከባከብና ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነት የሁላችንም ነው።
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በኩላቸው
የሸዋሊድ በአል ባህላዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ የኢትዮዽያዊነትና የጋራ ማንነታችንን በሚያጎላ መልኩ በታላቅ ድምቀት እንዲከበር አድርገናል ብለዋል።
ይህ በመሆኑም በርካቶች የሚታደሙበት የሰላም የፍቅርና የአብሮነት አውድማ እየሆነ መጥቷል።
ሁለቱም ስራዎቻችን በቱሪዝም ዘርፉ የተሰናሰሉ እና በሀረሪ ክልል ፈጣን የማህበራዊና የኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ ሀረርን ወደ ቀድሞው ክብሯና ገናና ታሪኳ መልሰናል ሲሉም ገልጸዋል።
የዘንድሮ የሹዋሊድ በዓል የጎዳና ላይ ሩጫ በማድረግ ተጠናቋል።
በዚህም የ'ቪዚት ሐረር' የጎዳና ላይ ሩጫ በታሪካዊቷ ፈረስ መጋላ ተደርጓል"::
የሹዋሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ "ቪዚት ሐረር" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና መነሻና መድረሻውን ታሪካዊው ፈረስ መጋላ ላይ ያደረገው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ፌስቲቫል፤ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ታዋቂ አትሌቶችና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
#getutemesgen

በቻይና ታላቅ ግንብ ላይ ጉዳት ያደረሱ ሁለት ሴቶች ታሰሩ
"በቪዲዮ እየተቀረጸች መቧጨር ጀመረች" ሲል አንድ ምስክር በግርምት ተናግሯል።
አንዲት ሴት በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ በሆነው ስፍራ ላይ ስሟን በኩራት ቧጭራ ጽፋ ነበር።
ነገር ግን ደስታዋ ብዙ አልቆየም፤ ፖሊሶች በፍጥነት ደርሰው ሴቶቹን ይዘዋቸው ሄደዋል።
ከቻይና ማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ

ውበት ሞልቶ እየፈሰሳት ነው
#ethiopia | በፍቅሯና በሰላሟ የምትታወቀው ሐረር ከተማ ዛሬ ደግሞ ውበት ሞልቶ እየፈሰሳት ትገኛለች።
በዩኔስኮ ሁለት ቅርሶችን በማስመዝገብ ቀዳሚ የሆነችው ሐረሪ ክልል አመታዊው የሹዋሊድ በዓል እያከበረች ትገኛለች።
በዓሉን የሚያከብሩ የክልሉ እንደዚሁም በአሉን ለመታደም ከሀገር ውስጥና ከባህር ማዶ የመጡ እንግዶች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ በአለም ቅርስነት መዝገብ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶቸ መካከል የሹዋሊድ በዓል አንደኛው ነው።
ይህ ኢትዮጵያን በአለም የሚያስተዋውቀው ድንቅ በዓል ታሪኩን በሚመጥን መንገድ በየአመቱ እየተከበረ ይገኛል።
እናም ዛሬ እየተከበረ በሚገኘው በዚሁ በአል ላይ ሐረሪ የውበት አክሊል አላብሷታል።
በአሉን አስመልክቶ የሀረሪ ክልል መንግስት ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፏል።
በዓሉ የክልሉን ህዝቦች የመቻቻል፣ የአብሮነትና የሰላም እሴት በማጉላትና የቱሪዝም ዘርፉን በማጎልበት ረገድ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጿል።
በዓሉ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን እንዲሁም የክልሉን ልማትና ዕድገት የበለጠ ማጠናከር በሚያስችል መልኩ በደማቅ ዝግጅት እየተከበረ ይገኛል።
የሸዋሊድ በዓል በተሳካ መልኩ ለማክበር የተለያዩ ኮሜቴዎች ተዋቅረው ዝግጅት ሲደረግ የቆየ ሲሆን፥ የሐረርን ታሪክ፣ እሴትና ባህል የሚያስተዋውቁ ሁነቶች ለታዳሚዎች እንደሚቀርቡ ነው የተገለጸው፡፡
የክልሉ መንግስት ባስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በዓሉ አብሮነት፣ ፍቅር፣ ሰላምና ወንድማማችነት የሚጠናከርበት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

3 months ago
ሸካ፦ የኢትዮጵያ ድንቅ ቅርስ ፣ የጥቁር ወርቅና የድንግል ተፈጥሮ ምሥጢራዊ ምድር
#ethiopia | የሸካ ደን ዝም ብሎ የዛፎች ስብስብ አይደለም፤ ይልቁንም ተፈጥሮ በምድር ላይ የዘረጋችው መለኮታዊ አረንጓዴ ዕልፍኝ እንጂ ።
እግርን ወደዚህ ደን ማስገባት ማለት ፣ ከከተማው የኮንክሪት ግርግርና ከኑሮ ውጥረት ርቆ ፣ የፍጥረት ምስጢር ወደሚፈታበትና የሰማይና ምድር ድንበር ወደሚሰረዝበት ተዓምራዊ ዓለም መግባት ነው ።
ይህ በዩኔስኮ የተመዘገበ የባዮስፌር ክምችት ፣ የያዛቸው ሰማይ-ጠቀስና ዕድሜ-ጠገብ ዛፎች እንደ ግዙፍ አምዶች ቆመው የሰማይን ጣሪያ የተሸከሙ ይመስላሉ ።
ጥቅጥቅ ያሉ ቅጠሎቻቸው የፀሐይን ብርሃን በጥበብ አጥልለው ፣ ምድርን በዘላለማዊ ቅዝቃዜና ድንግዝግዝ እያጠመቁ ፣ ለሚመጣው እንግዳ የነፍስ እረፍትን በነፃ ይቸራሉ ።
እዚህ ምድር ላይ እያንዳንዱ የውኃ ጠብታ እንደ ክሪስታል የሚፈስ የሕይወት ምንጭ ነው ።
ከጥንታዊ ቋጥኞች ሥር የሚፈልቁ ምንጮችና በድንጋዮች ላይ እየተጋጩ የሚወርዱ ወንዞች የሚያሰሙት ሹክሹክታ ፣ በሺዎች ከሚቆጠሩ አእዋፋት ሰማያዊ ዝማሬና በዛፎች ላይ ከሚፈነጩ ብርቅዬ ዝንጀሮዎች ድምፅ ጋር ተደምሮ ፣ አእምሮን ከጭንቀት የሚያነፃ ተፈጥሯዊ ኦርኬስትራ ይፈጥራል ።
በደኑ እምብርት ውስጥ ፣ የሰው እጅ ሳይነካው በተፈጥሮ ምስጢራዊ ጥበብ የበቀለው ብርቅዬው የዱር ቡና ፣ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክና የደኑን ለምለምነት አጣጥሞ የያዘ የ**"ጥቁር ወርቅ"** መፍለቂያ ነው ።
ጭጋጉ በግዙፍ ዛፎች መሃል እንደ ነጭ መጋረጃ ሲንሳፈፍ፣ ደኑ ከምድር ተለይቶ በደመና ላይ የተገነባ የቅዱሳን መኖሪያ እንጂ ተራ መሬት አይመስልም ።
"ወደዚህ አረንጓዴ ገነት መጓዝ ፤ ለሳንባዎ ንፁህ ኦክስጅንን ፣ ለዓይንዎ ድንቅ ግብዣን ፣ ለልብዎ ደግሞ የማይረሳ ትዝታን ማክረም ነው ።"
ራስዎን ከተፈጥሮ ጋር ለማገናኘት ፣ በድንግልናዋ ከምትመካው ሸካ ጋር ለመተዋወቅና የፈጣሪን ጥበብ በአካል ለመመስከር ዛሬውኑ ወደዚህ የሰላም ምድር ይገስግሱ ።
ሸካ ደን በማይጠፋ ለምለምነቱና በክፍት እጆቹ ይጠብቅዎታል ።
Samuel Mekuanint Tadess✍️✍

ፊቼ ጫምባላላ፦
የሲዳማ ዘመን መለወጫ በመጪው ቅዳሜና እሁድ ይከበራል
#ethiopia | በዓለም የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበው የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ "ፊቼ ጫምባላላ"፣ በመጪው ቅዳሜና እሁድ (መጋቢት 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም) በውቧ ሐዋሳ ከተማ በደመቀ ሁኔታ እንደሚከበር ተገልጿል።
የሲዳማ አባቶች ዘመንን የመቁጠር ጥበባቸውንና ሀገር በቀል ዕውቀታቸውን ለትውልድ ያስተላለፉበት ይህ በዓል፣ የሰላም፣ የዕርቅና የአንድነት ተምሳሌት ነው።
✨ የበዓሉ ልዩ ገጽታዎች
ባህላዊ እሴት፦ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ ይቅርታ የሚደረግበትና የአብሮነት እሴት የሚጎለብትበት ታላቅ ዕለት ነው።
የሐዋሳ አዲስ ገጽታ፦ ዘንድሮ በኮሪደር ልማት ይበልጥ የተዋበችው ሐዋሳ፣ በዓሉን ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች ልዩና ማራኪ ድባብ እንደምትፈጥርላቸው ተጠቁሟል።
የቱሪዝም ንቅናቄ፦ የክልሉን የቱሪዝም መዳረሻዎች ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን፣ ካርኒቫሎችንና ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ያካትታል።
🎨 "ኑ ወደ ሲዳማ እንሂድ!"
በዚህ መሪ ቃል ታዋቂ ሰዎችና አርቲስቶች የሚሳተፉበት ሰፊ የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ ይገኛል። የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ እንደገለጹት፣ ለበዓሉ አከባበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።
🤝 የእንግዳ ተቀባይነት ጥሪ
የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የሚመጡ በርካታ እንግዶችን በለመደው የኢትዮጵያዊ ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት እንዲያስተናግዱ ጥሪ ቀርቧል።
አይዳዶ! (እንኳን አደረሳችሁ!)
#ፊቼጫምባላላ #ሲዳማ #ሐዋሳ #ኢትዮጵያ #ባህልናቱሪዝም #ficheechambalaalla #sidama #hawassa #ethiopia #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

