13 days ago
ያለፈው ዓመት "ኢትዮጵያ" የሚለው ስም ኢንተርኔት ላይ በብዛት ተፈልጓል
#ethiopia | በ47ኛው የዓለም የቱሪዝም ቀን ጉባኤ ላይ የተገኙት የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሠላማዊት ካሳ፣ ባለፈው በጀት ዓመት "ኢትዮጵያ" የሚለው ስም በዓለም አቀፍ የጎግል ፍለጋ መረብ ላይ በከፍተኛ ደረጃ መጠየቁንና ይህም የሀገሪቱን ተቀባይነትና የጎብኚዎች ትኩረት ማሳደጉን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ 1.6 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ሀገሪቱን የጎበኙ ሲሆን ዘርፉ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማንቀሳቀስ ችሏል።
በተጨማሪም ለ18 ዓመታት ሳይሻሻል የቆየው የቱሪዝም ፖሊሲ በአዲስ መልክ የጸደቀ ሲሆን አዲስ አበባ 210 ዓለም አቀፍ ኹነቶችን በማስተናገድ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከልነቷን አጠናክራለች።
ሚኒስትሯ አሁንም የሀገሪቱን ዕምቅ የቱሪዝም አቅም ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ተጨማሪ ሥራ እንደሚጠይቅ አሳስበዋል።
credit : Hagerie Television
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#ኢትዮጵያ #ቱሪዝም #የቱሪዝምሚኒስቴር #አዲስአበባ #የዓለምየቱሪዝምቀን #ethiopia #ethiopiantourism #visitethiopia

20 days ago
ዓለም ሊያያት የሚጓጓላት ኢትዮጵያ፦ የታሪክ፣ የባህል እና የተፈጥሮ መስህቦች ምድር
******************** #visitethiopia #landoforigins #ethiopiantourism #travelethiopi
1 month ago
ሀዋሳ : እየተሞሸረች ነው
* የሀገራችን አበይት ሁነቶች ማዕከል እና የልማት ምሳሌ የሆነችው ሀዋሳ
#ethiopia | ሀዋሳ እያሳየች ያለችው ፈጣንና ሁለገብ እድገት የብዙዎችን ትኩረት በመሳብ የሀገራችን ዋና ዋና ኩነቶች የሚካሄዱባት መሪ ከተማ እንድትሆን አድርጓታል።
የከተሞች ልማት ጥናቶች እንደሚያስረዱት አንዲት ከተማ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እድገት ማዕከል ለመሆን እንዲሁም የፈጠራ አቅምን ለመሳብ በቴክኖሎጂ፣ በክህሎት እና በመቻቻል መርሆዎች ላይ መገንባት ይኖርባታል። ሀዋሳም ይህንን ሳይንሳዊ እውነታ ከዘመናዊ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ጋር በማጣመር የኢኮኖሚና የቱሪዝም ዘርፏን ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረች ትገኛለች።
የከተማ ሶሲዮሎጂስቶችና ስትራቴጂስቶች እንደሚናገሩት ዘመናዊ ከተሞች ተወዳዳሪና ሳቢ ለመሆን መሠረተ ልማቶቻቸውን በጥናት ላይ በተመሰረተ ኢንቨስትመንት መለወጥ አለባቸው።
በዚህ ረገድ ሀዋሳ በርካታ አህጉራዊና ሀገራዊ ሁነቶችን በብቃት ማስተናገድ የቻለችው በዚሁ መርህ በተከናወኑ አበይት የልማት ሥራዎች ነው።
የከተማዋን የቱሪዝም ገጽታ በሥነ-ምህዳራዊ መንገድ የሚቀይረውና የተፈጥሮ ሀብቷን በጥራት የሚያጎላው ታላቁ የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ትግበራ መቀጠሉ ለዚህ ማረጋገጫ ነው።
በተጨማሪም የከተማዋን ውበት፣ ፅዳት፣ የትራፊክ ፍሰትና የቦታ አጠቃቀም በከፍተኛ ደረጃ ያሻሻሉ የሁለተኛው፣ ሦስተኛው እና አራተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተጠናቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
በከተሞች ሶሲዮሎጂ ጥናት ማህበራዊ ሀብት ተብሎ የሚጠራው የህዝቦች የእርስ በእርስ ትስስር፣ እምነትና መቻቻል ለከተሞች ዘላቂ ሰላምና የኢኮኖሚ ህልውና መሠረት ነው።
ሀዋሳ የሃይማኖታዊና የባህላዊ እሴቶች መቻቻልና ድምቀት መገለጫ መሆኗን በተግባር አሳይታለች።
በዩኔስኮ የማይጨበጥ የሰው ልጅ ባህላዊ ወካይ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው ታላቁ የሲዳማ ብሔር አዲስ ዓመት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በታላቅ አደባባይ መከበሩ የከተማዋን ባህላዊ የቱሪዝም ሳቢነት አጎልቶታል።