ኑ… ወደ ሲዳማ እንሂድ!
እንኳን ለ"ፍቼ ጫምባላላ" በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
#ethiopia | የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ፣ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት መገለጫ የሆነው "ፍቼ ጫምባላላ" በዓል መጋቢት 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም በድምቀት ይከበራል።
ይህ በዓለም የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ ከተመዘገበ 10 ዓመታትን ያስቆጠረ ታላቅ በዓል ነው።
የዘንድሮውን በዓል ልዩ የሚያደርጉ ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦
🎨 የጥበብ ቤተሰቦች ጉዞ ወደ ሲዳማ
አንጋፋና ወጣት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ያካተተ የኪነ-ጥበብ ቡድን ወደ ሲዳማ ክልል ሊያመራ ነው። የዚህ ጉዞ ዋና ዓላማዎች፦
በዓሉን ከክልሉ ሕዝብና ከሀገር ውስጥና ከውጭ ቱሪስቶች ጋር በጋራ ማክበር።
የሲዳማን የቱሪዝም ሀብቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ።
በክልሉ ያለውን የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር የድርሻቸውን መወጣት።
🤝 አዘጋጆችና መሪ ቃል
ይህ የቱሪዝም ንቅናቄ ፕሮግራም የተዘጋጀው፦
በሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ እና
ጎልደን ሬሽዮ (Golden Ratio) በተሰኘ ተቋም ትብብር ነው።
መሪ ቃል፦ ‹‹ኑ… ወደ ሲዳማ እንሂድ!››
የመርሐ-ግብሩ ክንውን
የጥበብ ቤተሰቦቹ በውቧ ሐዋሳ ከተማ እና በተለያዩ የክልሉ የቱሪስት መዳረሻዎች በመዘዋወር፣ ከእንግዳ ተቀባዩ የሲዳማ ሕዝብ ጋር ባህላዊ እሴቶችን የሚጋሩ ይሆናል።
አይዳዶ!
(እንኳን አደረሳችሁ!)
የፍቼ ጫምባላላ በዓል የሰላምና የብልጽግና ይሁንልን!
#ፍቼጫምባላላ #ሲዳማ #ሐዋሳ #ቱሪዝም #ኢትዮጵያ #ጥበብ #sidama #ficheechambalaalla #ethiopia #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

እንኳን ለሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ‹‹ፍቼ ጫምባላላ›› በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
መጋቢት 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም በድምቀት የሚከበረውን የዘንድሮውን የፍቼ -ጫምባላላ ዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የሐገራችንን አንጋፋና ወጣት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ያካተተ የኪነ-ጥበብ ቡድን ወደ ሲዳማ ክልል ሊያመራ ነው፡፡
ቡድኑ የሠላም፣ የዕርቅ፣ የአንድነትና የፍቅር መገለጫ የሆነውንና በዓለም የማይዳሰስ ቅርሥነት በዩኔስኮ ተመዝግቦ 10 ዓመታትን የተሻገረውን የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፍቼ-ጫምበላላን ከመላው ኢትዮጵያውያን፣ ከተለያዩ የዓለም አገራት ከሚጎርፉ የውጪ ቱሪስቶች እና ከክልሉ ሕዝብ ጋር ለማክበር፣ የሲዳማን የቱሪዝም ሐብቶች በዓለም-ዓቀፍ ደረጃ በሥፋት ለማስተዋወቅ እንዲሁም ተጨማሪ የቱሪስት ፍሰትን መጨመር ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
በክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ እና ጎልደን ሬሽዮ በተሰኘ ተቋም ትብብር የተዘጋጀው ይህ የቱሪዝም ንቅናቄ የጉዞ መርሐ-ግብር ‹‹ኑ… ወደ ሲዳማ እንሂድ›› የሚል መሪ ቃል ተሰጥቶታል።
የጉዞው ተሳታፊ ጉምቱ የጥበብ ቤተሰቦች የዘመን መለወጫ በዓሉን በውቧ ሐዋሳ ከተማ እና በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻ ማዕከላት በመዘዋወር ከእንግዳ ተቀባዩ የሲዳማ ሕዝብ ጋር እንደሚያከብሩ ከቡድኑ አስተባባሪዎች ለመረዳት ተችሏል።
ኑ… ወደ ሲዳማ እንሂድ!
https://www.facebook.com/s...

''የቡና ዛፍ፣የፍቅር ዛፍ ነው''
📌2ኛው የኢትዮጵያ የቡና ባህል ፌስቲቫል በአድዋ ድል መታሰቢያ ተካሄደ!
#ethiopia | የኢትዮጵያን ጥልቅ የቡና ባህልና ለሀገር አንድነት ያለውን ፋይዳ የሚያሳይ 2ኛው የኢትዮጵያ የቡና ባህል ፌስቲቫል ታሪካዊ በሆነው በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት ተከናውኗል።
በዋርካ ኮፊ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አዘጋጅነት "የቡና ባህላችን ለሀገራዊ አንድነታችንና ለኢኮኖሚ እድገታችን" በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ ፌስቲቫል፣ ከቡና መጠጣት ስነ-ስርዓት ባለፈ ትልቅ ሀገራዊ ግብን ያነገበ ነው።
የፌስቲቫሉ ዋና ዋና ክንውኖች
* የዩኔስኮ (UNESCO) ንቅናቄ፦ የዋርካ ኮፊ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሰአዳ ሙስጠፋ እንደገለጹት፣ ይህ ፌስቲቫል የኢትዮጵያ የቡና ባህል በዓለም አቀፉ የቅርስ ተቋም (UNESCO) እንዲመዘገብ የሚደረገው ጥረት አካልና ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።
* ባህላዊ ውበት፦ የአስራ አንዱም ክልሎች ልዩ የቡና አፈላል ስነ-ስርዓት፣ ማራኪ ባህላዊ አልባሳትና የቁሳቁስ አውደ-ርዕይ ለዕይታ ቀርቧል።
* ጥበብና ባዛር፦ ከቡናው መዓዛ ጋር ተደምሮ የስዕል ኤግዚቢሽኖች፣ የእደ-ጥበብ ስራዎች ባዛር እና የተለያዩ ዝግጅቶች መርሃ-ግብሩን አድምቀውታል።
በተጨማሪም በነገረ ቡና ላይ ያተኮረ ውይይት የተከናወነ ሲሆን ''የቡና ዛፍ፣የፍቅር ዛፍ ነው'' የሚሉ እና ልዩ ልዩ ሃሳቦችን በውስጣቸው የያዙ የውይይት ሃሳቦች ተነስተዋል።
የክብር እንግዶች
በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል ተወካዮች፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የቅርስ ጥበቃ ባለሙያዎች፣ የቡና ላኪዎችና ተመራማሪዎች ተገኝተው የኢትዮጵያን የቡና ጥበብ ታዝበዋል።
ይህ ፌስቲቫል ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን፣ ቡናን ከማህበራዊ ትስስርና ከኢኮኖሚ እድገት ጋር አቀናጅታ የያዘች ድንቅ ሀገር መሆኗን ለዓለም ዳግም ያስመሰከረ ሆኖ አልፏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #coffeeculture #warkacoffee #adwamemorial #unesco #ethiopiancoffee #unity #economicgrowth #addisababa

4 months ago
☕️ የኢትዮጵያ የቡና ባህል ቀን ፌስቲቫል በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ሊካሄድ ነው! 🇪🇹✨
#ethiopia | ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን፣ ለዓለም ልዩ የሆነ የቡና ሥነ-ሥርዓት ባህል ያበረከተች ሀገር ናት።
ይህንን የቆየ ማህበራዊ መስተጋብራችንን ለማክበርና ይበልጥ ለማስተዋወቅ የተዘጋጀው ታላቁ ፌስቲቫል ለ2ኛ ጊዜ ሊካሄድ ዝግጅቱን አጠናቋል።
የፌስቲቫሉ ዋና ዋና ነጥቦች፦
📅 ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም.
📍 በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም
👥 ከ2 ሺህ 5 መቶ እስከ 3 ሺህ የሚደርሱ የህብረተሰብ ክፍሎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
🎯 ዓላማው፦ የቡና ሥነ-ሥርዓት ባህላችንን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ፣ ለዓለም ለማስተዋወቅና በዩኔስኮ (UNESCO) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ግፊት ለማድረግ ነው።
የዋርካ ቡና ኃ/የተ/የግል ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሰዓዳ ሙስጠፋ እንደገለጹት፤ ይህ ፌስቲቫል ቡና ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባለፈ ያለውን ጥልቅ ማህበራዊ ትስስር የሚያሳይ ነው።
በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በመታደም የኢትዮጵያን የቡና ባህል እንዲያደምቅ ጥሪ ቀርቧል።
ኑ! የጥቁር ወርቃችንን ሽታና የሥነ-ሥርዓቱን ውበት አብረን እናጣጥም! ☕️🌿
#ethiopiancoffee #coffeeculturefestival #unesco #warkacoffee #adwamuseum #addisababa #ethiopia #coffeeceremony #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

የጥቁር ወርቁ አዲስ ምዕራፍ፦ ዋርካ ኮፊ እና የኢትዮጵያ ኤክስፖርት ማርኬት ስልታዊ ጥምረት
የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚካሄደው የቡና ባህል ፌስቲቫል፣ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጉዞ አዲስ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው። ዋርካ ኮፊ እና የኢትዮጵያ ኤክስፖርት ማርኬት (EEM) የተፈራረሙት ስምምነት እንዲሁ የወረቀት ላይ ፊርማ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን "ጥቁር ወርቅ" ከጥሬ ምርትነት (Commodity) ወደ "ባህላዊ የንግድ ኃይል" (Cultural Economic Power) የማሸጋገር ስልታዊ ቃል-ኪዳን ነው።
ዋርካ ኮፊ እና "የልምድ ኢኮኖሚ" ትንሳኤ
በዘመናዊው የንግድ ዓለም "ምርት መሸጥ" አርክቷል። ሸማቾች ዛሬ የሚፈልጉት ዕቃን ሳይሆን "ትርክትን" ነው። የዋርካ ኮፊ መስራች ወ/ሮ ሰዓዳ ሙስጠፋ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓቱን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ መነሳሳታቸው፣ ይህንን የቆየ ባህል ወደ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ኃይል የመቀየር ስልት ነው።
ይህ በንግድ ፍልስፍና "Experience Economy" ይባላል። ዋርካ ኮፊ ለዓለም እያቀረበ ያለው ቡናን ብቻ ሳይሆን፣ ያ ቡና ተቆልቶ፣ ተወቅጦ፣ በጄበና ፈልቶ የሚቀርብበትን "ቅዱስ" ሥነ-ሥርዓት ነው።
ይህ ሥነ-ሥርዓት የንግድ ምልክቱ (Brand) አካል ሲሆን፣ ምርቱ በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪ የማይገኝለት "ልዩ ዋጋ" (Premium Value) እንዲያገኝ ያደርገዋል። ሸማቹ ለዋርካ ኮፊ የሚከፍለው ለካፌይኑ ብቻ ሳይሆን፣ ለታሪኩ፣ ለሽታው እና ለኢትዮጵያዊቷ እናት ጥበብ ጭምር ይሆናል።
የዓለም አቀፍ ተሞክሮ፦ ከጃፓን ሻይ እስከ ፈረንሳይ ወይን
ዋርካ ኮፊ የጀመረው ይህ ንቅናቄ በሌሎች ሀገራት ታላቅ የኢኮኖሚ ለውጥ አምጥቷል፦
የጃፓን "ቻኖዩ" (The Way of Tea): ጃፓኖች የሻይ አፈላል ሥነ-ሥርዓታቸውን እንደ መንፈሳዊ ጥበብና ሀገራዊ ኩራት ለዓለም ሸጠዋል። ዛሬ በለንደን ወይም በኒውዮርክ የጃፓን ሻይ ቤት የሚገባ ሰው የሚከፍለው ለቅጠሉ ሳይሆን ለክብሩና ለሥርዓቱ ነው።
የፈረንሳይ "ቴሮዋር" (Terroir): ፈረንሳውያን ወይናቸውን የሚሸጡት "ከየትኛው አፈር በቀለ?" በሚል ትርክት ነው። ለፈረንሳይ ወይን የሚከፈለው ከፍተኛ ዋጋ፣ ምርቱ ከሀገሪቱ ታሪክና ባህል ጋር ጥብቅ ቁርኝት ስላለው ነው።
ዋርካ ኮፊ እና EEM የኢትዮጵያን ቡና ከታሪካዊው የአድዋ ድል እና ከዩኔስኮ ምዝገባ ጋር ሲያቆራኙት፣ የኢትዮጵያ ቡና "የዓለም ቅርስ" የሚል ማህተም ያርፍበታል።
ይህ ደግሞ በኢኮኖሚክስ "Price Inelasticity" (የዋጋ ተለዋዋጭነትን መቋቋም) ይፈጥራል፤ ባህሉን የወደደ ሸማች ዋጋው ቢጨምር እንኳ ቡናውን መግዛቱን አያቆምም።
ማኅበራዊ ትስስር እንደ መፍትሔ
ባህል ፈላስፎች እንደሚነግሩን፣ ቡና በኢትዮጵያ ምድር "ማኅበራዊ ሙጫ" (Social Glue) ነው። ፈላስፋው ዋልተር ቤንጃሚን ስለ አንድ ነገር "ኦራ" ወይም ልዩ መንፈሳዊ ግርማ ይናገራል። የኢትዮጵያ ቡና ሥነ-ሥርዓት "ኦራው" ያለው በጋራ መጠጣትና በመመካከር ላይ ነው።
ዋርካ ኮፊ ይህንን "ኦራ" ወደ ፌስቲቫል መድረክ ማውጣቱ፣ የባህል ዲፕሎማሲን ከንግድ ጋር የማዋሃድ ጥበብ ነው። ፈላስፋው ማርቲን ሐይዴገር "መኖር ማለት በአንድ ቦታ ላይ በጋራ መገኘት ነው" እንደሚለው፣ የቡና ስነ-ስርአት ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚገኙበት፣ የሚወያዩበትና ሰላምን የሚሰብኩበት "ብሔራዊ መኖሪያቸው" ነው።
ይህንን መኖሪያ ለዓለም ማሳየት ደግሞ የሀገርን ገጽታ የመገንባት (Nation Branding) ትልቁ መሣሪያ ነው።
ጥሬ ዕቃ ወደ እሴት ጭማሪ
ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ ዓለም አቀፍ የቡና ገበያ 90% የሚሆነው ትርፍ የሚገኘው ከቆላ፣ ከማሸግና ከታሪክ ግንባታ (Branding) ነው። ኢትዮጵያ ግን አሁንም አብዛኛውን ቡናዋን የምትልከው በጥሬው ነው።
የዋርካ ኮፊ እና የEEM ስምምነት ይህንን ክፍተት ለመድፈን የሚከተሉትን ነጥቦች ታሳቢ ያደርጋል፦
የቱሪዝም ትስስር: ጥናቶች እንደሚጠቁሙት "የባህል ቱሪስቶች" ከመደበኛ ቱሪስቶች 30% የበለጠ ወጪ ያደርጋሉ። ፌስቲቫሉ ከ3,000 በላይ ሰዎችን መሳቡ፣ ለሆቴሎችና ለእደ-ጥበብ ባለሙያዎች ቀጥተኛ ገቢ ያስገኛል።
የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ: የቡና ሥነ-ሥርዓት በዋናነት በሴቶች የሚመራ በመሆኑ፣ ዋርካ ኮፊ ይህንን ባህል ሲያሳድግ በዘርፉ ያሉ እናቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ያደርጋል።
የገበያ ተደራሽነት: ባህሉ ሲታወቅ፣ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም ገበያ ላይ ያለው ተፈላጊነት ይጨምራል። ሸማቾች ቡናውን ብቻ ሳይሆን የሸክላ ጀበናዎችን፣ ዕጣንንና ባህላዊ ቁርሶችንም መፈለጋቸው አይቀሬ ነው።
መደምደሚያ
የካቲት 14 በአድዋ ሙዚየም የሚበራው የረከቦት ሻማ፣ ለኢትዮጵያ ኤክስፖርት አዲስ ብርሃን ነው። ዋርካ ኮፊ የጀመረው ይህ ንቅናቄ፣ ቡናችንን ከኩባያ አውጥቶ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ እንደ "የጥበብ ስራ" እንዲታይ ያደርገዋል።
ይህ ስምምነት ነገ የኢትዮጵያ ቡና ቤቶች በፓሪስና በኒውዮርክ ጎዳናዎች ላይ እንደ "ባህል ማዕከል" እንዲቆሙ መንገድ ይከፍታል። ሸማቹ ቡናውን ሲጠጣ፣ የእጣኑን መዓዛ እና የጀበናውን ውበት አብሮ ያጣጥማል። ዋርካ ኮፊ ባህላችንን ለዓለም በማጋራት፣ ኢኮኖሚያችንን የማሳደግና ማንነታችንን የማጽናት ታላቅ ቃል ኪዳን ገብቷል።