በዓመት ሁለት ጊዜ በድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል እንዲሁም በጥምቀት በዓል በርካታ ምዕመናን ከሀገር ውስጥና ከባህር ማዶ ወደ ሀዋሳ መምጣታቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ እነዚህ ቅርሶች ለከተማዋ መልካም ስም ግንባታና ለረጅም ጊዜ የቱሪዝም ፍሰት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።
አንዲት አካባቢያዊ ከተማ ከዓለም አቀፍ ፍሰቶች ጋር የምታደርገውን ስትራቴጂያዊ ትስስር ማጠናከር እንዳለባት የሚጠቀሰው ፅንሰ-ሀሳብ በሀዋሳ በተግባር ታይቷል።
የሀዋሳ አየር መንገድ፣ የሆቴልና የእንግዳ ተቀባይነት ዘርፍ ዘመናዊነት ከተማዋን ለዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ምቹ አድርጓታል።
ከልዩ ልዩ ክፍለ ዓለማት የመጡ ታዋቂ እንግዶች የታደሙበት ዓመታዊ ጉባኤ በሀዋሳ መካሄዱ የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያሳየ ሁነት ነበር።
በተለይም የአሜሪካ አምባሳደር በከተማዋ ያደረጉትን ስኬታማ ቆይታ ተከትሎ ሀዋሳ ለአሜሪካን ስፔስስ ምቹ መዳረሻ መሆኗ የከተማዋን ዲፕሎማሲያዊ፣ ትምህርታዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ወደ አዲስ ደረጃ አሸጋግሮታል።
ግዙፍ የስፖርት፣ የባህልና የመዝናኛ ኩነቶች ለከተሞች መሠረተ ልማት ማበብ፣ ለንግድ መነቃቃትና ለህዝብ ግንኙነት የሚፈጥሩትን ሁለገብ ኃይል ሀዋሳ በአግባቡ ተጠቅማበታለች።
ከተማዋ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀውን የግማሽ ማራቶን ሩጫ፣ የኢትዮ ቴሌኮም እና የልወቅሽ ኢትዮጵያ ሩጫ ውድድሮችን በብቃት አስተናግዳለች።
የመከላከያ ሠራዊት 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ 302 ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉበት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ታጅቦ የተከበረው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ በዓል የከተማዋን አቅም የገለጹ ናቸው።
ከመላ ሀገራችን የተሰበሰቡ ከ15 ሺህ በላይ ታዳሚዎች የተሳተፉባቸው ሦስት ግዙፍ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ከመስተናገዳቸው ባሻገር፣ በሁለቱም ጾታዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ለተከታታይ 30 ቀናት ጨዋታቸውን በሀዋሳ ማድረጋቸው የከተማዋን የስፖርት ማዕከልነት አጠናክሮታል።
በአጠቃላይ እነዚህ አበይት ሁነቶችና የልማት ሥራዎች በጥናት በተደገፈ የኮሪደር ልማት፣ በሆቴልና እንግዳ ተቀባይነት ዘርፍ እንዲሁም መሠረተ ልማት እድገት የተገኙ ፍሬዎች ናቸው።
ይህ ሁሉ አቅም ሀዋሳን ውብ መዳረሻና ተመራጭ የኮንፍረንስ ማዕከል ከማድረጉም ባሻገር የከተማዋን ገቢ በትልቁ እያሳደገው ይገኛል።
ይህች ውብ የሲዳማ ዋና ከተማ ሀዋሳ ዛሬም አቅሟን አውጥታ ሌሎች ግዙፍ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶችን ለማስተናገድ ይበልጥ ተዘጋጅታለች።
እናንት ያገሬ ልጆች
ግልጽነት ለዘላለም ይኑር!
ሀዋሳ : እየተሞሸረች ነው!
* ሀዋሳ - የሀገራችን አበይት ሁነቶች ማዕከል እና የልማት ምሳሌ ለመሆን እየታተረች ነው።
ፊት አውራሪው፤
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እና አመራራቸው፣ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች፣ ባለሀብቶች - ባለጸጋዎች (በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ) የከተማዋ መንግስት ኮሙኒኬሽን እንዲሁም የሽቅርቅሯ ሀዋሳ ወዳጆች ልባዊ ምስጋናችን ተቀበሉ።
መሥራት ጀግንነት ነው፤
ማድነቅ ደግሞ መሠልጠን ነው።
የሚሠሩ እጆችን እናደንቃለን፤
እናከብራለን!!!
እጅ እንነሳለን!