ቱሪዝም ልጇን አጣች!
"ውብ ሀገርን ይዤ መጥቻለሁ!"
#ethiopia | የጋቶ ወንዝን እንደተሻገራችሁ የምታገኟት የኮንሶዎች መንደር ፍጨጫ ትባላለች፡፡ ከፍተኛ የአሸዋ ምርት የሚገኝበትን ካይሌ ወንዝ እንዳለፋችሁ ካራት ከተማ ትገባላችሁ፡፡
ዘሪሁንን የተዋወቅሁት ካረት፣ ኮንሶ ልዩ ወረዳ ነበር።
ዱሮ ዱሮ የኮንሶ ብሔረሰብ የሚኖረው በ49 የተከለሉ አምባ መንደሮች ውስጥ ነበር፡፡ አሁን ሰባቱ አምባ መንደራት ፈርሰው 42ቱ ብቻ ቀርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 12ቱ መንደሮች የላይኛውና የታችኛው ዶከቱ፣ ታራ፣ ጋሞሌ፣ ቡሶ፣ ኦላንታ፣ መጨሎ፣ መጨቄ፣ ጎጫ፣ ሁሉሜ፣ ቡርኩዳና ቡርጆ የጥበቃ ከለላ ድንበር "ሦስቱ የጎሳ መሪዎች የሚያስተዳድሯቸው ‹‹የተቀደሱ ደኖች››፤ ጋሞሌ አምባ መንደር የሚገኘው ‹‹ሙራ ካላ››፣ በላይኛው ዶካቱ ‹‹ሙራ ባማሌ››፣ በፋሻ ‹‹ሙራ ቁፋ›› እንዲሁም ኩሬ ሃርዳ ዶከቱ፣ ሃርዳ መጨቄ፣ ሃርደ ዱራይቴና ሀርዳ ቡሶ (ጥንታዊ ባሕላዊ ኩሬዎች) የላቀ ዓለም አቀፍ ቅርስ እንዳላቸው ታምኖ በዩኔስኮ ተመዝግበዋል፡፡
ነፍሱ ይማርና ከኃይለመለኮት አግዘው ጋር
ኮንሶ አምባ መንደር በተደጋጋሚ ለሥራ ስንጓዝ ከሠራዊት ኮንሶ ጋር ዘሪሁን ግርማን አናጣውም ነበር።
የኮንሶ ልጅ፤ ዘሪሁን መምህራን ( እናቱና አባቱ ) መኖሪያ ቤት ከረት ከተማ፣ ኮንሶ ተስተናግደናል። ቤተሰቦቹ ከኮንሶ ወደ አርባምንጭ ተጉዘው መኖር እንደጀመሩ ነግሮኝ ነበር።
ዘሪሁን - ከዚህ በታች የላከልኝ መልዕክት ለአገርና ለሕዝብ አጋርቼለት ነበር።
"ዘሪሁን ግርማ #zerihun Girma ነኝ። የባህል የቱሪዝምና የሆስፒታሊቲ ጋዜጠኛ እና አማካሪ ከአስር /10/ አመታት በላይ በሬዲዮ ዘርፍ በዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም፣ በደቡብ ኤፍ ኤም 100.9 እና በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የሬዲዮ ጣቢያዎች እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የኢትዮጵያን ባህል ቱሪዝም እና የሆስፒታሊቲ ዘርፍን ሳስተዋውቅ እና ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ኘሮግራሞችን ሳቀርብ ቆይቻለሁ።
ነገር ግን የብዙ ወዳጆቼ እና የሬዲዮ አድማጮቼ ጥያቄ ያለኝን ልምድ እና ስለኢትዮጵያ በጉዞ ያወኳቸውን በምስል ማሳየት እችል ዘንድ በቴሌቪዥን ፕሮግራም እንድመጣ ነበር።
ይሁንና ፈጣሪ የፈቀደው ነውና የሚሆነው አሁን ጊዜው ደርሷል።
ውብ ሀገርን ይዤ መጥቻለሁ!"
ውብ ሀገር
በኢሳት ቴሌቪዥን ከቅዳሜ፣ ሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓም - ዘወትር ቅዳሜ ምሽት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ ይቀርብ ነበር።
ዘርሁን ግርማ
ሀገራችን ኢትዮጵያ ታላቁን የቱሪዝም አርበኛ ነበር። በድንገተኝ ሞት አጣነው።
የሀገራችን የሆስፕታሊትና ቱሪዝም አምባሳደር የሆነው ወንድማችን ዘሪሁን ግርማ በድንገተኝ ሞት ተለየን።
ዘሪሁን ግርማ የቱሪዝም ሞተር፣ ተጓዥ ጋዜጠኛ፣ የውብ ሀገሬ ቲሌቪዥን ፕሮግራም መሥራች፣ የቱሪዝም ባለሙያወች ድምፅ ነበር።
#ኮዞባቱ ኾራ አታ ኾንሶ ሰኔ 20-21/2017ዓ.ም በዓል አዘጋጅ ነበር።
ቱሪዝምን አውርቶ የማይጠግበው፣ በሀገሩ የሚኮራ፣ በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን የሀገራችንን ቱሪዝምን በማስተዋወቅ፣ ብዙ የሠራ፤ የታተረ የውብ ሀገር ጋዜጠኛ ድንገተኛ ሞት እጅግ በጣም አሳዝኖናል።
የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር በጋዜጠኛ ዘሪሁን ህልፈት መግለጫ አውጥቷል።
"...ቱሪዝም ልጇን አጣች፣ቱሪዝምን አውርቶ የማይጠግበው በሀገሩ የሚኮራው በሬድዮ እና በቲቪ የሀገራችንን ቱሪዝምን በማስተዋወቅ ብዙ ለመስራት ብዙ ለመሮጥ ሀገሩን በሰፊው ለማስተዋወቅ የውብ ሀገር ብሎ የጀመረው የማህበራችን መስራች እና አባል ወንድማችን ጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ ድንገተኛ ሞት እጅግ በጣም አዝነናል"
ዘሪሁን
ከሐያት 49 ወደ አርባምንጭ ከለሊቱ 7:00 ሰዓት አስከሬኑ በክብር ተሸኝቷል።
ዘሪሁን ግርማ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበር።
ለቤተሰቡ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ ፣ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ እግዚአብሔር ያጽናችሁ።
ነፍስ ይማር።

በኢራን የቅድስት ድንግል ማርያም ክብር ተገለጠ !
#ethiopia | የኢራን መንግሥት በቴህራን የሚገኘዉን ዋናዉን የምድር ውስጥ የባቡር መስመር 6 የሚገኘውን አዲሱን የሜትሮ ጣቢያ “የቅድስት ማርያም ሜትሮ ጣቢያ።” ስትል ሰየመችው ።
ከክርስቶስ ልደት በኋላ 66 አመተምህረት ከክርስቶስ አስራሁለቱ ሃዋርያት አንዱ የሆነዉ ሀዋርያ ታዴዮስ ክርስትናን በተሰበከችዉና
ዛሬ ላይ የሙስሊም አብላጫ ቁጥር ባለባት ሀገር ውስጥ፣ እንደዚህ አይነት ክርስትያናዊ ሥነ ሕንፃ የተላበሰው እና በሃይማኖታዊ እና በባህላዊ ተምሳሌትነት አጉልቶ የሚያሳይ
ጎዳና መሰየሟ የህዝብን ትኩረት ከመሳቡ ባሻገር ለብዙ የምዕራባውያን ታዛቢዎች ያልተጠበቀ ተብሏል ።
የዚህ ጣቢያ ግድግዳዎች በቅድስት ማርያም እና በኢየሱስ ክርስቶስ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ምስሎች ያጌጡ ሲሆኑ በኢራን ሃይማኖታዊ ጥበብ ተመስጦ የተሰሩ ዲዛይኖች፣ በአብርሃም ሃይማኖቶች ተከታዮች መካከል የጋራ መከባበርን ያመለክታሉ።
በአርመኖች ዋና ከተማ ውስጥ ካሉት በጣም ውክልና ካላቸው የክርስቲያን ቤተመቅደሶች አንዱ በሆነው በሳርኪስ ካቴድራል አቅራቢያ የሚገኘው ጣቢያው በክርስቲያኖችም ሆነ በሺዓ ሙስሊሞች ዘንድ ለለከበረችው ለድንግል ማርያም ክብር ሲባል "ቅድስት ድንግል ማርያም" (ሃዝራት ማርያም ሞጋዳስ) ተብሎ መሰየሙም ተገልጿል ።
የኢራን ክርስቲያንኖች ይህ ጣቢያ በመከፈቱ ደስታቸውን እየገለፁ ሲሆን
በቴህራን የምትኖር ናዛኒን የተባለች ክርስቲያን ልጃገረድ በኢንስታግራም ላይ እንዲህ ስትል ጽፋለች፡- “በየቀኑ በዚህ መንገድ አልፋለሁ። የቅድስት ማርያምን ምስል በቴህራን ሜትሮ መሃል ላይ ስትመለከቱ በጣም ጥሩ ስሜት ይሰማኛል። በእውነት የኩራት ምንጭ ነው።”
በኢስፋሃን የምትኖር ክርስቲያን ልጃገረድ ፓሪሳ በኤክስ ላይ እንዲህ ስትል ጽፋለች፡- “ይህ ጣቢያ ግልጽ መልእክት ይዟል፡- ኢራን ለሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ኢራናውያን አድርገው ለሚቆጥሩ የሃይማኖት ተከታዮች ሁሉ አገር ናት።” ብላለች።
ይህ ጣቢያ የቴህራን የምድር ውስጥ ባቡር መስመር 6 25ኛ ጣቢያ ሲሆን በካሪም ካን ዛንድ ጎዳና እና በኦስታድ ነጃቶላሂ ጎዳና መገናኛ ላይ፣ በሴንት ሳርኪስ ካቴድራል አቅራቢያ ይገኛል።
የምዕራብ እስያ የዜና ኤጀንሲ ስለ ጣቢያው እንዲህ ሲል ዘግቧል ።
ኢራን፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች ምድር
“የቅድስት ድንግል ማርያም ጣቢያ” በተመረቀበት ወቅት፣ ኢራን እንደገና የሃይማኖቶች መካከል የሚደረግ ውይይት መፈክር ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ ታሪካዊ ማንነት አካል መሆኑን አሳይታለች።
ከአካይመኒድ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አብሮ የመኖር እና የሌሎችን እምነት የማክበር መንፈስ በኢራን ባህል ውስጥ ተሸፍኗል - ይህ ባህል በቴህራን የምድር ውስጥ ባቡር ውስጥ እንኳን በውበት እና በመረጋጋት እራሱን ያሳያል። በማለት አስነብቧል ።
የኢራን የመንግስት ሚዲያዎች ስያሜውን የባህል አብሮ የመኖር ምልክት አድርገው ገልጸውታል፣ የኢራን፣ መንግሥት እንደ ክርስቲያኖች፣ አይሁዶች እና ዞራስትሪያኖች ላሉ ታሪካዊ የሃይማኖት አናሳዎች የአምልኮ ነፃነትን እውቅና ይሰጣል ። የዚህ ጣቢያ ምረቃ ለድንግል ማርያም የጋራ ፍቅርን ያሳያል
ብለዋል ።
ብዙ ተጠቃሚዎች እርምጃውን “ያልተጠበቀ” ግን “አዎንታዊ” ሲሉ ተቀብለውታል ።
ከአናቶሊያ እስከ ኢንደስ ወንዝ ከካውካሰስ እስከ ፋርስ ባህረ ሰላጤ ድረስ የተዘረጋችዉ ከክርስቶስ ልደት በፊት ሺህ ዓመታት የሚመዘዝ ታሪክ ባለቤቷ ፋርስ ክርስትናን ቀድመዉ ከተቀበሉ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ዛሬ ላይ የምንጠቀምበትን ሂሳብ ማስላት ለአለም አስተምራለች ጃላለዲን ሩሚ እና ኦማር ካያምን የሚያህሉ ግዙፍ ገጣሚዎችን በስነህንፃ፣ በፍልስፍና፣ በሕክምና የተራቀቁ ልጆች ያሏት ፋርስ ።
600 የሚጠጉ አብያተ ክርስቲያናት መገኛ ስትሆን 90 ያህሉ በብሔራዊ የሀገር ኩራት ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ሦስት ገዳማትን ደግሞ በዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ አስመዝግባለች ።
ታዴ የማመይ ልጅ

የጥበብ ደም ማነስ፦ የ18 በመቶው እውነታ እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት የህልውና አደጋ
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት የታየው የዩኒቨርሲቲዎች መስፋፋት በብዙዎች ዘንድ "የቁጥር አብዮት" ተብሎ ሲወደስ ቆይቷል። ከመሬት እንደሚበቅል እንጉዳይ በየክልሉ የተተከሉ ዘመናዊ ሕንፃዎች፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን እቅፍ አድርገው ሲቀበሉ ማየት ለሀገር ተስፋ ነበር። ይሁን እንጂ፣ ሰሞኑን በትምህርት ሚኒስቴር ይፋ የተደረገው አንድ መርዶ መሰል መረጃ የዚህን አብዮት ውስጣዊ ይዘት ፍንትው አድርጎ አሳይቷል፦
የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መምህራን የዶክትሬት ዲግሪ (PhD) ስብጥር 18 በመቶ ብቻ ነው።
ይህ ቁጥር ተራ አኃዝ አይደለም፤ የሀገሪቱን የዕውቀት ማገር የነቀነቀ፣ ጥበብ በደረቀበት ምድር ላይ የቆምን መሆናችንን የሚያሳብቅ "የአእምሮ ደም ማነስ" ምልክት ነው። 82 በመቶው የሀገሪቱ ከፍተኛ ትምህርት የሚመራው ገና በሁለተኛ ዲግሪና በለጋ ወጣት መምህራን መሆኑ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚረከበው ትውልድ በምን ዓይነት የዕውቀት ጥራት ላይ እንዳለ ያሳስባል።
1. የቁጥሮች ቋንቋ እና የዓለም አቀፉ መድረክ መርዶ
በዓለም አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት የሚለካው በሕንጻዎች ርዝመት ወይም በተማሪዎች ብዛት ሳይሆን፣ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚመነጨው አዲስ ዕውቀት (Knowledge Production) ነው። የዓለም ባንክ እና የዩኔስኮ (UNESCO) ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ አንድ ሀገር ወደ ኢንዱስትሪ ሽግግር ለማምራትና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ቢያንስ 40% እና ከዚያ በላይ የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው መምህራን ያስፈልጓታል።
የኢትዮጵያን 18% ከጎረቤት ሀገራት ተሞክሮ ጋር ስናነጻጽረው እውነታው ይበልጥ ልብ አንጠልጣይ ይሆናል። ለምሳሌ ኬንያ ይህንን ቁጥር ከ35% በላይ ለማድረስ ያደረገችው ጥረት በምስራቅ አፍሪካ የቴክኖሎጂ ማዕከል (Silicon Savannah) እንድትሆን አስችሏታል። ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ቁጥሩን ወደ 50% በማስጠጋቷ አህጉራዊ የምርምር ቁንጮ ለመሆን በቅታለች። በኢትዮጵያ ግን አሁንም 82 በመቶው ትምህርት የሚሰጠው በወጣት መምህራን መሆኑ፣ ተማሪዎች ከአዲስ የምርምር ግኝቶች ይልቅ የቆዩ ንድፈ-ሀሳቦችን ብቻ እንዲቀሰሙ አድርጓቸዋል።
ይህ ሁኔታ "ዕውር ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ጉድጓድ ይገባሉ" የሚለውን ስጋት እውን ያደርገዋል።
2. የእውቀት ነፃነት ወይስ የዲግሪ ክምችት?
ታላቁ የግሪክ ፈላስፋ ፕላቶ በ"ሪፐብሊክ" መጽሐፉ ላይ "ፈላስፋ ነገሥታት" ሀገርን መምራት እንዳለባቸው ሲሰብክ፣ እውቀት ከሥልጣን ጋር መጣመር እንዳለበት ያምን ነበር። በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች "እውነትን" ከመፈለግ ይልቅ "ምስክር ወረቀት" ለማተም የሚሯሯጡ ፋብሪካዎች ሲመስሉ ይስተዋላል።
ከልብ ለማስተማር የሚተጉም ተቋማትም እንዳሉ መካድ የለብንም።
ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪውን ለነፃነትና ለፈጠራ ከማዘጋጀት ይልቅ፣ ለሥራ ቅጥር ወረፋ ሲያዝጋጁ ብዙ ጊዜ ተስተውለዋል።
ጀርመናዊው ፈላስፋ ማርቲን ሄይዴገር ስለ ቴክኖሎጂ ሲተነትን፣ ቴክኖሎጂ መሣሪያ ብቻ ሳይሆን "የመግለጫ መንገድ" ነው ይላል።
ኢትዮጵያ 1,200 መምህራንን ወደ ህንድ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች (IIT) ለመላክ ማቀዷ፣ ሄይዴገር እንደሚለው "የሰው ኃይል ክምችት" የመፍጠር ትልቅ ጥረት ነው። ሆኖም ሚዛናዊው ጥያቄ፦ እነዚህ መምህራን ሲመለሱ የህንድን ቴክኖሎጂ ይዘው ይመጣሉ ወይስ የኢትዮጵያን ችግር በቴክኖሎጂ የሚፈታ አእምሮ?
ለውጡ የሚመጣው በዲግሪው ብዛት ሳይሆን በዲግሪው ውስጥ ባለው የነፃነት መንፈስ ነው።
3. የሀገራት ተሞክሮ፦ የደቡብ ኮሪያ እና የህንድ ትምህርት
ኢትዮጵያ ልትማርባቸው የሚገቡ ሁለት ታላላቅ ተሞክሮዎች አሉ። አንደኛው የደቡብ ኮሪያ ተዓምር ነው። በ1960ዎቹ ኮሪያ ከኢትዮጵያ በታች የነበረች ደሃ ሀገር ነበረች። ምስጢራቸው ግን መምህራኖቻቸውን ወደ ውጭ መላክ ብቻ አልነበረም፤ የተመለሱት ምሁራን በሀገራቸው "የመንግስት ሳይንቲስት" ተብለው ትልቅ ክብርና ደመወዝ እንዲያገኙ ማድረጋቸው ነው።
ዛሬ ኮሪያ የሳምሰንግና የሃዩንዳይ ባለቤት የሆነችው በዚያ የጥራት መሠረት ላይ ነው።
በሌላ በኩል የህንድ ተሞክሮ ድብልቅ ነው። ህንድ ዛሬ የዓለም የቴክኖሎጂ ማዕከል ለመሆን የቻለችው በ IIT አማካኝነት ቢሆንም፣ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ምርጥ ምሁራኖቿን ለሲሊኮን ቫሊ (USA) አሳልፋ ትሰጣለች (Brain Drain)።
ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር የጀመረችው ስምምነት ተስፋ ሰጪ ቢሆንም፣ ምሁራኑን በሀገር ውስጥ የሚያቆይ (Retention) ሥርዓት ካልተዘረጋ ግን "ለሰው ሀገር ነፃ የሰው ኃይል ማሰልጠን" ይሆንብናል።
4. ልበ አንጠልጣዩ እውነታ፦ ለምን አይመለሱም?
ኢትዮጵያ ባለፉት 20 ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ መምህራንን ወደ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ እና እስያ ልካለች። ተመልሰው ሀገራቸውን ከማገልገል ይልቅ በሄዱበት መቅረትን የመረጡ እንዳሉ የአደባባይ ሀቅ ነው። ለምን?
የደመወዝ ማነስ፦ የአንድ የPhD መምህር የወር ደመወዝ ኑሮን ለማሸነፍ በመክበዱ
የምርምር መርገጥ፦ ለምርምር የሚመደበው በጀት ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) ከ 0.5% በታች መሆኑ።
የአካዳሚክ ነፃነት፦ ዩኒቨርሲቲዎች ከፖለቲካ ተጽዕኖ ነፃ አለመሆናቸው።
5. የመፍትሔ አቅጣጫ
መንግስት አሁን የጀመረው የ1,200 መምህራን ስልጠና "የደም ልገሳ" ያህል አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ደም የተለገሰው ሰውዬ ውስጣዊ ቁስሉ ካልታከመ ደሙ መፍሰሱ አይቀሬ ነው። ለውጡ እንዲመጣ የሚከተሉት ነጥቦች በቅንጅት መተግበር አለባቸው፦
የምሁራን ክብርና ማበረታቻ፦ የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው መምህራን ጥሩ የኑሮ ሁኔታ ሊመቻችላቸው ይገባል።
ከፖለቲካ ነፃ የሆነ አመራር፦ ዩኒቨርሲቲዎች ለዕውቀት ብቻ ታማኝ የሆኑ አመራሮች ያስፈልጓቸዋል።
የምርምር በጀት ማሳደግ፦ ራሳችንን ለመፍጠር ደግሞ ለምርምር የሚሆን ገንዘብ መመደብ ግዴታ ነው።
ማጠቃለያ
የ18 በመቶው እውነታ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ያለበትን ከባድ ችግር ቢያሳይም፣ አሁን የተጀመሩት እንቅስቃሴዎች ግን እንደ "ለውጥ ማለዳ" ሊታዩ ይችላሉ። ኢትዮጵያ በኮንክሪት ሕንጻዎች መኩራቷን ትታ፣ በአእምሮ ግንባታ ላይ ካልተረባረበች፣ ዩኒቨርሲቲዎቻችን ወደፊት "የመቃብር ስፍራዎች" መሆናቸው አይቀሬ ነው። 1,200 መምህራን ብቻ ሳይሆኑ፣ 1,200 የነፃነት እና የፈጠራ አውድማዎች ያስፈልጉናል።