#hawassa #sidama #ethiopiantourism #development #events #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

አምባሳደር አሚን አብዱልቃድር በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ የእውቅና ሽልማት ተቀበሉ
#ethiopia | በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱት አምባሳደር አሚን አብዱልቃድር የተዘጋጀላቸውን የእውቅና ሽልማት ተቀብለዋል።
አምባሳደር አሚን በሀገራችን የሆቴልና ቱሪዝም መስክ ውስጥ ያከናወኗቸውን አበይት ተግባራት አከናውነናል።
አምባሳደር አሚን ለአዳዲስ አሰራሮችና ለላቀ ለውጥ ያላቸው ፍላጎት፣ ከሀገር ፍቅርና ከተግባቢ ባህሪያቸው ጋር ተይዞ የተዋጣላቸው ሀገራዊ መሪ አድርጓቸዋል።
በሚኒስትርነት ማዕረግ ሀገራቸውን ባገለገሉበት ወቅት ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ አድርገው በማንሳትና አዎንታዊ ገጽታዋን በመገንባት ረገድ ፈር ቀዳጅ ሚና ተወጥተዋል።
ታዋቂ የኪነ ጥበብ ሰዎችን፣ የሃይማኖት አባቶችን እና ታዋቂ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ አካላትን አስተባብረው በመምራት ኢትዮጵያን ለዓለም አስተዋውቀዋል።
ይህ ጥበብ የተሞላበት አመራራቸው የኢትዮጵያ ባህል፣ ቅርስና የቱሪዝም ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥበብና በክብር እንዲንፀባረቅ አድርጓል።
የሆቴሎች ደረጃ ምደባ ፈር ቀዳጅ፡ በኢትዮጵያ የሆቴል ዘርፍ ታሪክ የመጀመሪያውን የሆቴሎች ደረጃ ምደባና የመታወቂያ አሰራር በማስፋፋት የአገልግሎት ጥራት በዘመናዊ መለኪያ እንዲመራ መሠረት ጥለዋል።
ዘርፉን ወደ ሙያዊነት ማሸጋገር፡ በተለምዶ ይካሄድ የነበረውን አሰራር በመቀየር ዘርፉ በሙያዊነትና በጥራት እንዲመራ በማድረግ ለብዙ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥረዋል።
የሰው ኃይል አቅም ግንባታ፡ ከመላ ሀገሪቱ የተመረጡ ባለሙያዎችን ለአንድ ዓመት ሙሉ በማሰልጠን የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉን በሰለጠነ የሰው ኃይል የማጠናከር ሥራ ሰርተዋል።
የኢትዮጵያ የቱሪዝም ብራንድ ማዘመን፡ ሀገራችን ለዘመናት ትጠቀምበት የነበረውን "13 Months of Sunshine" የሚለውን መለያ ወደ አዲሱ "Land of Origins" በማሸጋገር የኢትዮጵያን የቱሪዝም ምስል በዓለም አቀፍ ደረጃ አድሰዋል።
ተቋማዊ መዋቅሮችን መገንባት፡ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ካውንስል፣ የቱሪዝም ቦርድ እና የቱሪዝም ድርጅት እንዲመሰረቱ በማድረግ ዘርፉ ጠንካራ ተቋማዊ መሠረት እንዲይዝ አድርገዋል።
የትምህርትና ስልጠና ሥርዓትን ማጠናከር፡ በሙያ ትምህርትና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የባህልና ቱሪዝም ትምህርት ኮርሶች እንዲዘጋጁ በማድረግ ለዘርፉ ማደግ ወሳኝ የሆነውን የሰው ኃይል ማፍሪያ መንገድ ቀይሰዋል።
ለቅርሶችና ተፈጥሮ ሀብት ሕጋዊ ጥበቃ ማድረግ፡ ፓርኮች፣ ጥብቅ ቦታዎችና የቅርስ ሥፍራዎች በሕግ እንዲከለሉና በፓርላማ በይፋ እንዲታወጁ በማድረግ የሀገር ሀብት ለትውልድ እንዲተላለፍ አስችለዋል።
የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ማደስ፡ ፓርኩ ከአደጋ ዝርዝር እንዲወጣ ለ5 ዓመታት የተዘረጉ ጥብቅ የአመራር፣ የጥበቃና የሕግ መስፈርቶችን በብቃት በማስተባበር ውጤት አምጥተዋል።
የማይዳሰሱ ቅርሶችን በዩኔስኮ ማስመዝገብ፡ ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ኮሚቴ ውስጥ በአመራርነት እንድትሳተፍ ከማድረግ ባሻገር የመስቀል፣ የቻምበላላ፣ የገዳ ሥርዓት እና የጥምቀት በዓላት በዓለም አቀፍ የማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ እንዲመዘገቡ በማድረግ ታሪካዊ አሻራ አኑረዋል።
እነዚህ አበርክቶዎች ለሀገራችን የሆቴል፣ የቱሪዝም፣ የባህልና የቅርስ ዘርፎች የተጣሉ ዘላቂ ተቋማዊ መሠረቶች ናቸው።