ለአለም ስልጣኔ ያስተማረችዉ ሀገር !
" ዛን ዜንዲጊ አዛዲ ሴት ህይወት ነፃነት "/ኢራናውያን /
በሰዉ ልጆች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆስፒታል ገንብታ ማከም የጀመረች ።
#ethiopia | በአልጀህብራን ቀመር ሂሳብ አስልታ ለአለም ያስተማረች ። ኬሚካል በማዋሀድ የጥበብ የተራቀቀች ። በአርክቴክቸር ሳይንስና ዲፕሎማሲ በመካከለኛው ምስራቅ አሀዱ ያለች ።በጠቢባን ልጆቿ በቀጠናው ለመጀመሪያ ጊዜ ድሮን አምርታ ለገበያ ያቀረበች የሴቶችን የመማር ነፃነት በመስጠት 70 % ሴቶች በዲግሪ ደረጃ ያስመረቀች ። ሴቶችን ማስተማር እንብዛም ባልሆነበት ቀጠኒ 25% የሀገሪቱን የኒኩሊየር ሳይንቲስቶች ለሴት ልጆቿ የሰጠች ።በፕላኔታችን በምዕራባውያን ማዕቀብ ብዛት ቀዳሚ የሆነች የአለም ፖለቲካ የወሬ ማጣፈጫ ሀገረ ኢራን ።
እነሆ በዛሬው አለምን እንወቅ ዝግጂታችን ወገንተኛዉ የአዉሮጳዉያን ሚዲያዎች ክፉዋን ብቻ እየጠቀሱ የሚነግሩን ጥንታዊቷን ኢራንን ልንጎበኝ ወድደናል ።
አብራችሁን ስትዘልቁ ቀደምት ኢትዮጵያዊን ሀበሾች መኖርያ የሆነችዉን በባህል ከእኛ ጋር የምትመሳሰለዉን ከእግር እስከ እራሷ እየቃኘን ስለሀገሪቱ ሰምታችሁት የማታዉቁትን ታሪክ እንነግራችኋለንና ከፓለቲካ ምልከታ ገለል ብላችሁ ሌላ ገፅታዋን ለማየት አብራችሁን ዝለቁ ።
መቼም እኛ ኢትዮጵያዊያን ከምንታወቅበት አንዱ መግደርደርና እንብላ እንጠጣ የሚል ሰወኛ ግብዣችን ነዉ ታዲያ ይህ ባህል በእኛ ብቻ አይደለም ኢራንም ዉስጥ ወላ በሬስቶራን ወይም በካፌ እንብላ እንጠጣ መባባል ። እየፈለጉም ቢሆን መግደርደርን ከእነ ሙሉ ክብሩ እናገኘዋለን ።
ደግሞ ሌላ መቼም እንግዳ በቤት ለማስተናገድ ቡና ማፍላት የተለመደ ነዉ እነሱም ታሮፍ በሚሉት የእኛን መሰል ባህል ሻይ አፍልተዉ እግር አጥበው አልጋ ለቀው ያስተናግዳሉ ።
እንደ ታሪክ አዋቂዎች ከሆነ በኢራን ከሚገኙ በርካታ ዝርያዎች መካከል በደቡባዊ ኢራን ሆርሙዝጋን ግዛት የሚኖሩት ከ4 ክፍለዘመን ጀምሮ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ ጉዳይ የሚሳተፉ መነሻቸው ከኢትዮጵያ እንደሆነ የሚነገርላቸው በአሴርያዉያን ስርዎ መንግስት ጎልተዉ የነበሩ ከሀበሻ የሄዱ አፍሮ ኢራናውያን አስተምረዋቸዉ ይሆናል ።
ወጋችን ከተገረምኩበት ጉዳይ ልሰልስ
ከሰሞኑ አንዳንዶቹ የኢራንን 1 ዶላር በሚሊዮን ተመነዘረ የሚል የገንዘብ ጉዳይ አንስተው ሙድ ለመያዝ ሲሞክሩ አይቻለሁ ። በእርግጥ ማዕቀቡ ጉዳት ቢኖረውም የኢራን የገንዘብ ቁጥር የሚጀምረው ከአምስት ሽህ ሪያል ነዉ ማለትም የእኛ አስር ሳንቲም እንደማለት ። ለማንኛውም ኢራን የብር ኖቶ በቁጥር ሲሰማ ቢያስደነግጥም የ ሁለት ሚሊዮን ድረስ ኖቶች አሉ ።
ከአሜሪካ ጋር በገባችበት እሰጣ ገባ ያልተጣለባት የማዕቀብ ናዳ የለም ። ምናልባት ሀገሪቱ ኢራን ባትሆን ኑሮ የማዕቀቦቹን ናዳ የሚሸከም ጫንቃ ሊኖራት አይችልም ።
ይህ ማዕቀብ ያላጎበጣት ኢራን ምንም ጥሬ እቃ ከዉጭ ማስገባት ባትችልም 50 ዶላር ባልሞላ ወጭ ተምዘግዛጊ ሰዉ አልባ ድሮኖች ። ሰማይ ሰንጣቂ ሚሳኤሎች ቀላልና ከባድ መሳርያዎች ተሻግራ 60% የተብላላ ኒኩሊየር ባለቤት መሆን ችላለች ።
የአያቶላሆቹ በራስ መቆም ምሳሌዎች ናቸዉ ። ዘጠና ከመቶ የመኪናውን ክፍል በራሷ የምትሰራቸዉ የጭነት የትራንስፖርት ሞተርና የግል "ኢራን ኮድሮ" ሳይፓ "ፋርስ ኮድሮ " የመኪና ብራንዶችን በአመት 1 ሚሊዮን መኪኖች አምርታ ትሸጣለች ።
ሀገሪቱ ትላንቷን አጥብቃ ትወዳለች ። ዋና ከተማዋ ታሪክን ከባህል ዘመናዊነትን ከፓለቲካ ጋር ያጣመረች ከተማ ናት ። ከእነዚህም መካከል የከተማዋ እንብርትና የሀገሪቱ የእርቀት ስሌት ዜሮ ዜሮ ተብሎ የሚጀመርበት የፋርስን ስልጣኔ ለማስታወስ የተገነባው አዛዲ ታወር የአለማችን ስድስተኛው ረጂሙ ታወር ሚላት ታወር ጨምሮ ማንነቷን ገላጭ አርክቴክቸር ዉጤቶች ። ከ400 አመታት በላይ እድሜ ያለዉ የግራንድ ባዛር ዛሬም በድምቀት የፋርስ ምንጣፎችን የሀገር በቀል ምርቶች ይሸጡበታል ።
ከ60 በላይ ዩንቨርስቲዎች መገኛ የሆነችው ቴህራን በመካከለኛው ምስራቅ ትልቅ እንደሆነ የሚነገርለት ሜትሮ ዘመናዊ ትራንስፖርት በከረሜላ መግዣ ዋጋ ለህዝብ አገልግሎት ይሰጣል ።
የዱባይን ዱባይ ሞል የቻይናውን ሳዉዝ ቻይና ሞል በመብለጥ የአለማችን ትልቁ የገበያ ሞል በኢራን ይገኛል 2ሚሊዮን ካሬ ይሰፋል ።
በቴህራን የፐርሺያን ስልጣኔ 2050 አመት መታሰቢያ ባከበረችበት ወቅት በ24 አመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ንድፉ የተሰራ የነፃነት ሀዉልት የከተማዋ ግርማ ነዉ በየቀኑ አምስት ሚሊዮን ተሳፋሪዎች የሚያስተናግደው ዘመናዊ የምድር ዉስጥ ባቡርና ሜትሮ አገልግሎት በመስጠት ከጎረቤቶቿ ትለያለች ።
ከቴህራን ወጣ ስንል ደግሞ የኢራንን መንፈሳዊ ከተማ ማሻድን እናገኘዋለን ። በአመት 25 ሚሊዮን ጎብኝዎችነ የምታስተናግድ ከምድራችን ትላልቅ የእምነት ስፍራዎች አንዱ የሆነዉን መስጊድ የያዘች በሽአ አማኞች ቅድስት የተባለች ከተማ ናት ።
ኢስፋሀን ደግሞ የሀይማኖት መቻቻል የሚታይባት የአይሁዶች ቤተ እምነት የክርስትያን አብያተክርስቲያናት መሳጂዶች ጎን ለጎን የሚገኙባት ዩኔስኮ በቅርስነት የመዘገባት ከተማ ናት ።
የአያቶላሆቹ ሀገር በሀገርነት ሽህ አመት የሚለው ቁጥር ከሚያዉቁት ጥቂቶች አንዷ ከጫካ ወጥቶ ቤት ቀልሶ መኖር የጀመረባት የመግስታዊ ስርአት አስተዳደር በመስኖ ማረስ ከቃል አልፎ በፅሁፍ መግባባት መነሻው ከዚሁ ነዉ ።
አለማችን ላይ ለዘመናት የራሷን የቀን አቆጣጠር እስካሁን የምትጠቀም የራሷ ካላንደር ያላት ባህልን ከታሪክ በራስ የመቆም መቻልን ከዘመናዊነት በማዋሀድ እልፍ የቱሪስት መዳረሻዎች የያዘች ብትሆንም የአለም ስርአት በጣለባት ማዕቀብ ተጠቃሚ አልሆነችም
ለማሳረግያ አንድ ታሪክ እናካፍላችሁ ።
እስራኤል እና ኢራን የዛሬን አያድርገው እና ወዳጅ ሀገራት ነበሩ ያዉም የአሜሪካዉን ሲአይኤ ያልደረሰበት ምስጢር የተጋሩ ወዳጆች ።
ዛሬ ካልተጋደልን የሚሉት ሁለቱ ፍቅራቸዉ ለአይታ ያስቀና ነበር እስራኤል ዙርያውን ያሉ የአረብ ሀገራት ነዳጅ አንሸጥም ባሏት ወቅት ኢራን በሯን ከፍታ ከመስጠት ባሻገር ከአሜሪካ ተደብቀው ፕሮጀክት ፍላወር የተባለ የአሜሪካን ሚሳኤሎች እስራኤላውያን በእዉቀት ኢራን በገንዘብ ተባብረው ያመርቱም ነበር ።
ከአራት አስርታት ዓመታት በፊት እስራኤል ሀገር ለመሆን እና በአንድ እግሯ ለመቆም ስትጣጣር በነበረበት ወቅት ለእስራኤል የሀገርነት እውቅና ለመስጠት ቀዳሚ ከነበሩ ሁለት የእስልምና እምነት ተከታይ ሀገራት መካከል ኢራን አንዷ ነበረች።
ኢራን የአየር መቃወሚያ መርከቦች ራዳሮች ሌሎችም መሳርያዎች በእስራኤል በኩል ይቀርብላት ነበር ዛሬ ላይ የሁለቱ ሀገራት ግጭት መንስኤ የሆነው ኒኩሊየር እንድታመርትም የእስራኤል ተሳትፎ አለበት ።
ሞሳድ በመካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገራትን የሚሰልልበት ቢሮዉ ቴህራን ላይ ነበረው በአሁኑ ጊዜ በቴህራን ከ30 ሽህ በላይ እስራኤላዉያን ይኖራሉ ትላንት ተመልካችና ሰሚ የሚቀናባቸዉ ሁለቱ ሀገራት በሀይማኖት የተጀቦነ ፖለቲካ ነጠላቸዉ እንጂ ህዝብ ለህዝብስ ጥላቻ የለባቸውም ። ማን ያዉቃል ነገ ደግሞ ፍቅራቸው ሊመለስ ይችላል ።