ክቡር አምባሳደር አሚን ለሀገራቸው ላሳዩት ፍቅር፣ የለውጥ አርበኝነትና ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል።
እንኳን ደስ አልዎት።
#ethiopiantourism #hotelandtourism #cultureandheritage #ambassadoramin #landoforigins #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የሀገራዊ ስኬት፣ የቅርሶች ዘላቂነት እና የአህጉራዊ ተሞክሮ አዲስ ከፍታ
********************
መንግሥት የቱሪዝም ዘርፍን ከአምስቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ አድርጎ በትኩረት እየሰራበት በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ በዘርፉ እየተካሄዱ ያሉ መሠረታዊ ለውጦች የኢኮኖሚ ገቢን ከማሳደግ ባሻገር የሀገራችንን ዘመን ተሻጋሪ የታሪክና የባህል ቅርሶች ኅልውና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ታሪካዊ መደቦች ሆነዋል።
በአሁኑ ወቅት ዘርፉ ከባህላዊ የጉብኝት ዘይቤ ወጥቶ ወደ ዘመናዊ፣ ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ የልማት ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል።
እንደ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ባሉ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የተገነቡት አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜና ወጪ በመጨመር ሀገራዊ ገቢውን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳደጉ ሲሆን፣ ዘመናዊ የቲኬት ማግኛ መንገዶች፣ የዲጂታል ማስታወቂያዎችና የሳይበር ደኅንነት ሥርዓቶች በመዘርጋታቸውም የአገልግሎት ጥራትና የገቢ አሰባሰቡን ቀልጣፋ አድርገውታል።
ይህ አገራዊ ስኬት የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ከመሆኑ ባሻገር፣ ከቱሪዝም ከሚገኘው ገቢ የተወሰነው የታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን ጥገና፣ ደኅንነትና እንክብካቤ በቀጥታ እንዲደግፍ የሚያደርግ አሠራር እንዲዘረጋ በማስቻል ትልቅ ምሳሌነትን ፈጥሯል።
የማኅበረሰብ አቀፍ ቱሪዝም መተግበሩ ደግሞ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከዘርፉ በቀጥታ ተጠቃሚ እንዲሆንና ቅርሶቹን የራሱ አድርጎ እንዲጠብቃቸው በማድረግ የሕዝብ ባለቤትነትን አረጋግጧል።
በጥቂት የታወቁ መዳረሻዎች ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ወደ አዳዲስና አህጉራዊ ደረጃቸውን የጠበቁ መዳረሻዎች ማስፋፋቱ የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብት በአዲስ ገጽታ ለዓለም ያስተዋወቀ ሁነኛ አጋጣሚ ሆኗል።
ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ እያረጋገጠች ያለችው ይህ አዲስ እመርታ የኢኮኖሚ ዕድገትን ከቅርስ እንክብካቤ ጋር አጣጥሞ ማስኬድ እንደሚቻል ለአፍሪካ አህጉር ትልቅ ተሞክሮና አርአያ የሚሆን ስኬት ነው።
የታሪካችን እና የባህላችን መገለጫ የሆኑ ቅርሶች ለወደፊቱ ትውልድ ሳይበላሹና ሳይደፈርሱ እንዲሸጋገሩ የተዘረጋው ይህ አስተማማኝ መደብ፣ ሀገራችን በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ የቱሪዝም መድረክ ላይ ያላትን መሪነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ይበልጥ የሚያጎለብተው ይሆናል።
በአድማሱ አራጋው
#ebc #ethiopiantourism #visitethiopia #tourismdevelopment #africanheritage #sustainabletourism

2 months ago
የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ነገር ...
#ethiopia | በኢትዮጵያ አፋር ክልል በዳናኪል ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘውና ሁልጊዜም ንቁ የሆነው የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ላቫ ሀይቅ በሳይንቲስቶችና በጎብኚዎች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ ይገኛል።
ሦስቱ አህጉራዊ የመሬት ንጣፎች የሚገናኙበትና የሚራቀቁበት ይህ ስፍራ፣ አህጉራት እንዴት እንደሚከፈሉና የምድር የውስጥ ሙቀት እንዴት እንደሚገለጽ የሚያስረግጥ ህያው የተፈጥሮ ቤተ-ሙከራ ሆኖ ያገለግላል።
ይህ በባሳልቲክ ድንጋይ የተገነባው እሳተ ገሞራ የማይቋረጥ የላቫ ሀይቅ የሚገኝበት ሲሆን፣ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ሙቀት፣ በጨው ሜዳዎችና በጂኦተርማል እንቅስቃሴዎች የተከበበ በመሆኑ ለአካባቢው ልዩ የተፈጥሮ ውበት ሰጥቶታል።
ስፍራው አስቸጋሪና ሞቃታማ የአየር ንብረት ያለው ቢሆንም፣ ከዳሎልና ከአሳሌ ሀይቅ ጋር በመሆን የሀገሪቱን የጂኦ-ቱሪዝም መስህብ ከፍ አድርጎታል።
በተጨማሪም በዚሁ አካባቢ የሚገኘው የስምጥ ሸለቆ ተፈጥሮአዊ ሀብት የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርክ እውቅና ለማግኘት ከፍተኛ አቅም እንዳለው ተጠቅሷል።
ዩኔስኮ ለስፍራው ገና ይፋዊ እውቅና ባይሰጥም፣ ለወደፊቱ የጂኦፓርክ ልማት ተስፋ ካላቸው ቀዳሚ ቦታዎች አንዱ አድርጎ ለይቶታል።
ለዚሁ እውቅና በዕጩነት ከተያዙት የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ፣ በውብ ቀለማትና በፍልውሃ ምንጮች ያሸበረቀው ዳሎል፣ ከባህር ወለል በታች 120 ሜትር ዝቅ ብሎ የሚገኘው የዳናኪል ዝቅተኛ መሬት፣ የዘመናት የጨው ማውጣት ባህል የሚከናወንበት የአሳሌ ሀይቅ፣ የአፍደራ ሀይቅ እና የሉሲ አፅም የተገኘበት ታሪካዊው የአዋሽ ታችኛው ሸለቆ ይጠቀሳሉ።
ይህ ስፍራ የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርክ እውቅና ማግኘቱ ድንቅ የሆኑ የስነ-ምድር ቅርሶችን ለመጠበቅ፣ ዘላቂ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ለማስፋፋት፣ የአካባቢውን ህብረተሰብ ተሳትፎና የሥራ ዕድል ለማሳደግ እንዲሁም ለሳይንሳዊ ምርምሮችና ለትምህርት ዘርፍ የጎላ ጥቅም ያበረክታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ertaale #afar #geopark #unesco #danakildepression #ethiopiantourism #volcano #geology #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
ኢትዮጵያን በልባቸው ያነገቡት የቱሪዝም አምባሳደር፤ ከአዲስ አበባ እስከ አሜሪካ የምግብ ትራክ
#ethiopia | ታላላቅ ታሪኮች ብዙ ጊዜ የሚጀምሩት ባልታሰቡ አጋጣሚዎች ነው። የአቶ አበራ ዋሲሁን የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነበር።
በ12 ዓመታቸው በአዲስ አበባ ተክለሃይማኖት አካባቢ መንገድ የጠፉ ሁለት ጣሊያናውያን ቱሪስቶችን በመርዳት እና የኢትዮጵያን ታሪክ በማስተዋወቅ የመጀመሪያውን የአስጎብኚነት ጉዞ ጀመሩ።
በዚያን ቀን የተቀበሉት 20 ብር ሽልማት ከገንዘብ በላይ የሀገር ፍቅርና የቱሪዝም አገልግሎት መንፈስን በልባቸው አስርጎ አስቀመጠ።
ከዚያ ጀምሮ ለአራት አስርት ዓመታት በቱሪዝም ዘርፍ ያሳለፉት ጉዞ በብዙ ስኬቶች የተሞላ ነው። ከአስጎብኚነትና ከሹፌርነት ተነስተው የራሳቸውን "አበራ አስጎብኚ ድርጅት" በመመስረት የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሯዊ ውበት ለዓለም ማስተዋወቅ ችለዋል።
ለቢቢሲ ጋዜጠኞች፣ ለአውሮፓ ኅብረትና ለአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢዎች ያበረከቱት አገልግሎትም በሙያቸው ያላቸውን ብቃት ያሳያል።
በ2012 በአሜሪካ "Ethio USA Tours" የተሰኘውን ድርጅታቸውን በመመስረት የኢትዮጵያን ታሪክና የቱሪዝም ሀብት ለዓለም አቀፍ ተጓዦች ማስተዋወቅ ቀጠሉ። ኮቪድ-19 የቱሪዝም ዘርፉን ቢያዳክምም፣ የሀገር ማስተዋወቅ ተልዕኳቸው አልቆመም።
በአዲስ አቅጣጫ "MULU FEST LLC" የተሰኘ የምግብ ትራክ በመጀመር በዋሽንግተን ዲሲ፣ ቨርጂኒያና ሜሪላንድ የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግብ፣ ባህልና እንግዳ ተቀባይነት ለብዙዎች እያስተዋወቁ ይገኛሉ።
ከአዲስ አበባ ጎዳናዎች የጀመረው ሕልማቸው ዛሬ በዓለም ሌላ ጫፍ የኢትዮጵያን ስም በክብር እያስጠራ ይገኛል። አቶ አበራ ዋሲሁን በሥራቸው የኢትዮጵያ ባህል፣ ቱሪዝምና ምግብ እውነተኛ አምባሳደሮች መሆን የቻሉ ተምሳሌት ናቸው።
#ethiopia #tourism #culture #ethiopiancuisine #ethiopiantourism #diaspora #getutemesgen #ኢትዮጵያ #ቱሪዝም #ባህል #አበራዋሲሁን #ጌጡተመስገን