🌼 የፍቅርና የምስጋና ስጦታ የሆነው የጌዴኦ ህዝብ "ዳራሮ" በዓል በሸራተን አዲስ ደመቀ!
#ethiopia | "ወደ ዩኔስኮ ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ነው"
በጌዴኦ ማህበረሰብ ዘንድ እንደ አዲስ ዓመት እና የዘመን መለወጫ የሚከበረው ታላቁ “ዳራሮ” በዓል፤ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል በድምቀት ተከብሯል።
ዳራሮ ምንድን ነው?
✅ የጌዴኦ ህዝብ ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲስ ዘመን መሸጋገሩን የሚያበስርበት፣
✅ ማህበረሰቡ ለአባ ገዳዎች ስጦታ ይዞ በመቅረብ ምርቃት የሚቀበልበት፣
✅ ለፈጣሪ ምስጋና እና ለቀጣይ ዘመን ምርት ጸሎት የሚደረግበት፣
✅ የሰላም፣ የስጦታ እና የምስጋና በዓል ነው።
በሸራተን አዲስ በተዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ፤ በዓሉ በዩኔስኮ (UNESCO) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ አስፈላጊው የመረጃ ማደራጀት ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
ዋናው በዓል የፊታችን አርብ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በዲላ ከተማ በድምቀት ይከበራል።
እንኳን አደረሳችሁ!
#dararo #gedeo #newyear #culture #sheratonaddis #unesco #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

የጌዴኦ ዘመን መለወጫ "ዳራሮ" በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ
#fastmereja I የጌዴኦ ብሔር የዘመን መለወጫ "ዳራሮ" በዓል "ዳራሮ ለባህልና ለቱሪዝም ዕድገት" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በሸራተን አዲስ ሆቴል በድምቀት ተከብሯል። በበዓሉ አከባበር ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ አርቲስቶችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
በዓሉ የጌዴኦን ብሔር ማንነትና ጥንታዊ የሀገር በቀል እውቀትን ለዓለም የሚያስተዋውቅ ከመሆኑም ባለፈ፣ ለሀገሪቱ የቱሪዝም ሀብት ትልቅ ግብዓት እየሆነ ይገኛል። በአሁኑ ወቅትም ይህንን ድንቅ የባህል እሴት ሳይበረዝ ለትውልድ እንዲተላለፍና በዓለም የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ ሰፊ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
ዳራሮ ከአካባቢ አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ መከበሩ የጌዴኦን ዞን ከማስተዋወቅ ባለፈ፣ በዞኑ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ታምኖበታል። በበዓሉ ላይ የተገኙ የመዲናዋ ነዋሪ የብሔሩ ተወላጆችም፣ በዓሉ በአዲስ አበባ መከበሩ ባህላቸውን ለማጉላትና አንድነታቸውን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