Sponsored by
Surafel
3 months ago
ኢትዮጵያን ያላትን የቱሪዝም ጸጋ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማስተዋወቅ የጋዜጠኞች ድርሻ የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን ማስተዋወቅ እና የጎብኚዎችን ቀልብ በመሳብ የቱሪዝም ዘርፉን ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ሞተር ማድረግ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑ ተገለጸ።
ይህንን ግብ ከዳር ለማድረስም መገናኛ ብዙኃን በየአካባቢው የሚገኙ ጸጋዎችን ፈጠራ በታከለበትና ማራኪ በሆነ አቀራረብ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
በቱሪዝም ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አለማየሁ ጌታቸው እንደገለጹት፣ አገሪቱ ያሏትን እምቅ የቱሪዝም ሀብቶች በተሳለጠ መንገድ ለማስተዋወቅ የሚዲያው ሚና ወደር የለውም ብለዋል።
በቅርቡ የተመሰረተው የቱሪዝም ዘርፍ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ፎረም ዋነኛ ዓላማም ይኸው ገጽታን የመገንባት፣ የማስተዋወቅ እና የሽያጭ ሥራን በተናበበ መልኩ ለመምራት ነው። ሚዲያው የሰዎችን ቀልብ በሚስብ አግባብ መረጃዎችን ሲያቀርብ፣ ሰዎች እንዲጓጉ፣ እንዲመኙ እና የጉዞ ዕቅድ አውጥተው በጀት እንዲመድቡ ከፍተኛ መነሳሳትን ይፈጥራል ብለዋል።
አቶ አለማየሁ እንደገለጹት፣ ማስተዋወቅ የቱሪዝም ስኬት ቁልፍ መሣሪያ ነው። ጎብኚዎች ወደ ስፍራዎቹ መጥተው ማኅበረሰቡ በጥሩ ሁኔታ ሲያስተናግዳቸውና የተደሰቱበትን የጉዞ ልምዳቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ሲያጋሩ የቱሪስቶች ፍሰት በሶስት እና አራት እጥፍ ይጨምራል ብለዋል።
በመላ አገሪቱ ከስምንት መቶ በላይ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ተለይተው እያንዳንዱ ወረዳ እና ዞን የየራሱን መዳረሻዎች እንዲያለማ አቅጣጫ ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል።
መገናኛ ብዙኃን እነዚህን መረጃዎች ከሚኒስቴሩ "ላንድ ኦፍ ኦሪጂን" (Land of Origins)፣ ከ"ማይስ" (MICE)፣ እንዲሁም ከክልል የቱሪዝም ፕላትፎርሞች በተለያዩ ቋንቋዎች በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ይሁንና ጋዜጠኞች ጥሬ መረጃዎችን ከማሰራጨት ባለፈ መዳረሻዎቹን በአካል በመጎብኘትና በማጣጣም ስሜትን የሚስቡና ሕያው የሆኑ ዘገባዎችን ለተመልካች ማድረስ እንደሚገባቸው አቶ አለማየሁ በማሳሰብ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen
#ethiopia #ethiopiantourism #landoforigins
#miceethiopia

4 months ago
በአዲስ አበባ ስታዲየም :
የዊ ሻምፒዮንስ ( We Champions 2026 )
የስፖርት ፌስቲቫል እየተሰናዳ ነው
#ethiopia | የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ከ22 ዓመታት ረጅም የጥበቃ ጊዜ በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማሸነፉን አስመልክቶ፣ ይህንን ታሪካዊ ድል ለማክበር የተሰናዳውና በሀገራችን የመጀመሪያው ግዙፍ የስፖርት መድረክ የሆነው የዊ ሻምፒዮንስ 2026 ( We Champions 2026 ) የእግር ኳስ ፌስቲቫል በመጪው ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም በታላቅ ድምቀት እንደሚከናወን ተጠቁሟል።
በጎርደን ኢንተርቴይመንት አዘጋጅነት ለሚቀርበው ለዚህ ትልቅ ሁነት አዋሽ ባንክ በአፕክስ ኖብል ፕሮግራሙ አማካኝነት ዋነኛ ስፖንሰር በመሆን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
ይህ ልዩ መርሃ ግብር የስፖርቱን ፍቅር፣ ታማኝነትን፣ ባህልን፣ መዝናኛንና ስፖርታዊ እሴቶችን በአንድ ላይ በማስተሳሰር ከ30 ሺህ በላይ የእግር ኳስ አፍቃሪያንን፣ የዓለም አቀፍ ስፖርት ተዋናዮችንና እውቅ ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ ላይ የሚሰበስብ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው የደስታ መግለጫ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ዝግጅቱ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በበለጠ ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የስፖርት መገናኛ ብዙኃንንና የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችን ትኩረት በመሳብ የሀገሪቱን የቱሪዝም ፍሰት፣ የባህል ገጽታ እንዲሁም ትላልቅ ዓለም አቀፍ ኩነቶችን የማስተናገድ ብቃት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግ ታምኖበታል።
በዕለቱ ከሚታደሙት የክብር እንግዶች መካከል የቀድሞው የአርሰናልና የቱኒዥያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ራዲ ጃይዲ የሚገኝበት ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተደራሽነትና ተፅዕኖ ካላቸው የእግር ኳስ ሚዲያ አንዱ የሆነው የኤኤፍቲቪ መስራቾችና ተወካዮችም በዝግጅቱ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ መረጋገጡን በመግለጫው ላይ አስታውቀዋል።
ወደ ስታዲየም ለመግባት የሚያስችሉ የትኬት ሽያጮችን አስመልክቶ አዘጋጆቹ በሰጡት ማብራሪያ፣ መግቢያ ትኬቶችን ማግኘት የሚቻለው በአዋሽ ባንክ የአፕክስ ኖብል ፕሮግራም በኩል ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።
የመዝናኛ ክፍሉን ይበልጥ ማራኪና ድምቅ ለማድረግ ከአስር በላይ ታዋቂና ወጣት የሙዚቃ አርቲስቶች የተጋበዙ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ታደለ ሮባ፣ ልጅ ሚካኤል (ፋፍ)፣ ሳሚ ዳን፣ አስማማው እሸቱ፣ ራሄል ጌቱ፣ ሮማን ማይክ፣ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ሚካ ያኖ፣ አማኑኤል የማነ፣ አዲስ ሙላት፣ እዩ ፀጋ እና ኩሉ ሱሌ ይገኙበታል።
የአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ለታዳሚዎች ክፍት የሚሆን በመሆኑ፣ ተመልካቾች በጊዜ በመገኘት ቦታቸውን እንዲይዙ አዘጋጆቹ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
#wechampions2026 #arsenal #awashbank #apexnoble #gordonentertainment #aftv #radhijaidi #footballfestival #ethiopiantourism #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
ኢትዮጵያ እንዴት የዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና የሀያላን ሀገራት ማዕከል ሆነች? #ethiopia #dylanpage #visitethiopia #ishowspeedethiopia #ethiopiantourism #landoforigins #addisababacorridor
5 months ago
ከአይሾ ስፒድ እስከ ዲላን ፔጅ
***
ኢትዮጵያ እንዴት የዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና የሀያላን ሀገራት ማዕከል ሆነች?
#ethiopia #dylanpage #addisababa #visitethiopia #gerd #ishowspeedethiopia #ethiopiantourism #landoforigins #addisababacorridor
5 months ago
ከአቧራ ወደ ዐሻራ፤ ከቅርስ ወደ ቁርስ
*************
በቅርብ ዓመታት ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍን ከተራ የኢኮኖሚ ምንጭነት ባለፈ ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላም፣ ለብዝኃነትና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገንቢያ ስትራቴጂካዊ መሣሪያ አድርጋ በመውሰድ ላይ ትገኛለች።
ሀገራችን በታሪክ፣ በባሕልና በተፈጥሮ ያላትን እምቅ ባለጠግነት ለመጠቀም ቱሪዝምን ዋነኛ የኢኮኖሚ ምሰሶ ያደረገች ሲሆን፣ ይህም መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት፣ ገቢን ለማሳደግና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር መሠረት ሆኗል።
መንግሥት የመንግሥትና የግል ዘርፍ ቅንጅትን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በመምራት፣ ቱሪዝም የጋራ ታሪክን የሚያሳይና ብሔራዊ ማንነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እንዲሆን እያደረገ ነው።
ይህን ዘርፍ ለማሳደግ ለ16 ዓመታት ሳይሻሻል የቆየው የቱሪዝም ፖሊሲ በአዲስ መልክ ተሻሽሎ በሚኒስቴር ደረጃ እንዲደራጅ መደረጉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን አሳድጎታል።
በተጨማሪም የስብሰባ፣ የጉዞ፣ የኮንፍረንስና የኤግዚቢሽን (MICE) ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ወደ ተግባር የገቡ ሲሆን፣ የአሠራር ሥርዓቱን ለማዘመን የኢ-ቪዛና የዲጂታል አሠራሮች ተዘርግተው የቱሪስት ፍሰቱን አቀላጥፈዋል።
እንደ “ገበታ ለሀገር”፣ “ገበታ ለሸገር” እና “ኮሪደር ልማት” ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ ሀብትን ከልማት ጋር በማስተሳሰር ለሀገር ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል።