5 months ago
🕊️ የጥምቀት በዓል ዙሪያ የከተማ አስተዳደሩ እና የቤተክርስቲያኗ አባቶች መከሩ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጪውን የጥምቀት በዓል አከባበር አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጉን አስታወቀ።
✨ "የዓለም ሀብት የሆነው በዓል" — ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከውይይቱ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት፣ የጥምቀት በዓል የሃይማኖቱ ተከታዮች በዓል ብቻ ሳይሆን በዩኔስኮ የተመዘገበ "የዓለም ሀብት" መሆኑን ገልጸዋል። በዓሉ የከተማዋ የድምቀት ምንጭ እና የበርካታ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች መዳረሻ መሆኑንም አክለዋል።
🏗️ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች
በውይይቱ ላይ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* ሃይማኖታዊ እሴት፦ በዓሉ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ እና ፍፁም ባማረ መልኩ በሁሉም ስፍራዎች እንዲከበር ስምምነት ላይ ተደርሷል።
* የዝግጅት ሂደት፦ አጠቃላይ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተሳካ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆኑ ተረጋግጧል።
* ሁለንተናዊ ድጋፍ፦ የከተማ አስተዳደሩ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ ከንቲባዋ አረጋግጠዋል።
አስተዳደሩ እንደሌሎች የአደባባይ በዓላት ሁሉ፣ ጥምቀትም የአዲስ አበባን ሰላምና ውበት ለዓለም በሚያሳይ መልኩ እንዲከበር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስታውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ጥምቀት #አዲስአበባ #ኢትዮጵያ #ባህልናቱሪዝም #ኦርቶዶክስ #ከንቲባአዳነች #epiphany #timket #addisababa #ethiopia #unesco

💦 ጎንደር ለጥምቀት ዝግጁ ናት! 🍋🌿
"በዓሉን ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እናክብር!"
- ብጹዕ አብነ ዮሐንስ
#ethiopia | የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አብነ ዮሐንስ ገለጹ።
የብጹዕነታቸው አባታዊ መልዕክትና ጥሪ፡-
✅ ለምዕመናን: በዓሉ ከድምቀቱ ባለፈ መንፈሳዊ ትርጉሙ እንዳይሸረሸር፤ ቅዱስነቱን እና ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር አደራ ብለዋል።
✅ ለነዋሪዎች: የጎንደር ህዝብ ለሚመጡት እንግዶች የተለመደውን ኢትዮጵያዊ የፍቅር እና የክብር አቀባበል እንዲያደርግ አሳስበዋል።
✅ ለእንግዶች: የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ይህንን በዩኔስኮ የተመዘገበ ቅርስ በቦታው ተገኝተው እንዲያከብሩ ጥሪ ቀርቧል።
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! ጎንደርን ለመታደም ያሰበ ማን አለ? ✋
#ጌትነት ተመስገን
#timket2018 #gondar #ethiopianepiphany #fasilidesbath #orthodox #ethiopia #travelethiopia #culture

🎨 "ኪነ-ጥበብ የኢትዮጵያውያን የልብ ትስስር ነው!"
- ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ
#ethiopia | በጎንደር ፋሲለደስ አብያተ-መንግሥታት የተደረገ ልዩ የታሪክ እና የባህል ጉብኝት!
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ፣ የኪን-ኢትዮጵያ ልዑክ አባላት፣ አባገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን በዩኔስኮ የተመዘገበውን እና የጎንደር ግርማ ሞገስ የሆነውን የአፄ ፋሲለደስ አብያተ-መንግሥታትን ጎብኝተዋል።
ቁልፍ መልዕክቶች:
✅ አንድነት: ሚኒስትሯ እንደገለጹት፤ የኪነ-ጥበብ ስራዎች የህዝቦችን ባህላዊ ትስስር በማጉላት ለብሔራዊ አንድነት ወሳኝ ሚና አላቸው።
✅ የኪን-ኢትዮጵያ ሚና: ቡድኑ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረኮች (ቻይና፣ ሩሲያ፣ ጃፓን) ከማስተዋወቅ ባለፈ፤ በሀገር ውስጥም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን እያጠናከረ ይገኛል።
✅ ልማት እና ቅርስ: ልዑኩ ከታሪካዊው ቤተ-መንግስት በተጨማሪ በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችንም ተመልክቷል።
ታሪክን ከጥበብ፣ ቅርስን ከልማት ያጣመረ ውብ ጉብኝት!
#ጌትነት ተመስገን
#gondar #fasilghebbi #kinethiopia #artforunity #ethiopia #cultureandsports #visitethiopia

የአፋር ባህላዊ ሕግን ‘ማድዓ’ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተሰራ ነው
የአፋር ባህላዊ ሕግን (ማድዓ) በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ እየተሰራ ነው።
የማድዓ ባህላዊ ሕግን በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ለማስቻል ከየካቲት 3 እስከ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሕዝባዊ ኮንፍረንስ ይካሄዳል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሀሚድ ዱላ እንዳሉት፤ ኮንፍረንሱ ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በጋራ ያዘጋጁት ነው።
በኮንፍረንሱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች እንዲሁም የጅቡቲ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ሱልጣኖች እና የጎሳ መሪዎች ይሳተፋሉ ብለዋል።
የክልሉ የቋንቋ ባህልና ታሪክ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀቢብ መሀመድ በበኩላቸው፤ ኮንፍረንሱ ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ቀጣናዊ ትስስርን ያጠናክራል ሲሉ ተናግረዋል።
የማድዓ ባህላዊ ሕግን በዩኔስኮ በማስመዝገብ የዓለም ሀብት እንዲሆን ከማስቻል ባለፈ በክልሉ ያለውን የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
FBC

🍽️ ክትፎን ጨምሮ አራት የጉራጌ ዕሴቶች ወደ ዩኔስኮ (UNESCO) ሊያመሩ ነው
#ethiopia | የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ፣ ታዋቂውን የጉራጌ ክትፎን ጨምሮ አራት የጉራጌ ባህላዊ እሴቶችን በዓለም የማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ ለማስመዝገብ ጥናት መጀመሩን አስታወቀ።
🥩 ክትፎ፦ ከምግብነት በላይ የሆነ የማንነት መገለጫ
የጉራጌ ክትፎ በዩኔስኮ ቅድሚያ ከተሰጣቸው እሴቶች መካከል ቀዳሚው ነው። ክትፎ ለጉራጌ ማህበረሰብ ምግብ ብቻ ሳይሆን የእንግዳ መቀበያ፣ የማህበራዊ ትስስር እና የጥበብ መገለጫ ነው። በአሁኑ ወቅት የክትፎ አዘገጃጀት፣ ከቆጮ፣ ከሚጥሚጣ እና ከንጥር ቅቤ ጋር ያለው ቁርኝት በጥልቀት እየተጠና ይገኛል።
📜 ሊመዘገቡ የታጩት አራት የኩራት ምንጮች፦
* የክትፎ አዘገጃጀት ጥበብ፦ ልዩ የሆነው የማክተፍ፣ የቅመማ ቅመም አጠቃቀምና የማቅረብ ስነስርዓት።
* ባህላዊ የክብ ቤት አሰራር፦ ያለ ሚስማር የሚገነባውና ለዘመናት የሚቆየው፣ የምህንድስና ጥበብ የታየበት የቤት አሰራር።
* የጎርደና የዳኝነት ስርአት፦ ለማህበራዊ ሰላምና ፍትህ የሚጠቀሙበት ጥንታዊና ውጤታማ የዳኝነት ስርዓት።
* የጀፎረ (መንደር) አወቃቀር፦ ለጋራ መስተጋብር በሚመች መልኩ የሚሰሩ ሰፋፊ መንገዶችና ማራኪ የመንደር አቀማመጥ።
📍 የጥናቱ ሂደት ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመረጋ እንደገለጹት፣ ለኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል። ጥናቱ እንደተጠናቀቀ ሰነዱ በቀጥታ በፈረንሳይ ፓሪስ ለሚገኘው የዩኔስኮ ዋና መስሪያ ቤት ለውሳኔ ይላካል።
ከዚህ በተጨማሪ በዞኑ የሚገኙ ዕድሜ ጠገብ መስጂዶች፣ ጥንታዊ ኪታቦች፣ ገዳማትና ታሪካዊ ዋሻዎች ለቱሪስት መስህብነት እንዲውሉ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ጉራጌ #ክትፎ #ዩኔስኮ #ቅርስ #ኢትዮጵያ #ባህል #ቱሪዝም #የጉራጌባህል #gurage #kitfo #unesco #ethiopianheritage #tourismethiopia

Comments