እነዚህ ተቋማዊ ጥረቶች እንደ እንጦጦ፣ ወንጪ፣ ሃላላ ኬላ እና ኮይሻ ያሉ መዳረሻዎችን ወደ ሥራ በማስገባት የቱሪስቶች ቁጥር ከ781 ሺህ ወደ 1.3 ሚሊዮን እንዲያድግ ማድረጉን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ይህም የውጭ ምንዛሪ ገቢን በከፍተኛ መጠን ከማሳደጉም በላይ በሆቴልና በአስጎብኚ ዘርፎች ለሺዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል። ኢትዮጵያ በዓለም ቱሪዝም ድርጅት እንድትሸለም ከማድረጉም ባሻገር፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሦስት አዳዲስ ቅርሶችን በዩኔስኮ በማስመዝገብ የታሪክ ክብረ-ወሰን እንድታስመዘግብ አስችሏታል።
ኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋናና በዓለም የተመረጠች መዳረሻ በማድረግ የቱሪስት ፍሰቱን እስከ 7.3 ሚሊዮን ለማድረስ ሰፊ ራዕይ ተቀምጧል።
ይህንን ለማሳካት አዳዲስ የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻዎችን ማስፋፋት፣ የታሪካዊ ቅርሶች ጥገናን ማዘመን፣ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ማበረታታትና የመሠረተ ልማት አውታሮችን ማሻሻል በትኩረት እየተከናወነ ነው።
በቀጣይም ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገልግሎቱን ማዘመንና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ተጨማሪ የሥራ ዕድል መፍጠር የመንግሥት ዋነኛ ትኩረት ሲሆን፣ ይህም ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገትና ለዜጎች የኑሮ ደረጃ መሻሻል ጉልህ ሚና ይኖረዋል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopiantourism #landoforigins #visitethiopia #miceethiopia

7 months ago
የኢትዮጵያ ገጽታ በታዋቂ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች አማካኝነት ለዓለም ሊተዋወቅ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ባህላዊ ውበቶች፣ ታሪካዊ ቅርሶች እንዲሁም የዘመነ የአኗኗር ዘይቤን በዲጂታል አማራጮች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል።
"ኢንፍሉዌንሰር ቱር 2026" የተሰኘው ይህ መርሃ ግብር በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ታዋቂ የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በማሳተፍ የሀገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት የታለመ ንቅናቄ ነው።
ይህ ታላቅ ጉዞ ታዋቂ ግለሰቦች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በመዘዋወር ከማህበረሰቡ ጋር እንዲገናኙና ያዩትን ተጨባጭ እውነት በከፍተኛ ጥራት ለተከታዮቻቸው እንዲያጋሩ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
ፕሮጀክቱ በዋናነት የቱሪስት መዳረሻዎችን ከማስተዋወቅ ባለፈ፣ የወጣቶችን ተሳትፎ የሚያሳድጉ የዩኒቨርሲቲ ጉብኝቶችን፣ ማህበረሰብ ተኮር የበጎ አድራጎት ተግባራትን እና የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ያካትታል።
በተጨማሪም በየክልሉ የሚገኙ አዳዲስ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ከታዋቂዎቹ ጋር ተቀናጅተው እንዲሰሩ በማድረግ የዘርፉን ዕድገት ለማፋጠን ታቅዷል።
መርሃ ግብሩን በበላይነት የሚመራው ኤን ዜድ ኮሙኒኬሽን ሲሆን፣ ድርጅቱ የኢንፍሉዌንሰሮችን አስተዳደር፣ የዘመቻ አፈጻጸምና አጋርነት ስራዎችን በኃላፊነት ያከናውናል ተብሏል።
በፕሮጀክቱ ላይ የሚሳተፉ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን ማንነት ያለ ምንም ክፍያ በፈቃደኝነት ለማስተዋወቅ የተስማሙ ሲሆን፣ ይህ ተግባራቸው ለሀገራዊ ኩራትና ለዓለም አቀፍ እውቅና ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል።
ፕሮጀክቱ ከሚዲያ ተቋማት፣ ከንግድ ድርጅቶችና ከከተማ መስተዳድሮች ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አዘጋጁ ኤን ዜድ ኮሙኒኬሽንስ በሰጠው መግለጫ አስተዋውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiopia #influencertour2026 #visitethiopia #digitalmarketing #ethiopiantourism #contentcreators #africarising #landoforigins #influencermarketing #azcommunication

Comments